Wednesday, December 10, 2014

መልዕክት ጨርቆስ ፖፖላሬ ከሚገኙ እስረኞች

December 10,2014
ትግላችን በመደገፍ በተለይም በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት የደረሰብንን የህወሓት/ኢህአዴግ ጭካኔያዊ እርምጃ በመቃውም ከጎናችን ለቆማችሁ በዓለም ዙሪያ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ምስጋናችን እናቀርባለን፡፡ በሰልፉ ወቅት ድብደባን ጨምሮ የደረሰብን በደል በመቃወም በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ሰላማዊ ሰልፍ መውጣታችሁን ሰምተናል፡፡ ትግላችን በመደገፍና ከጎናችን በመቆማችሁ ምስጋናችን ላይ ያለ ነው፡፡ ወደፊትም ከጎናችን እንደምትቆሙ እንተማመናለን፡፡ 

በእኛም ላይ ሆነ በየ እስር ቤቱ የሚገኙት የትግል ጓዶቻችን ላይ የሚደርሰው ግፍና ጭካኔ ያሳስበናል፡፡ በተለይ አዲስ አበባ ፖሊስ ወይንም ሶስተኛ እየተባለ የሚጠራው እስር ቤት ውስጥ ታስረው የሚገኙት የትግል ጓዶቻችንና አጋሮቻችን ላይ ከፍተኛ ደብደባ ተፈጽሞባቸዋል፡፡ ለየ ብቻቸው ጨለማ ቤት ውስጥ እንደታሰሩም ሰምተናል፡፡ ከዚህም ባሻገር ኮተቤ አካባቢ የሚገኙት የትግል አጋሮቻችን ሽንት ቤት ውስጥ መታሰራቸውን ሰምተናል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ (ሶስተኛ) ታስረው የሚገኙት የትግል ጓዶቻችን የሚደርስባቸውን በደልና ጭካኔ አስመልክቶ ከዛሬ ታህሳስ 1/2007 ዓ.ም ጀምረው የርሃብ አድማ ሊያደርጉ እንደሆነ ሰምተናል፡፡ ይህ የትግሉ አንድ አካል ነው፡፡ በተለያዩ እስር ቤቶች የሚገኙት ጓዶቻችን ላይ የሚፈጸመው በደልና ግፍ ምክንያት እኛም ጨርቆስ ፖፖላሬ እስር ቤት ውስጥ ሆነን ትግላችን እየቀጠልን ነው፡፡ በትግል ጓዶቻችን ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት በአስቸኳይ ካላቆመ እኛ ፖፖላሬ እስር ቤት የምንገኝ ታሳሪዎች አንድ ነገር ለማድረግ እየተዘጋጀን ነው፡፡

ያለ መስዋዕትነት ድል የለም!

No comments: