Monday, February 3, 2014

በነአቡበከር መሀመድ የክስ መዝገብ የመከላከያ ማስረጃ ለመከታተል የተያዘው ቀጠሮ ወደ መጋቢት 20 ተሸጋገረ።

Feb 3/2014
18 ተከሳሾች ያሉበት ይህ መዝገብ ዛሬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት ቃሊቲ ነበር ሊታይ ቀጠሮ ተይዞ የነበረው።ተከሳሾቹ በጠበቆቻቸው አማካኝነት ከ400 በላይ የሚሆኑ የመከላከያ ማስረጃዎችን ማዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።
ከሳሽ የፌደራል አቃቢህግ አቀራረባቸውን አስመልክቶ ለፍርድ ቤቱ ተቃውሞ ያቀረበ ሲሆን ፥ ማን ለማን እንደሚመሰክር እና ጭብጡን እንዲያቀርቡ ጠይቋል።ግራ ቀኙን የመረመረው ፍርድ ቤቱ የአቃቢህግን አቤቱታ በመቀበል ጭብጥ አስይዙ ብሎ ሲበይን ፥ የተከሳሽ ጠበቆች ይህን ለማድረግ የአንድ ወር ጊዜ ጠይቀዋል።ችሎቱ የራሱን የጊዜ ሰሌዳ ከግምት ውስጥ በማስገባት ፥ በብይኑ መሰረት መዝገቡን ለመመልከት ለመጋቢት 20 2006 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

No comments: