Tuesday, March 26, 2013

የአማራው ስቃይ ቀጥሎል ከቤኒሻንጉል ክልል የተፈናቀሉ 59 የአማራ ተወላጆች በመኪና መገልበጥ አደጋ ሕይወታቸው አለፈ

ከኢሊባቡር ክፍለ ሃገር በወያኔያዊ አጠራር { ቤኒሻንጉል ክልል] ኢትዮጵያዊነታቸው ተረስቶ ጎሳቸውን በማየት ብቻ እንዲፈናቀሉ የተደረጉ ከ 60 በላይ “አማራዎች ” ላይ በደረሰው የመኪና አደጋ ከተሳፋሪዎች ውስጥ 59ኙ ሲያልቁ አንዱ ብቻ ለመትረፍ እንደበቃ ኢሳት ዘገበ:: ይሀው በክልልህ ኑር የ ሚለው እና በመላ አገሪትዋ ተሰባጥረው በ ሚገኙ አማራው ብሄር ተወላጆች ላይ ብቻ ያነጣጠረው የማፈናቀል ዘመቻ ቀጥሎ ውሎ የማግዋግዋዙ ድርጊት ሲፈጸም አደጋው እንደደረሰ ዘገባዎቹ አስረድተው …ያለ ክልል ተብዬ ውጪ የሚኖር አማራ ብቻ ነው ወይ? ብዙ ትግሬዎች ብሎም ሌሎች ብሄሮች ይህንኑ ያደርጉ የለም ወይ? እንዴት አቅሙ በማይመጥን በጭነት መኪናስ እንዲግዋግዋዙ ይደረጋል? ሹፌሩስ ማን ነበር ?ለምንስ ከነሱ ተለይቶ በህይወት ተረፈ? በ እንዲህ አይነት ሁኔታስ እስከመቼ ይቀጥላል? ህንዶች እና ቻይኖች በክልሉ ሰፋፊ መሬቶች እየተሰጣቸው “አንድ ኢትዮጵያዊ ግን በገዛ አገሩ መኖር የማይችለው ለምንድን ነው ነው? የሚሉ ጥያቄዎች በአሁኑ ሰአት አደጋውን በሰሙ ሰዎች ዘንድ ያሳደረ ሲሆን :ምናልባትም ስለ ሁሉም ነገር ዝርዝር ይኖራልም ተብሎ ይጠበቃል…
ኢሳት ዜና:-ከአካባቢው ተፈናቃይ አርሶ አደሮች ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው አደጋው የተፈጠረው፣ ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረው መኪና ትክሻ በምትባል ቀበሌ ውስጥ ጀዴሳ በሚባል ወንዝ ውስጥ ገብቶ ነው።
ከትናንት ወዲያ በተፈጠረው አሰቃቂ አደጋ ለሞቱት ሰዎች የደረሰላቸው ሰው አለመኖሩን ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይገልጽ የፈለጉ ተፈናቃይ አርሶደሮች ተናግረዋል።
ከሞቱት መካከል ህጻናትና ሴቶችም ይገኙበታል። በአደጋው ዙሪያ የክልሉን ባለስልጣናት ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።
በተመሳሳይ ዜናም በዛሬው እለት በርካታ አርሶ አደሮች በክልሉ ልዩ ሚሊሺያ ጥቃት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል።
የክልሉ ባለስልጣናት የሚፈናቀሉት ሰዎች በህገወጥ መንገድ ወደ ክልሉ የገቡ ናቸው ሲሉ ለአዲስ አድማስ መናገራቸው ይታወሳል።
የዜጐች ከቦታ ቦታ የመዘዋወር መብትን በተለከተ አስተያየታቸውን የሰቱት የሕግ ባለሞያ አቶ ግዛው ለገሠ የሕገ-መንግሥቱ አንቀፅ 32 “የመዘዋወር ነፃነት” በሚል ርእስ ስር ‹‹ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም በሕጋዊ መንገድ አገሪቱ ውስጥ የሚገኝ የውጭ ዜጋ፤ በመረጠው የአገሪቱ አካባቢ የመኖርና የመኖሪያ ቦታ የመመስረት እንዲሁም በፈለገው ጊዜ ከአገር የመውጣት መብት እንዳለው መደንገጉን ለጋዜጣው ገልጸዋል።

No comments: