Sunday, October 6, 2013

ወያኔና ጽንፈኝነቱ ! ኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔን መቃወም ብቻ ሳየሆን አለመደገፍ በራሱ ከተቃዋሚነት ጎራ ይፈርጃል ።

Okteber6/2013

ወያኔ ከጽንሰቱ ጀምሮ ፣ ውለደቱና እድግቱ የሆነው ጽንፈኝነትና ዘረኝነት ሆኖ ከሚታወቅበት ተነስተን ባሁኑ ወቅት አክራሪነትን ሲቃወም እና ሌሎችን ሲወነጅል መስማቱ <ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ> ያስብላል ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔን መቃወም ብቻ ሳየሆን አለመደገፍ በራሱ ከተቃዋሚነት ጎራ ይፈርጃል ።
ነጋዴው ለሃገሪቱ የሚያስመዘግበው የንግድ ዕድገትና ለዜጎች የሚከፍተው የስራ ዕድል እና ተያያዥ አስተዋጾኦች ባሻገር ወያኔን መደገፉን በተለያየ መልኩ ካላስመሰከረና በተጨማሪም ንግድ ቤቱ ግድግዳ ላይ የማቹን ጠ/ሚ ፎቶ በመስቀል የመለስ አምልኮ ተከታየነቱን ካላረጋገጠ ያገልግሎቱ ጠቀሜታ በ ዜሮ ተባዝቶ ከንግዱ አለም ጨዋታ ውጪ ይደረጋል።

ገበሬው ማዳበሪያ ለማግኘትና ዘርቶ ለማጨድ ወያነ ባዘጋጀለት መንገድ ብቻ መግዋዝ ይኖርበታል። ይህን ማድረግ ካልቻለ ግን ከፍተኛ ትጽእኖ የሚደርስበት ሲሆን ከዚያም አልፎ በቀጥታ የሚያረሰው መሬት ተነጠቆ ለልመና ለስደት ሊዳረግ ይችላል።

የሀይማኖት አባቶች የመለስን አምልኮ ካለስብኩ በተቃዋሚ ፓለቲከኞች ጎራ ይምድባሉ
የመንግስት ሰራተኛ ሆኖ ለመቀጠር ቢጫው የወያነ የአባልነት ካርድ ከትምረት ማሰረጃና ከስራ ልምድ በላይ ዋንኛ የቅጥር መስፈረት ነው ።

ተማሪውም ከከፍተኛ የት/ም ተቐማት ተመርቆ ለመውጣት (የትምር ጠራት ችግሩ እነዳለ ሆኖ) የወያኔ አባልነት ፎርም እንዲሞላ ይገደዳል።
ፍርድ ቤቶች በህግ የበላይንት ሳይሆን ለወያኔዎች በሚመች መልኩ በንጹሀን ዜጎች ላይ በግፍ ይፈርዳሉ።

ዜጎች መኖሪአቸው ተነጥቆ ለወያኔ አባላትና ለደጋፊዎቻቸው ተሰጥቶ ለጎዳና ህይወት ይዳረጋሉ ።

ሰላማዊ ታጋዮች ፣ጋዜጠኞች ግለሰቦች የሀይማኖት መሪዎች ለወያኔ ያልተመቸ ማንኛውም ዓየነት እንቅስቃስ የሚያደርግ አካል በአሸባሪነትና በአክራሪት ተፈርዶበት እስር ቤት ይወርወራሉ።

ወያኔ አገራችንን ከተቆጣጠረበት ጀምሮ እስካሁን ድርስ ስንፈኝነትንና እና አክራሪነትን በተቀነባበረ መልኩ ሬት ሬት እያለን ሲግተን የቆየና ዘረኝነትን በየቦታው ሲሰብክና ህዝቡን ሲያወክ የኖረና በተግባር ያሳየን መሰሪ ቡድን አሁን ደሞ ባዲስ መልኩ በቲዮሪ ላስተምራችሁ ብሎ የዩነቨረሲቲ ተማሪዎችን እያስገደደ ይገኛል። ይህ ባዲስ መልኩ የሚንቀሳቀሱበት አካሄድ ጤናማ ያልሆነና ሰራአቱ የህብረተሰቡን ያመለካከት አቅጣጫ በማስቀየር የፈለጉት ኢሰባዊ የሆነወን ያገዛዝ እድሜያቸውን ለማራዘም ያቀዱት ነገር እነዳለ ያሰታውቃል።
ወያኔን የሚያሰጋው እና እንዲህ እንቀልፍ የሚነሳው የወጣቱ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ እያደረገ ያለውን አምጽ እነድሆነ የታወቃል። ወጣቱ ትውልድ ዘመናዊ ባርነትን እሺ ብሎ የማይቀበል ተፈጥሮ ሰጠችውን ነጻነት በአምባገነኖች ሲነጠቅ ዝም የማይል በመሆኑ ለወያኔ አገዛዝ የማያመች ሆኖበታል ።
ሰሞኑን ሀገር ውስጥ እየታየ ያለው በተለይ ወያኔ በኢትዮጵያ ውስጥ ያጸደቀው የጸረሽብር ህግ ሳይገታው ህዝቡ ለነጻነቱ ለመታገል ዝምታን ሰብሮ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን በገለጸበት እና ባሳየው ወኔና ቁጣ ወያኔን ማሸበሩ በወቅቱ ከድሬዎችና ፈደራል ፖሊስ ካደርጉት ህገወጥ እንቅስቃሴ ማረጋገጥ ይቻላል። ወያኔን እነቅለፍ መነሳት እና እነዲ ማሸበር ልኛ የነጻነት ቀናችን መቅረቡን ከበስበስ የቆየው ለወያኔ አገዛዝ ደግሞ መውደቂያው መቅረቡ የሚያሳይ ነው ።

No comments: