Sunday, August 18, 2013

ህዝባዊ ተቃዉሞ እየተስፋፋ የመጣዉ ለምንድን ነዉ?

 ሰዎች መንግስት ፍላጎታቸዉን እንደሚያሟላላቸዉና የይኮኖሚዉ ስርዓት እንደሚፈልጉት እንደሆነ ከተሰማቸዉ ተቃዉሞ ለማሰማት ኣያስቡም ::ችግሮች ቢኖሯቸዉ እንኴ ስርዓቱን ተከትለዉ ችግሮቻቸዉን ለመፍታት ይጥራሉ፤ በሌላ በኩል ግን ህዝቡ፤ባለስልጣናት በሙስና የተዘፈቁ እንደሆነ ፤የፍትህ መጔደልና ስርዓቱ ጥቂቶችን ብቻ የሚጠቅም እንደሆነ ሲሰማዉ ተቃዉሞ የሚቀሰቀስበት ሁኔታ ይፈጠራል።
ብዙ ጊዜ ሰዎች እርምጃ ለመዉሰድና ችለዉ የኖሩትን ነገር ለመለዉጥ የሚያነሳሳቸዉ የሆነ ምክንያት ይኖራል።ለምሳሌ ሞሀመድ ቡኣዚዚ ታህሳስ  17 ቀን2010 ሁሉ ነገር ከኣቅሙ በላይ የሆነበት ፤ በቱኒዚያ ጎዳናዎች ሸቀጥ እያዞረ የሚሸጠዉ ይህ የ26 ዓመት ወጣት የተሻለ ስራ ዓለማግኘቱ በራሱ ሆድ ዓስብሶታል። በዚያ ላይ ደግሞ ምግባረ ብልሹ ባለስልጣናት ጉቦኛ መሆናቸዉ ዓበሳጭቶታል።ይህ እንዳይበቃዉ በዚህ ዕለት ጠዋት ላይ ተቆጣጣሪዎች መሀመድ እያዞረ የሚሸጠዉን ፍራፍሬ ወሰዱበት።ሊወሰድበት ሲል ለመከላከል ሞከረ በዚህ ጊዜ ዓንዴት ፖሊስ በጥፊ እንደመታችዉ የኣይን ምስክሮች ገልፀዋል።
በደረሰበት ሁኔታ ዉርደት የተሰማዉ መሀመድ ኣቅራቢያዉ ወደሚገኘዉ የመንግስት መስሪያ ቤት በመሄድ ቅሬታዉን ቢያሰማም ጀሮ የሚሰጠዉ ኣላገኘም።በዚህ ግዜ መሀመድ ከመስሪያቤቱ ፊት ለፊት ታዲያ ምንሰርቼ ልብላ ብሎ ጮኽ።ከዚያም ሰዉነቱ ላይ ተቀጣጣይ ፈሳሽ ካርከፈከፈ በኋላ ክብሪት ለኩሶ ህይወቱን ኣጠፋ።መሀመድ የወሰደዉን እርምጃ ተከትሎ በቱኒዚያም ሆነ በሌሎች ኣገሮች ህዝባዊ ኣመጽ በመቀስቀስ ለመንግስት ግልበጣ ምክንያት ሆኗል።
ሙስና እና ፍትህ መጔደል ከመቸዉም ጊዜ ይበልጥ ዛሬ በጣም ተስፋፍቷል።መረጃዎችም በሞባይል ስልኮች በፌስቡኮች በዜናማሰራጫዎች (...) በመሳሰሉት በፍጥነት ስለሚሰማ  በርካታ ሰዎች ተቃዉሞኣቸዉን በኣንድ ግዜ በማሰማት መንግስትን በኣጭር ግዜ ማስወገድ ይቻላል።እርግጥ የሰዉ ልጆች ጨቌኝ ስራቶችን የመቃወም የሞራል ግዴታ እንዳለባቸዉ ይሰማቸዋል።ለምሳሌ መሀመድ ቡኣዚዚ፤የኔሰዉ ገብሬ እና ሌሎችም ሰዎች የወሰዱት ርምጃ ድምፃቸዉን ለማሰማት የሚያስችል የተሻለ ኣማራጭ እንደሌለ ስለሚሰማቸዉ ነዉ።በቅርቡ መምህር የኔሰዉ ገብረሬ  ራሱን ለኣሰቃቄ ሞት በመስጠት ዛሬ በፍትህና በዴሞክራሲ እጦት የሜቃጠለዉን በኑሮ ዉድነት እና በድህነት የሜነደዉን የህዝብ ኑሮ ለመላዉ ኣለም ለማሳየት ራሱን በማቃጠል በቁሙ የሜቃጠለዉን ህዝብ በተምሳሌትነት ኣሳይቷል።ይህን በማድረጉ በኣገራችንና በኣለም ዙሪያ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል።ህዝባዊ ተቃዉሞ ያለማቌረጥ ሰባኣዊ ክብራችን እስኪጠበቅልን፤መብቶች እስከሚከበሩልን፤እኩልነት እስኪረጋገጥልንና ፍትህ እስኪሰፍንልን ድረስ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት እዉን እንዲሆን ያለማቌረጥ ብሶትን በኣደባባይ መግለፅ ኣለብን።
ኣዘጋጅ ባይሌ ደርሰህ

No comments: