Friday, October 4, 2013

ገዢው ፓርቲ በጠራቸው ስብሰባዎች ላይ ሁሉ ተቃውሞ ገጠመው

Oktober 4 / 2013

መስከረም ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ባለፈው ሳምንት በመላ አገሪቱ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችን እየሰበሰበ በ2005 የስራ አፈጻጸምና የ2006 ዓም በጀት እቅድ ትግበራ ላይ ሲያወያይ ቢሰነበትም፣ ለኢሳት ሚደርሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በሁሉም ቦታዎች ላይ በተደረጉት ስብሰባዎች ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጥሞታል።

በአዳማ የተካሄደውን ስብሰባና ተሰብሳቢዎች ያቀረቡዋቸውን ቅሬታዎች ኢሳት ቀደም ብሎ የዘገበ ሲሆን፣ በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን በአርማጭሆ ወረዳ የነበረው ስብሰባም እንዲሁ በተመሳሳይ ተቃውሞ መጠናቀቁን በውይይቱ የተሳተፉ የመንግስት ሰራተኞች ገልጸዋል።

በውይይቱ ላይ በርካታ አጀንዳዎች የነበሩ ሲሆን፣ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ የተነሱት ጉዳዮች ተሰብሰባዊውን በከፍተኛ ሁኔታ አወዛግበዋል።

በ2006 ዓም የጸረ ሰላም ወይም የጥፋት ሀይሎችን ማምከን የሚል በእቅድ እንዲካተት በቀረበው አጀንዳ ላይ ጸረ ሰላም ማን ነው የሚለው ጥያቄ በተሰብሳቢው ተነስቶ የመድረኩ መሪዎች የተለያዩ መልሶችን ሰጥተዋል። የዞኑ የጸጥታ ጉዳዮች ሀላፊ የሆኑት አቶ ወርቁ ሀ/ማርያም ” ነሀሴ ወር ገደማ 30 የሚሆኑ ሰዎች በጎንደር ከተማ ህዝቡን ተነስ በማለት ሲቀሰቅሱ የነበሩ ሰዎች ጸረ ሰላም ሀይሎች ናቸው።” በማለት አንድነት ፓርቲ በጎንደር ያካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ በምሳሌነት አንስተዋል።

ሌላው የሲቪል ሰርቪስ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ገዛሀን ተክሌ በበኩላቸው ” የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን ተሰጠ ብሎ መናገር ጸረ ሰላምነት ነው” ሲሉ አብረራርተዋል። ባለስልጣኑ አክለውም ህገመንግስቱን ለመጣስ የሚነሳ ሁሉ ጸረሰላም ተብሎ ይፈረጃል ብለዋል።

የጸጥታ ጉዳዮች ዘርፍ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ደግሞ ” ከመድረክ አፈንግጦ መውጣትና ሳያስፈቅዱ መናገር፣ ሳያስፈቅዱ ጽሁፍ መጻፍና ማሰራጨት፣ ሳያስፈቅዱ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ፣ በጥፋት መልእክተኝነት ያስፈርጃል ሲል ገልጸዋል።
አቶ ፈንታ የተባሉ ባለስልጣንም እንዲሁ ” የጎንደርን መሬት ኢህአዴግ አሳልፎ እየሰጠ ነው ” ብሎ መናገር ጸረ-ሰላም ተግባር ነው በማለት የራሳቸውን ትርጉም አቅርበዋል።

ስለ ጸረ ሰላም ሀይሎች፣ አክራሪነትና ሽብረተኝነት ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ትምህርት እንዲሰጠጥ በቀረበው ሀሳብ ላይ ደግሞ በስብሰባው የተሳተፉ ተቃውሞአቸውን ገልዋል። ተሳታፊዎቹ ከ15 ዓመት በታች ያሉ ህጻናትን ስለ ሽብረተኝነት፣ አክራሪነትና ጸረሰላም ሀይሎች ማስተማር በህጻናቱ ላይ የስነልቦና ጫና ይፈጥራል በማለት ተከራክረዋል።

ሌላው አወዛጋቢ የነበረው ነጥብ ” ኢህአዴግ የ2006 እቅድን ተቋሞችን በድርጅት አባላት በመሙላት እናሳካለን በማለት ያቀረበው ” ሲሆን፣ ተሰብሳቢዎቹ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ሁሉ በድርጅት አባላት ከሞላችሁ የተቃዋሚ ድርጅት አባላትን ምን ልታደርጉዋቸው ነው?” በማለት ጥያቄ አንስተዋል።

ለሱዳን ተላልፎ የተሰጠውን መሬት በተመለከተ የአካባቢው ሰራተኞች የሁለቱን

No comments: