Sunday, December 29, 2013

መንግስት ይግባኝ ጠየቀ ፣ይግባኙ የተጠየቀባቸው ሰዎችን ስም ዝርዝር ይዘናል

December 28/2013

የደህንነት ሃይሎች በአንዳዶቹ ቤት ሲመላለሱ ነበር :: የጁነዲን ሳዶ ባለቤት ወይዘሮ ሀቢባ መሐመድ በአቃቤ ህግ ይግባኝ ተጠየቀባቸው:: 

መከላከያ ምስክር ሳያስፈልጋቸው በነፃ ከተለቀቁት የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ አባላት እና ወንድሞች መካከል አቃቤ ህጉ ይግባኝ የጠየቀባቸው ሙስሊሞች ስም ዝርዝር ይፋ ሆነ፡፡የፌደራሉ አቃቤ ህግ ፍርድ ቤቱ በነፃ እንዲሰናበቱ ከወሰነላቸው 10 ሙስሊሞች መካከል በ 6ቱ ላይ ይግባኝ እንደጠየቀባቸው ዘግበን ነበር፡፡
በዚህም መሰረት ስም ዝርዝራቸው የደረሰን ሲሆን ከህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች መካከል አንዱ የሆኑት ኡስታዝ ጀማል ያሲን ይግባኝ የተጠየቀባቸው ሲሆን የተቀሩት ደግሞ ሼህ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ሼህ አብዱራህማን፣ኡስታዝ ሀሰን አሊ፣ወንድም አሊ መኪ እና በ ወ/ሮ ሃቢባ መሃመድ ላይ አቃቤ ህጉ ይግባኝ እንደጠየቀባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
የፊታችን ሰኞም ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
1. ኡስታዝ ጀማል ያሲን
2. ሼህ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ፣
3. ሼህ አብዱራህማን፣
4. ኡስታዝ ሀሰን አሊ፣
5. ወንድም አሊ መኪ እና
6. በ ወ/ሮ ሃቢባ መሃመድ ( የጁነዲን ሳዶ ባለቤት) ላይ የፉደራሉ አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቋባቸዋል፡፡
የዚህ መሰሉ የይግባኝ ድራማ ፍርድ ቤቱ ገለልተኛ እና ነፃ ነው ለማስባለል ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ውድቅ በማድረግ ፍትሃዊ ውሳኔ እንደወሰነ ለማስመስሰል እንደሚጥር ይጠበቃል፡፡
የደህንነት ሃይሎችም በአንዳዶቹ ቤት ሲመላለሱ እንደነበር ምንጮች አክለው ገልፀዋል፡፡

No comments: