Monday, August 12, 2013

የሽብርተኝነት ምንጭ ጭቆና ነው! (ገዛኽኝ አበበ ከኖርዌይ)

ከ ገዛኽኝ አበበ
August 12/2013
ደርጎች 'ወንበዴዎች' አሉን፤ ኢህአዴጎች 'አሸባሪዎች' አሉን። ያው ነው፤ ገዢዎች ለስልጣናቸው አስጊ የሆነ ሰው (ወይ ቡድን) ሲያጋጥማቸው ስም ሰጥተው የማጥላላት ዘመቻ ያካሂዳሉ።የስልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም የሚጠቀሙበት ቃላቶች ናቸው ::ይኸውም ያለስማቸው ስም እየሰጡ ያለ ተግባራቸው ተግባር እና ያልሰሩትን ስራ እንደሰሩ በማድረግ ስማቸውን ማጥላላት ነው::
የማጥላላቱ ዘመቻ ዋና ዓላማ ለስልጣን ስጋት የሆኑ ሰዎች ከህዝብ ለመነጠል ነው፣ ድጋፍ እንዳያገኙ ለማድረግ። እንደ እኔ  እንደ እኔ ግን አሸባሪም ሽብርተኛም እነዚው መንግስታቶች ናቸው::
ግን 'ወንበዴዎች' ወይ 'አሸባሪዎች' እንዴት ይወለዳሉ? እንዴትስ ያድጋሉ? የውንብድና ወይ ሽበራ ምንጭ ጭቆና ነው። የጭቆና ምንጭ አምባገነንነት ነው። አምባገነንነት በሰው ህይወት፣ አስተሳሰብና ሃይማኖት ጣልቃ መግባት ይጨምራል።
ህዝብን በሃይል እና በጉልበት  ለመግዛት ጣልቃ መግባት የህዝቦች ነፃነት ማፈን ያመጣል። የሰዎች ነፃነት ማፈን የህዝቦች መብት መጣስ ነው። ህዝቦች መብታቸው ሲጣስ መብታቸውን የሚስያከብሩበት መንገድ ያፈላልጋሉ። ስለዚህም በጉልበት እና በሃይል መብታቸውን እና ነጻነታቸውን ጨፈልቆ እየገዛቸው ካለው ሃይል እራሳቸውን ነፃ ለማውጣት እራሳቸውን ያደራጃሉ ይደራጃሉ ነጻ እንወጣበታለን ብለው በሚያስቡበት በማንኛቸውም መንገድ ይንቀሳቀሳሉ እንግዲህ ይህ ነው መንግስት በማይፈቅደው መንገድ መብታቸው ለማስከበር ሲንቀሳቀሱ 'ሕገወጥ' ተብለው 'ወንበዴዎች' ወይ 'አሸባሪዎች' ይሰየማሉ። መንግስት 'ሕግ ለማስከበር' በሚል ሰበብ የሃይል እርምጃ ይወስዳል። መጀመርያ ሕግ የጣሰ አካል ግን መንግስት ነው፣ የዜጎችን መብት በመጣስ። እናም ችግሩ እየተባባሰ ይሄዳል። ከተባባሰ ደግሞ የሃይል ሚዛን እንጂ የመደገፍና የ መቃወም ጉዳይ አይሆንም::
ስለዚህ ውንብድና ወይ ሽበራ የሚወለደው ከጭቆና ሲሆን የሚያድገውም በመንግስታዊ ያልተፈለገ የሃይል እርምጃ ነው። መንግስት በያዘው መንገድ ከቀጠለ ሀገራችን ወዳልተፈለገ የብሄርና የሃይማኖት ብጥብጥ ልትገባ ትችላለች።
መንግስት ችግሩ የመፍታት ግዴታ እንጂ የማባብስ መብት የለውም። አሁን እየተወሰደ ባለው የሃይል እርንጃ ምክንያት ብዙ ሙስሊሞች ሳያስቡት ወዳልተፈለገ በሃይል መብትን የማስከበር ተግባር ሊገቡ ይችላሉ። በደርጋዊ እርምጃ ምክንያት ብዙ የትግራይ አርሶአደሮች ሳያስቡት ከህወሓት ጎን ተሰልፈው ለመዋጋት ወስነው ነበርና።
  ስለዚህ አሁነም መንግስት ወደደ ጠላም አሁን እየታየ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የሙስሊሞች ጉዳይ መፍትሔ ያሸዋል። ይህም ከሃይማኖት አልፎ የሀገር ጉዳይ እየሆነ የመጣው የመብታችን ይከበር የመብት ጥያቄ የሙስሊሙ ወገኖቻችን ጥያቄ ሳይሆን የእያንዳንዱ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ጥያቄ ነው። የሰዎችን መብት እና ነጻነት በሃል እና ስልጣንን መካታ በማድረግ በጉልበት ተገዙ በማለት ለነጻነቱ ደግሞ የሚነሳ ህዝብ በአሸባሪ ጓራ መፈረጅ ትክክለኝነት አይመስለኝም::

እንደእኔ እንደ እኔ ጅብ እራሱ ነክሶ እራሱ ይጮኸል እንደሚባለው ወያኔም ሕዝቡን በሀይል በጉልበት እየጨቆነ መግዛት እስካለቆመ ድረስ እሱ እንደሚለው ለነጻነት መታገል እና መብታችን ይከብር ብሎ መጩህ ሽብርተኝነት ከሆነ   የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ መንግስት  ጭቆና ነጻ እስኪወጣ ትግሉ ይቀጥላል::

 ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

No comments: