Wednesday, June 19, 2013

ቤኒሻንጉል:- በዜጎች መፈናቀል ሳቢያ የም/ቤት አባላት ታሠሩ

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ምክር ቤት ትናት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በክልሉ ነባር የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች መፈናቀል ምክንያት ናቸው ያላቸውን 2 የምክር ቤት አባላትን ያለ መከሰስ መብት አነሳ።
 
Map of Benishangul-Gumuz Region - Ethiopiaያለ መከሰስ መብታቸው ተነስቶ በቁጥጥር ስር ውለው በህግ እንዲጠየቁ የተደረገው በክልሉ ከማሺ ዞን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መለተጊ ቦጋለና የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሃላፊው አቶ ገርቢ በጊዜው ናቸው።
 
እነዚህ አመራሮች የክልሉ መንግስትና ፓርቲው በማያውቀው ሁኔታ በዞኑ ያሶ ወረዳ ነባር የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆችን እንዲፈናቀሉ ማድረጋቸው በመረጃ በመረጋገጡ ነው እርምጃው የተወሰደባቸው።
 
በዚህ የማፈናቀሉ ተግባር ተሰማርተዋል ተብለው የተጠረጠሩ 18 የሚደርሱ ከቀበሌ እስከ ዞን የሚገኙ አመራሮች ጉዳያቸው እየተጣራም ይገኛል።
 
የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ይስሀቅ አብዱልቃድር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት ፥ የክልሉ መንግስት ጉዳዩን በማጣራት ባአሁኑ ጊዜ ተፈናቃዮች ተረጋግተው ወደቀያቸው ተመልሰው መደበኛ ኑሮዋቸውን እያከናወኑ ነው።
***************
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው 2ኛ አስቸኳይ ጉባዔው በአማራ ክልል ተወላጆች ማፈናቀል ላይ ተሳታፊ ናቸው ያላቸው ሁለት የምክር ቤቱ አባላትን ያለመከሰስ መብት አነሳ፡፡
ምክርቤቱ ያለመከሰስ መብታቸውን ያነሳው በክልሉ የካማሺ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የዞኑ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊን ነው፡፡

ምክር ቤቱ በዋና አስተዳዳሪው አቶ ወልተጂ በጋሎ እና በኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ በአቶ ገርቢ በጊዜ ላይ ከክልሉ ፓሊሲ ኮሚሽን እና ከፍትህቢሮ የምርመራ ቡድኖችን አደራጅቶ መረጃዎችን በማጠናከር ግለሰቦቹን ለህግለማቅረብ የሚያስችል ጥልቅ ምርመራ መደረጉን ገልጿል፡፡
የግለሰቦቹ አድራጎት የክልሉ መንግስትና ህዝብን ስም ያጎደፈ በመሆኑ ከስልጣናቸው ተነስተው በህግ እንዲጠየቁ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፡፡
 

No comments: