Tuesday, October 14, 2014

አበበ ገላው ፕሬዘዳንት ኦባማ በተገኙበት ስብሰባ ላይ ለፕሬዘዳንቱ ደብዳቤ አደረሳቸው፡፡

October 14,2014

አበበ ገላው ፕሬዘዳንት ኦባማ በተገኙበት ስብሰባ ላይ ለፕሬዘዳንቱ ደብዳቤ አደረሳቸው፡፡ አርብ ዕለት እንደጉርጎሪያን አቆጣጠር ጥቅምት 10 በሳንፍራንሲስኮ በሚገኘው የዳብሊው ሆቴል በዲሞክራቲክ ናሽናል ኮሚቴ /ዲኤንሲ/ አማካኝነት የተደረገለትን ግብዣ አጋጣሚ በመጠቀም ከፕሬዘዳንቱ ጋር አንድን ስብሰባ የተከታተሉ ሲሆን እንደሚሰጥ ቃል በገባው ለፕሬዘዳንቱም በተወካያቸው አማካኝነት ደብዳቤ እንዲደርሳቸው አድርጓል፡፡
አበበም በዕለቱ ባስተላለፈው መልዕክት ያገኘነውን አጋጣሚ ሁሉ ሰፊውን ህዝብ እና የተከበረችውን ሃገራችን ኢትዮጵያን ድምፅ ማሰማት አለብን ብሏል፡፡ የምዕራባዊያን ሃገራት ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ አምባገነን መንግስታትን እንደሚረዱ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ እና ፖሊሲና ስትራቴጅዎቻቸውን እንዲከልሱ እንዲሁም ከሰብአዊ መብቶች መጠበቅ አለመጠበቅ ጋር በቀጥታ ማያያዝ እንደሚገባቸው በሁሉም አጋጣሚዎች ማሳወቅ ይገባልም ተብሏል፡

No comments: