Wednesday, August 13, 2014

የአዲስ አበባ መስተዳድር በቤቶች ግንባታ ዙሪያ ለምርጫ እንዲደርስ በሚል አስቸኳይ ትእዛዝ ሰጠ

Auggest13/2014
ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ40 በ60 በሚባለው የቤቶች መርሃግብር የታቀፉ የዲያስፖራ አባላት ከቀጣዩዓመት ምርጫበፊት ቤት እንዲሰጣቸው የአዲስ አበባ መስተዳድር መመሪያመስጠቱ ታውቋል። ሆኖምየጠቅላላተመዝጋቢውንየቤትፍላጎትለመሸፈንበትንሹከ16 ዓመታትበላይጊዜን እንደሚወስድ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ የአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ኢንተር ፕራይዝ እስካሁን 13ሺህ 800 ቤቶችን በሰንጋተራ እና ቃሊቲ ክራውን ሆቴል በመሳሰሉ አካባቢዎች ላይ እየገነባ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ፣ እነዚህን ቤቶች እስከሚቀጥለው ዓመት አጋማሽ ድረስ ለዕድለኞች ለማስተላለፍ ታቅዷል።

የአስተዳደሩ ምንጮች እንደገለጹት ቤቶቹ ከቀጣይ ዓመት ምርጫ በፊት ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው እንዲተላለፉ ከአስተዳደሩ መመሪያ ተሰጥቷል። ሆኖም ለ40 በ60 የቤቶች ፕሮግራም የተመዘገበው ጠቅላላ ሕዝብ ቁጥር 164 ሺህ 779 ያህልሲሆንአስተዳደሩግን በዓመትከ10 ሺህቤቶችበላይቤቶችን
የመገንባት አቅም ባለመፍጠሩ የተመዘገቡትን ብቻ ለማዳረስከ16 ዓመታት በላይ ጊዜን እንደሚፈልግ የአስተዳደሩ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ ይህ ደግሞ ከዛሬ ነገ የመኖሪያ ቤት ባለቤት አስቆራጭ ዜና ነው ብለዋል፡፡ በ20/80 በተለምዶኮንዶሚኒየምፕሮግራምየምርጫ 97ን መቃረብ ታሳቢ አድርጎ ሲጀመርከ 350ሺ በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪ መኖሪያ ቤት እፈልጋለሁ ብሎ መመዝገቡን ያስታወሱትምንጮቹ ፣ ፕሮግራሙ 10 ዓመታት ያህል ቆይቶ መመለስ የቻለው ግን 100 ሺ በታች ቤት ፈላጊዎችን ጥያቄ ነው ብለዋል፡፡በዚህ መረጃ መሠረት የጠቅላላ ተመዝጋቢውን ፍላጎት ለሟሟላት ተጨማሪ ከ20 ዓመታት በላይ ጊዜ ንእንደሚወስድ አፈጻጸሙ በራሱ የሚናገርነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የአስተዳደሩ ምንጭ እንደሚሉት መንግሥት በአዲስ አበባበዓመት ለቤቶች ግንባታ ብቻ ከ2 እስከ 3 ቢሊየን ብር እያወጣ መሆኑን አስታውሰው ከዚህ በላይ ለማውጣት የፋይናንስ አቅም ችግር መኖሩን፣ገንዘቡ ቢገኝም በግንባታ አፈጻጸምበኩል የአቅም ችግር በመኖሩ በአጭር ጊዜ የመኖሪያ ቤት ፍላጎትን ለመመለስ የማይችልበት አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም እንደገለጹት ደግሞ ዲያስፖራው በፈለገበት አካባቢ ቤት ለመስራት ይችል ዘንድ ክልሎች መመሪያ እንዲያወጡ መታዘዙን ገልጸዋል። ሁሉም ክልሎች ተመሳሳይ የሆነ መመሪያ ባለማውጣታቸው ለዲያስፖራው ቤት ለማደል የታቀደው እቅድ የተፈለገውን ውጤት አለማምጣቱን ገልጸዋል። ይሁን እንጅ ኢሳት የአዲስ አበባን አዲሱን ካርታ ዝግጅት አስመልክቶ ከወራት በፊት በሰራው ዘገባ፣ የቤት ግንባታ መርሃግብሩ የተሰናከለው በአዲስ አበባ የቤት መስሪያ ባዶ ቦታ በመጥፋቱ ነው። ቀደም ብሎ የኦሮምያን ልዩ ዞኖች ወደ አዲስ አበባ በመጠቅለል የቤት መስሪያ ቦታዎችን ለማግኘት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ የኦሮምያ ክልል አንዳንድ ባለስልጣናትና አብዛኛው የኦሮሞ ተወላጅ በመቃወሙ እቅዱን በቀላሉ ተግባራዊ ማድረግ አልተቻለም። ዲያስፖራው ከአዲስ አበባ ውጭ ያሉ ቦታዎችን እንዲጠይቅ ለማግባባት ኢምባሲዎች የስራ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ለአባይ ግድብ በቦንድ ስም ገንዘብ በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ገንዘብ ለማሰባሰብ የታቀደው እቅድ አለመሳካቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምነዋል። ከፍተኛ ገንዘብ ይገኝበታል የተባለው የአሜሪካ የቦንድ ሽያጭ አምና ጭራሽ አልተካሄደም ብሎ መናገር እንደሚቻል ሚኒስትሩ ገልጸዋል። በሁሉም አገሮች ያለው የቦንድ ሽያጭ ደካማ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ ፣ ለድክምቱ ዝርዝር ምክንያቶችን አላቀረቡም።

የዶ/ር ቴዎድሮስ ገለጻ፣ ኢሳት ከዚህ ቀደም የቦንድ ሽያጩ በውጭ አገር አለመሳካቱን ሲዘግብ የቆየውን ያረጋገጠ ሆኗል። በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ገንዘብ ለመሰብሰብ በገዢው ፓርቲ በኩል የሚዘጋጁትን ዝግጅቶች አጥብቆ ሲቃወም እንደነበር ይታወቃል። አቶ መለስ የአባይን ግድብ እቅድ ይፋ ሲያደርጉ በውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ 1 ቢሊዮን ዶላር ያዋጣል የሚል እምነት ነበራቸው፣ ይሁን እንጅ እስካሁን ባለው መረጃ በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ከ20 ሚሊዮን ዶላር በላይ ሊያዋጣ አልቻለም።

No comments: