Thursday, March 13, 2014

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ግምገማ

march13/2014

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ያተኮረ ውይይት ጄኔቭ ስዊትዘርላንድ ውስጥ ዛሬ ተካሂዷል ። የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ባዘጋጁት በዚሁ ውይይት ላይ በኢትዮጵያ ይፈፀማሉ የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በዝርዝር ቀርበዋል።
Karte Äthiopien englisch
መንግሥት የሰብዓዊ መብት አያያዙን እንዲያሻሽል ያግዛሉ የተባሉ ሃሳቦችም ተሰንዝረዋል ። በስበሰባው ላይ የተካፈሉት የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች ለተሰነዘሩት ወቀሳዎች የበኩላቸውን መልስ መስጠታቸው ተገልጿል ።በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ያተኮረው ውይይት ዛሬ የተደረገው ከ25,ተኛው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጉባኤ ጎን ለጎን ነው ። የውይይቱ ዓላማም በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ያተኮረ ዝርዝር ዘገባ ለተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በመጪው ግንቦት ከመቅረቡ አስቀድሞ ስለሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው ። ስበስባውን ካዘጋጁት ዓለምዓቀፍ ድርጅቶች አንዱ መቀመጫውን ጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪቃ ያደረገው ሲቪኩስ የተባለው ድርጅት የፖሊሲና የጥብቅና ጉዳዮች መኮንን ቶር ሆድንፌልድ ስብሰባው በተለይ በሶስት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መወያየቱን ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።
ከነዚህም እጎአ በ2009 ዓም የወጣው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራት ህግ አንዱ ነው ። ህጉ ከባድ ተፅዕኖ ማሳደሩና መዘዞቹም በውይይቱ መነሳታቸውን ሆድንፌልድ ገልፀዋል ። « በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ መብት ለሚታገሉ ድርጅቶች በሚለገሰው ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ እርዳታ ላይ በተጣሉትን ገደቦች ላይ ተነጋገግረናል በዚህ ህግ ምክንያት በኢትዮጵያ ዓለም ኦቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች አይሰሩም ። በርካታ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶችም ከሰብዓዊ መብት ጋር የተገናኙ ሥራዎች ማካሄድ አቁመዋል ወይንም ከነጭራሹ ተዘግተዋል »
መድረኩ ትኩረት ሰጥቶ የተወያየበት ሌላው ጉዳይ ደግሞ ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት ላይ ያደርጋል የተባለው ጫና ነበር ።
«ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከተገቢው የህግ ሂደት ውጭ እንዲሁም በልዩ ደንቦች ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት ላይ የተጣሉትን ገደቦችም በውይይቱ ተነስተዋል ። በተለይ ስብሰባው በኢትዮጵያ 12 ጋዜጠኞች በቨረ ሽብሩ ህግ ምክንያት መከሰሰሳቸውኢትዮጵያ ውስጥ በህጋዊ መንገድ የጋዜጠኝነት ተግባራቸውን ሲያከናውኑ ርዕዮት ዓለሙና እስክንድር ነጋ የመታሰራቸውም ጉዳይ ላይም ትኩረት ሰጥቶ ተነጋግሯል ።
ሆድንፌልድ እንደሚሉት በውይይቱ በኢትዮጵያ የነጻ ሚዲያ መገደብም ተነስቷል ። በጎርጎሮሳውያኑ 2012 5ጋዜጦች መዘጋታቸው በአሁኑ ሰዓትም ኢንተርኔ ት ከሚጠበቀው በላይ ቅድመ ምርመራ ይካሄድበታል ዓለም ዓቀፍ መገናኛ ብዙሃንንና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችን የሚያነሱ ድረገፆች በኢትዮጵያ እንዳይሰሙና እንዳይታዩ በመንግሥት ይታገዳሉ ሲሉ ተወያዮቹ መገለፃቸውን ተናግረዋል ሆድንፌልድ የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ መብት አያያዙን እንያሽሽልም ሃሳቦች ተሰንዝረዋል ።
« 2009 ዓም የበጎ አድራጎት ና የሲቪክ ማህበራት መተዳደሪያ ደንብ እንዲሰረዝ ወይም እንዲሻሻል ሁለተኛ የፀረ ሽብር ህግ በደል መፈፀሚያና ጋዜጠኖችን ማፈኛ እንዳይሆን እንዲሰረዝ በፀረ ሽብሩ ሕግ ምክንያት የታሰሩ ጋዜጠኞችና የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች በሙሉ እንዲፈቱ እንዲሁም ተቃዋሚዎችና ሰላማዊ ሰልፈኞች ከሚቀጥለው ዓመት ምርጫ በፊት የመሰብሰብ መብታቸውን እንዲጠቀሙ እንዲደረግ ሃሳብ ቀርቧል ።»
ዶቼቬለ ስለ ውይይቱ ና ስለተሰጡት አስተያየቶች የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮችን ለማነጋገር ያደረገው ሙከራ አልተሳካም ። ሆኖም በውይይቱ ላይ የተካፈሉት የሰብዓዊ መብት ተመራማሪው አቶ ያሬድ ኃይለ ማርያም ያኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮችለመድረኩ የሰጡትን አስተያየት አጋርተውናል ።
ሂሩት መለሰ
ተኬሌ የኋላ

AUDIOS AND VIDEOS ON THE TOPIC


No comments: