Saturday, November 23, 2013

ዲፕሎማቱ በትዕዛዝ ኢትዮጵያውያኑን ስደተኞች ወዳልታወቀ ስፍራ ሰደዱ

November 22, 2013 

12ነፍሰ ጡሮችን ጨምሮ 200 ስደተኞች የደረሱበት አልታወቀም
saudi ethio11


በሳውዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ይገኙ የነበሩ 12 ነፍሰ ጡሮችን ጨምሮ ከ 200 በላይ ስደተኞች በዲፕሎማቱ ትዕዛዝ ወዳልታወቀ ስፈራ ተወሰዱ ።
በሪያድ ልዩ ስሙ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው አካባቢ ሰሞኑንን የተቀሰቀሰውን ሁከት ተከትሎ አያሌ ወግኖቻችን መገደላቸው እና በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ይታወቃል። ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ወገኖቻችን ህይወት አስከፊ ገጽታ ላይ ባለበት ሁኔታ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ውስጥ ከአንድ አመት በላይ ተጠልለው እንደቆዩ የሚነገርላቸው እነዚህ ወገኖች ወዳልታወቀ ስፈራ መወሰዳቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል።
አሰሪዎቻቸው ከሚፈጽሙባቸው ግፍ እና በደል ራሳቸውን ለመታደግ ቀደም ብለው ወደ ኮሚኒቲው ግቢ እንደመጡ የሚነገርላቸው እኚህ ወግኖች፤ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች ጉዳዩቻቸውን ተከታትለው ሊያስፈጽሙላቸው ባለመቻሉ በተጠቀሰው የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ በሚገኝ አንድ ኮንቴነር ውስጥ ሲሰቃዩ መኖራቸውን የአይን ምስክሮች አክለው ገልጸዋል። ከ12 በላይ ነፍሰጡሮች እና የአእምሮ በሽተኞችን ጨምሮ ከ200 በላይ ስደተኞች በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ያለምንም የህክምና እርዳታ ሲሰቃዩ ከከረሙት እህቶቻችን ውስጥ 3ቱ በሞት መለየታቸውንና 5ቱ ለአእምሮ ጭንቅት መዳረጋቸው ከኢትዮጵያ ህዝብ ልብ የማይጠፋ መሪር ሃዘን መሆኑንን የሚናገሩ ወገኖች ሰሞኑንን መንፉሃ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ሁከት ተከትሎ ወደ ሳውዲ አረቢያ እንደ ገባ ለሚነገርለት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ልኡካን ቡድን ገበናችንን ያጋልጣሉ በሚል ስጋት ዲፕሎማቱ እነዚህን ወገኖቻችንን ወደ አልታወቀ ስፍራ በአውቶብስ ጭነው መውሰዳቸው ታውቆል።
ስደተኞቹ ያሉበት ሁኔታ እስካሁን በውል እንደማይታወቅ የሚናገሩት የሪያድ ምንጮች ምናልባት ወደ አገራቸው ለመግባት ለፖሊስ እጅ ሰጥተው በየጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ከሚሰቃዩ ወገኖቻችን ጋር ቀላቅሎዋቸው ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ያጠናክራሉ። ዲፕሎማቱ የሚፈሩት ነገር ከሌለ በቀር እነዚህ ወገኖች በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ኮኔትንር ውስጥ ላለፉት ወራት ያሳለፉትን የችግር እና የመከራ ጊዜያቶች ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ጉዳዩቻቸውን ባሉበት በማስፈጸም ወደ ሃገር በመላኩ ረገድ ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባ እንደነበር ውስጥ አዋቂዎች ይገልጻሉ። ዲፕሎማቱ የፈጸሙት ድርጊት ወገናዊነት የጎደለው መሆኑን የሚገልጹ ምንጮች የተጠቀሱት እህቶቻችን ኮሚኒቲው መጠለያ ግቢ ውስጥ በነበሩባቸው ጊዜያቶች አንዳንድ እህቶቻችን ተመርጠው በዲፕሎማቱ ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ በሚል ሽፋን ማታ ማታ ከማደሪያ ኮንቴነር ክፍላቸው እየተጠሩ እዛው ኮሚኒት ግቢ ውስጥ በሚገኝ አንድ ጽ/ቤት ውስጥ ለሰአታት ቆይተው ይወጡ እንደነበር በማስታወስ በእህቶቻችን ላይ ጾታዊ ጥቃት ሳይፈጸምባቸው እንደማይቀር ጥርጣሬያቸውን ይገልጻሉ።
እንዲህ አይነት አስጸያፊ ድርጊት አልፎ አልፎ የሚሰማ መሆኑንን የሚገልጹ ወገኖች በሪያድ አንዲት ኢትዮጵያዊት ወጣት ላይ መከስቱን ተከትሎ ኮሚኒቲው አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ወጀለኛውን ፍ/ቤት በማቆም 60 ሺህ ሪያል ካሳ እንዲከፍል ማስወሰናቸውን የሚያወሱ አንድ አባት፤ ጉዳዩን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተከታትሎ እንዲያሰፈጽም አደራ ቢሰጡም ሃላፊነቱን በብቃት ሳይወጣ በመቅረቱ ወንጀለኛው ከእስርቤት ተለቆ ተበዳይ እህት ሰሞኑንን ከሌሎች ወገኖቻችን ጋር ወዳልታወቀ ስፍራ እስከተወስደችበት ጊዜ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቴ ግቢ ውስጥ በህመም ስትሰቃይ እንደነበር እማኝነታቸውን ሰጥተዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ በጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት በሚገኙ እህቶቻችን ላይ ተመሳሳይ ጥቃት መሞከሩን የሚናገሩ የአካባቢው ምንጮች አንዲት ወጣት በቆንስላው ጽ/ቤት ዘበኛ ጾታዊ ጥቃት ተፈጽሞባት ጉዳዩ ፍ/ቤት ደርሶ እንደነበርና በቆንስላው የመንግስት ባለስልጣኖች ተድበስበሶ መቅረቱ የሚያስታውሱ ወገኖች በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ጊቢ ይኖሩ ከነበሩ ስደተኞች ውስጥ የ12ቱ ነፍሰ ጡር እህቶቻችን ጉዳይ ሳይጣራ ሰሞኑንን በዲፕሎማቱ ትዕዛዝ ከኮሚኒቲው ግቢ ባስቸኳይ እንዲለቁ መደረጉ የአካባቢውን ማህበረሰብ ጥርጣሬ የበለጠ ያጠናክረዋል ብለዋል።
Ethiopian Hagere በፌስቡክ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ከጅዳ በዋዲ የላኩት

No comments: