Wednesday, August 6, 2014

የአርባ ምንጭ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎች ታሰሩ

August 6/2014
ሐምሌ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዞኑ ፖሊሶች ትናንት ከሌሊቱ 10 ሰአት ላይ ወደ ሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አመራሮች መኖሪያ ቤት በመሄድ ፍተሻ ካደረጉ በሁዋላ ፣ አመራሮችን ወስደው አስረዋቸዋል።

የፍርድ ቤት ማዘዣ ይዘናል በማለት ፍተሻ ያካሄዱት ፖሊሶች በአንደኛው ቤት ውስጥ ሁለት ፍሬ ጥይቶችን ማግኘታቸውን ሲያስታወቁ፣ በሌሎች መኖሪያ ቤቶች ደግሞ ቪዲዮ ካሜራዎችን፣ ፊልሞችንና የተለያዩ ወረቀቶችን ሰብስበው ወስደዋል። የአንደኛው አመራር የቅርብ ሰው የሆነ ለኢሳት ሲናገር፣ ፖሊሶቹ ጠመንጃ በሌለበት ሁለት ጥይቶችን አገኘን ማለታቸው አስቂኝ ነው ካለ በሁዋላ፣ ሁለቱንም ጥይቶች ፖሊሶች ራሳቸው ይዘው መምጣታቸውንና አገኘን ብለው መናገራቸውን ገልጿል።

ሉሉ መሰለ፣ በፈቃዱ አበበ፣ ነጻነት መተኪያና ኢ/ር ጌታሁን በየነ የተባሉት አመራሮች ገሚሶቹ በአርባ ምንጭ ከተማ ቀሪዎቹ ደግሞ ከከተማው ወጣ ብሎ በሚገኝ እስር ቤት መታሰራቸው ታውቋል። ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነውን አቶ የሽዋስ አሰፋን እንዲሁም የፓርቲው አባል የሆነቸውን ወይንሸት ሞላን በቅርቡ ማሰሩ ይታወሳል።

መንግስት በሽብር ሰበብ ካለፉት ሁለት ወራት ጀምሮ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ይዞ አስሯል። አንዳንድ ወገኖች የአሁኑን እስር ከመጪው ምርጫ ጋር እያያዙት ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ በአገሪቱ ውስጥ የሚታየው የኑሮ ውድነትና የፍትህ እጦት በህዝቡ ዘንድ የፈጠረውን  ስሜት ተቃዋሚዎች እንዳይጠቀሙበት አስቀድሞ የመከላከል እርምጃ እየተወሰደ ነው ይላሉ።

በሌላ ዜና ደግሞ ዋስትና የተፈቀደላቸው ሙስሊም ፖሊሶችና የሰማያዊ ፓርቲ አባሏ ወ/ት ወይንሸት ሞላ እንደገና እንዲታሰሩ ተደርጓል። ሪፖርተር እንደዘገበው በአንዋርመስጊድውስጥ በቅርቡ ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት አስተባብረዋል ተብለው የታሰሩ ሙስሊምየፖሊስአባላት ፣ የታሰሩት የአድማ በታኝ ፖሊስ አባላት መሆናቸውን መታወቂያ በማሳየታቸው ብቻ መሆኑን ለፍርድ ቤት ተናግረዋል።

ሐምሌ 29 ቀን 2006 ዓ.ም.በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ማስቻያ ችሎት ለአራተኛ ጊዜ በቀረቡበት ወቅት በግጭቱ አለመሳተፋቸውን ተናግረዋል። ኮንስታብል አብዱራህማን  ወንድሙን ለመጠየቅ በሚሂደበት ጊዜ፣የፀሎት ሰዓት ስለደረሰበት አንዋር መስጊድ ሰግዶ በመመለስ ላይ እንዳለ መያዙን ገልጿል።

ኢንስፔክተር መሐመድ የሱፍ ደግሞ በመስጊድ ውስጥ እየሰገደ በነበረበት ወቅት ግጭቱ በመነሳቱ እዚያው መቆየቱንና መታወቂያውን ለአንድ የፖሊስ አባል ሲያሳይ ‹‹ውስጥለምንገባህ? ፖሊስ ሆነህ እንዴት እዚህ ልትገባ ቻልክ?›› ተብሎ መያዙን ገልጿል። ኢንስፔክተር ሙሃመድ  እሱ በመስጊድ ውስጥ ባለበት ጊዜ ከውጭብጥብጥመነሳቱን ገልጾ፣ እንኳንስ ለክስ ይቅርና ለምስክርነት እንደማይበቃ ገልጿል፡፡  “ፖሊስሆ ኖበ መስጊድ ውስጥ ወይም አካባቢ መገኘት የማይቻል ከሆነ፣ይህንን እንደትምህርት እንደሚወስደው በመናገር በዋስ ከእስር ተለቆ፣ወደፊት የሚጠየቅበት ጉዳይ ካለሥራውን እየሠራ እንዲጠባበቅ ፍርድቤቱን” መጠየቁን ጋዜጣው ዘግቧል።

ሌላው እስረኛ ምክትል ኢንስፔክተር አደም መስጊድ ውስጥ እንደነበረና  ብጥብጡ ካበቃ በኋላ ከቀኑ አሥር ሰዓት ላ ይመያዙን ገልጾ፣  ፖሊስ በመሆኑ ብቻ መያዙን እንዲሁም ከተያዝኩበት ቦታ እስከጣቢ ያድረስ እየተደበደበ መወሰዱን ” ተናግሯል፡፡ለ19 ቀናትመታሰሩን፣  ቤቱ ሲፈተሽ ምንም ነገር አለመገኘቱን፣  ሙስሊምበመሆኑብቻመጠየቅ እንደሌለበት አስረድቷል።

ከዚህ ቀደም  የፀጥታ (ኢንተለጀንስ) ሥራስትስራ እንደነበርናተገቢያልሆነባህሪ በማሳየቷ ቢሮ ውስጥ እንድትሠራ መደረጓን በመርማሪ ፖሊሶች ለፍርድ ቤት የተነገረላት ምክትል ሳጅን ሳሊና መሐመድ ፣ፖሊስ ለምርምራ በሚል የሚወስደውን የጊዜ ቀጠሮ ተቃውማለች።

እንደ ጋዜጣው ዘገባ ሳጅን ሳሊና “መርማሪ ፖሊስ መረጃ ለመሰብሰብ ከበቂ በላይ ጊዜ መውሰዱንና የፌዴራል ፖሊስ በብጥብጡ ዕለት የቀረፀውን የቪዲዮ ማስረጃ እንዲሰጠው በደብዳቤ  ጠይቆእየተጠባበቀ መሆኑን ለፍርድ ቤት ያስረዳው ተገቢ አለመሆኑን”ተናግራለች።

” እሷ የኦዲዮ ቪዥዋል ክፍል ሠራተኛ እንደነበረች በማስረዳት ፖሊስ ለማስረጃ የሚፈልገውም ሥልመኖሩን በደብዳቤ ሲገልጽ በአሥር ደቂቃ ውስጥ ማግኘት እንደሚቻል አስረድታለች፡፡

ቤቷን፣ተንቀሳቃሽስልኳንናየሚፈልጉትንነገርሁሉመርምረውናፈትሸውምንምያገኙባትነገርእንደሌለአስረድታ፣የተሰጠው ቀን ከበቂ በላይ መሆኑን በመጠቆም ተጨማሪ ጊዜ ሊፈቀድ እንደማይገባ ተቃውማለች፡፡” ፖሊስ ከፍርድ ቤት ለቀረበለት ጥያቄ ፣” ፖሊስ 12 ተጠርጣሪዎች በዕለቱ በሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን፣ንብረት ማውደማቸውን፣የደበደቧቸው ፖሊሶችና ሰላማዊ ሰዎች በተለይ በሆስፒታል ኮማ ውስጥ ያሉት መናገር እንደማይችሉ በማስረዳት፣ የተጎዱት ሰዎች ባይድኑ ተጠርጣሪዎቹ ዋስትና በሚከለክለው የሰው መግደል ወንጀል ተጠርጥረው ስለሚከሰሱዋስትናእንዳይፈቀድላቸው” ጠይቋል።

የሰማያዊ ፓርቲ አባልየሆነችው ወ/ትወይንሸት ሞላ፣እምነቷ በማይፈቅድላት ቦታ በብጥብጡ ውስጥ መገኘቷንና ብጥብጡን ስታበረታታና የተለያዩመፈክሮችን የያዙ በራሪ ረቀቶችን ስትበትን እንደነበርፖ ሊስ ገልጿል የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድ እምነቷ እስልምና ቢሆንም፣በሁከቱ ቦታ ተገኝታ ስትመራና ስታግዝ ነበር ሲል መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል።

የሰማያዊፓርቲአባሏወ/ትወይንሸትመርማሪዎቹየወሰዱትየምርመራጊዜበቂመሆኑንተናግራለች፡፡ ወይንሸት በፖሊስ የቀረበውን ውንጀላ አስተባብላለች።

ጋዜጠኛአዚዛመሐመድምወደሥፍራውየሄደችውሥራዋንለመሥራትብቻ መሆኑን ተናግራለች። ፍርድ ቤት በመጨረሻም ተጠርጣሪሙስታዝመንሱር፣  የሰማያዊፓርቲአባልወ/ትወይንሸት ሞላና የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድ እያንዳንዳቸው በአምስት ሺሕ ብር ዋስ እንዲለቀቁ በማዘዝ፣ በሌሎቹተጠርጣሪዎችላይየስምንትቀናትጊዜበመፍቀድ ለነሐሴ 7 ቀን 2006 ዓ.ም. ተለዋጭቀጠሮሰጥቷል፡፡

ሦስቱ ተጠርጣሪዎች በአምስት ሺሕ ብር ዋስ እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ ቢወስንም፣  መርማሪ ፖሊስ በሰዓታት ልዩነት ለአዲስ አበባ ከተማ ነክ ሰበር ሰሚችሎት ይግባኝ አቅርቦ፣ ‹‹ይፈቱ›› የሚለውን ውሳኔ በማሻር በሦስቱም ተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማ ሪየሰባት ቀናት የምርመራ ጊዜጠይቆ ተፈቅዶለታል።

No comments: