![](https://blogger.googleusercontent.com/img/b/R29vZ2xl/AVvXsEgvdMd7BnV-InYWMCEEW4sSYnKWljKd8H-vlKamVixJLFWr17T-EZTaF-mqYNdC7FEfkFfid9A9I-vXMAxQLAc8KDaxema2d2PJozVCwczAAObXijKTYbLYKe-6Iin8X-lv7jY0cL3_Ckk/s1600/BeFunky_BeFunky_CIMG1882.jpg.jpg)
መቼ ነው የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት በዚህ ርኩስ ባህሪውና ድርጊቱ የሚቀጥለው ?
ገዛኸኝ አበበ
![](https://blogger.googleusercontent.com/img/b/R29vZ2xl/AVvXsEhDArpFOWM8GXIot40tWsE3OWXFR7xRraUZP_AzYu0XmbpNyPXCMggde59OHXHcWpTcaS7tkT0iJJ8qwJD802yfq7Aag4Eh4jhuXTTFRei856MhSX7_LFrq6yEVVdSdau7cLdRBCMGFh7A/s1600/last+ned+(2).jpg)
ወያኔዎች እኔ ከሞትኩኝ ሰርዶ አይብቀል እንደሚባለው የሀገሬቱን ሀብት እየዘረፉ እና እየቦጠቦጦ እንዳሻቸው መኖርን አልበቃም ብሏቸው ቅንጣትም ያክል ስለ ኢትዮጵያም ቢሆን ስለ ኢትዮጵያዊነት ግድ እንደሌላቸው በሚያሳይ መንገድ በማን አለብኝነትና በግድ የለሽነት ለግል እና ለእራሳቸው የፖለቲካ ጥቅም ቀደምት አባቶቻችን ለሀገራችን ዳር ድንበር መስዋዕት የሆኑለትን እና ደማቸውን ያፈሰሱለትን መሬታችንን ድንበራችንን እንኮን ሳይቀር ለባህድ አገራት በመስጠት ላይ እንዳሉ ሲሰማ ማንንም ኢትዮጵያዊ የሆነ ዜጋ ሁሉ የሚያስቆጣ እና የሚያንገበግብ ነው ብዬ አስባለው:: በጣም የሚገርመው እና የሚያሳዝነው ነገር ወያኔዎች የገዛ ወገኖቻችንን የሀገሪቱን ዜጓች ሀብት እና ንብረት ካፈሩበት ሀገርና መሬት ላይ ሀብትና ንብረታቸውን እየዘረፉና ቤታቸውን እየፈረሱ ከሚኖሩበት ቄዬ እያባረሩ ለውጭ አገር ሰዎች ደግሞ የሀገሬቷን መሬት እየቸበቸቡ መኖርን የለመዱበት ተግባራቸው መሆኑ ነው ::
እያደር ብዙ ይሰማል እንደሚባለው የወያኔን መንግስት አሁንም ዝም ካልነው ሌላ ብዙ አስርት የመከራ አመታትን መጋፈጥ ሊኖርብን ነው፡፡ እስከመቼ ዝም እንደ ምንለው ግን ወገን አይገባኝም ፡፡ ወያኔ እያደረገው ስላለው አረመናዊ ድርጊት ፋታ ልንሰጠው አይገባም :: አሁንም ህፃን፤ ወጣት፤ ጐልምሳና አዛውንት ወገኖቻችን ሲረግፍ፤ ሲሰደዱ ፣ የኢትዮጵያ ገጽታ ሲበላሽና ፣ በደምና በአጥንት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየውን የሃገራችንን ዳር ድንበር የወያኔ መንግስት ለባዕድ አሳልፎ ሲሰጥ ማየት ከሆነ ህልማችን መልካም! ግን ይህንን የሚያልምም ሆነ የሚመኝ ንፁህ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም፤ ከራሳቸው ከወያኔ ሆድደር ካድሬዎች በስተቀር፡፡ ስለዚህ ወገኔ ሆይ ይህንን መንግስት ዝም ብለን ልናየው አይገባም፡፡ ወይም እንደ ፈለገ ሊፈነጭብን ቦታ መስጠት የለብንም፡፡ እስካሁን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሰው ጭቆናና በደል እንዲያውም በምን አለብኝነት የኢትዮጵያን ቅርጽ እና ታሪክ የሚያበላሸውን የወያኔ እንቅስቃሴ ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጋ ዘር፣ ጎሳና ፆታ ሳይለይ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውነትን እያጠፋ ባለው በወያኔ መንግስት ላይ ሆ ብለን በአንድነት በመነሳትና በመጮህ ይበቃል ልንለው እና ልናስቆመው የግድ ነው፡፡
በቃ በቃ በቃ !!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!!
No comments:
Post a Comment