Wednesday, December 25, 2013

በስዊድን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ላልተወሰነ ጊዜ ተዘጋ

December 25/2013




































(ዘ-ሐበሻ) “ባለፉት ወራት በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ክርስቲያናዊ ያልሆኑ ሥነምግባራቶች በመከሰታቸውና ያለመግባባት በመፈጠሩ፤ ይህን ተከትሎ በማህበረ ምህመናኑ (አባቶች፣ እናቶች፣ ወንድሞች፣ እህቶችና ህፃናት ላይ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ግምት ውስጥ በማስገባት ከነገ ታህሳስ 13 ቀን 2013 (December 21,2013) ጀምሮ መንፈሳዊ አገልግሎቱን ለጊዜው እንድናቋርጥ ተገደናል” ይላል በስዊድን ስቶክሆልም ከተማ ውስጥ የሚገኘው የመንበረ ጸባዖት ቅድስ ሥላሴ ቤ/ክ ደጃፍ ላይ የተለጠፈው ማስታወቂያ።

የዘ-ሐበሻ የስዊድን ዘጋቢ ባስተላለፈው መረጃ መሠረት ቀድሞ ገለልተኛ ሆኖ የተመሠረተው ይህ ቤተክርስቲያን በአንዳንድ መዘምራን እና የማህበረቅዱሳን አባላት አማካኝነት በተነሳ ጥያቄ የዛሬ ሁለት ዓመት የአቡነ ጳውሎስ ስም በቅዳሴ ላይ እየተጠራ ግን በገለልተኛነቱ እንዲቆይ ተወስኖ አቡነ ጳውሎስ ካረፉ በኋላም የ6ኛው ፓትሪያሪክ አቡነ ማቲያስ ስም እየተጠራ በገለልተኛነት ቆይቶ ነበር። እንደ መረጃ ምንጫችን ገለጻ ከ2 ወራት በፊት እንደገና፤ በቤተክርስቲያኑ አንዳንድ መዘምራን እና የማህበረ ቅዱሳን አባላት ባነሱት ጥያቄ ቤተክርስቲያኑን ወደ ኢትዮጵያው ሲኖዶስ ስር ለማስገባት እንስቃሴ ተጀምሮ አሁን ያለው የቤተክርስቲያኑ ቦርድ በአዳዲስ ሰዎች እንዲተካ፣ የሰበካ ጉባኤውም አስተዳደር በአዲስ መልክ እንዲዋቀር፤ እንዲሁም ቤተክርስቲያኒቱ በካህናቱ እንድትመራ ጥያቄ አቅርበዋል።

በእንደዚህ ያለ ሁኔታ ውስጥ ያለው የስቶክሆልሙ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ከገለልተኛነት ወደ ኢትዮጵያው ሲኖዶስ ለማስገባት ውሳኔ እንዲሰጥ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ባለበት በዚህ ወቅት ይህን ተከትሎም በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ቦርዱ በመግለጫው ላይ እንዳለው ክርስቲያናዊ ያልሆኑ ሥነምግባራቶች መከሰትና ያለመግባባትም መፈጠር ጀምሯል።

የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር ቦርድ እና ሰበካ ጉባኤው ይህን አለመግባባት ለማብረድ ቤተክርስቲያኑን ላልተወሰነ ጊዜ መዝጋቱን ያሳወቀ ሲሆን “ወደፊት ያለውን ሂደት ለማህበረ ምዕምናን እና ምዕመናቱ እናሳውቃለን” ብሏል።

No comments: