Sunday, August 24, 2014

ወያኔ እስካሁን ድረስ የግንቦት ሰባት የሃገር ቤት መዋቅር በፍጹም እጇ ላይ እንዳልገባ ተረጋግጧል።

August24/2014
ምንሊክ ሳልሳዊ
በሀገሪቱ የስራ ማቆም አድማ እና የተማሪዎች አመጽ ያሰጋል ።

ከመጭው ምርጫ በፊት በኢትዮጵያ ውስጥ የስራ ማቆም አድማ እና የተማሪዎች አመጽ እንደሚያሰጋ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ለሕወሓቱ አለቃ ጸጋይ አርብ እለት የቀረበው ሪፖርት መግለጹን ምንጮች ጠቁመዋል። ምንጮቹ እንዳሉት በወያኔ ውስጥ ስልጣኔን አጣለሁ እፈረካከሳለሁ የሚለው ከፍተኛ ሽብር የፈጠረው ፍራቻ እየተባባሰ መሄዱን እና ወያኔ ለመጭው አርባ አመታት እቆያለሁ የሚለውን ሃሳቡን ሊያኮላሽብኝ ይችላል ያለውን ሁሉ እርምጃ ቢወስድ ምንም አይነት ውጤት እንደማያገኝ እና በይበልጥ ጥላቻ እያሰፋ እንደሚመጣ በተሰበሰበው የመረጃ ሪፖርት ተገልጿል ።

የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች የሚያስተባብሩ ከሆነ ሕዝቡ የሚከፈለውን መስእዋትነት ለመክፈል ወደኋላ የማይል መሆኑን የጠቆመው ሪፖርት የከተማው የተማረውም ያልተማረውም ሕብረተሰብ በወያኔ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ ስላለው ለመጭው ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የስራ ማቆም አድማ እና የተማሪዎች አመጽ ያሰጋል ሲል ሪፖርቱ ተናግሯል። እንደ ምንጮቹ አገላለጽ ክሆነ የሃገር ቤት ፓርቲዎች በተለይ ሰማያዊ እና መኢአድ ይህንን እንቅስቃሴ ያስተባብራሉ የሚል የሕዝቡንም አትኩሮት መሳብ እንደቻሉ ሲታወቅ አንድነት እና መድረክ ፓርቲ ውስጥ ያሉ እና ያሰጋሉ የሚባሉ መዋቅሮችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረቱ መቀጠሉን ሪፖርቱ አውስቷል።

በወያኔ አስተዳደር እና ባልተማሩ ባለስልጣናቱ እንዲሁም ክድሬዎቹ ሕዝቡ እየተማረረ እንደሆነ እና መንግስታዊው ውሸትና ወመኔነት፣ ሙስና ከፈጠረው የኑሮ ድቀት ጋር ተደማምሮ መጨው ጊዜ ለወያኔ ገሃነም እንደሆነበት በግልጽ የተቀመጠ ሲሆን አብዛኛው የገዢው ፓርቲ አባላት ሳይቀሩ በድርጅቱ ሁኔታ እና ኢዲሞክራሲያዊነት እንደማይደሰቱ እንዲሁም ሕዝቡ እያገለላቸው ሲሆን የሚቀርባቸዉም ሕዝብ ከአንገት በላይ መሆኑን እየገለጹ ስለሆነ የድርጅቱን መኖር እንደማይፈልጉ ታውቋል። አንዳንድ አባላቱ ድርጅቱን ከደርግ ኢሰፓ ጋር እንደሚያመሳስሉት እና በ97 ምርጫ የወሰዱትን እርምጃ በገዢው ፓርቲ በሆነው ድርጅታቸው ላይ ሊወስዱ ይችላሉ ሲል ሪፖርቱ አስቀምጧል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ወያኔ እስካሁን ድረስ የግንቦት ሰባት የሃገር ቤት መዋቅር በፍጹም እጇ ላይ እንዳልገባ ተረጋግጧል። የደህንነት አካላቶች ባደረጉት ማጣራት ግንቦት ሰባት ብለው የተጠቆሙት በራሳቸው መዋቅር ውስጥ ያሉ እና የሃገር ቤት ተቃዋሚዎችን እንዲሰልሉ የተላኩ የገዢው ፓርቲ አባሎች ሆነው ማግኘታቸው ጭራሽ ኢሕአዴግን ውዝግብ ውስጥ እንደከተተው ታውቋል። ከኢሕአዴግ ጽ/ቤት ለደህንነት ቢሮ የተላከው መረጃ እንደሚጠቁመው የግንቦት ሰባት አባልነት የተባሉት አብዛኛዎቹ ለድርጅቱ ጠቃሚ መረጃ የሚያመጡ ሰዎች ሲሆኑ ስለ ግንቦት ሰባት ግን ምንም መረጃ ያላመጡ እና የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ይገልጻል።

ወያኔ ምንም አይነት የግንቦት ሰባት መዋቅር ፍንጭ አለማግኘቱ ጭንቀት ውስጥ ስለከተተው በእስር ቤት ያጎራቸውን ወጣቶች በግንቦት ሰባት ዙሪያ ስለላ እንዲሰሩ እና ክትትል እንዲያደርጉ ማሰልጠን ቢፈልግም የመለመላቸው ወጣቶች ፈቅደኛ ሊሆኑለት እንዳልቻሉ ታውቋል፡፤ በቅርቡ እንደተፈታ የሚናገር አንድ ወጣት የላከው መረጃ እንደሚያሳየው የፈለገውን ገንዘብ እንደሚስጡት እና የፈለገው አገር እንደሚልኩት በመግለጽ አብሯቸው እንዲሰራ እና የግንቦት ሰባትን እንቅስቃሴ ተከታትሎ መረጃ እንዲያቀብላቸው ቢያስገድዱት በፍጹም አለመስማማት እንደተለያቸው ተናግሯል። አስተያየት ሰጪዎች ወያኔ ስልጣንን ለማቆየት በሚያደርገው ጥረት የተለያዩ የስለላ መረቦችን እንደሚዘረጋና ተቃዋሚዎች ከዚህ እንዲጠነቀቁ እንዲሁም ተመሳስለው ከሚመጡ ሰርጎ ገቦች ራሳቸውን በመጠበቅ የየፓርቲያቸውን የደህንነት ክፍል እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል።#ምንሊክስልሳዊ

No comments: