Monday, November 18, 2013

ጉዞ በኢሕአዴግ ዴሞክራሲ ባቡር

November 18/2013

መድረክ ህዳር 8 ቀን 2006 ዓ . ም በአረብ ሃገር የሚገኙ ወገኖቹን ድምፅ ለማሰማት በአ / አበባ ሳውዲ ኤምባሲ ቅዋሜ ለማቅረብ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ መከልከሉን ሰማሁ . ምን መስማት ብቻ የአ / አበባ መስተዳድርን የክልከላ ደብዳቤ አነበብኩት . የክልከላ ደብዳቤው በከፊል እንዲህ የሚል ነው , -

" ሆኖም ግን በዕለቱ በከተማዋ ተደራራቢ ዓለም አቀፍ ጉባዔዎች በማካሄድ ላይ ያሉ እና በቅርቡም ለማካሄድ ዝግጅት ያጠናቀቁ ስለ አሉ እውቅና የተጠየቀበትን የሰላማዊ ሰልፍ ተገቢውን የፖሊስ ጥበቃ ለማካሄድ አስቸጋሪ በመኾኑ የተጠየቀውን የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ ተቀባይነት ያላገኘ መኾኑን እንገልጻለን . "

ገርሞኝ የክልከላ ደብዳቤውን ደጋግሜ አነበብኩት . ደጋግሜ ባነበብኩት ቁጥር የ " ዲሞክራሲያችን ባቡር " ጉዞ ታሰበኝ . " ዲሞክራሲ " እና " ባቡር " የሚባሉት ቃሎች ደግሞ የአሜሪካንን ተረት አስታወሱኝ . ምነው ቢሉ ? በዲሞክራሲ መንገድ ከ 200 ዓመት በላይ የተጓዘች አሜሪካ ነቻ - እንደነገሩን . ታዲያ ከእነሱ ተረት ካላጣቀስን ከማን ልናጣቅስ ነው ? ሆሆሆ .... !

የሆኖ ሆኖ እንደተረታቸው እንተርት .

አሜሪካኖቹ በባቡር እየተጓዙ ነው አሉ . ጉዞው 24 ሰዓት ሙሉ ካለዕረፍት የሚደረግ ነው ; እረፍት ቅብርጥሴ ; አቁሙልኝ .... ምናምን ብሎ ነገር የለም . በዚህ የተነሳ ሁሉም የራሱን ስንቅ ይዟል . አናም ባቡሩ ጉዞውን ቀጥሏል .... ጠዋት የተነሳው ባቡር እኩለ ቀን አጋመሰ . የምሳ ሰዓት ደረሰ . ሁሉም ሰው ምሳውን አውጥቶ መብላት ጀመረ . የአጋጣሚ ነገር ሆኖ ከአንድ ሰው በቀር ሁሉም አንድ ዓይነት ምግብ ነው የሚመገበው . ያ ብቸኛ ሰው ግን ምሳውን አሳ ነው የያዘው . ደግሞም አበላሉ ቄንጠኛ ነው . አሳውን ያወጣና ጭንቅላቱን ቅንጥስ አድርጎ ለብቻ ያስቀምጥና ሌላውን ቅርጥፍጥፍ አድርጎ ይበላል . እንደገና ሌላ አሳ ያወጣና ጭንቅላቱን ቆርጦ ያስቀምጥና የተቀረውን የአሳ ክፍል ቅርጥፍጥፍ አድርጎ ይበላል .

በዚህ አበላሉ የተገረመው አጠገቡ የተቀመጠው ሰውዬ አሳ በሊታውን እንዲህ አለው -

" የአሳው ጭንቅላት ይበላል እኮ "

" አውቃለሁ " አለ አሳ በሊታው . " የአሳ ጭንቅላት ከአፉ ጀምሮ ኩርሽምሽም እየተደረገ እንደሚበላ አውቃለሁ "

" ታዲያ ለምን አትበላውም ? "

" ጭንቅላቱን የማልበላው ; ልሸጠው ስለፈለግኩ ነው " አለ - በኩራት .

" ለማን ነው የምትሸጠው ? "

" ጭንቅላታቸው ለማይሰራ ! "

ይኼኔ ጠያቂው ሰውዬ አሰበ . አሰበ አሰበና እንዲህ አለው -

" ታዲያ ለምን እኔ አልገዛህም "

" ይቻላል ! "

" ስንት ስንት ነው የምትሸጠው ? "

" ሁለት ሁለት ዶላር "

በዚሁ ተስማሙ . እናም ተገበያዩ . ገዢው አንዱን የአሳ ጭንቅላት አነሳና ከአፉ ጀምሮ መኮርሸም ጀመረ . አንዱን የአሳ ጭንቅላት እየበላ ግማሹ ላይ ሲደርስ አንዳች ነገር ታወሰውና ወደ ሻጩ ዞር አለና እንዲህ ሲል ጠየቀው -

" ግን አንተ ሙሉውን አሳ ስንት ነው የገዛኸው ? "

" አንድ ; አንድ ዶላር ..... "

ይኼኔ ገዢው ተናደደ . በንዴት " እንዴት ታታልለኛለህ " እያለ ተንጨረጨረ .

ገዢው እየደጋገመ " እንዴት ታታልለኛለህ ? " እያለ ሲንጨረጨር ሻጩ የሰጠው መልስ ነው የተረቱ መቋጠሪያው .

" ምን አታልልሃለሁ ! ይኸው ጭንቅላትህ ሰራ ! " የሚል ምላሽ ነበር የሻጩ ምላሽ .

እና እኔ ይህን ተረት ለምን መጥቀስ ፈለግኩ ?

ኢህአዴግ ባለፉት በርካታ ዓመታት ስለዲሞክራሲ ምሉዕነት ሲጠየቅ , " የዲሞክራሲ ጉዞ ረዥም ነው " የሚል መልስ ነበር የሚሰጠው . በሌላ አገላለፅ " በዲሞክራሲ ሥርዓት ባቡር ውስጥ ነን ; ጉዞውን ለመፈፀም ረዠም ርቀት መጓዝ ያስፈልጋል ," ሲለን ነበር .

የሆኖ ሆኖ የዲሞክራሲው ባቡር በተባለው ጉዞ ውስጥ ተሳፈርን . ተጓዝን . ተጓዝን . ተጓዝን . የኢህአዴግ ዲሞክራሲ መቁረስ ላይ ታደምን .

ከዚያስ ?

እኛ አሳ ይዘን ተገኘን .

ኢህአዴግ " ልግዛችሁ " አለን .

እኛም " ግዛን " አልነው .

ከ " ገዛን " በኋላ " ምን ታታልኙላችሁ " እያለ የሚንጨረጨር ይመስላል - ኢህአዴግ .

ከላይ በተረቱ ውስጥ የአሳ ጭንቅላት የገዛው ሰውዬ ስህተቱ አንድ እና አንድ ነው . የሙሉውን አሳ ዋጋ አስቀድሞ አለመጠየቁ ነው ስህተቱ . የኢህአዲግም ስህተት ተመሳሳይ ነው . የሙሉውን ዲሞክራሲ ዋጋ በውል ለይቶ አለማወቁ ነው . ስለዚህ ነው ሰባራ ሰንጣራ ሰበብ እየፈለገ የዲሞክራሲውን ጉዞ በክልከላ የሚያጅበው .

ስለዚህ ኢህአዴግና ኢሕአዴጋውን ከሁሉ አስቀድሞ ይህ የክልከላ ዲሞክራሲ ባቡር ጉዞ መጨረሻው የት ነው ? ብለው ራሳቸውን ቢጠይቁ ነው የሚሻለው .

እንደው ለማለት ያህል እንጂ ; ............ ?
================= ጉዞ በኢሕአዴግ ዴሞክራሲ ባቡር ============

No comments: