Wednesday, October 16, 2013

ሁላችንም ለእውነተኛ ትግል መስዋዕት ለመሆን እራሳችንን ማነሳሳት ይጠበቅብናል::

Oktober 16/2013
ከገዛኸኝ አበበ ኖርዌይ

ዛሬ ሀገራችን ኢትዮጵያ ካለችበት የኢህአዲግ ስርአት ለመላቀቅ እና ከገባችበት ፖለቲካዊ ማህበራዊ እና ኢኮኖሜያዊ ውድቀት ወጥታ ህዝቡም ከወያኔ ስርዓት ተላቋ ወደ ተሻለ እና ወደ ተረጋጋ ሕይወት ለመድረስ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ድርሻ መወጣት እና በሁሉም አቅጣጫ እና በሚችለው መንገድ መታገል ይጠበቅበታል:: ዛሬ ላይ ወያኔ ኢህአዲግ የእምነታችንን ነጻነት እያሳጣን የዜጎቻችን ሰብዓዊ መብት እየረገጠ እና የዜግነት ክብራችንን እና ነፃነታችንን በመግፈፈ የባርነት ኑሮ እየኖርን እንገኛለን::  ግን እስከ መቼ ብለን እራሳችንን ልንጠይቅ ያስፈልጋል::

 ይህንን ጨቆኝ እና ገዳይ ስርዓት በቃወም ለእምነታቸው ነጻነት ለዜጓች ሰብዓዊ መብት መከበር እየታገሉ  ያሉ ብዙ ወንድሞቻችን እና ህህቶቻችን  ለእንግልት ፥ ለእስር እና ለስቃይ ተዳርገዋል እስከ አሁን ድረሰ ደግሞ ባልሰሩት በደል በእስር ላይ የሚገኙ ወገኖቻችን በእየ እስር ቤቱ መስዋትን እየከፈሉ ይገኛሉ :: እውነታኛ ትግል መስዋትነትን የሚጠይቅ ሲሆነ  ሁላችንም ለዚህ ትግል በአንድነት በመተባበር መነሳሳት  ይጠበቅብናል ::  በአንድነት ተባብረን ከታገለን የኢትዮጵያን ትንሳዬ የምናይበት ቀን ሩቅ መስሎ አይታየኝም::

ይህን ትግል ለተወሰኖ ሰዎች እና ለተወሰኑ ፖለቲካ ፖርቲዎች የምንተወው ሳይሆን በማንኛውም መንገድ እና አቅጣጫ ትግሉን እያካሄዱ ያሉትን አብረን ከጓናቸው ልንቋም ትግሉን ልናቀጣጥለው እና በምንችለው መንገድ ልንደግፋቸው ይገባል ባይ ነኝ ::

  ዛሬ ላይ ወያኔ ኢህአዲግን እየተቃወሙ ያሉ የተቀዋሚ ፓርቲዎች ሁለት አይነት አመለካከት እና እምነት ይዘው ኢህአዲግን እየተፋለሙት ይገኛሉ:: በአንድ ወገን ትግላችንን በሰላማዊ መንገድ በማካሄድ ኢህአዲግን ማዳከም ማሽመድመድ  እና ማስወገድ ይቻላል የሚል ሲሆን በሌላው ወገን ያሉት ደግሞ ወያኔ ኢህአዲግን የምንለማመጥበት ዘመን አብቅቷል ወያኔ ክብር የማይወድለት ስለሆነ በትጥቅ ትግል በመደራጀት እና በመታገል ነው ኢህአዲግን ማስወገድያለብን  የሚል አመለካከት አላቸው :: ይህንንም እምነታቸውን እውን ለማድረግ  ሰላማዊን ትግል የሚያምኑት ይዘው የተነሱትን ዓላማ ላማስፈጸም በቆራጥነት በመነሳት በብዙ መንገድ እየሞከሩት እና ለሰላማዊ ትግል ህዝቦችን እያደራጁ  ይገኛሉ::  ነገር ግን ይህ የፓርቲዎች አካሄድ እና እያደረጉት ያሉት ሰላማዊ ትግል ለገዢው ፓርቲ ለኢህአድግ የተዋጠለት አይመስልም::  ብቻውን በአንባ ገነንነት እና በማን አለኝነት ህዝብና በሀይል  እና በጉልበት መግዛት የለመደ ስለሆነ ለዚህ ለሰላማዊ ትግል የተነሱትን የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃይላቸውን ለማዳከም ንብረታቸውን በማውደም መሪዎቻቸውን እና አባሎቻቸውን በማሰር ዋጋ እያስከፈላቸው ይገኛል:: እያየነው ያለውም ይህንኑ ነው  ባለፈው ጊዜ የሰማያዊው ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ወያኔ ኢህአዲግ እያደረሰባቸው ስላለው ግፍ እና ጫና ሲናገሩ የትኛውንም አይነት መስዋዕት ልንከፍል ዝግጁ ነን  ነበር ያሉት  ኢንጅነሩ ሲናገሩ እስከ ህይወት መስዋዕትነት ልንከፍል እንችላለን ከትግላችን ግን የሚያቆመን የለም ብለዋል::  በርግጥ ማንኛውም ትግል መስዋዕትነት ይጠይቃል:: በቆራጥነት እና በጽናት ከታገልን ግን የተከፈለውን ያህል መስዋዕት ተከፍሎ ለውጥን ማምጣቱ አይቀርምና ::

በሌላው ወገን ያሉት ደግሞ ወያኔ ኢህአዲግን የምንለማመጥበት ዘመን አብቅቷል ወያኔ ክብር የማይወድለት ስለሆነ በትጥቅ ትግል በመደራጀት መታገል አለብን የሚል እምነት ይዘው በሚችሉት መንገድ ሁሉ መስዋዕትን ለመክፈል ቆርጠው የተነሱትን ቆራጦች በየአቅጣጫው ለዓላመቸው መስዋትነትን እየከፈሉ ሲገኙ ሕይወታቸውንም መስዕዋት ለማድረግ መነሳታቸውን በቆራጥነት እየወጁ እንደሆነ እናውቃለን::  ወያኔን ለማስወገድ በሁሉም አቅጣጫ የምናደርገው ጉዙ እና ትግል ቀላል የማይሆን መስዋዕት የሚያስከፍልም ቢሆን በእውነትእና በቁርጠኝነት ከታግለን ኢትዮጵያን ከዚህ አስከፊ ስርዓት ነፃ የምናወጣበት ቀን ቅርብ ነው::  ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ደግሞ ለዘመናት ሲገዛን ፣ ሲጨቁነን እና ሲያሰቃየን የነበረውን ይህን ዘረኛ መንግስት ይበቀኻል በቃህ ብለን በእውነት ከእነዚህ ፓርቲዎች ጓን በመቆም እና በመሰለፍ ለእውነተኛ ትግል እራሳችንን ማነሳሳት  ይጠበቅብናል :: ጌዚያችንን መስዋዕት፣ ገንዘባችንን መስዕዋት ፣ዕውቀታችንን መስዋዕት ፣ ለማድረግ ቆርጠን እንነሳ:: ከእነዚህ ፓርቲዎች ጎን እንቁም ትግሉንም እንቀላቀል::

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ 

No comments: