Friday, December 27, 2013

ብኣዴን – የሕወሓት አሽከሮች እና ለውጥ ፈላጊዎች ተፋጠዋል::

December26/2013

 :በቅርቡ ጠቅላላ ጉባዬ ሲጠራ የደፈረሰው ይጠራል ተብሎ ይጠበቃል::
የጄነራል አበባው ስልክ መጠለፍ አሁንም በጦር ሰራዊቱ ውስጥ ያለውን ሽኩቻ እና ዘረኝነት ያመለክታል::
ምንሊክ ሳልሳዊ :- የሟቹን የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በሕወሓት እና በብኣዴን መካከል ልዩነቶች የሚፈጥሩ ሁኔታዎች ተከስተው አሁንም በስፋት ቀጥለው ይገኛሉ::የተለያዩ የብኣዴን ሰዎችን በሰብብ አስባብ የሚያንጠባጥበው ሕወሓት አሁንም አሽከሮቹን አሰማርቶ ለውጥ ፈላጊዎችን ወደ ገደል ለመግፋት አየተሯሯጠ ነው:: የብኣዴን ካድሬዎች የለውጥ ጥያቄዎች ማንሳታቸውን ተከትሎ ከሕወሓት አሽከር ከሆኑት ጋር በስብሰባ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ስብሰባው እንደተበተነ ታውቋል::
FDRE States flags
በዚህ ሳምንት ውስጥ ሁለት ግዜ የካድሬዎች ስብሰባ ተጠርቶ የመጀመሪያው በሕወሓት አሽከሮች እና በለውጥ ጠያቂዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ስብሰባው ሲበተን ...ለሁለተኛ ጊዜ የተጠራው ስብሰባ በከፊል ካድሬዎቹ ስላልመጡ ለሚመጣው ሳምንት የተላለፈ መሆኑን ታውቋል::በሕወሓት አሽከሮች እና በብኣዴን ለውጥ ፈላጊ ካድሬዎች መካከል የተነሳው ፍጥጫ የሕወሓት አመራሮች በሃይል ሊፈቱት ይችላሉ የሚል ስጋት ጨምሯል::

አዲስ በወጣው እቅድ መሰረት በአማራው ክልል በድጋሚ አዲስ የፓርቲ አደረጃጀት ጥርነፋ እንደሚደርግ እና በዚህ መካከል አስቸጋሪ እና አድመኞች የጸረ ሰላም እና የጸረ ሕዝብ ሃይሎችን የመደምሰስ እንዲሁም በአዲሱ የፓርቲ አደረጃጀት ውስጥ አስፈላጊው ጥቅማጥቅሞችን ለአዳዲስ አባላት መስጠት የሚል ይገኝበታል::ውስጥ ውስጡን እየቀሰቀሱ ችግር በፓርቲው ላይ የሚፈጥሩ ካድሬዎችን በማስወገድ በአዳዲስ መተካት የሚሉ እቅዶች ተይዘዋል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሕወሓት የጦር መኮንኖች የአማራ እና በኦሮሞ ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ዘረኝነት እያራመዱ መሆኑ ታውቋል:: የተለያዩ ማእረጎች የስልጣን እርከኖች እና ወታደራዊ ጥቅማጥቅም የሚሰጠው ትግሪኛ ተናጋሪ ለሆኑ ብቻ ነው ሌሎቹ ምንም የሚወረወር ፍርፋሪ የላቸውም::በሰራዊቱ ውስጥ ዘረኝነት መንሰራፋቱ እንዲሁም አደርባዮች መስፋፋታቸው አስፈላጊውን ለውጥ እንዳይመጣ ያደረገው መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል::ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዜና ጄኔራል አበባውን ጨምሮ የቀድሞ የብኣዴን ታጋዮች እና የዛሬ የጦር ሰራዊቱ መኮንኖች ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት ሊፈጥሩ ይሽላሉ በሚል ስልካቸው ተጠልፎ እንደነበር ታውቋል:: የከፍተኛ መኮንኖቹ ስልክ መጠለፉ እንደታወቀ እሰጥ አገባዎች የተደረጉ ሲሆን ስብሰባ ይጠራል ያሉት የሕወሓት ጄኔራሎች አስካሁን ዝምታን መርጠዋል:; ይህ በሰራዊቱ ውስጥ የተንሰራፋው ሽኩቻ እና ዘረኝነት ተስፋፍቶ መቀተሉን ያመለክታል ሲሉ ምንጮቹ ተናግረዋል:: በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ሰፋ ያለ ዘገባ ይቀርብበታል::

No comments: