Wednesday, May 21, 2014

በጋዜጠኞቹ እና በጦማሪያኑ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተሰጠ

May 21/2014 
ሰበር ዜና፡- ፍርድ ቤቱ በተጠረጠሩት ጋዜጠኞችና ጦማሪያን ላይ የ10 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ፈቀደ
-    “ከአሸባሪ ድርጅቶች ጋር ስልጠና ወስደዋል፤ ብርም ተቀብለዋል” ፖሊስ
-    “ስልጠና የወሰዱት ‘አርቲክል 19’ እና ‘ፍሪደም ሀውስ’ ከተሰኙ በአሜሪካና በእንግሊዝ መንግሥታት ዕውቅና ከተሰጣቸው ዓለም አቀፍ ህጋዊ ድርጅቶች ነው” ጠበቆች

ምስጢራዊ በሆነ መንገድ በህቡዕ በመድራጀት፣ በህጋዊ መንገድ ስልጣን የያዘውን መንግስት በህገወጥ መንገድ ከስልጣን ለማውረድ በማሰብ፣ ውጪ ሀገር ከሚገኙ አሸባሪ ድርጅቶች ጋር በመስማማትና ሀገሪቱን ለማተራመስ ትዕዛዝ በመቀበል የገንዘብና የስልጠና ድጋፍ በመውሰድ፤ በአገሪቱ ላይ ብጥብጥ ለማስነሳትና ብጥብጡንም ለመምራት በመንቀሳቀስ የሽብር ተግባር ፈፅመዋል ሲል የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን በሶስት መዝገቦች ከፋፍሎ እየመረመራቸው የሚገኙት ጋዜጠኞችና ጦማሪያን የ28 እና የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው።
ቅዳሜ ግንቦት 10 ቀን 2006 ዓ.ም በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንደኛ አራዳ ምድብ ችሎት በቅድሚያ የቀረቡት በእነ አጥናፍ መዝገብ ስር የሚገኙት ጦማሪያኑ አጥናፍ ብርሃነ፣ ናትናኤል ፈለቀ እና ጋዜጠኛ ኤደም ካሳዬ ናቸው።
በተመሳሳይም በእነዘላለም መዝገብ ስር የዞን ዘጠኝ ጦማሪውና የህግ መምህሩ ዘላለም ክብረት፣ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስና ጋዜጠኛ አስማማው ወ/ጊዮርጊስ እንዲቀርቡ ተደርጓል።
ሁለቱ መዝገቦች ተለያይተው ቢቀርቡም የምርመራ ቡድኑ በሁሉም መዝገቦች ላይ ተመሳሳይ ሀሳብ ያቀረበ ሲሆን በክርክር ይዘትም ሲታይ የሶስቱም ተመሳሳይነት የሚታይበት ነው።
ተጠራጠሪዎቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ችሎት ቀርበው ፖሊስ በጠየቀው እና ፍርድ ቤቱም በፈቀደው የ10 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ውስጥ ፖሊስ ያከናወናቸውን ተግባራት ዳኛው በመጠየቅ የተጀመረው ይህ ችሎት ከፖሊስ የተገኘው ምላሽ፣ “ተጠርጣሪዎቹ የተፃፋፏቸውን ፅሁፎች ለማስተርጎም በሂደት ላይ መሆናቸውን፤ የምስክሮችን ቃል ለመቀበል የማስፈራራት ሁኔታ በመግጠሙ አዳጋች መሆኑን፤ ቀሪ ግብረአበሮችን በአድራሻ መለዋወጥ ምክንያት አለመያዛቸው በመጥቀስ ለዚህም ድርጊቱ በቡድንና በህቡዕ የሚከናወን መሆኑን ለፍርድ ቤቱ አስረድቶ ሊፈፀም የታቀደው የሽብር ተግባር ነው ሲል ተጨማሪ 28 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።
በተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች በኩልም፤ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ካዋለ 23 ቀናት ቢልፉም ምንም አዲስ ነገር አለመፈፀሙን በመጠቆም፤ ሲጀመር ለጥርጣሬው ዋና ምክንያት አድርጎ ያቀረበውን በማህበራዊ ድረ-ገፅ ላይ መፃፍ የሚል ሃሳብ ቀይሮ የሽብር ተግበራ ፈፅመዋል ማለቱ አዲስ እንደሆነባቸው፤ ለዚህም ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ከመዝገቡ መርምሮ በመደበኛ የወንጀል ህግ ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጥ አሳስበዋል። አያይዘውም መርማሪ ቡድኑ በመዝገቡ በይፋ የጠቀሰው ኢትዮጵያም ሆነ አለማቀፋዊ የሽብር ድርጅት አለመኖሩን በማስታወስ ተጠርጣሪዎቹ ስልጠና ወስደዋል ከተባለም የአሜሪካና የእንግሊዝ መንግስታት እውቅና ከሰጧቸው “አርቲክል 19” እና “ፍሪደም ሀውስ” ከተባሉ ድርጅቶች እንደሆነ፣ እነዚህም በአለም አቀፍ ደረጃ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ላይ የሚሰሩ ሕጋዊ ተቋማት ናቸው ሲሉ አስታውሰዋል።
ፖሊስም በሰጠው ምላሽ፤ ድርጊቱ በቡድንና በህቡዕ የተፈፀመ መሆኑን፤ ምስክሮች ቃላቸውን እንዳይሰጡ በተጠርጣሪዎቹ ግብአበሮች ዛቻና ማስፈራሪያ እየተፈፀመባቸውና አድራሻቸውን እንዲቀይሩ መደረጋቸው ቃላቸውን ለመቀበል አዳጋች እየሆነበት መምጣቱን፤ ከተጠርጣሪዎቹ ኢሜይሎች የተገኙት ማስረጃዎች አስተርጉሞ ለማቅረብ በሂደት ላይ መሆኑን እና በዳታ ክፍሉ ውስጥ ፖሊስ ያለው ኮምፒዩተር አንድ ብቻ በመሆኑ በኢሜይል የቀረቡትን ፅሁፎች መርምሮ ለመጨረስ እንቅፋት እንደሆነበት ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።
የግራ ቀኙን ሀሳብ የመረመረው ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ባለፈው የተሰጠውን የ10 ቀናት የምርመራ ጊዜ ቀጠሮን በሚገባ እንዳልተጠቀመበት አስታውሶ፤ ነገር ግን መዝገቡ ከሽብር ድርጊት ጋር የተያያዘ ለጥርጣሬ የሚያበቃ በቂ ምክንያት አለኝ ካለ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሊሰጠው ይገባል በሚሉት በሁለቱም መዝገቦች ላይ የ28 ቀናትን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል። በመሆኑም ተጠርጣሪዎቹ ሰኔ 7 ቀን በ2006ዓ.ም እንዲቀርቡ ታዟል።
በተያያዘም በማግስቱ እሁድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው ሶስተኛ መዝገብ በጦማሪያኑ አቤል ዋበላ፣ በፍቃዱ ኃይሉና ማህሌት ፋንታሁን የቀረቡ ሲሆን በችሎቱ የተሰየሙት ዳኛ ከመቀየራቸው ውጪ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን አባላቱ ከቅዳሜው መዝገብ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሃሳብ የያዘ ደብዳቤ በማቅረብ ጉዳዩን ለመመርመር ተጨማሪ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ፍ/ቤቱን ጠይቋል።
ፖሊስ በተሰጠው የጊዜ ቀጠሮ ውስጥ ስላከናወናቸው ተግባራት በፍርድ ቤቱ ሲጠየቅ፤ “ፖሊስ ወረዳቸውን ተቀብሎ ኢሜይላቸውን ፈትሸናል። ከዚያም ውስጥ ከሽብርተኛ ድርጅት ጋር የተፃፃፉትን መልዕክት አግኝተናል” የሚል ምላሽ ሰጥቷል። ያም ሆኖ ይህ አገኘነው የሚሉትና የተላኩትን መልዕክት ከመዝገቡ ጋር መያያዝ አስመልክቶ ፍርድ ቤቱ ላቀረበው ጥያቄ ፖሊስ፤ አለማያያዙን ተናግሯል። ይህን ተከትሎም ዳኛዋ፣ “መዝገቡ እንደሚያሳየው መጀመሪያ ሲከፈት ከተከፈተበት የጥርጣሬ ምክንያት በተለየ የጠቀሳችሁ አዲስ ነገር የለም” በሚል በፖሊስ ከሽብር ሕጉ ጋር በማገናኘት የጠየቀውን የ28 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ውድቅ በማድረግ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለግንቦት 24 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጥሯል።
በሁለቱም ቀናት በፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በርከት ያሉ የተጠርጣሪዎቹ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመድ፣ የአገር ውስጥና የውጪ ጋዜጠኞች እንዲሁም አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ተገኝተው ነበር።

No comments: