Friday, August 30, 2013

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሰማያዊ ፓርቲ 3 ከፍተኛ አመራሮችን ነሀሴ 26 የሚደረገውን ሰልፍ በተመለከተ እንወያይ የሚል ጥሪ አቀረበ፡፡

መንግስት በአዲስ አበባ ከተማ እየተንቀሳቀሱ ባሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች ፍራቻ ያደረበት ይመስላል ።ለዚህም ሲል አስቸኳይ የሆነ እነወያይ የሚል ጥሪ ለሰማያዊ ፓርቲ አቅርቦአል ይህም የሆነበት ምክንያት በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚደረጉትን ህዝባዊ ስብሰባዎች በፍርሃት ውስጥ ስላስገባው እና እንቅስቃሴው ወደ ሌላ ነውጥ ገብቶ መንበረ ስልጣኑን ሊያሳቱን ይችላሉ በሚለው ስጋት የተሞላ እንደሆነ ከተለያዩ ቦታዎች የደረሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ ።

ሆኖም መንግስት ስልጣኔን ሊያሳጡኝ  ይችላሉ ብሎ የሚጠረጥራቸውን ሰዎች በተለያዩ የፈጠራ ክስ እና በአላስፈላጊ የሆነ ሰበአዊ መብት እረገጣ መቀጠሉን እና ብዙሃኑን ህብረተሰብ አሸባሪ እያለ መጥራት ከጀመረ 7ኛ አመታትን አስቆጥሮአል ።ይህ በእንዲህ እንዳለ ለዚህ ስብሰባ ተጋባዥ ይሆናሉ ተብሎ ከሰማያዊ ፓርቲ ስም ዝርዝራቸው ለፖሊስ ኮሚሽን እንዲቀርብ የተደረጉት ይገኛሉ ከዚህ ጥሪ ተከትሎ ግን ምን ሊመጣ እንደሚችል መገመት አስቸጋሪ ሆኖአል ።

1. ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት (የፓርቲው ሊቀመንበር)
2. አቶ ስለሺ ፈይሳ (የፓርቲው ም/ሊቀመንበር)

3. አቶ እንዳሻው እምሻው በመሆን ለውይይቱ አዲስ አበባ ፖሊሰ ኮሚሽን ይገኛሉ፡፡ መንግስት ለምን ጥሪውን በአስቸክውይ ሊያደርገው ወሰነ ሰሞኑንስ መንግስት የጠራውን ስብሰባ ለምን በሌላ ጊዜያት ሊቀይረው አለወሰነም ፣የተቃዋሚዎቹን የስብሰባ ጥሪ ተመልክቶ ለምንስ መንግስት በእለቱ እንዲወሰን አጸደቀ የሚሉት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችም እየተነሱ ይገኛሉ በውይይቱ ሰአትም ሊጠየቁ ይችላሉ ተብሎ ይገመታል!

No comments: