Tuesday, November 19, 2013

በቺካጎ እና አካባቢዋ የሳኡዲ አረቢያን ግድያ አስመልክቶ ከፍተኛ የሆነ የተቃውሞ ሰልፍ ተከናወነ !

November19/2013

በዛሬው እለት በከተማዋ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያኖች የተካሄደው ይሄው ተቃውሞ ከቶምሰን ህንጻ (ከከተማው ከንቲባ ራሃም ኢማኑኤል ቢሮ )ጀምሮ የጎዳና ላይ ሰላማዊ ሰልፍ እና የዜጎቻችን መብት እና ክብር ይጠበቅ በሚል የተጀመረው የተቃውሞ ሰልፍ በደማቅ ሁኔታ ተጀምሮ በደማቅ ሁኔታ እንዳለቀ እንዲሁም የቺካጎ እና አካባቢዋንም ህብረተሰብ ያስደነቀ ልዩ ትእይንት እንደነበር ለማወቅ ተችልአል ። እንደ ማለዳ ታይምስ ዘጋቢ መረጃ ከሆነ በወቅቱ የተካሄደው ይሄው ሰላማዊ ሰልፍ ከመንግስት እና ከተቃዋሚ አባላቶች መካከል ጥቂቶቹ እንደተገኙ እና በሰልፉ ላይ ድምጻቸው እንዳሰሙ ተገልጾአል ።በወቅቱ የተካሄደው ይሄው ሰላማዊ ሰልፍ ከመንግስት እና ከተቃዋሚ አባላቶች መካከል ጥቂቶቹ እንደተገኙ እና በሰልፉ ላይ ድምጻቸው እንዳሰሙ ተገልጾአል ።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የቺካጎ እና አካባቢዋ የሚገኙ ወጣቶች በመሰባሰብ ድምጻቸውን ለስቴት ዲፓርትመንቱ ለማሰማት ከፍተኛ ጥረት ከማድረጋቸውም በላይ በተለያዩ የአሜሪካ ሚዲያዎች ላይ የአየር ሰአት አግኝቶ የሳኡዲውን ንጉስ አብደላን ለመውቀስ ያስችል ዘንድ ለመገናኛ ብዙሃኖች ጥሪ ቢደረግም በትላንትናው እና በዛሬው እለት በተካሄደው የተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ሪፖርተሮቻችን የተን ወደ ኢንዲያና እና ሌሎች ከተሞች ለሪፖርታዥ ስራ ሄደዋል ይህንን ጉዳይ ማንም ትተከታትሎ ሊሰራላችሁ አይችልም ሲሉ ተሰምተዋል ። ሆኖም ግን እንደተረዳነው ከሆነ ከሳኡዲ አረቢያ ጋር ያለቸውን የወዳጅነት ግንኙነት እና ጥቅም ላለማጣት የሚያደርጉት ትልቅ ጥረት መሆኑን ለመረዳት በቅተናል ።

በመላው አለም ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥትቶት የዜና ሪፖርት ሽፋን ሲያገኝ እና የኢትዮጵያኖች ድምጽ ሲሰማ በአሜሪካ ምድር ብቻ ይህንን ዜና ለመስራት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው እስካሁን ድረስ የሳኡዲ ህዝብ በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ከፈጸሙ ጀምሮ አንዳችም ነገር ሪፖርታዥ ሊሰሩ እንዳልቻሉ በተግባርም አሳይተውናል ።ይህ በእነድዚህ እንዳለ በዚሁ በሰላማዊ ሰልፍ ላይ የሳኡዲ አረቢያ ተወላች የሆነ ወጣት በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በመገኘት ሲገልጽ የህዝቡ ጉዳይ ሳይሆን ይህንን ነገር ያደረገው የመንግስቱ አስተዳደር ነው ብሎ ሳይጨርስ ህዝቡ በንዴት ወደ ድብደባ በማምራቱ በችሂካጎ ፖሊስ ዲፓርትመንት የእለቱ የሰልፉ አስከባሪዎች በቁጥጥር ስር ውሎ ህይወቱን ሊያተርፉት ችለዋል ። ይህ ወጣት ቀድሞ እንደገለጸው ከሆነ እኛም መንግስቱን እንቃወመዋለን ለተደረገው ነገር ሁሉ እናወግዛለን ሆኖም በኢትዮጵያኖች ላይ የተደረገውን ነገር ሁሉ አብረን እንድንቃወም በቅርቡ በጠራነው ሰልፍ ላይ ብትገኙልን ደስ ይለናል ብሎ ያቀረበውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ  የድምጽ ማጉያው ቢሰጠውም ህዝቡ ፋታ ሳይሰጠው ወደ ድብደባ ማምራታቸው ተገቢ አልነበረም ሲሉ አንዳንድ ነዋሪዎች ተቃዎሞአቸውን አሰምተዋል ።


በዛሬው እለት ከዋሽንግተን ዲሲ ጀምሮ እንግሊዝ ፣ቺካጎ እና ሌሎችም አለማት ላይ የተደረጉት የተቃውሞ ሰልፎች ከፍተኛውን ድምጽ ያገኛል ተብሎ የሚታሰብ መሆኑ ይህ በሃገራችን ላይ የሚደረገውን ጥቃት  ለመከላከል የሚያሳይ ትልቅ እመርታ እንደሆነ በግልጽ ኢትዮጵያዊነታቸውን አሳይተዋል ። 




No comments: