Friday, February 28, 2014

በኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮጵያኖች በዛሬው እለት ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ (ከገዛኸኝ አበበ ኖርዌይ)

February 28/2014



























ዛሬ የካቲት 21/2006 ዓ ም እለት በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች ከተለያየ ስፍራ በመሰባሰብ ደማቅ እና ደስ የሚል ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ሲያደርጉ ውለዋል :: በዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የኢሳት ቲሊቨዥን ጋዜጠኞች የሆኑት ጋዚጠኛ ደረጄ ሀብተወልድ ከኒዘርላንድ  እና ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀጸላ ከለንደን የተገኙ ሲሆን እነኚህ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች በጊዜው የነበረው ብርድ እና ዝናብ ሳይበግራቸው ድምጻቸውን ሲያሰሙ ውለዋል:: ሰላማዊ ሰልፉ በሁለት አላማዎች ላይ በማተኩር የተደረገ ሲሆን ረዳት ፓይለት ሃይለመድን አበራን በመደገፍ እና የወያኔ መንግስት የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን አሳልፉ እየሰጠ ያለውን ድርጊት በመቃወም ነበር::

የመጀመሪያው ሰላማዊ ሰልፍ ሕዝቡ በቀኑ አስራ ሁለት ሰአት ኦስሎ በሚገኛው ሲውዘርላንድ ኢንባሴ በመገኛት የተጀመረ ሲሆን የሰልፉም ወና አላማ የነበረው የሲውዘርላንድ መንግስት ረዳት ፓይለት ሃይለ መድህን አበራ ለአረመኔው የኢትዮጵያ መንግስት አሳልፎ እንዳይሰጥ እና ረዳት ፓይለት ፓይለት ሃይለ መድህን አበራ በሲውዘርላንድ መንግስት የፖለቲካ ጥገኝነት እንዲያገኝ ለመጠየቅ ሲሆን በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተለያዩ መፈክሮች  ተሰምተዋል  ከነዚህ ውስጥም ጥቂቶቹ ሃይለ መድህን ሰላማዊ እና ንጹህ ሰው ነው ስለዚህ  ሲውዘርላንድ መንግስት ጥገኝነት እንዲሰጠው ሃይለ መድህን ጀግና ነው በጭቆና እና በመከራ ውስጥ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ መከራ ለማሳየት  ሲል ነው ወጋ የከፈለ እንጂ ወነጀለኛ አይደለም እና ሌሎችንም መፈክሮች ሲያሰማ ውለዋል::


በመቀጠለም ጕዞቸውን ወደ  ኖርዌይ የወጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በማድረግ   አባቶቻችን ደማቸውን ያፈሰሱበትን የኢትዮጵያጵያን መሬት እና ድንበር የወያኔ መንግስት ለሱዳን አሳልፈው እየሰጡ ያለውን ተግባር በማውገዝ የተለያዩ መፈክሮች ያሰሙ ሲሆን የኖርዊይ መንግስትም ይህን አረመኔ እና ለሀገሩ ለድንበሩ እና ለገዛ ለሕዝቡ ደንታ የሌለውን የወያኔ መንግስት ከመርዳት እንዲቆጠብ ጠይቀዋል ::

የኖርዌይ መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የጠበቀ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳለው እና የወያኔንን መንግስት በገንዘብ ከሚረዱ ሀገሮች ግንባር ቀደሞ ኖርዌይ መሆኖ ይታወቃል::


No comments: