Thursday, December 5, 2013

ከሳውዲ ዓረቢያ ከተመለሱ ስደተኞች መካከል 8 ሺህ ሴቶች ነብሰ ጡር ናቸው ተባለ::


December 5/2013

ከሳውዲ ዓረቢያ ከተመለሱ ስደተኞች መካከል 8 ሺህ ሴቶች ነብሰ ጡሮች መሆናቸውን FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የመካከለኛው ምስራቅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀማል በክር ዋቢ በማድረግ ዘገበ ። 

ከተጠቀሱት ነፍሰጡር እህቶቻችን መሃከል በሪያድ እና በጅዳ የሚገኙ የኮሚኒ ግዜያዊ መጠለያ ከገቡ በሃላ አስገድዶ መድፈር ወንጀል ሳይፈጸምባቸው እንዳልቀረ ምንጮች ገለጹ ።

እስከ ትናንት ባለው መረጃ መሰረት የወንዶች ቁጥር 58 ሺህ 529 ፣ የሴቶች ቁጥር 28 ሺህ 943 ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 8 ሺ ሴቶች ነፍሰ ጡሮች መሆናቸው ታውቋል።

የህጻናት ቁጥር ደግሞ 4 ሺህ 51 መድረሱ ለማወቅ ተችሏል።

በአሁኑ ወቅት ካሳዑዲ ተመላሽ ኢትዮጵያን እንግልት እንዳይገጥማቸው ከመንገዶች ባለስልጣን ጋር በመተባበር ጊዜያዊ መናኻሪያ እንደተቋቋመና ለአብነትም በትናንትናው እለት ብቻ ከ 4 ሺህ 20 በላይ ዜጎች ወደየቅያቸው እንዲመለሱ መደረጉን በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የመካከለኛው ምስራቅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀማል በክር ተናግረዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ አሰሪዎቻቸው ከሚፈጽሙባቸው ግፍ እና በደል ለመታደግ ቀደም ሲል ባዲራቸው ወደ ተሰቀለችበት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት እና በጅዳ ቆንስላ ግቢ ተጠልለው ከነብሩ እህቶቻችን መሃከል ከ 15 በላይ ነፍሰጡሮች መሆናቸው መዘገቡ ይታወሳል ።

እነዚህ ለስራ ወደ ሳውዲ አረቢያ አቅንተው በለስ ያልቀናቸው ወገኖች በተጠቀሱት የኮሚኒት ማዕከላት ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ እየተባለ ማታማታ ባዶ ክፍል ውስጥ ለሰአታት ቆይተው ይወጡ እንደነበር የሚናገሩ ምንጮች በተጠቀሱት እህቶቻችን ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በኮሚኒቲው አላፊዎች አሊያም በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ሳይፈጸምባቸው እንዳልቀረ አክለው ይገለጻሉ። የተጠቀሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ አንዳንድ ወገኖች ጉዳዩን ለማጣራት ያደረጉት ሙከራ በሁለቱም « በጅዳ እና በሪያድ » ኮሚኒት ግቢ ውስጥ ተጠልለው የነብሩ እህቶቻችን የሪያዱን ግርግር ተከትሎ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ ወደ አልታወቀ እስርቤት መወስዳቸው የሚገልጹ የአይን እማኞች ነፍሰጡሮቹ እስካሁን ያሉበትን እና የተፈጸመውን ወንጀል ለማጣራት እንዳልተቻለ ይገልጻሉ።

ይህንን ጉዳይ በተመለክተ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ተጠልለው የነበሩ 12 ነፍሰጡር እህቶቻችን ስም ዘርዝር እና የኢትዮጵያ አድራሻቸው እጃችው እንደገባ የሚገልጹ እንዚህ ወገኖች ወደፊት የእህቶቻችንን ሞራል በማይነካ ሁኔታ እንደአስፈላጊነቱ በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን አሳዛኝ እና ዘግናኝ ድርጊት ለህዝብ ይፋ ለማድረግ ይሞከራል ብለዋል ።

Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

No comments: