Friday, December 6, 2013

ድብልቅልቁ የወጣው ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ኢህአዴግን ጨርቁን አስጥሎታል፡፡

December 5/2013

ፋሽስቶች ለኢትዮጵያውያንና ለሌሎች ካልሆነ በስተቀር ለአገራቸው ህዝብ ክብር ነበራቸው፡፡ እነ ሌኒንም ቢሆን ለአገራቸው አንድነት እንጅ ተገንጣይነት አልሰሩም፡፡ አረቦቹ ለአገራቸው ጥቅም ሲሉ ነው ኢትዮጵያን ይጠሉ የነበሩት፡፡ የአስተሳሰባቸው መርዝነት ለእኛ እንጅ ለራሳቸው ህዝብ አልነበረም፡፡ ምንም ያህል ቢያብዱና ቢሰክሩ ለአገራቸው ህዝብ ክብር ነበራቸው፡፡ ለብሄራዊ ጥቅማቸው ይጨነቁ ነበር፡፡ በግራዚያኒ ላይ የጣሊያን ግራ ዘመም ፓርቲዎች በነጻነት ተቃውሞ አሰምተው በሰላም ገብተዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን ግንወገኖቻቸው በተጨፈጨፉበት ጎዳና እንደገና ተደብድበዋል፡፡ ታስረዋል፡፡ ይህ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ የተለከፈ መንግስት ከያኔው ጨፍጫፊዎችም በላይ ይሆንብኛል፡፡ ስካር ሱስ ነው፡፡ 
በሽታም ጭምር፡:

 እንዲህ የጠደባለቀ መርዛማ አልኮል መጎንጨትን ልማዱ ያደረገ ድሮ ሰክሮ የሚሰራውን ጉዳይ ምሎና ተዘክሮ እተዋለሁ ቢልም የሚሰራው ግን ያው የስካሩን፣ የእብደት ተግባሩን ነው፡፡ ለግራዚያኒ የቆመው ኢህአዴግ ከውስጥም ከውጭም ተቃውሞ ሲገጥመው ስህተቱ ስካሩ መሆኑን ሳይረዳው ቀርቶ አይደልም፡፡ ግን ለሳውዲዎች ቆሞ ደገመው፡፡ ድብልቅልቁ የወጣው ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ግን ኢህአዴግን ጨርቁን አስጥሎታል፡፡ ለዛም ነው ይህን ያህል ያበዱት የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› የአልኮል መጠን ስንት ቢሆን ነው?›› ብየ የጠየቁት፡፡ ከወራት በፊት ለግራዚያ ሲቆም አብዮታዊ ዴሞክራሲ ምን ያህል እንደሚያሰክር፣ እንደሚያሰብድ አሰይቶናል፡፡ ይህ ከእነ ሞሶሎኒ የተወሰደው የአልኮል ክፍል መሆኑ ነው፡፡ ከሳምንታት በፊት ኢትዮጵያውያንን በአረብ ዱላ ገረፈ፡፡ ይህኛው ከአረቦቹ ጥላቻ የተዘነቀው የአብዮታዊ ዴሞክራሲ አልኮል ነው፡፡ አሁን ደግሞ የአጤ ምኒልክን ሙት አመት አታከብሩም ብሎ ከልክሏል፡፡ ይህኛው የሁሉም ውጤት ነው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ መጨረሻ ቀላቅሎ ያለ አቅሙ አይኑን ጨፍኖ የተጎነጨው ይህኛውን አልኮል ነው፡፡ ጸረ ኢትዮጵያውይነት! የአሁኑ ጣሊያኖች የምኒልክ ታሪክ እንዳይወደስ የሚፈልጉበት ምንም አይነት ምክንያት የለም፡፡ እነ ሌኒን በሚሉት መልኩ ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› የሚባለው አገራችን ውስጥ የለም፡፡

 የስታሊን ጠባብ ብሄርተኝነት፣ የምዕባራዊያኑ ‹‹ካፒታሊዝምና ዴሞክራሲ›› በስም ደረጃ፣ የአልባኒያና የቻይና አምባገነንነት፣ የሻዕቢያና አረብ አገራት ጥላቻ፣ የሞሶሎኒ ፋሽዝም……ተደባልቀው የተሰራ ውጥንቅጡ የጠፋበት ‹‹ርዕዮት ዓለም›› ነው፡፡ የአሁኑ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ከሁሉም ጎን የወሰደው መጥፎ ጎናቸውን እንጅ መልካሙን አይደለም፡፡ እነዚህ የየዘመኑን ትውልድ ያሰከሩ አስተሳሰቦችን መጠናቸውን ሳያውቅ የደባለቀው አብዮታዊ ዴሞክራሲ ከአልኮንነትም አልፎ መርዝ ወደመሆን ደርሷል፡፡ አልኮል ብቻውን ከሚወሰደው በላይ ሲደባለቅ ያሰክራል፡፡ ያሳብዳልም፡፡ አሁን ደገሞ ለድሮዎቹ፣ አድዋ ላይ ለተሸነፊት ጣሊያኖች ቆሞ ከለከለ፡፡ ኢህአዴግ ከአረቦቹ፣ ከፋሽስቶቹ፣ ከእነ ስታሊን….የደባለቀውን የውስጡን ጥላቻ በአብዮታዊ ዴሞክራሲው አልኮል አወጣው፡፡ ይህን ታዲያ ከስካርና ከእብደት ውጭ ምን ይሉታል? እኔ ይህን ናላ አስቶ፣ ጨርቅ አስጥሎ በአገር ህዝብ ላይ የሚያዘምት፣ ህዝብ ላይ የሚያስጨክን፣ ብሄራዊ ጥቅምን የሚያስጠላ ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› የአልኮል መጠኑን መገመት አልቻልኩም፡፡ ከመጠን በላይ መሆኑን፣ መርዛማነቱ ማመዘኑን ከመገመት ውጭ! ግን ኢህአዴግ እስከመቼ እንዲህ ጨርቁን ጥሎ ይዘልብናል?

 ሚኒልክ ሳልሳዊ  አትላንታ

No comments: