Sunday, November 10, 2013

ከወያኔ ተሿሚ ጄኔራሎች አንዱ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ብር የዘረፈ ሙሰኛ መሆኑ ታወቀ

November 10/2013

ሱዳን ዉስጥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ሆኖ በማገልገል ላይ የሚገኘዉና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሚመራዉ እንዲሁም በቅርቡ ወያኔ የሌተና ጄኔራልነት ሹመት የሰጠዉ ሌተናንት ጄኔራል ዮሀንስ ገብረመስቀል ተስፋማርያም አዲስ አበባ ዉስጥ በህገወጥ መንገድ የገነባቸዉ የንግድ ህንጻዎች በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዋጋ እንደሚያወጡ ለጄኔራሉ ቅርበት ያላቸዉ ሰዎች ተናገሩ። የጦር ኃይሎች ኤታማጆር ሹሙን ጄኔራል ሳሞራ የኑስን ይተካል ተብሎ የሚነገርነለት ጄኔራል ዮሀንስ ገብረመስቀል ካለፈው አመት መጋቢት ወር ጀምሮ ወይም አዲሱን በተመድ ሰላም ጥበቃ በኩል የተሰጠዉን ሀላፊነት ከተቀበለ በኋላ በወር ከ10ሺ ዶላር በላይ እንደሚከፈለዉ ቢታወቅም አዲስ አበባ ዉስጥ የገነባቸዉን ህንጻዎችን መስራት የጀመረዉ ከአዲሱ ሸመት በፊት በመሆኑ ይህን ያክል ገንዘብ ከዬት አመጣ የሚሉ ጥያቄዎች ከየቦታዉ በመወርወር ላይ መሆኑ ታዉቋል።
ሱዳን አብየ ዉስጥ የሚገኘውን የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባረ ጦር የሚመራዉና በድክመቱና በምግባረ ብሉሽነቱ ዘወትር የሚወቀሰዉ ጄኔራል ዮሃንስ ገብረመስቀል በቦሌ ክፍለ ከተማ ካልዲስ ኮፊ እየተባለ ከሚጠራው ድርጅት ጀርባ የገነባዉ ግዙፍ ህንጻ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን፣ በዋጋ ደረጃ ከ90 እስከ መቶ ሚሊዮን ብር ያወጣል ተብሎ ይገመታል። ግለሰቡ በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎችን ከመኖሪያ ቤታቸው በተጨማሪ ድርጅቶች አሉዋቸው። ጄኔራል ዮሃንስ ገብረመስቀል እንደማንኛዉም የሰራዊቱ አባል በደሞዝ የሚተዳደር ግለሰብ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ከ17 አመት የጫካ ዉስጥ ኑሮ በኋላ ባዶ እጃቸዉን አዲስ አበባ ከገቡት የወያኔ አባላት ዉስጥ አንዱ ነዉ። ይህ መሆኑ እየታወቀ ጄኔራል ዮሃንስ ገብረመስቀል 90 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ህንጻ ማሰራት መቻሉ የሚያሳየን ህወሀትና ኢህአዴግ ዉስጥ የተሰገሰጉ ሙሰኞች ኢትዮጵያን ምን ያክል ግጠዉ እንደበሏት ነዉ እንጂ አንድ በደሞዝ የሚተዳደር ጄኔራል ከባንክ ተበድሬ ቤት ልስራ ቢል እንኳን አንድ መኖሪያ ቤት ከሚያሰራ ገንዘብ ዉጭ ባንክም ቢሆን 90 ሚሊዮን ብር ብድር አይሰጠዉም።

No comments: