Friday, June 14, 2013

በደቡብ ጎንደር ዞን መምህራን በደንነት ሀይሎች ታፍነው ተወስደዋል

ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በደብረ ታቦር ከተማ ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ እና ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ የተባሉ መምህራን ትናንት ማታ እና ዛሬ ጠዋት በደህንነት ሐይሎች ታፍሰው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።

... መምህር ታደሰ መንግስቴና መምህር ፈቃዱ ጌትነት የሚባሉ በ ፈቀደ እግዚ ኮሌጅ ውስጥ አስተማሪዎች ሲሆኑ መምህር አሸናፊ አለሙ ደግሞ የሁለተኛ ደረጃ መምህር ነው። አብይ ሃይሌ እና ማስረሻ የተባሉ ወጣቶችም እንዲሁ ታፍነው ተወስደዋል።

 ታፍነው ከተወሰዱት መካከል የሁለቱ የቅርብ ጓደኛ የሆነ ወጣት እንደገለጸው ቤተሰቦቻቸው የአካባቢውን ፖሊሶች ሲጠይቁ ” የት እንደተወሰዱ አናውቅም” የሚል መልስ ተሰጥቷቸዋል። በጉዳዩ ዙሪያ የፌደራል ፖሊስ አዛዦችን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
 

No comments: