Tuesday, October 29, 2013

ሁላችንም እኔም የአገሬ ጉዳይ ያገባኛል ብለን ትግላችንን ይበልጥ ማጠንከር አና መቀጠል ይጠበቅብናል::

 October29/2013
ገዛኽኝ አበበ ከኖርዌይ

የወያኔን መጥፎ አካሂድ እና አንባ ገነንት በስርአቱ እና በሚገባ የተረዳን ሰዎች የሁል ጊዜ  ምኞታችን እና ትግላችን ኢትዮጵያ ከዚህ ጨካኝ እና ዘረኛ አገዛዝ ነጻ የምትወጣበትን ቀን በመናፈቅ ነው :: አገራችንን ከዚህ ከመጥፎ ስርአት የምትወጣበት ቀን ማምጣት እና የወያኔን እድሜ ማሳጠር የምንችለው እኛው ነን :: ማንም አገሬን እወዳለው የሚል ዜጋ ሁሉ አገሩ ያለችበት ሁኔታ ሊያሳስበው የአገሩም ነገር ግድ ሌለው ያስፈልጋል:: ምን አልባት ይህ ነገር የማይዋጥላቸው ወያኔ እና የወያኔ ካድሬዎች ብቻ ናቸው ::

  ስለ አገር ተጨባጭ ሁኔታ ማውራት እና ስለ ዜጓች መቆርቆር ፖለቲከኛ መሆን ሳይሆን  ከአንድ አገሬን እውዳለው  ከሚል ጤናማ እና ንጹህ ዜጋ የሚጠበቅ ነው ::  ዛሬ ወያኔ ኢህአዲግ በሕዝባችን ላይ ግፍ እና በደል እያደረሰ እንዳለ በግልጽ እየታየ ያለ እና ሁሉም ሰው የሚያውቀው ሀቅ ነው :: ስለሆነም በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለው በደል ልንቆረቆር እና ከቀን ወደ ቀንም ወደ መጥፎ አቅጣጫ እየሄደ ያላው የአገራችን ሁኔታ ሁላችንም ግድ ሊለን እና ሊያሳስበን ይገባል ባይ ነኝ ::  የአገራችንን ጉዳይ ለፖለቲከኞች ወይም ለተወሰኑ ሰዎች የምንተወው ነገር አይደለም:: አገራችንን ካለችበት  መጥፎ ሁኔታ ለማውጣት ሁላችንም መረባረብ እና በማንኛውም መንገድ ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅብናል ::

 ሁሉም ሰው እንደሚያቀው በአሁኑ ግዜ  በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው ጨካኝ እና አንባ ገነንነት ስርዓት የተነሳ ብዙ ሰዎች ለስደት ፣ ለእንግልት ፣ ለስቃይ እና ለመከራ ሲዳረጉ ዜጓች ይገደላሉ ፣ ይታሰራሉ ፥ ታስረውም ደግሞ በየእስር ቤቱ  ይገረፋሉ፣ይደበደባሉ ዘግናኝ እና የሰበዓዊ መብቶች ጥሰቶች  ይፈጸምባቸዋል:: ይህ ሁሉ ነገር እየሆነ  በዜጓቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን ዘግናኝ በደል እና ግፍ እያዩ እና እየሰሙ ዝም ማለት እና በቸልተኝነት ማለፍ  ከጤነኛ ሰው የሚጠበቅ አይደለም::  ምክንያቱም ይህ ሁሉ በደል እና ግፍ እየተፈጸመባቸው ያለው ዜጓች የእኛው ወንድሞች እና እህቶች ናቸውና :: ስለዚህ ይህን ግፍ እና በደል እያደረሰ ያለውን የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ሁላችንም ልናወግዘው በቃህ ልንለው በወገኖቻችን ላይ ስለሚደርሰው ግፍ እና በደል  ልንቆረቆር ይገባል ባይ ነኝ ::

የወያኔ የኢህአዲግ መንግስት በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ እና በደል አግባብ ያልሆነ እና ማንም ንጹህ እሊና ያለው ኢትዮጵያዊ የሚቀበለው አይመስለኝም :: እነ እርዮት አለሙ እነ አስክንድር ነጋ እንዲሆም እንደነ ውብሸት ታዬ ያሉ አገር ወዳድ ዜጎች ምንም ወንጀል ሰርተው ሳይሆን በእስር ቤት ውስጥ የሚሰቃዩት  ስለ ፍትህ ፣ስለ ነጻነት ስለ ጻፉ የወያኔን መጥፉ አካሄድ በብዕራቸው ስላወገዙ ነው:: ስለዚህ የእነዚህ ወንድሞቻችን እና እህታችን ስቃይ እኛንም ሊያመን እና ሊሰማን ያስፈልጋል :: እነ እርዮት እና እነ እስክንድር ብቻ አይደሉም  በእስር  ቤት ውስጥ እየተንገላቱ ያሉት  ሙስሊም ወንድሞቻችን እነ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ፣ እነ ኡስታዝ ያሴን ኑር፣ እነዲሁም እንደነ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል የመሳሰሉት የሀይማኖት ሰዎች ምንም ወንጀል ሰርተው ወይንም ወያኔ ኢህአዲግ እንደሚለው አሸባሪ ሆነው አይደለም :: ዜጓች የመብት የፍትህ፣ የነጻነት ጥያቄ ስለጠየቁ  እንደ ወንጀለኛ ተቆጥረው መታሰር የለባቸውም ::  ለፍትህ እና ለእውነት ስለቆሙ በእየ እስር ቤቱ መሰቃየት የለባቸውም ::

ዛሬ  የወያኔን መጥፎ አካሄድ ስለተቹ ብቻ እና በወያኔ መጥፎ  የዘር እና የፖለቲካ ጥላቻ አመለካከት ባልሰሩት ግፍ እና በደል በእስር ላይ የሚገኙ የፓለቲካ ሰዎች እነ አንዷ አለም አራጌ ፣ እነ ናትናሄል መኮንን፣ እነ አሳምነው ብርሃኑ እና እንዲሁም ብዙ የኦሮሞ ተወላጆች እነ በቀለ ገርባ እና ኦልባና ለሊሳ የመሳሰሉ ወገኖቻችን ባልሰሩት ወንጀል ፍትህ በሌለበት አገር በእስር ቤት እየተሰቃዩ ነው ያሉት :እኔ በጥቂቱ እነዚህን ጠራው እንጅ በወያኔ የበትር አለንጋ እየተገረፈ የሌለ የለም :: የአማራው ፣ የሱማሌው፣ የቤንሻንጉሉ የሀረሪው፣ የደቡቡ፣ የትግራዩ ተወላጅ ሳይቀር በወያኔ የጭቆና አገዛዝ በስቃይ ላይ ነው ያለው  ::  ስለዚህ የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ እና በደል ፣ የሕዝባችንን ስቃይ እና መከራ ግድ ብሎን  ባገኛነው መንገድ እና አጋጣሚ በመጠቀም  ለአለም ሕዝብ ሁሉ ማሰማት የዜግነት ግዴታችን መሆን አለበት::

እነዚህ ወገኖቻችን ስለ አገራቸው እና ስለ ሕዝባቸው ፍትህ እና ነጻነት ሲሉ ነው  እንጂ  የወያኔን ነገር ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው መኖር በቻሉ ነበር ነገር ግን ህሊናቸው አልፈቀደላቸውም የሕዝባቸው ሰላም እና ነጻነት ፍትህ ማጣት እና መጨቆን ሊቀበሉት ስላልቻሉ ሕዝብን ረግጦ መግዛት የለመደው የወያኔ መንግስት በእስር እያንገላታቸው የሚገኛው:: ለእኛ እነዚህ  ሰዎች ምሳሌዎቻችን  እና ጀግኖቻችን  ናቸው ስለሆነ ዛሬ እኛ እንደ እስክንድር፣  እንደ ርእዮት፣  እንደ አንዷአለም፣  እንደ አቡበከር፣  እንደ በቀለ  እንደሌሎቹም ጀግኖች ታጋዮች ስለ ፍትህ እና ስለ ነጻነት የአገራችን ጉዳይ ግድ ብሎን ለነፃነታችን መታገል ያስፈልገናል:: የእነሱ ስቃይ የእኛ ስቃይ የእነሱ መከራ የእኛ መከራ ነው ::  እኔ ፖለቲካ አልወድም ስለ ፖለቲካም አያገባኝም የምንለው ጉዳይ አይደለም ጉዳዩ ፓለቲካ ሣይሆን የነጻነት ነው:: በፊስ ቡክ እና በብሎግ ገጽ ላይ ከምለቀው አገር ነክ ዜናዎች እና ጹሁፎች የተነሳ አንዳንድ የማቃቸውም የማላቀቸውም  ሰዎች በፊስ ቡክ መልክት የሚጽፉልኝ መልእክት በጣም ነው የሚያስገርመኝ ከሚጽፉልኝ መልክቶች ውስጥ አንተም ፖለቲካ ጀመርክ ፖለቲካ አያምርብክም በል አርፈክ ተቀመጥ ወዘተ...... የሚሉት ቃላቶች በጣም የሚያስገርሙኝ ናቸው እኔ ፖለቲከኛ አይደለውም ነገር ግን የአገሬ ጉዳይ ግድ ይለኛል ::ስለ አገር ፍትህ እና ነጻነት ማወጅ፣  ስለ አገር ተጨባጭ ሁኔታ ማውራት እና ስለ ዜጓች መቆርቆር ፖለቲከኛ መሆን አይደለም እና ንግግራቸው ብዙም አያስገርመኝም ::

ዛሬ አገራችንን ከወያኔ ስርአት ነጻ ለማውጣት ሃይማኖት ፣ ጾታ፣ ጎሳ እና ብሔር ሊይዘን አያስፈልግም  እያንዳንዳችን በየትኛውም አቅጣጫ እና መንገድ የምናደርገው እንቅስቃሴ የወያኔን መንደር እንደሚረብሸው እና እንደሚያስደነብረው ማወቅ አለብን :: እኔም የተረዳውት እና የተገነዘብኩት ይህንን ነው:: ለእኔ ከማሰብ እና ወይም ደግሞ ከለመረዳት የተነሳ ይሁን አንዳንድ ሰዎች  አንተም ፖለቲካ ጀመርክ: ፖለቲካ አያምርብክም በል አርፈክ ተቀመጥ ከሚሉት ቃላቶች ውጭ ከወያኔ ተላላኪዎች በፊስ ቡክ በውስጥ መልእክት የሚደርሱኝ የስድብ እና የማስፈራሪያ ቃላቶች  በተቃዋሚ  ዊብ ሳይት፣ ፊስ ቡክ፣  ብሎግ፣ ቲዩተር እና በመሳሰሉት ማህበራዊ ድህረ ገጾች   እየተሰራ ያለው ቅስቀሳ (propaganda) ወያኔ ምን ያክል እየተረበሸ እና እየደነበረ እንዳለ የሚጠቁሙ ቃላቶች ከወያኔ አሽከሮች በፊስ ቡክ በውስጥ መልእክት የሚደርሱኝ የስድብ እና የማስፈራሪያ ቃላቶች ይመሰክሩልኛል:: ወያኔ ኢህአዲግ: ምስጥ እየበላው እንዳለ እና እየተቦረቦረ እንዳለ  እንጨት ሆኖል::  በአሁኑ ሰአት  እኛ እያደረግነው ባለ ትግል ውስጥ ውስጡን የኢህአዲግ መንግስት  እየተበላ እና እየተቦረቦረ እንደሆነ እንድናውቅ እና ሁላችንም እኔም የአገሬ ጉዳይ ያገባኛል ብለን ትግላችንን ይበልጥ ማጠንከር አና መቀጠል ይጠበቅብናል:: በምስጥ እየተበላ እና እየተቦረቦረ ያለ እንጨት አንድ ቀን መውደቁ አይቀርም እና ትግላችንን እንቀጥል::

         ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ::



No comments: