Wednesday, October 2, 2013

የአዜብ መስፍን የመያዝ እድል እየሰፋ ነዉ የሙስና ንሰሃ አባቷ እና ባልደረባዋ ተይዟል።

Oktober 2 / 2013
የአዜብ መስፍን የመያዝ እድል እየሰፋ መቷል። የሙስና ንሰሃ አባቷ እና ባልደረባዋ ተይዟል። በከፍተኛ ደረጃ በሙስና በመዘፈቅ ያለአከራይ ከባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ለቁጥር የማይገመት ሃብት አፍርተዋል የተባሉት ሃያሁለት አካባቢ የሚገኘው የኮሜት ሕንጻ ባለቤት አቶ ገብረስላሴ ሃይለማርያም (አለቃ ገብረስላሴ) በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ በባለስልጣናት ዙሪያ ከፍተኛ መደናገጥ ተፈጥሯል። የካፒታል ሆቴል ባለቤት የሆነው ልጃቸውም እንዲሁ ሁኔታዎች እየተጣሩበት ሲሆን የአለቃ ገብረስላሴ የሙስና መዝገቦች ከገብረዋህድ ጋር የተቆራኙ እና ከዚህም ጋር በተያያዘ አዜብ መስፍንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ይውላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የሙስና ንሰሃ አባት የሚባሉት እና በአቋራጭ የከበሩት በማናለብኝ ጭነት እና በትዕቢት በመንግስት ባለስልጣናት የሚመኩት አለቃ ገብረስላሴ ባለፉት አራት ወራት ከተያዙት እና የአዜብ መስፍን የሙስና አጋሮች ከሚባሉት መላኩ ፋንታ፣ ገብረዋህድ ፣ወ/ጊ ፣ነጋ ገ/እግዜር ፣ስማቸው ከበደ፣ ከተማ ከበደ እና ሌሎች የሙስና ባላባቶች ጋር እንደተያዙ ወዲያውኑ የቃሊቲን ቂሊንጦ ጎራ ተቀላቅለዋል።

እስካሁን ድረስ በፍርድ ቤት የቀረበባቸው የክስ ዝርዝር ባይታወቅም በመጪው የጥቅምት 14 እና 18 2013 ክሱ የሚሰማ መሆኑ ታውቋል። ውስጥ አዋቂዎች እንደሚሉት አለቃ ገብረስላሴ ክስ ሳይመሰረትባቸው ቃሊቲ መውረዳቸው አጠያያቂ ነው ሲሉ ተደምጥጠዋል። ሆኖም እንደመርማሪዎቹ ምንጮች ከሆነ የተከሰሱት በገብረዋህድ መዝገብ ጋር በአንድነት እንደሆነ ታውቋል። ፋይሉ አካባቢ ያሉ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በተከለከለው ከፍራንኮ ቫሉታ በመጠቀም በህገወጥ መንገድ ሲሚንቶ አስገብተዋል የተለያዩ እቃዎችን ቀረጥ ሳይከፍሉ አስገብተዋል በጉቦ እና በህገወጥ ገንዘብ ዝውውር ወዘት የሙስና ተግባራት ከባለስልጣናት ጋር ተመሳጥረዋል በሚለው ፋይል የተካተቱ ሲሆን በዚህ ፋይል ደግሞ የአዜብ መስፍን የሙስና አጋሮች ገብረዋህድ እና ሚስቱ ሃይማኖት እንዲሁም የስዬ አብርሃ ወንድም ምህረተአብ ይገኙበታል::
 
 ምንሊክ ሳልሳዊ

No comments: