Saturday, February 15, 2014

አቶ አስራት ጣሴን ወህኒ ቤቱ አልፈታም አለ

February 15/2014

በትላንትናው ዕለት በሁለት አመት ገደብ የአምስት ወር እስራት ተፈርዶባቸው እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ቢሰጥም የቂሊንጦ ወህኒ ቤት አቶ አስራትን እስከ ሰኞ እንዳይለቅ መመሪያ እንደደረሰው ማንነታቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የቂሊንጦ ወህኒ ቤት ሃላፊ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡
በዛሬው እለት የአቶ አስራት ጣሴን ከእስር መውጫ ወረቀት ይዘው ቂሊንጦ የተገኙት የአንድነት ፓርቲ አባላት ከወህኒ ቤቱ ቀና ምላሽ አላገኙም፡፡ የወህኒ ቤቱ ሃላፊዎች ከእስር መውጫ ወረቀቱን ለያዙት የአንድነት አባላት “እናንተ ያመጣችሁትን ወረቀት አንቀበልም እኛ ራሳችን ሄደን ማምጣት ነው የምንፈልገው” ብለዋቸዋል፡፡ አንድ ማንነታቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የቂሊንጦ ወህኒ ቤት ሃላፊም በስልክ ለፍኖተ ነፃነት “አቶ አስራት ቅዳሜና እሁድንም በእስር እንዲያሳልፉ መመሪያ ተሰጥቷል፡፡” የሚል አስገራሚ መረጃ ሰጥተዋል፡፡

አቶ አስራት ያልታደሙበትን ችሎት “ዘልፈዋል” በሚል ህገወጥ ክስ መቀጣታቸው ይታወቃል፡፡
1932304_592068054211466_1461382284_n

No comments: