Wednesday, August 7, 2013

የተፈናጠረው 11ኛ ሰአት – የወያኔ የመጨረሻው የጥላቻ አጣብቂኝ

 የታሰሩትን መፍታት ለኢሕኣዴግ የፖለቲካ ኪሳራ ያስከትላል::


የታሰሩትን መፍታት ለኢሕኣዴግ የፖለቲካ ኪሳራ ያስከትላል:: ለሊቱን በስብሰባ ተወጥሮ ያደረው ወያኔ መስማማት ተስኖታል:: አደርባዮች እና የድል አጥቢያ አርበኞች ጨንቋቸዋል::ከየተኛው ወገን እንደሚለጠፉ ግራ ገብቷቸዋል::

  የደህንነት እና የህወሓት ወታደራዊው ክንፍ በተጠንቀቅ ላይ ነው:: ባለስልጣናቱ ከውጪው አለም እየተደረገባቸውን ጫና እና ግፊት በፍጹም አንቀበለም የሚል ድምዳሜ ላይ ለመድረስ እርስ በእርስ ሲላተሙ አድረዋል:: ሃገራችን የጥበበኛ ህዝቦች እና የጥበበኛ መሪዎች ሃገር የምትሆንበትን ጊዜ የምንፈልግ እኛ ለውጥ ፈላጊ ልጆቿ ዛሬ ላይን ተቀምጠን ትላንትን የምንመኝ ለነገው ትውልድ የማናስብ በፍርሃት ድባብ ተውጠን ስደትን እና ገንዝእብን የምናሳድድ መሆናችን በመታወቁ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ስልጣኑንን እንዴት አስረዝሞ ሃገር ወዳድ የሆኑ ጠላት የሚላቸውን ኢትዮጵያውያንን ነቃቅሎ የሚያጠፋበት ስልት በቡድናዊ አምባገነንነት እየዶለተ እና በስልጣን ሽኩቻ እርስ በእርሱ እየተባላ ባለበት ወቅት እኛ አንድነት አጥተል በጋራ ዘመም በቀኝ አክራሪ እና ባፈጀ ባረጀ የፖለቲካ ግራውንድ እየተሽከረከርን ህዝብዊ መቆላለፍን ልንፈጥር አለመቻላችን ለአገዛዙ አመቺ አድርጎታል:: እስኪ የወያኔን ስጋት ያነቡ ዘንድ ጋብዘናል::

ከትላንት ሃምሌ 28 ሊነጋ የተበተነው የወያነው የውጥረት ስብሰባ በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ ነበረ ለሊቱን የተጓዘው::እንደቀድሞው እቅዳችን ትራንስፎርሜሽናችን ልማታችን ምናምናችን ዲሞክራሲያችን ሰላማችን የጼረ ህዝቦቻችን ...ምናምን የሚል አልነበረም ..በአተካሮ የተሞላ ውጥረት የነገሰበት አድርባዮች ፍራቻ ይነበብባቸው የነበረበት የነባር ታጋዮች ጩሐት ውይይቱት ደበላልቆት ያደረበት እንደነበር በስብሰባው ላይ የነበሩ የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጭ ተናግረዋል::
የት ከርሞ ከየት እንደመጣ ወዴትስ ሄዶ እንደነበር በማይታወቀው የአምባገነን ቡድን አስተባባሪ በደብረጽዮን የተመራው ይህ አተካራዊ ስብሰባ የወያኔ አባላቱን ለከፍተኛ ፍጥጫ ከመዳረጉም አርፎ ዘለፋ እና ዛቻ እንዲሁም የቀድሞ ጉዳዮች ወቀሳ ያካተተ የነበረ ሲሆን በብኣዴን ነባር አባላት እና በጫካው ሕወሓት እንዲሁም በሕወሃት የከተማ ህዋስ እና በጫካው ሕወሓት መካከል ከፍተኛ የሆነ ጭቅጭቅ ተስተናግዷል:: ዋናው አትኩሮት የነበረው ይላሉ የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ወቅታዊው የአንድነት ፓርቲ እንቅስቃሴ;የሙስሊሙ ጥያቄ; የምእራባውያን ጫና;እና የዲያስፖራው ድጋፍ በተመለከተ ነበር::
የስብሰባው ላይ አነጋጋሪ የነበረው የአንድነት ፓርቲ ጉዳይ በስፋት መንቀሳቀስ በዚሁ ከቀጠለ ካለው የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ችግር አኳያ ህዝቡ ሆ! ብሎ ሊነሳ ስለሚችል ከዚህ ቀደም እንደተለመደው ፓርቲውን በወከባ እና በጥቅም ማክሰም ወይንም ከፓርቲው ጋር መደራደር እስከሚሉ ጨከን ያሉ ሃሳቦች ተንጸባርቀዋል:: ከፓርቲዎች ጋር መደራደር የሚባል ነገር አይዋጥልኝም የሚሉት አለቃ ጸጋዬ በቁጣ እና በጩኽት ይህንን የመደራደር ሃሳብ ያቀረበችውን የሕወሓት የከተማ ህዋስ አባልን ያመጣንሽ እኮ እንድትጦሪን እንጂ ጠላት እንድትሆኚን አይደለም በማለት በቋንቋቸው አይሆኑ ዘለፋ ዘልፈዋታል::ቤቱ በዝምታ ድባብ እንዲዋጥ ያደረጉት የጫካው ሕወሓቶች የታገልነው ለድርድር አይደለም ሲሉ ተደምጠዋል:: ሰማያዊ ፓርቲ ቢነሳም ብዙም አያሰጋንም በሚል ታልፏል::
ከኦህዴድ ሙክታር ብቻ የተካፈለበት ይህ ስብሰባ 16 የህወሃት ጄኔራሎች የተመከሩ ይመስል ጂንስ በጃኬት ለብሰው ነበር በስብሰባው ላይ የተገኙት :: በአሁን ሰአት የደህንነቱ እና የወታደሩ ክፍል በተጠንቀቅ ሊሆን ይገባዋል በሚል የሚያሳዝን አንደበት መናገር የጀመሩት አቶ በረከት አትኩረውት የነበረው በሙስሊሙ እና በዲያስፖራው ጉዳይ ነበር :: ሙስሊሙች ጥያቄያቸው ሰፍቶ አለምም ጆሮ ሰቷቸዋል እንሱን ዝም ማሰኘት አሊያም ለፖለቲካ ስልት መጠቀም አስፈላጊ ነው ቢሉም የታሰሩትን መፍታት ለኢህኣዴግ የፖለቲካ ኪሳራ ስለሆነ ያለንን ሃይል መጠቀም አለብን ብለዋል:የዲያስፖራው ጥላቻ ከ60% ወደ 90% አድጓል:: 10% ደሞ ንብረት አገር ቤት ያፈሩ ወይም ከፖለቲካ ነጻ ነን የሚሉ ግለሰቦች ሲሆኑ ይህ ደሞ 10% ደጋፊ ሳይሆን የምንላቸው ለንብረቶቻቸው እና ለቤተሰቦቻቸው ደህንነት የሚለማመጡ ብንል ይቀላል :: በዲያስፖራው ዘንድ ያለው ጉዳይ ብዙም ተስፋ ሰጪ ስላልሆነ ሊታሰብበት ይገባል ብለዋል:: ይህ የራሳችን የፖሊሲ ውጤት ነው ብለው ደፍረው የሚናገሩ አባላት አልተገኙም::
የህወሃት አንጋፋ ታጋዮች የተሳተፉበት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ያልተጠሩበት ጥቂት ብኣዴኖች እና አንድ ኦህዴድ የፈጠጡበት ይህ ስብሰባ የምእራቡን ጫና በተመለከተ ሰፋ ያለ የዲፕሎማቲክ ስራ እና ዝርዝር ሪፖርት ይዞ የማስረዳት ስራ እንዲሰራ የሕወሓት የውጪ ጉዳይ አትኩሮት እንዲሰጥበት ያደረገ ሲሆን ለአንድ አገር የውጪ ፖሊሲ የአንድ ፓርቲ ሰዎችን እንዲሰሩ ማዘዝ በአንዳንድ ተሰብሳቢዎች ላይ አግራሞትን ፈጥሯል::ምንም አይነት ስምምነት ያልታየበት ይህ ስብሰባ በፍጥጫ በአተካሮ እና በጩኽት የተሞላ ቢሆንም አብዛኛዎቹ አንጋፋ ታጋዮች ማስታውሻቸው ላይ ሲቸከችኩ ተስተውለዋል::
ወደማይፈታ ችግር ራሱን እየወሰደ ያለው ቡድናዊው አምባገነን ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ እንዳለ የሚያሳየው ይህ ጨለማ የሚደረግ ስብሰባ አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን ሰዎች እየተመረጡ ደጋፊዎች እየታዩ እየተጠራሩ በጎጥ እና በመንደር በመሰባሰብ ሃገርን ወደማትወጣበት አዘቅት ቁልቁል እየከተቷት ነው:: በመጪው ቀናቶች የሚጠሩ ስብሰባዎች በእነዚሁ ወቅታዊ ጉዳዮን ላይ አተኩርው እንደሚወያዩ ይጠበቃል መልካም የለሊት ስብሰባ::  ምንልክ ሳልሳዊ

No comments: