Sunday, June 9, 2013

አንድነት ፓርቲ የሰኔ 1 ሰማዕታትን በልዩልዩ ዝግጅቶች ዘከረ

ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓ.ም በመንግስት ሀይሎች በግፍ የተጨፈጨፉ የሰላማዊ ትግል ሰማዕታትን ለመዘከር አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ያዘጋጀው መርሀግብር ትላንት ተካሄደ፡፡

 ቀበና አካባቢ በሚገኘው አንድነት ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ሰማዕታቱን ለማሰብ በህሊና ፀሎት በተጀመረው በዚሁ መርሀ ግብር ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሲሆኑ ከሳቸው በመቀጠል የአንድነት ፓርቲ አዲስ አበባ ዞን ሰብሳቢ አቶ ትዕግስቱ አወሉ ዕለቱን የሚመለከት ንግግር አድርገዋል፡፡

ከ300 በላይ ታዳሚዎች በተሳተፉነት በዚህ መርሀግብር ላይዕለቱን የተመለከቱ ግጥሞች በገጣሚ መላኩ ጌታቸው ቀርበዋል፡፡ የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ነብዩ ኃይሉ ዕለቱን አስመልክቶ የነበረውን ትዕውስታ ለታዳሚው አካፍሏል:: የመርሀግብሩ አዘጋጆች ሰኔ አንድ በግፍ ከተገደሉ ዜጎች መካከል 42 የሚሆኑትን ስምና የአገዳደል ሁኔታ በመቀንጨብ አቅርበዋል፡፡ የታሳሪዋ ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ አባት አቶ አለሙ ጌቤቦ የመዝጊያ ንግግር ካደረጉ በኋላ በቅርቡ በማዕከላዊ ታስሮ ድብባና እስር ሲፈፀምበት በነበረው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ የተመራ የጧፍ ማብራት ስነስርአት ተካሂዶ መርሀግብሩ ተጠናቋል፡፡ 

No comments: