Monday, August 5, 2013

የአንድነት ሰልፎች የመጀመሪያ ድሎች መንግስት ከ4 ዓመት በኋላ በፀረሽብርተኝነት ህጉ ላይ የውይይት መድረክ አዘጋጀ

ስኬት አንድ!!!!!!!!!!!! የአንድነት ሰልፎች የመጀመሪያ ድሎች መንግስት ከ4 ዓመት በኋላ በፀረሽብርተኝነት ህጉ ላይ የውይይት መድረክ አዘጋጀ ሪፖርት ጥንቅር በምንሊክ ሳልሳዊ ====================== አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የፀረ ሽብርተኝነት ህጉን ለማሻር የጀመረው የፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ በሀገር ውስጥና በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ማግኘቱንና የመዋያያ አጀንዳ መሆኑን ተከትሎ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ድርጅት ህጉ ከፀደቀ ከ4 ዓመት በኋላ ፓርቲዎች በህጉ ላይ ያላቸውን አቋም የሚያስረዱበት መድረክ አዘጋጀ፡፡

 ኢቲቪ አንድነት ፓርቲን ጨምሮ ለተለያዩ ፓርቲዎች ደብዳቤ የላከ ሲሆን አንድነት ፓርቲ በበኩሉ በ5 የክልል ከተሞች ለሚያደርገው ህዝባዊ ንቅናቄ አመራሮቹን ስላሰማራ የውይይት መድረኩ እንዲራዘምለት ጥያቄ አቅርቧል፡፡ አንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል የጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ በስኬት እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል፡፡

No comments: