Saturday, October 19, 2013

ኃ/ማሪያም ደሳለኝ “መንግስት ፈርቷል እያላችሁ ራሳችሁን አታሞኙ” ሲል ማሾፉ ተሰማ

October 18/2013

ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት አንዴ “ቀይ መስመር ረገጣችሁ” አንዴ ሰላማዊ ሰልፍ እከለክላለሁ፤ ሌላ ግዜ ደግሞ ኢህአዴግ ለተቃዋሚዎች ጥያቄ መልስ ሰጥቷል እያለ የባጥ የቆጡን ሲቀባጥር የሰነበተዉ የወያኔዉ ሎሌ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ በዚህ ሳምንት ደግሞ በተወካዮች ምክር ቤት ተገኝቶ ““መንግስት ፈርቷል እያላችሁ ራሳችሁን አታሞኙ” ብሎ በመደንፋት “ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም” የሚባለዉን የአገራችንን ተረት የሚያስታዉስ የፈሪ ንግግር አድርጓል። ጠ/ሚኒስቴር ተብዬዉ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ከዚያ እንቅልፋም ፓርላማ አባላት ለቀረቡለት ጥያቄዎች መልስ ሲሰጥ መንግስት የጎዳና ላይ ነውጥ ከሚያሰቡት ሀይሎች ጋር ለመነጋገር የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል። ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋር እንኳን መነጋገር እነሱ ባለፉበት መንገድ ማለፍ የሚፈራዉ ኃ/ማሪያም የጎዳና ላይ ነውጥ ከሚያሰቡት ሀይሎች ጋር ካሁን በኋላ አንነጋገርም ማለቱ አንዳንዶችን ያስገረመ ቢሆንም ብዙ የፖለቲካ ተንታኞች አባባሉን የተለመደ የወያኔ የቃላት ጨዋታ ነዉ ብለዉ የኃይለማሪያምን ንግግር አጣጥለዉታል።

በተቃዋሚዎች ፓርቲዎች በኩል የሚቀርበው ጥያቄ ሁሉ ቅጥ ያጣ ፍረጃና የጥላቻ ፖለቲካ ብቻ ነዉ ያለዉ ሎሌዉ ሀይለማርያም ደሳለኝ የጎዳና ላይ ነውጥ እናደርጋለን ብለዉ የሚያስቡ ሀይሎች ሀሳባቸውን እንዲያቆሙ ጠይቋል። በመቀጠልም የጎዳና ላይ ነውጥ ለማስነሳት ስለሚያስቡ ኃይሎች በቂ መረጃ አለን ስንል “መንግስት ፈርቶ ማስፈራራት ጀመረ” እንባላለን ሆኖም ይህ መንግስት አይፈራም፣ ታሪኩም ባህሪውም እንደዛ አይደለም በማለት የሚያዉቀዉን የኢትዮጵያዉያንን የጀግንነትና የአይበገሬነት ታሪክ ትቶ የማያዉቀዉን፤ የሌለዉንና በታሪክ ያልተመዘገበዉን የወያኔን አለመፍራት “ይህ መንግስት ፈርቷል እያላችሁ እራሳችሁን አታሞኙ፣ መንግስት አይፈራም የህዝብ መንግስት ነው” እያለ ያለ ሀፍረት ተናግሯል። ዘረናዉ የወያኔ አገዛዝ ወይ እሱ እራሱ አይጫወትበት ወይ ሌሎቹን አያጫዉት ብቻዉን ጨምድዶ የያዘዉን ኳስ የወያኔዉ ተላላኪ ኃ/ማሪያም ጌቶቹ ሄደህ ተናገር ያሉትን ትእዛዝ ለመፈጸም ብቻ ሲል ብቻ “ኳሱ እናንተ እጅ ላይ ነው” በማለት አባባሉን እንኳን በዉል ያልተረዳዉን ምሳሌ ተናግራል።

No comments: