Monday, February 17, 2014

ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በባህር ዳር ከተማ – የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም

February 17/2014

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፣ በባህር ዳር ከተማ የካቲት 16 ቀን ፣ ከመኢአድ ጋር በመሆን በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ፣ የባህር ዳር እና የአካባቢዉ ሕዝብ፣ በነቂስ እንዲወጣ፣ ከፍተኛ የቅስቀሳ ዘመቻ እንደተጀመረ የሚገልጹ ዘገባዎች እየደረሱን ነዉ።
bahir_dar
«አንድነታችን ከልዩነቻትን በላይ ነው» ፣ «የአማራዉን ሕዝብ ያዋረዱ የብአዴን/ኢሕአዴግ ባለስልጣናት ለፍርድ ይቅረቡ» «ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በባህር ዳር ከተማ የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም፣ ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ» የሚሉ አባባሎችን የያዙ ፣ በኮከብ የለሽ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ያሸበረቁ፣ ፖስተሮች ተዘግጅተዉ እየተበተኑ ሲሆን፣ በሶሻል ሜዲያዎችም ዘመቻው የተጧጧፈ ይመስላል።
የባህር ዳር ከተማ፣ ከአዲስ አበባ ቀጥላ አለች የምትባል፣ ትልቅ ከተማ እንደመሆኗ፣ በዚያም ደግሞ የሚገኘዉ የብአዴን ኢአሕዴግ አፈናና ጫና በጣም ከባድ በመሆኑ፣ የስለፍ አስተባባሪዎች ትልቅ መስዋእትነት እየከፈሉ በቆራጥነትና በድፍረት ሥራ እየሰሩ እንደሆነ የሚናገሩት ያነጋገርናቸው አንድ የፓርቲው አመርር አባል፣ በተቀረዉ የኢትዮጵያ ግዛት፣ እንዲሁም በዉጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮዮጵያዊያን፣ ከባህር ዳር ሕዝብ ጎን እንዲሰለፉ ጥሪ አቀርበዋል።
በአካል እንኳ መገኘት ባይቻልም፣ በጸሎት፣ በምክር፣ በሶሻል ሜዲያ በሚደረጉ ቅስቀሳዎች፣ እንዲሁም በገንዘብ መደገፍ እንደሚያስፈልግ የገለጹት የአመራር አባሉ፣ «ይህ አይነቱ እንቅስቅቅሴ ዉጤት ሊያመጣ የሚችለዉ ሁሉም ሳይፈራና ሳይሸማቀቅ፣ የድርሻዉን ሲያበረክት ብቻ ነዉ» ሲሉ ጠንከር ያለ አስተያየት ሰጠዋል።

No comments: