Saturday, December 7, 2013

የማንዴላን ስርአተ ቀብር ለማከናወን አስከሬኑ በፕሪቶሪያ ስትሪት ላይ ለህዝብ እይታ ለስንብት ይቀርባል

December 7/2013

በማንዴላ ስርአተ ቀብር ላይ የመጀመሪያው የጥቁር አፍሪካ አሜሪካዊው ፕረዚዳንት ኦባማ እንዲሁም ዲልማ ሮዜፍ በስራተ ቀብሩ ፕሮግራም ላይ ስንብታቸውን ለማድረግ ለጉዞአቸው ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል ፣በዚህ ሳምንት መግቢያ ላይ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚበሩ ተገልጾአል ።
እንደ ደቡብ አፍሪካ መንግስት ገለጻ ከሆነ አስከሬኑ በደቡብ አፍሪካ ዋነኛ አደባባይ ላይ የሚዞር ሲሆን ከዚያም አልፎ በፕሪቶሪያ ጎዳና ላይ ለተወሰነ ሰአት ለህዝብ እይታ ይቀርባል ሲሉ የመንግስት ቃል አልቀባይ የሆኑት ኒዮ ሞሞዱ ተናግረዋል ።
የማንዴላ አስከሬን ለተወሰነ ሰአት የሚቆየው በስቴት ዩኒየን ህንጻ ላይ በሚገኘው ሰፊ ጎዳና ላይ ሲሆን ይህም ሮብ ሃሙስ እና አርብ ቀናቶች ብቻ ልህዝብ እንደሚቀርብ አክለው ገልጸዋል ።ይህም ሲሆን በ95 አመታቸ የአረፉበትን የኔልሰን ማንዴላን የሙት ቀናት አስሩን ቀናቶች የመታሰቢያ ቀን ተደርገው እንደሚታሰቡም አያይዘው የገለጹ ሲሆን በመቀጠልም 90.000 ሰዎችን እና ከዚያም በላይ ይይዝል ትብሎ የሚታሰበው የስዌቶ ስታዲየም የቀጣዩን የመጨረሻውን የመሰናበቻ ፕሮግራም ያከናውናሉ ሲሉ የመንግስ ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።ይህም ስታዲየም በ2010 የመጨረሻውን የአለም አቀፍ እግር ኳስ የተከናወነበት ሜዳ ሲሆን ማንዴላም ከህዝብ ጋር ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የታዩበት (የተሳተፉበት )ሜዳ ነው ።
በዚህ አጋጣሚ የተለያዩ የአለም መንግስታቶች የሃዘን መግለጫቸውን እየላኩ ሲሆን የኡናይትድ ኔሽን ፕረዚዳንት ባንኪ ሙን እና የደቡብ ኮሪያው ፕረዚዳንት ዛሬጠዋት መል እክታቸውን አስተላልፈዋልእንደ ማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል መሰረት ከሆነ፣
የመጀመሪያው የአሜሪካው ጥቁር ፕረዚዳንት እና የቀድሞው የአሜሪካ ፕረዚዳን ጆርጅ ደብሊው ቡሽ ከባለቤታቸው ጋር ላውራ ቡሽ ወደ ደቡብ አፍሪካ አብረው በአየር ፎርስ በተሰኘው ፕሌን በመጭው ሳምንት ለቀብሩ እንደሚበሩ ዋይት ሃውስ አስታውቆአል በሌላም በኩል የቀድሞው የአሜሪካው ፕረዚዳንት እና በወቅቱ ኔልሰን ማንዴላ ስልጣን ሲይዙ በፕረዚዳንትነት ስልጣን ላይ የነበሩት ቢን ክሊንተን ጉዞ ለማድረግ ወስኛለሁ በቦታውም ላይ እገኛለሁ ሲሉ መደመጣቸውን የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጄይ ካርኒ ገልጾአል ።ስለ ባራክ ኦባማ አጠቃላይ መግለጫ ሰሞኑን ይሰጣል ።በሌላም በኩል የብራዚል ብቸኛ ሴት ፕረዚዳንት ዲልማ ሮዜፍ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ደቡብ አፊካ እንደምታመራ ከቢሮዋ የወጣው መረጃ ያመለክታል ።
የመታሰቢያ ፕሮግራሙ ከነገ ጀምሮ ይጀመራል ደቡብ አፍሪካዎችም ተጋብዘዋል ቤተ ክህነቶች ፣የእስልምና መስጂዶች መጅሊሶች እንዲሁም ሌሎችም ህዝቦች በቦታው ላይ ተገኝተው ጸሎቶቻቸውን እንዲያደርጉ ጥሪው ከደቡብ አፍሪካ መንግስት ለህዝብ በመገናኛ ብዙሃን መተላለፉን የማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ይጠቁማል ።

No comments: