Friday, October 31, 2014

ማዕከላዊ የሚታሰሩት የጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች ቁጥር አሻቅቧል * በርካታ የጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል

October 31,2014
የህወሓት/ኢህአዴግ ባለስልጣናት በኢንቨስትመንት ስም የጋምቤላን ክልል ነዋሪዎች እያፈናቀሉ በያዙት መሬት ምክንያት እንደተቀሰቀሰ የሚነገርለትና ለወራት በዘለቀው ግጭት ተሳታፊ ናቸው የተባሉ በርካታ የጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች ዛሬ ጥቅምት 20/2007 ዓ.ም በአራዳ ምድብ ችሎት መቅረባቸው ታወቀ፡፡
ነዋሪዎቹ ከጋምቤላ ክልል ወደ ማዕከላዊ ከመጡ በኋላ ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበዋል፡፡ ዜጎች ወደ ችሎቱ በሁለት የፖሊስ አውቶቡሶች የመጡ ሲሆን በቁጥር ቢያንስ 50 እንደሚደርሱ ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ችሎቱ በዝግ እንደተካሄደም ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከጋምቤላ ክልል የመጡት ዜጎች በአራዳ ምድብ ችሎት በቀረቡበት ተመሳሳይ ሰዓት የሸዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺና አብርሃ ደስታ የሚቀርቡ በመሆኑ በዚህ ችሎት ለመታደም የሄደው ህዝብ ከጋምቤላ የመጡት ዜጎች ላይ በተደረገው ጥብቅ ጥበቃ ምክንያት ከፍተኛ ፍተሻ እንደተደረገበት በቦታው የተገኘው የነገረ ኢትዮጵያ ዘጋቢ አረጋግጧል፡፡ በቦታውም ለጥበቃ የፌደራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስና የማረሚያ ቤት ፖሊስ እንደተገኙም ታውቋል፡፡ ዛሬ አራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡት የጋምቤላ ክልል ነዋሪች መቼ ወደማዕከላዊ እንደመጡ የታወቀ ነገር የለም፡፡
በሌላ በኩል ትናንት ጥቅምት 19/ 2007 ዓ.ም ወደ ማታ አካባቢ ጋምቤላ ክልል ውስጥ በተፈጠረውና ለወራትም የበርካታ ሰው ህይወት ከጠፋበት ግጭት ጋር በተያያዘ በርካታ ዜጎች በአውቶቡስ ተጭነው ወደ ማዕከላዊ መግባታቸውን የአይን እማኞች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ወደ ማዕከላዊ ከመጡት መካከል የአካባቢው ባለስልጣናትም እንደሚገኙበት የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች አክለው ገልጸዋል፡፡
በዛሬው ዕለት ችሎት የቀረቡትንና በትናንትናው ዕለት ወደ ማዕከላዊ የመጡን ጨምሮ ጋምቤላ ክልል ውስጥ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ማዕከላዊ የሚታሰሩት ዜጎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሸቀበ መሆኑም ተገልጾአል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ ለአንባቢዎቿ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማቅረብ ጥረት ታደርጋለች፡፡

United States call for the Ethiopian government to release journalists

October 31, 2014

U.S. Deeply Concerned by Sentence of Ethiopian Journalist

Press Statement
Jen Psaki
Department Spokesperson
Washington, DC
October 30, 2014
The United States is deeply concerned by the October 27 sentencing of Ethiopian journalist Temesgen Desalegn to three years in prison forU.S. Deeply Concerned by Sentence of Ethiopian Journalist “provocation and dissemination of inaccurate information.” Freedom of expression and freedom of the press are fundamental elements of a democratic society, and the promotion and protection of these rights and freedoms are basic responsibilities of democratic governments.
As President Obama stated during his meeting in September with Ethiopian Prime Minister Hailemariam, it is important that Ethiopia’s progress and positive example on economic development and regional conflict resolution extends to civil society as well. We urge Ethiopia to make similar progress with regard to respect for press freedom and the free flow of ideas and reiterate our call for the Ethiopian government to release journalists imprisoned for exercising their right to freedom of expression.

Thursday, October 30, 2014

ሚኒስትሮች ባልተወራረደ የመንግስት ገንዘብ ጉዳይ ላይ ጎራ ለይተው ተከራከሩ

October 30,2014
የፌደራል ዋና ኦዲተር፣ አባካኝ የመንግስት ተቋማት በሚል ለጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት እና ለተወካዮች ም/ክር ቤት አፈ ጉባኤ ያቀረበው ሪፖርት ለህዝብ ይፋ ይሁን አይሁን የሚለው ጉዳይ ሚኒስትሮችን አወዛግቧል።
943አቶ አባዱላ ገመዳ፣ አቶ ደመቀ መኮንን፣ አቶ አዲሱ ለገሰና አቶ ጸጋየ በርሄ፣ የፌደራል ኦዲተሩ ሪፖርት ለህዝብ በፍጹም ሪፖርት መደረግ የለበትም ብለው ሲከራከሩ፣ የመንግስት ጉዳዮች ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈርያት ከማል፡ ለህዝቡ ይፋ በሆነ መልኩ የማሳወቅ እርምጃ መውሰድ ይገባል የሚል አቋም አንጸባርቀዋል። አቶ በረከት ስምኦንና ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ለዘብተኛ የሆነ አስተያየት በመስጠት አቃም ለመያዝ በመቸገራቸው ጉዳዩ እልባት ሊያገኝ አልቻለም።
በውይይቱ ላይ የጥሬ ገንዘብ ሂሳብ ከመዝገብ /ሌጀር / ጋር የማይመሳከር መሆኑ፣ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ በቆጠራ ከተገኘው ጥሬ ገንዘብ በማነስ ሪፖርት የተደረገ መሆኑ፣ የጥሬ ገንዘብ ቆጠራ የማያደርጉ ወይም የጥሬ ገንዘብ ቆጠራ አድርገናል ቢሉም ማስረጀ ያላቀረቡ መሆኑ፣ በባንክ ሂሣብ ገቢ ለሆኑ ሂሣቦች የገቢ ደረሰኝ ያለማዘጋጀትና ያለመመዝገቡ፤ የባንክ ሂሳብ ማስታረቂያ የማያዘጋጁ መሆኑ፤በበጀት ዓመቱ መጨረሻ በባንክ ሂሳብ መግለጫ ዜሮ ከወጪ ቀሪ እየታየ አላግባብ በባንክ ያለ ገንዘብ ተብሎ ሪፖርት የሚደረግ መሆኑ፣ በወጭ ምንዛሬ ባንክ ያለ ገንዘብ /41ዐ2/ ተብሎ ሪፖርት የተደረገውን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የባንክ ሂሳብ መግለጫ ያልቀረበበት ሆኖ መገኘቱ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ድክመቶች ተብለው ተነስተዋል።

ስለመንግሥት ሂሳብ አያያዝ የወጣው ደንብ የደመወዝ ሰነድ ሂሳብ የወሩ ደመወዝ በሚከፈልበት ጊዜ የሥራ ማስኬጃ የሚመለከተው ደግሞ በተለይ የግዥ ሰነድ ከተሰጠበት ቀን አንስቶ በሰባት የሥራ ቀናት ውሰጥ እንዲጠናቀቅ ቢያዝም፣ በኦዲተር መስሪያ ቤቱ ከተመረመሩ መ/ቤቶች ውስጥ በ43 የፌደራል መንግስት መ/ቤቶች ብር 7 ቢሊዮን 99 ሚሊዮን 495 ሺ 265 ብር ከ01 ሳንቲም የሰነድ ሂሳብ በደንቡ መሠረት ሳይወራረድ ተገኝቷል፡፡

ሂሳባቸውን ባለማወራረድ ከፍተኛውን ድርሻ ከያዙት መስሪያ ቤቶች መካከል የትምህርት ሚኒስቴር ብር ከ451 ሚሉዮን ብር በላይ ፣ግብርና ቴክኒክ ሙያና ትምህርት ስልጠና ብር 232 ሚሊዬን ፣የመከላከያ ሚ/ር ብር 228 ሚሊዬን ፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ብር 225 ሚሊዬን፣ ጎንደር ዩንቨርስቲ 89 ሚሊዬን ፣መቀሌ ዩንቨርስቲ ብር 36 ሚሉዬን ፣ግብርናና ገጠር ልማት ሚ/ር የምግብ ዋስትና ዳይሬክቶሬት ብር 23 ሚሊዬን እና ማዕከላዊ ስታስቲክስ ብር 23 ሚሊዩን ብር ይገኙበታል ።

ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተወጣጣ ኮሚቲ ተቋቁሞ ባደረገው ጥረት የብር 767 ሚሊዮን 425 ሲ ከ 04 ሳንቲም ሰነድ የሚወራረድበትን መንገድ ለማመቻቸት እየሰራ መሆኑ ቢገለጽም ፣ በሌሎች መስሪያ ቤቶች ስላለው ሁኔታ በዝርዝር አልታወቀም።
ውዝፍ ሰነዱን በወቅቱ አለማወራረድ ለመንግስት ገንዘብ መጥፋት በር የሚከፍት ስለሆነ በአስቸኳይ መወራረድ እንዳለበት ፣ ለረጅም ዓመታት ሳይሰበሰቡ የተገኙት ሂሳቦች እንዲወራረዱ አስፈላጊው ክትትል እንዲደረግ፤ ሊሰበሰቡ በማይችሉት ላይ በመንግስት መመሪያ መሠረት ከመዝገብ እንዲሰረዙ እንዲደረግ ኦዲተር መስሪያ ቤቱ አስተያየቱን አቅርቧል።

በገቢ ግብር፣ቀረጥና ታክስ እንዲሁም በሌሎች ገቢ መሰብሰብ በሚፈቅዱ አዋጆች መሠረት የመንግስትን ገቢ የሰበሰቡ መሆኑን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ ደግሞ፣ በ1ዐ መ/ቤቶች ውስጥ 5 ቢሊዮን 492 ሚሊዮን 319 ሺ 53 ብር በተለያዩ ምክንያቶች ሳይሰበሰብ ተገኝቷል፡፡

ሂሳቡ ሳይሰበሰብ ከቀረበባቸው ምክንያቶች መካከል በትክክለኛው የታሪፍ ቁጥር (Harmonized System code) እና(custom procedure code) ባለለመደባቸው ያልታሰበሰበ ቀረጥና ታክስ ፣የመነሻ ዋጋ የተወሰነላቸው ዕቃዎች በመነሻ ዋጋው መሰረት ያልተሰተናገዱ ድርጅቶች መገኘታቸው ፣በማነፃፀሪያ ዋጋ መሰረት ቀረጥና ታክስ ባለመሰራቱ እና መ/ቤቶች ከሚፈፀሙት ግዥ ላይ ቀንሰው ማስቀረት የሚገባቸው ግብር ( Withholding tax) ፤የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሥራ ግብር ሳይቀነሱ መቅረታቸው የሚሉት በኦዲተሩ ሪፖርት ተመልክተዋል።

ስለሁኔታው ትኩረት ተሰጥቶት የመንግስት ህግና ደንብ ተከብሮ እንዲሰራ ፣ ያልተሰበሰበውም ገቢ እንዲሰበሰብ መስሪያ ቤቱ አሳስቧል። በገቢ ሰብሳቢ መ/ቤቶችና አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች በወጣው ህግና ደንብ መሠረት የመንግስት ገቢ በአግባቡ መሠብሰባቸውን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ ደግሞ በገቢዎች ጉምሩክ ባለስልጣን ስር ባሉ ሶስት ቅርጫፍ ጽ/ቤቶች ከወለድና ቅጣት መሰብሰብ የሚገባው ብር 323 ሚሊዮን 794 ሺ 818 ብር ከ43 ሳንቲም፤ በጉምሩክ የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት ብር 78 ሚሊዮን 973 ሺ 321 ከ94 ሳንቲም የአዲስ አበባ ኤርፖርት ቅ/ጽ/ቤት ሊሰበሰብ የሚገባው ብር 5 ቢሊዮን 934 ሺ 794 ከ47 ሳንቲም ከ6 ወር በላይ የቆየ ውዝፍ ሂሳብ የተገኘ ሲሆን ፤ የአዲስ አበባ የወጪ ዕቃዎች ማስተናገጃ ቅ/ጽ/ቤት የተወሰነላቸው የጊዜ ገደብ ጠብቀው ባለመጓጓዛቸው ተገቢ ቅጣት ከተወሰነላቸው ሾፌሮች እና ወኪሎች ያልተሰበሰበ ብር 30 ሺ 000.00 በድምሩ ር 394 ሚሊዮን 495 ሺ 607 ከ69 ሳንቲም በወቅቱ ያልተሰበሰበ ውዝፍ ገቢ ተገኝቷል፡፡

የተሰበሰበውን ገቢ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ ፣በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ስር ባሉ ሶስት ቅርጫፍ ጽ/ቤቶችና በሌሎች ሶስት መ/ቤቶች በድምሩ ብር 69 ሚሊዮን 753 ሺ 608 ከ97 ሳንቲም የገቢ ደረሰኝ እና የግብር ማሳወቂያ በፋይሉ ጋር ተያይዞ ባለመገኘቱ ምክንያት ፤ከማን እንደተሰበሰበ ሳይገለጽ በኮድ በመሰብሰቡ የተሰበሰበው ገቢ መሰብሰብ በሚገባው ልክ መሆኑን ለማረጋገጥ ባለመቻሉ የተሰበሰበው ገቢ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ሳይቻል ቀርቷል፡፡

በበጀት ዓመቱ የተሰበሰበው ገቢ በትክክል ተመዝግቦና በሂሳብ ሪፖርታቸው ተካቶ ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መቅረቡን ለማረጋገጥ ኦደት ሲደረግ ፤ 9 መ/ቤቶች ባቀረቡት ዓመታም የገቢ ሂሳብ ሪፖርት ውሰጥ ብር 659 ሚሊዮን 51 ሺ ሳይካተት ተገኝታል፡፡

ይህ ሪፖርት ለህዝብ ይፋ ቢሆን፣ ለመንግስት ከፍተኛ ኪሳራ እንደሚያመጣ የተከራከሩት የእነ አባዱላ ቡድን፣ ሪፖርቱ በታሹ ቃሎች እንዲቀርብ ይፈልጋል። ወ/ሮ ሙፈሪያ ደግሞ በመስሪያ ቤቶች ላይ እርምጃ መውሰድ ካልተጀመረ ችግሩ የከፋ እንደሚሆን ተከራክረዋል። አቶ በረከትና አቶ ሃይለማርያም አቋም ለመያዝ ተቸግረው ታይተዋል።

አቶ መለስ ዜናዊ ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ሪፖርት ሲቀርብላቸው ሪፖርቱ እንዲጣራ ከመጠየቅ ይልቅ፣ በጄኔራል ኦዲተሩ ላይ እርምጃ መውሰዳቸው የአንድ ወቅት መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። መንግስት ተገቢውን ቁጥጥር ባለማድረጉ በእያመቱ በመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚታየው የገንዘብ ጉድለትና ብክነት እየጨመረ ሲሆን፣ በአገሪቱ ለሚታየው ከፍተኛ ሙስናም አስተዋጽኦ እያደረገ ነው።

ኢሳት ዜና

ገዢው ፓርቲ ንፁሀን የፖለቲካ አመራሮች ጋዜጠኞችና ጦማሪያንን በደል ለማሳጠር እንዲቻል አንድነት ፓርቲ መላው ኢትዮጵያ ህዝብ እንዲነሳ ጥሪ አቀረበ

October 30,2014
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዛሬ በጽ/ቤቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ፡፡
ፓርቲው በሰጠው መግለጫ ገዢው ፓርቲ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለሥርዓቱ ያሰጉኛል የሚላቸውን ንፁሀን የፖለቲካ አመራሮች፣ ጋዜጠኞችና ጦማሪያንን በህገ ወጥ መንገድ ክስ መስርቶ ማሰሩ ሳያንስ ኢሰብአዊ በሆነ መንገድ በእስር ቤት እያሰቃያቸው ይገኛል፡፡ ፓርቲው ይህንን የበደል ዘመን ለማሳጠር እንዲቻል መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲነሳ ጥሪ እናቀርባለን ብሏል፡፡
997075_720293321388938_6063689389032781179_n
1920081_720292178055719_7443225194049807735_n
10392406_720292508055686_6642885533482986101_n10521791_720292608055676_1244395237942149339_n


አቡነ ማትያስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለን አካል አክራሪና አሸባሪ ካሉ በውግዘት እንደሚለዩ ቅዱስ ሲኖዶሱ በጥብቅ አስጠነቀቃቸው! የዕለቱ የምልአተ ጉባኤው ውሎ በድንገት ተቋረጠ

October 30,2014

  • ያደረውን የሕገ ቤተ ክርስቲያን አጀንዳ በፈቃዳቸው ትተው ሌላ ርእሰ ጉዳይ አንሥተዋል
  • የተቃወሟቸውን አባቶች በአሳፋሪ ንግግሮች በመዝለፍ ለማሸማቀቅ ሙከራ አድርገዋል
  • የሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አጀንዳ ቀጣይነት በድምፅ ሊወሰንበት እንደሚችል ተመልክቷል
  • እንደ ሕጉ ስብሰባውን በአግባቡ ካልመሩ ምልአተ ጉባኤው ሌላ ሰብሳቢ መርጦ ይቀጥላል
*                *               *
  • ‹‹ተጠሪነትዎ ለቅዱስ ሲኖዶስ ነው፤ በቤተ ክርስቲያን ሕግ ቢመሩ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱን ቢያከብሩ ይሻልዎታል፤ ሕግ አይገዛኝም ካሉ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንሔዳለን፡፡›› /ቅዱስ ሲኖዶሱ/
  • በቅ/ሲኖዶስ ከተወሰነው በተፃራሪ ማኅበሩ ለልዩ ጽ/ቤታቸው ሳያሳውቅ አንዳችም መርሐ ግብር እንዳያከናውንና ከስብሰባው መጠናቀቅ በኋላ የሚወስዷቸውን ሕገ ወጥ ርምጃዎች መከላከልን በተመለከተ መመሪያ እንዲሰጥ ብፁዕ ዋና ጸሐፊው እና ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጠይቀዋል፡፡
  • ‹‹ማኅበራት ገንዘባቸውን ወደ ማእከላዊ ካዝና ያስገቡ ይላሉ፤ የማኅበራት ዓላማ ገንዘብ ማሰባሰብ አይደለም፤ ገንዘብ አሰባሳቢ አይደሉም፤ ለተቋቋሙበት ዓላማ ያሰባሰቡትን ገንዘብ ግን እንዴት ሥራ ላይ እንዳዋሉት መቆጣጠር ይገባል፡፡››
  • ‹‹ዓላማዎ ማኅበሩን መዝጋት ነው፤ አይደለም? አይዘጋም!››
/የምልአተ ጉባኤው አባላት/
*               *             *
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አክራሪና አሸባሪ ሊባል የሚችልና የሚገባው አካል እንደሌለ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አባላት ገለጹ፡፡ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስም በማንኛውም መድረክ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለን አካል/ተቋም አክራሪና አሸባሪ ከማለት እንዲቆጠቡ ምልአተ ጉባኤው በጥብቅ አስጠንቅቋቸዋል፡፡
‹‹በቤታችን ውስጥ አክራሪና አሸባሪ የሚባል አንድም አካል የለንም፤›› ያሉት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ፓትርያርኩ ሌሎች በሌላ መድረክ እንደሚሉት፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለን አካል አክራሪና አሸባሪ የሚሉ ከኾነ ‹‹ተወጋግዘን እንለያያለን›› ሲሉ በአጽንዖት አሳስበዋቸዋል፡፡
ፓትርያርኩ በትላንቱ የስብሰባ ውሎ፣ በጽሑፍ ተዘጋጅቶ የተሰጣቸውን እየጠቀሱ ማኅበራትን ከአክራሪነትና አሸባሪነት ጋራ እያቆራኙ ማብራሪያ ለመስጠት ሞክረዋል፡፡ በምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ንግግራቸውም ቤተ ክርስቲያን በአክራሪነት የምትፈረጀው፣ ‹‹ማኅበራት በመንግሥትና በቤተ ክርስቲያን የማይታወቅ ሀብት ስለሚሰበስቡ ነው፤›› በማለት ‹‹በሕግ ማስተካከል አለብን›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ለዚኽም በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ‹‹ሕጋዊና ዘላቂ መፍትሔ አስቀምጣለኹ›› በሚል ለውይይት በቀረበው የማሻሻያ ረቂቅ÷ ማኅበራት ገንዘባቸውን ወደ መንበረ ፓትርያርኩ ገቢ እንዲያደርጉ የሚያስገድድና ተጠሪነታቸውም ለቅዱስ ሲኖዶሱ መኾኑ ቀርቶ ለፓትርያርኩ እንዲኾን የሚደነግግ አንቀጽ ካልገባ በሚል የምልአተ ጉባኤውን ሒደት ለተከታታይ ኹለተኛ ቀን እግዳት ውስጥ ከተውት ውለዋል፡፡
በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ የማሻሻያ ረቂቅ፣ የማኅበራትን ጉዳይ ጨምሮ በፓትርያርኩና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ መካከል ጎልተው የወጡ ሦስት ዐበይት ነጥቦችን ባስቀመጠው ልዩነት ትላንት የተጀመረው ፍጥጫ የተሞላበት ውይይት በዛሬ፣ ጥቅምት ፲፰ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. የቀትር በኋላ ውሎው ወደለየለት መካረር አምርቶ ብዙም ሳይቆይ ለስብሰባው በድንገት መቋረጥ ምክንያት ኾኗል፡፡
የስብሰባው ምንጮች እንደተናገሩት፣ ጠዋት ስብሰባው እንደተጀመረ ርእሰ መንበሩ ከትላንት ለዛሬ ስላደረው አጀንዳ ምንም ሳያሳውቁ በቀጥታ በደቡብ አፍሪቃ ከሊቀ ጳጳሱ ጋራ ስላለው አለመግባባት ወደተመለከተው አጀንዳ አለፉ፡፡ በአንዳንድ የስብሰባው ምንጮች መረጃ፣ ፓትርያርኩ ለአኹኑ እንተወውበሚል ወደ ግንቦት እንዲሸጋገር ጠይቀው እንደነበር ተጠቁሟል፡፡
ኹኔታው ለጊዜው በዝምታ ቢታለፍም በሻይ ዕረፍት ሰዓት ብፁዓን አባቶች በጉዳዩ ላይ ተነጋግረውበት ከዕረፍት መልስ የአርቃቂው ኮሚቴ አባል በኾኑት ብፁዕ አቡነ አብርሃም ጥያቄ ተነሥቷል፡፡
‹‹ለምን ወደ ሌላ አጀንዳ ይገባል፤ ጉዳዩ በዚኽ መልክ መታለፉ አግባብ አይደለም፤›› ያሉት ብፁዕነታቸው የልዩነት አቋም የተያዘባቸው የአጀንዳው ነጥቦች በውይይት እልባት እንዲያገኙ አልያም ምልአተ ጉባኤው በሕጉ መሠረት ድምፅ እንዲሰጥበት ጠይቀዋል፡፡
ፓትርያርኩም የትላንቱን አቋማቸውን እየመላለሱ ‹‹ገንዘባቸውን ገቢ ያደርጋሉ፤ ገቢ ካላደረጉ በተኣምር አናየውም፤ እርሱ ይቆይና ወደ ሌላው እንግባ፤››ይላሉ፡፡ ስለማኅበረ ቅዱሳን እያወሩ ከኾነ ያለአጀንዳው እንዳያነሡት በግልጽ ቢጠየቁም ቀጥተኛ ምላሽ ሳይሰጡ ‹‹ብቻ ገንዘባቸውን ገቢ ያደርጉ›› ይላሉ፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱም ‹‹ማኅበራት በበጎ ፈቃድ ለተነሡበት አንድ ዓላማ የቆሙ እንጂ ገንዘብ አሰባሳቢ አይደሉም፤ ለተቋቋሙበት ዓላማ ለመሥራት ያሰባሰቡትን ገንዘብ ግን እንዴትና ምን እንደሠሩበት መቆጣጠር ይገባል፤›› በሚል አቋማቸው ያለበትን ግድፈት እየነቀሱ የቀናውን ለማመላከት ይሞክራሉ፡፡ በትላንት ውሏቸው እንዳደረጉትም ፓትርያርኩ ‹‹ማኅበራት›› ሲሉ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን እንደተናገሩ በመውሰድ የማኅበሩ አጀንዳ በወቅቱና በቅደም ተከተሉ እንዲታይ ያማፅኗቸዋል፡፡
his grace abune Qewustos
ነገሩ ስልቻ ቀልቀሎ… እየኾነ ቢያስቸግር ታዲያ÷ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃምና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ‹‹ዓላማዎ ማኅበሩን መዝጋት ነው፤ አይደለም? ማኅበሩ በሕጉ ይሔዳል እንጂ አይዘጋም፤›› ብለዋቸዋል፡፡ ሌሎችም ብፁዓን አባቶች ቃላችኁ ቃላችን ነው ሲሉ አስረግጠዋል፡፡
የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ እስኪጠናቀቅ ማኅበሩ በዋና ሥራ አስኪያጁ ጽ/ቤት ሥር ኾኖ አመራር እየተቀበለ እንዲሠራ ቅዱስ ሲኖዶሱ ያሳለፈውን ውሳኔና መመሪያ ያስታወሱት የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስና የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ÷ ፓትርያርኩ ውሳኔውን በመጣስ ማኅበሩ ለልዩ ጽ/ቤታቸው ሳያሳውቅ ‹‹ስብሰባም ኾነ ከፊል ጉባኤ እንዳያደርግ›› ማስታወቃቸውንና የማኅበሩን መርሐ ግብሮች እያስተጓጎሉ መኾኑን ተናግረዋል፤ በዚኽ ተፃራሪ መመሪያና ከስብሰባው መጠናቀቅ በኋላ ሊወስዷቸው የሚችሉ መዋቅሩን ያልጠበቁ ሕገ ወጥ ርምጃዎችን መከላከልን የተመለከተ አቅጣጫ እንዲሰጥ ምልአተ ጉባኤውን ጠይቀዋል፡፡
ምልአተ ጉባኤው አንድ ቃል መኾኑን የተመለከቱት አቡነ ማትያስም ግትርነቱ እንዳላዋጣ አይተው ‹‹እሺ፣ ለነገ አሳድሩልኝ›› ማለት ይጀምራሉ፡፡ መግባባት ባለመቻሉና የምሳው ዕረፍት በመድረሱ ‹‹ለምሳ እንውጣና በኋላ እንገናኝ›› ሲባሉ ‹‹ቅድም በልተናልኮ፤ አኹንማ መሸ›› ማለታቸው ግርታም ፈገግታም አጭሯል፡፡
ይኹንና ከምሳ መልስም ‹‹ለነገ ይቀጠርልኝና አኹን ወደ ሌላው እንግባ›› ቢሉም ከዛሬ ለነገ ማስተላለፉ ከአማሳኝ መለካውያን ጋራ ለመዶለት ካልኾነ ትርጉም የሌለው ቢኾንም ጉዳዩ ለነገ የሚያድር ከኾነም ኹሉም ነገር አድሮ እርሱው አስቀድሞ ሳይቋጭ ወደ ሌላ አጀንዳ እንደማይገባ ቁርጡን ያሳውቃቸዋል፡፡
የስብሰባው ምንጮች እንደተናገሩት÷ ከዚኽ በኋላ የተሰማው የአቡነ ማትያስ አነጋገር፣ ሐሳባቸውን በሚሰጡ በእያንዳንዳቸው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ላይ በግል ያነጣጠረ፣ በርካሽና ተራ ቃላት ሌሎች አባቶች እንዳይናገሩ ለማሸማቀቅ የሞከሩበት፣ ከአባትነታቸውና ከሓላፊነታቸው አኳያም የማይጠበቅና ቂመኝነታቸውን ያሳየ ነበር፡፡ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ‹‹አንተኮ ጥንትም ጠላቴ ነኽ››፤ ብፁዕ አቡነ ገብርኤልንና ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስን ‹‹አንተኮ እኔን አልመረጥከኝም፤ ድምፅኽን ለሌላ ነው የሰጠኸው››፤ ብፁዕ አቡነ ሉቃስን ‹‹የማኅበሩ ጸሐፊና ሥራ አመራር አባል ነኽ›› ብለዋቸዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ‹‹ፓትርያርክ ቢኾኑም ለካ ቂመኛ ነዎት›› በማለት የቀድሞው አለመግባባት በይቅርታ የተፈታ መኾኑን ቢያስታውሷቸውም አቡነ ማትያስ ግን አልተገሠጹም፤ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ‹‹ሲኖዶሱን መስለው ከሲኖዶሱ ተግባብተው ይሒዱ፤ የያዙት አካሔድ ትክክል አይደለም›› ሲሉ ከቀድሞው ልምዳቸው እየተነሡ ቢመክሯቸውም አቡነ ማትያስ አልተገሠጹም፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፣ ‹‹እኔ በምልአተ ጉባኤው እንደተሰጠኝ ሓላፊነት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ነኝ፤ የማወራውም ስለ ሕግ ነው፤ ቅዱስነትዎም ሕጉን ተመርኩዘው ቢናገሩ ይበጅዎታል፤›› ብለው ቢያሳስቧቸውም አቡነ ማትያስ አልተገሠጹም፡፡
ስለኾነም ምልአተ ጉባኤው ሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ የስብሰባ ሥነ ሥርዐት በሚደነግገው መሠረት÷ ፓትርያርኩ ተጠሪነታቸው ለቅዱስ ሲኖዶሱ በመኾኑ ቅዱስ ሲኖዶሱን እንዲያከብሩ፣ እንደ ሕጉም ስብሰባውን በአግባቡ እንዲመሩ፣ ሕግ አይገዛኝም ካሉም ‹‹ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንሔዳለን›› ሲል ወደማሳሰብ ገብቷል፡፡ የአጀንዳውን ቀጣይነት በተመለከተ የተጀመረውን ርእሰ ጉዳይ በድምፅ አሰጣጥ ማሳለፍ እንደሚቻልተጠቅሶላቸዋል፤ ስብሰባውን በአግባቡ ካልመሩ ደግሞ ዋና ጸሐፊውን ሰብሳቢ በማድረግ መደበኛ ስብሰባውን ለመቀጠል እንደሚገደዱ በግልጽ አስጠንቅቀዋቸዋል፡፡
በሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቅ ላይ የተጀመረው ውይይት በኾነው መንገድ እልባት ካላገኘ ፓትርያርኩ እንደሚሉት ወደ ሌላ ርእሰ ጉዳይ ላለመግባት የወሰነው ምልአተ ጉባኤውም ያለወትሮው ከቀኑ 9፡00 ላይ የዕለቱን ውሎውን ከሰዓቱ በፊት አቋርጦ ተነሥቷል፡፡
በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ የቅዱስ ሲኖዶስ የስብሰባ ሥርዐት፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የሚመራው በፓትርያርኩ ርእሰ መንበርነት ነው፡፡ ፓትርያርኩ በልዩ ልዩ ምክንያት ስብሰባውን መምራት ባይችል በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በተመረጠ የሹመት ቅድምና በአለው አንድ አባት ስብሰባው ሊካሔድ ይችላል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የሚባለው ከአቅም በላይ የኾነ እክል ካላጋጠመ በቀር መላው አባላት የተገኙበት ጉባኤ ሲኾን ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በማናቸውም ስብሰባ ላይ ውሳኔዎችን ሲያሳልፍ÷ ሃይማኖትንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የሚመለከት ከኾነ በሙሉ ድምፅ ያልፋል፡፡ አንድን ጉዳይ ለመወሰን የአባላቱ ድምፅ እኩል በእኩል ከኾነ ቅዱስ ፓትርያርኩ ያለበት ያልፋል፡፡ አስተዳደርን በሚመለከት ጉዳይ ከኾነ ከተገኙት አባላት መካከል ከግማሽ በላይ በኾነ ድምፅ የተደገፈው ሐሳብ ያልፋል፡፡
ምንጭ፡ ሃራ ተዋህዶ

DENOUNCE THE ETHNIC CLEANSING AND MURDER OF AMHARAS

October 30.2014
Amharas and Oromos are the two largest ethnic groups (nationalities) in Ethiopia  and the ruling Tigrean Front (TPLF) has considered both as enemies and taken brutal actions against them. But in the TPLF political mentality (echoed sadly by  some foreign quarters), the Amharas are enemy no 1 and should be targeted for  all kind of brutalities ranging from ethnic cleansing, land grab, massacre and  deliberate impoverishment.
In the past two months more than 550 Amharas have been killed in the southern  regions and in Gambella – the repressive campaign continues ruthlessly. In the  past, the TPLF defined its struggle as anti Amhara and bamed al the ills of the  past regimes on Amharas as a people. For the past 23 years, the hapless people  have been forced to endure massacres of all sorts, the confiscation of their land,  the ceding of one of their fertile regions to the Sudan, forced resettlement, the  confiscation of their land and its annexation to Tigrai (the region of those in  power), imprisonment, exile, deliberate exposure to debilitating diseases, forced  sterilization and more. What has shocked many is that the brutal crimes against  Amharas has been more or less ignored by the international forces and  especially by those claiming to be concerned by human rights and democracy.
The regime commits untold crimes against the people in the Ogaden, Gambella  and other places but all this does not detract from the fact that under the rule of  the TPLF the Amharas are an especially endangered people.
Stop the Ethnic Cleansing of Amharas!
Stop all crimes against all Ethiopians!
Condemn the gross human rights Violations in Ethiopia!

NJUSTICE ANYWHERE IS INJUSTICE EVERYWHERE
SOCEPP, 30 RIGA COVE, WINNIPEG,MB
R2P 2Z7,CANADA
E MAIL: SOCEPP @AOL.COM or socepp@socepp.info
WEB SITE: www.socepp.info

SOCEP
-- -- ---

Wednesday, October 29, 2014

አዲስ አበባ ውስጥ ሌሊት የሚለጠፉ ወረቀቶችን ተከትሎ ውጥረት ነግሷል

October 29,2014
“መረጃ ለአንድ ለአምስት ማቀበል አለባችሁ” ፖሊስና ካድሬዎች
addis p

  • የበር መብራት ማጥፋት ክልክል ነው፤ በሕግ ያስቀጣል
  • “መውጫና መግቢያ ሰዓታችሁ መመዝገብ ይጀመራል ተብለናል” ነዋሪዎቹ
ከትናንት በስቲያ በጨርቆስ አካባቢ አንድ ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሎ መገኘቱን እና ሌሊት ላይ በቦሌ አካባቢ የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን የሚያስተጋቡ ወረቀቶች በየግድግዳውና የኤሌክትሪክ ምሶሶ ላይ ተለጥፈው መገኘታቸውን ተከትሎ በከተማዋ ውጥረት መንገሱን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
“አንድ የጨርቆስ አካባቢ ነዋሪ ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ ‹የጨርቆስ ወጣቶች› ተሰባስበው ይህን ድርጊት ይፈጽሙ ይሆናል ብለው በገመቱት ላይ ቁጣቸውን ገልጸው ነበር፡፡ በተለምዶ ካታንጋ ወደሚባል ስፍራ ሄደው ገዳዩን አውጡ ብለዋል፡፡ መኪኖችን ሰባብረዋል፡፡ ካታንጋ ምንም ፍንጭ ሲያጡ ወደ ፊላሚንጎ አምርተዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ፖሊስ የተወሰኑትን ይዟል፤ ያመለጡም አሉ፡፡ እስካሁንም ውጥረቱ አለ” ስትል አንዲት የአካባቢው ነዋሪ ለነገረ ኢትዮጵያ ተናግራለች፡፡
ቀደም ብሎ ተለጥፎ በተገኘው ወረቀትና በሟቹ ምክንያትም ፖሊስና የኢህአዴግ ካድሬዎች የተለያዩ ጫናዎችን በነዋሪዎች ላይ ማሳደር መጀመራቸው ታውቋል፡፡ “ለስድስት ወራት ችላ ብለውት የነበረው የአንድ ለአምስት አደረጃጀት ስብሰባ አሁን እንደገና ጀምረውታል፡፡ አደረጃጀቱ ስራውን ካቆመና ስብሰባ ካደረግን 6 ወራት አልፈውት ነበር፡፡ ከትላንት ጀምሮ ግን በግዳጅ ጀምረውታል” ሲሉ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
ምንጮች አክለው እንዳስታወቁት ነዋሪዎችን ፖሊስና ካድሬዎች በስብሰባ በመያዝ የተለያዩ የማሳመኛ ሰበቦችን እንደሚያነሱ ተገልጾአል፡፡ “ምርጫ ደርሷልና አብረን እንስራ፡፡ 97 የሆነውን ታውቃላችሁ፡፡ ያ እንዲሆን አንፈልግም፡፡ ስለሆነም ሙሉ ሌሊቱን በራችሁ ላይ መብራት ማብራት አለባችሁ፤ የተከራይ መታወቂያ ማየት አለባችሁ፡፡ እያንዳንዷን መረጃ ለፖሊስና ለአንድ ለአምስት አደረጃጀቱ ማቀበል አለባችሁ” እንዳሏቸውም ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በየስብሰባዎቹ በአብዛኛው የሚገኙት ሴቶች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ነዋሪዎች በግዳጅ በተፈጠሩት የአንድ ለአምስቱ አደረጃጀቶች መሪ ለመሆን የሚፈልግ አለመኖሩንም ምንጮች ተናግረዋል፡፡
“እያንዳንዱ ሰው የሚወጣ የሚገባበትን ሰዓት መመዝገብ ይጀመራል ተብለናል” የሚሉት ነዋሪዎቹ፣ “አከራዮች ተከራዮቻችሁ የሚገቡበትን ሰዓት ገደብ ማስቀመጥ አለባችሁ፤ የበር መብራቱንም ማጥፋት ክልክል ነው፡፡ ሌሊቱን ሙሉ መብራት ያላበራ ይቀጣል፤ ፍርድ ቤት ሁሉ ሊቀርብ ይችላል” ተብሎ በየስብሰባዎቹ እንደተነገራቸው የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ጨምረው አስረድተዋል፡፡ (ምንጭ፡ ነገረ ኢትዮጵያ)

ፕሬዚዳንት ኦባማ ስለኢትዮጵያ ምርጫ ምን ያህል “ያውቃሉ”? ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

October 29,2014
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ  

ፕሬዚዳንት ኦባማ .. 2015 በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው “ምርጫ” ምን ያህል ያውቃሉ? 
ባለፈው ሳምንት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በኢትዮጵያ ካለው የገዥው አካል የልዑካን ቡድን አባላት ጋር በዚህ በዋሽንግተን ዲሲ ላይ በመገናኘት እንዲህ የሚል ንግግር አሰምተው ነበር…”በዚህ ዓመት ጠቅላይ ሚስትር [ኃይለማርያም ደሳለኝ] እና መንግስታችሁ በኢትዮጵያ ምርጫ ለማካሄድ የዝግጅት እንቅስቃሴ በማደረግ ላይ ትገኛላችሁ፡፡ ስለዚያ ጉዳይ ጥቂት ነገሮችን አውቃለሁ…እናም ስለሲቪል ማህበረሰቡ እና ስለመልካም አስተዳደር እንደዚሁም ኢትዮጵያ እስከ አሁን ድረስ ያስመዘገበችውን አንጸባራቂ እድገት እና ተምሳሌትነት እንዴት አድርጎ ወደ ሲቪል ማህበረሰቡም ማሸጋገር እንደሚቻል ለመነጋገር ጥሩ አጋጣሚ ይፈጥርልናል…“  
ገና ከመጀመሪያው ጀምሬ አስተያየቴ ምን ላይ አንዳተኮረ ግልጽ ላድርግ፣ ይህ የአሁኑ ትችቴ ትኩረት አድርጎ የሚያነጣጥረው ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በተለየ መልኩ በፕሬዚዳንት ኦባማ ላይ ነው፡፡ ለዚህም ዋናው ምክንያቴ እርሳቸው በፈቃዳቸው በኢትዮጵያ የምርጫ ፖለቲካ  ውስጥ በተለይ “የማውቃው ነገሮች አሉ” በማለት እመር ብለው ዘለው ገብተውበታል፡፡ እንደዚህ ልዩ በሆነው መግለጫቸው ስለዚያ ምርጫ ጉዳይ የማውቃቸው ጥቂት ነገሮች አሉ በማለት በይፋ በማወጃቸው ስለዚያ ምርጫ ጉዳይ የሚያውቋቸው “ጥቂት ነገሮች” ምን እንደሆኑ በይፋ ለህዝብ ግልጽ ማድረግ እንዳለባቸው ለመጠየቅ እፈልጋለሁ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዚያች አገር በየጊዜው ምርጫ እየተባለ የህዝብ እና የመንግስት ሀብት ያለአግባብ እየባከነ ለይስሙላ የሚካሄደውን ምርጫ በማስመልከት እኔም የማውቃቸውን “ጥቂት ነገሮች” ለእርሳቸው ግንንዛቤ እንዲረዳቸው ላካፍላቸው እፈልጋለሁ፡፡ በፕሬዚዳንቱ ያልተጠበቀ የቃላት አመራረጥ እና አጠቃቀም ግራ ተጋብቻለሁ፣ በትክክል ምን ለማለት እንደፈለጉም ለማወቅ ጉጉት ያደረብኝ ሲሆን ይህ ፈሩን የለቀቀ የሸፍጥ አነጋገር ግን ሳልተች አንደአላልፍ ተገድጃለሁ፡፡
ፕሬዚዳንቱ ስለቀጣዩ የኢትዮጵያ ምርጫ “ጥቂት ነገሮችን” አውቃለሁ ሲሉ እንደ ስለላ ተቋም በሚስጥር የማውቀው ነገር አለ ማለታቸው ነውን? ፕሬዚዳንቱ ስለምርጫው ጥቂት የማውቃቸው ነገሮች አሉ ሲሉ ከዚህ ቀደም የተደረጉ የተጭበረበሩ እና በቀን ብርሀን የምርጫ ኮሮጆዎች እየተገለበጡ በሸፍጥ የተካሄዱ የይስሙላ ምርጫዎች ነበሩ ለማለት ፈልገው ነውን? እ.ኤ.አ በ2015 ስለሚካሄደው የኢትዮጵያ ምርጫ ፕሬዚዳንት ኦባማ የሚያውቋቸውን ጥቂት ነገሮች ግልጽ እንዲያደርጉልኝ በእርግጠኝነት ለማወቅ እፈልጋለሁ፣ ምክንያቱም የንግግራቸው ዳህራ አቀራረብ ጆርጅ ኦርዌል እንዳሉት “በቅጥፈት የታጀበን አንደበት እውነት ማስመሰል“ ከሚለው ጋር መሳ ለመሳ አስመስሎታል፡፡ ፕሬዚዳንቱ የሚያውቋቸውን ጥቂት ነገሮች ለማወቅ በዛር እንደተለከፈ ሰው መንቀጥቀጥ አለብን እንዴ?
እ.ኤ.አ በ2010 በኢትዮጵያ በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ሕወሀት) የበላይነት የሚመራው ገዥው ፓርቲ በጠራራ ጸሐይ የድምጽ ኮሮጆ እየገለበጠ በመዝረፍ እና ምርጫ በማጭበርበር 99.6 በመቶ የመራጮችን ድምጽ በማግኘት ጠቅላላ የፓርላማውን መቀመጫ እንደተቆጣጠረ ያውቁ ነበርን? ይህ የምርጫ ውጤት መቶ በመቶ (100%) ለመሆን የቀረችው የአንድ ፐርሰንት አራት አስረኛ ብቻ ነበረች፡፡
እ.ኤ.አ በ2010 የፕሬዚዳንት ኦባማ ብሄራዊ የደህንነት ምክር ቤት እንዲህ የሚል መግለጫ አወጣ፣ “የኢትዮጵያ ምርጫ ዓለም አቀፍ የምርጫ መስፈርትን የማያሟላ መሆኑን ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች ያረጋገጡት ስለሆነ ይኸ ጉዳይ አሳስቦናል…ከምርጫው ዕለት በፊትም እንኳ ለነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫ የሚሆን የተስተካከለ የምርጫ ሜዳ በስራ ላይ አልዋለም ነበር፡፡ ከቅርብ ዓመታት ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ መንግስት የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በማስፈራራት እና በማሸማቀቅ የፖለቲካ ምህዳሩን በማጥበብ የሲቪል ማህበረሰቡን እና  የነጻውን ፕሬስ እንቅስቃሴ ገድቧል…“ ብለው ነበር፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ ይህንን ሲሉ በአሁኑ ጊዜ የተቃዋሚ ፓርቲዎች እና አመራሮች በገዥው ፓርቲ አምባገነናዊ ማንአለብኝነት ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው፣ እየተሸማቀቁ፣ እየታሰሩ፣ እየተሰቃዩ እና በሸፍጥ የፍርድ ቤት ክስ እየተጉላሉ መሆናቸውን ያውቃሉ?
ፕሬዚዳንት ኦባማ ለመሆኑ እ.ኤ.አ በ2010 በተካሄደው የመጨረሻ አገር አቀፍ ምርጫ የምርጫ ዘገባ በማቅረባቸው ምክንያት ምርጥ እና የብሩህ አዕምሮ ባለቤት የሆኑት የኢትዮጵያ ጀግኖች ጋዜጠኞች ከሰብአዊነት በወረደ መልኩ በየእስር ቤቶች እየታጎሩ በመማቀቅ ላይ እንደሚገኙ ያውቃሉ? ክቡር ፕሬዚዳንቱ እ.ኤ.አ በ2010 የዓለም የፕሬስ ቀንን ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ተጣብቆ የሚገኘውን ገዥ አካል በስም እየጠሩ በተለይም በነጻ ፕሬሱ ላይ እያካሄደ ያውን ጭቆና በማውገዝ እንዲህ የሚል ንግግር አሰምተው አልነበረምን?፣ “በአሁኑ ጊዜ ህዝቦች ከምንጊዜውም በላይ በኢንተርኔት አገልግሎት፣ በተንቀሳቃሽ ስልክ እና በሌሎች ተገጣጣሚ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አማካይነት አስፈላጊውን መረጃ እያገኙ ባለበት ሁኔታ እንደ ቻይና፣ ኢትዮጵያ፣ ኢራን እና ቬንዙዌላ የመሳሰሉ አገሮች የህዝቦቻቸውን ሀሳብን በነጻ የመግለጽ ነጻነትን በመገደብ እና እነዚህን ዘመኑ ያፈራቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች እንዳይጠቀሙ በማድረግ ላይ ናቸው“ አላሉም ነበር እንዴ?
በኢትዮጵያ ባለው ገዥ አካል ቀያጅ የሆነው የበጎ አድራጎት እና ማህበራት አዋጅ መውጣት ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት ቁጥር እ.ኤ.አ በ2010 የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ብቻ ከነበረበት 4,600 ወደ 1,400 አሽቆልቁሎ መውረዱን ሊያስታውሱ ይችላሉን? እነዚህ የተረፉት ጥቂት ድርጅቶች ህልውናቸውን ለማቆየት ሲሉ የሰራተኞቻቸውን ቁጥር ከ90 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ በሆነ መጠን የቀነሱ መሆናቸውን አያውቁምን? እ.ኤ.አ በ2009 “ስህተት እንዳትሰሩ፣ የሲቪል ማህበረሰቡ–የሲቪል ቡድኖች መንግስቶቻቸው በተሻለ የማስተዳደር ብቃት እና መስፈርት ላይ እንዲሆኑ ያግዛሉ“ በማለት የሲቪል ማህበረሰቡን ሁኔታ በማስመልከት ያደረጉትን ንግግር ሊያስታውሱ ይችላሉን? በኢትዮጵያ ውስጥ እ.ኤ.አ በ2009 ወይም በ2010 ከነበረው ቁጥራቸው እጅግ በጣም ባነሰ ሁኔታ ጥቂት ብቻ የሆኑ ድርጅቶች በ2014 በሀገሪቱ ውስጥ ሁሉም በሚባል መልኩ የገዥው አካል ደጋፊ እና ታዛዥ በሆኑ ጥቃቅን የጎጆ ኢንዱስትሪ መሰል ድርጅቶች ባለቤትነት፣ ተግባሪነት እና አመራር ሰጭነት የሚንቀሳቀሱ ብቻ ናቸው ያሉት ብለው የተናገሩትን ሊያስታውሱ ይችላሉን?
ፕሬዚዳንት ኦባማ ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ እድሚያቸው በ20ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ የሆኑ ወጣት ወንዶች እና ሴቶች በፌስ ቡክ እና በሌሎች የማህበራዊ ድረ ገጾች አማካይነት ሀሳባቸውን በመግለጻቸው ብቻ አሸባሪ የሚል ታፔላ ተለጥፎባቸው በቀጥጥር ስር ውለው ወደ ዘብጥያ ተወርውረው በእስር ቤት በመማቀቅ ላይ እንደሚገኙ ያውቃሉን? በኢትዮጵያ ያለው የነጻው ፕሬስ በጭቆና ውስጥ ያለ መሆኑን፣ መታፈኑን እና  እየተዘጋ መሆኑን አያውቁምን? ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ ስድስት ታዋቂ ነጻ ህትመቶች ማለትም አፍሮ ታይምስ፣ አዲስ ጉዳይ፣ እንቁ፣ ፋክት፣ ጃኖ እና ሎሚ የተባሉ መጽሔቶች እንዲዘጉ ተደርገዋል፣ በደርዘን የሚቆጠሩ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞችም ወደ እስር ቤት እንዲወረወሩ እና ከሀገር እንዲሰደዱ ተደርገዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2012 የዓለም የፕሬስ ቀንን በማስመልከት “የጋዜጠኞችን፣ የጦማሪያንን እና የሰላማዊ አመጸኞችን በነጻ የመጻፍ እና የመናገር አቅም እንዳይገደብ ለመጠበቅ እና ምንም ዓይነት የበቀል እርምጃ እንዳይወሰድ እንዲሁም የጉዞ እቀባን ለማስቆም እና ሌሎች ቀጥተኛ ያልሆኑ የሳንሱር ስራዎችን አለማድረግ እና ዜጎች ዓለም አቀፋዊ የሆኑ መብቶቻቸውን ያለምንም ገደብ መጠቀም እንዲችሉ ማድረግ“ ብለው የተናገሩትን ሊያስታውሱት አይችሉምን? የተከበሩ ፕሬዚዳንት ኦባማ በኢትዮጵያ  ከዜጎች ፈቃድ እና ፍላጎት ውጭ በኃይል ተፈናጥጦ በማተራመስ ላይ ላለው ገዥ አካል መሪዎች “ወጣት የኢትዮጵያ ጦማሪያንን እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆኑትን ጋዜጠኞች በስም እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ እና ውብሸት ታዬ ከእስር ይፈቱ“ በማለት እስከ አሁን ድረስ ያቀረቡት ጥሪ የሌለ መሆኑን ያውቃሉን?
ፕሬዚዳንት ኦባማ ለመሆኑ የፕሬስ ነጻነት፣ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በከፍተኛ ጭቆና ውስጥ እየተሰቃዩ ባሉበት እና የፖለቲካ ምህዳሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ እየጠበበ በመጣበት ሁኔታ የሚደረግ የይስሙላ እና የሸፍጥ ምርጫ ከስም የዘለለ ፋይዳ ሊኖረው እንደማይችል ሊገነዘቡት ይችሉ ይሆን? እ.ኤ.አ በ2009 በጋና አክራ ላይ ለአፍሪካ ህዝቦች ያደረጉትን እንዲህ የሚለውን ንግግራቸውን “…ይህ ምርጫ ከማካሄድ በላይ ነው፣ እንደዚሁም ደግሞ በምርጫዎች መካከል ምን እንደሚደረግ የማወቅም ጉዳይ ነው፡፡ የጭቆና መገለጫዎች ብዙ ናቸው፣ በዚህም መሰረት ብዙ መንግስታት ምርጫ በማካሄድ ላይ ያሉትም እንኳ ህዝቦቻቸው በረሀብ አደጋ ችግር እየተሰቃዩ በህዝቦቻቸው ይወገዛሉ፡፡ የሀገር መሪዎች የሀገሮችን ሀብት ለግል ጥቅማቸው እያዋሉ እና ኢኮኖሚውን እየመዘበሩ ባሉበት ሁኔታ አንድ ሀገር ሀብት ማፍራት አትችልም…የትርፉን 20 በመቶ እና ከዚያ በላይ የሚሆነውን የአገር ሀብት የሚመዘብር መንግስት ባለበት ሀገር ማንም ቢሆን ከውጭ ሀገር ሄዶ መዋዕለ ንዋዩን ሊያፈስ አይችልም፣ የህግ የበላይነት ቀርቶ ጭካኔ እና የባርነት አገዛዝ በተንሰራፋበት ማህበረሰብ ውስጥ ለመኖር የሚፈልግ ማንም ሰው የለም፡፡ ያ ዴሞክራሲ አይደለም፣ ይልቁንም አንዳንድ ጊዜ ለይስሙላ ምርጫ እየተዘጋጀ ቢቀርብም ያ የለየለት አምባገነናዊነት ነው፡፡ እናም እንደዚያ ዓይነቱን የግፍ አገዛዝ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ለማስወገድ ጊዜው አሁን ነው፡፡“ በማለት የተናገሩትን አስመሳይ ንግግር ፕሬዚዳንት ኦባማ ሊያስታውሱት ይችሉ ይሆን?
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ እስከ አንገታቸው ድረስ በሙስና በተዘፈቁ አስመሳይ አምባገነን መሪዎች እና የእነርሱ ጋሻጃግሬዎች ኢኮኖሚውን በብቸኝነት አንቀው ይዘው እየመዘበሩ እራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን በማበልጸግ ላይ እንዳለሉ እንዲሁም አልፎ አልፎ የይስሙላ ምርጫ እያሉ በአገሪቱ ውስጥ ዴሞክራሲ እንዳለ በማስመሰል በዓለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚሰጠውን እርዳታ እና ብድር በማጋበስ ለግል ጥቅማቸው በውጭ አገር በሚገኙ ባንኮች የሂሳብ አካውንት እየከፈቱ በማጨቅ ያሉ ዘራፊዎች እና ማፊያ ጭልፊቶቸ መሆናቸውን ፕሬዚዳንት ኦባማ ሊያውቁ ይችላሉን? እ.ኤ.አ በ2008 እጩ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ታውቃላችሁ፣ ለማቆንጀት ሲባል የዓሳማን ከንፈር ቀለም መቀባት ትችላላችሁ፣ ሆኖም ግን ዓሳማው አሁንም ቢሆን ያው ዓሳማ ነው፣ ዓሳማነቱን አይቀይርም፡፡ አንድን የጠነባ ዓሳ በወረቀት ጠቅልሎ ለውጥ ማለት ይቻላል፡፡ ከስምንት ዓመት በኋላም ቢሆን ያው መጠንባቱን አይተውም፡፡“ እንደዚሁም ሁሉ ቆንጆ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማስመሰል ምርጫ የሚባል የጠነባን ቀለም በምርጫ ካርድ በመጠቅለል የዘራፊዎችን ከንፈር መቀባት ይቻላል፣ ሆኖም ግን የሚደረገው የይስሙላ ሽርጉድ ምርጫ ውጤት ከ23 ዓመታት የሸፍጥ ምርጫም በኋላ ያው በዘራፊዎች ከንፈር ላይ ሆኖ መጠንባቱን የማይለቅ መሆኑን ፕሬዚዳንት ኦባማ በውል ተገንዝበውት ይሆን? ወሮበላነትን ምርጫ በሚባል የጠነባ ነገር በምርጫ ካርድ ወረቀት መጠቅለል ይቻላል፣ ሆኖም ግን ከ23 ዓመታት በኋላም ቢሆን ያው መጠንባቱን እንደማይተው ፕሬዚዳንት ኦባማ አልተረዱም ይሆን?
ስለምንናገረው ነገር ማወቅ፡ .. 2015 በኢትዮጵያ ምርጫ ሊኖር ይችላልን?
“ፖለቲካ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ“ በሚል ርዕስ ባዘጋጁት በባለ 1946 ገጽ ድርሰታቸው ጆርጅ ኦርዌል እንዲህ በማለት ጽፈው ነበር፣ “ሀሳብ ቋንቋን የሚያሻግት ከሆነ ቋንቋ እራሱም ሀሳብን ያሻግታል፡፡“ መጥፎ አጠቃቃም በህዝቦች መካከል በዘልማድ ይተላለፋል፣ የተሻለ እውቀት ባላቸው ሰዎችም ቢሆን እንኳ፡፡ ኦርዌል እንዲህ የሚል የመከራከሪያ ጭብጥ አቅርበው ነበር፣ “የፖለቲካ የቃላት አጠቃቀም ውሸትን እውነት ለማስመሰል ተብሎ የሚዘጋጅ ነው፣ እናም  የተከበረን ነገር እውነት በማስመሰል ይገድላል፣ ባዶ ነፋስን ጠንካራ እና ጠጣር በማስመሰል፡፡“
እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ፕሬዚዳንት ኦባማ የሚያወሩት ሁሉም ነገር ባዶ ነፋስ/ውሸት ነው፣ ሸፍጥ የተሞላበት ምርጫ ለማካሄድ የሚነገር ቋንቋ እውነት ሊመስል ይችላል እናም ወሮበላነት የተከበረ ዴሞክራሲ ይሆናል፡፡ በአሁኑ የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ “ምርጫ” የሚለው ቃል መሰረተቢስ እና እርባናቢስ ነው፡፡ “እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ምርጫ ይካሄዳል” ማለት ወይም ደግሞ “እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው ምርጫ ጥቂት የማውቀው ነገር አለ” የሚለው አባባል የፕሮፌሰር ኖአም ቾምስኪን አባባል እንዳለ የሚደግም እና ትርጉመቢስ እና እርባናየለሽ የሆነ ሆኖም ግን በሰዋስዋዊ አግባቡ ትክክል የሆነ ዓረፍተ ነገር ማለት ሲሆን “ቀለም የሌላቸው አረንጓዴ ሀሳቦች በብስጭት ይተኛሉ” እንደማለት ነው፡፡ በኢትዮጵያ “ምርጫ” ማለት በሶስት ቀለበት የሰርከስ ላይ ተውኔት የሚተወን ምርጫ የሚባል የህዝቡን ድምጽ በተቀነባበረ ሌብነት እና ዝርፊያ የሚነጠቅበት ከመሆን የዘለለ ፋይዳ የለውም፡፡ እንደዚህ ዓይነቱነን የተጭበረበረ የዘረፋ እና የውንብድና ሂደት ምርጫ ነው ማለት ውሸት ማለት እውነት ነው እንደማለት ነው፡፡
ፕሬዚዳንት ኦባማ እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው ምርጫ ጥቂት የማውቀው ነገር አለ ብለው ከማወጃቸው በፊት ጥቂት ኢትዮጵያወያን/ት እና የተወሰኑ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሀን ስለዚሁ ጉዳይ ሲነጋገሩበት ነበር፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩ እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ የሚካሄደው ምርጫ የምርጫ ዘዋሪ ቀበኛው ልዩው መሀንዲስ ያለፈው መለስ ዜናዊ በሌለበት በዚህ ወቅት እውነት ነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫ የሚካሄድ ስለመሆኑ ወይም አለመሆኑን አስመልከቶ ትንሽም ቢሆን ተስፋ ስለመኖሩ እና አለመኖሩ ሙያዊ ትንታኔ እንድሰጥ ጥያቄ ቀርቦልኝ ነበር፡፡ ተስፋ በቆረጠ መልኩ “የምን ምርጫ?” ነበር ያልኩት፡፡ ወያኔ ምርጫውን አሁንም በድጋሜ ይሰርቃል፡፡ ጥቂቶቹ የዘረፋውን እርግጠኛ እውነትነት ባረጋገጠ መልኩ የምጸት ሳቅ ነበር የሳቁት፡፡ ጥቂቶቹ ደግሞ የምርጫ ቅስቀሳ ተብየው በዘራፊው የገዥ አካል በይፋ ሲጀመር የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት በተቀናጀ እና በተደራጀ መልኩ ዘርፈ ብዙ የሆነ የሰላማዊ አመጽ እና እንቢተኝነት ዘመቻ ሊያካሂዱ እና የምርጫውን እርባናየለሽነት ለአገር ውስጥ እና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሊያጋልጡ ይችላሉ በማለት ነግረውኛል፡፡ እንዲህ የሚል ጥያቄ ተጠየቅሁ፣ “የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች እራሳቸውን ከምርጫው ሊያገልሉ ይችላሉን?“ በሚሊዮን ዶላሮች የሚያወጣ በአንድ ወይም በሌላ መልኩ የተጠየቅሁት ጥያቄ ደግሞ “የወያኔው የፖሊት ቢሮ አባላት ኃይለማርያም ደሳለኝን (የይስሙላ ጠቅላይ ሚኒስትር) አሽቀንጥሮ በመጣል በሌላ አሮጌ እና ነባር በሆነ የጫካ ዘብ ይተኩ ይሆን“ የሚል ነበር፡፡ (የወያኔ አለቆች በ2015 በሚደረገው አገር አቀፍ ምርጫ ኃይለማርያም ዳሳለኝን በማስወገድ በቀጥታ ወደ ቅርጫት ይጥሉታል የሚል ግምት አለኝ!)
.. 2015 ስለሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ኃይለማርያም ደሳለኝ ምን ይህል ያውቃሉ? 
እ.ኤ.አ ጁን 11/2014 ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አፍሪካ ዘገባ/Africa Report ለተባለ የዜና ወኪል በሰጡት ቃለመጠይቅ ነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫ ይካሄዳል የሚል የሀሰት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ለማንኛውም የሰጡት ቃለመጠይቅ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
.. 2015 በሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተወካዮች ምክር ቤት ብዙ መቀመጫዎችን ያገኛሉ ብለው ያስባሉን 
ምርጫዎች እስካሉ ድረስ ትኩረት ማድረግ የምንፈልገው በሂደቱ ላይ ነው፡፡ የምርጫ ሂደቱን በህዝቦቻችን ፊት ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻ፣ ፍትሀዊ እና ታማዕኒነት ያለው ማድረግ አለብን፡፡ ከዚያ በተረፈ ውጤቱ የህዝቡ ነው፡፡ እነዚህ ብዙ መቀመጫዎች ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ወይም ደግሞ ለኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህዴግ) ይሰጣሉ ብየ ለመገመት አልችልም፡፡
የምርጫ ሂደቱ ዴሞክራሲያዊ ይሆናል ብለው ያምናሉ?
ተቋማዊ ሂደታችን፣ ህጎቻችን እና ደንቦቻችን ሙሉ በሙሉ እንከን የላቸውም፡፡ ህጉ በእራሱ አይደለም እንቅፋት የሚሆነው፣ ሆኖም ግን እነዚህን ህጎች ከመተግበሩ ላይ ነው፡፡ ስለሆነም ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚመሩበት የምርጫ መመሪያ ህገ ደንብ/Cod of Conduct አዘጋጅተን በስራ ላይ አውለናል፡፡ በማያወላውል መልኩ ለዚህ ህገደንብ ተገዥ መሆን ምርጫውን የበለጠ ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻ፣ ፍትሀዊ እና ለህዝብ ታዕማኒነት እንዲኖረው ያደርገዋል፡፡
2010 አገር አቀፍ ምርጫ ጋር ተመሳሳይ ውጤት የሚኖረው ከሆነ እና አንድ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ዕጩ ብቻ አሸንፎ ወደ ፓርላማ የሚገባከሆነ ይኸ ሁኔታ በመንግስት ላይ የሚኖረውን ታዕማኒነት ከጥርጣሬ ላይ ሊጥለው ይችላል ብለው ያስባሉን?
ይህንን አላስብም ምክንያቱም ውሳኔው በህዝቡ የሚወሰድ ከሆነ ሁላችንም በዚያ ውሳኔ ላይ መስማማት አለብን፡፡ የምርጫው ውጤት አንዳንድ ጊዜ ለአንዳንዶቻችን ቢመቸንም ባይመቸንም ምንም ይሁን ምን ውጤቱን መቀበል አለብን፡፡
በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ኃይለማርያም ደሳለኝ የእርሳቸውን (ይቅርታ የህወሀትን ማለቴ ነው) የ2015ን ምርጫ እና እንዴት አድርገው የ2010ን የምርጫ ውጤት እንዳለ በመድገም በዝረራ በማሸነፍ ድልን ሊቀዳጁ እንደሚችሉ እና በእንዴት ዓይነት ማጭበርበር ዝርፊያውን ለማስኬድ እንዳቀዱ ባለሶስት ምላስ አጠቃላይ የምርጫ ስትራቴጂ ነድፈዋል፡፡ ይኸውም፣
1ኛ) እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ የሚካሄደው አገር አቀፍ የምርጫ ሂደት ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻ፣ ፍትሀዊ እና በህዝብ ዘንድ ታዕማኒነት ያለው እንዲመስል የመንግስት የመገናኛ ብዙሀንን እና ሀብትን በመጠቀም የኢትዮጵያን ህዝብ ማታለል፤
2)  ፍጹም እና እከንየለሽ የሆኑ ተቋማዊ ሂደቶቻችንን፣ ህጎቻችንን እና ደንቦቻችንን ወደ ተግባር በማሸጋገር፤
3ኛ) ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የፈረሙትን እና የተቀበሉትን የምርጫ ህገ ደንብ እንዲቀበሉት እና እንዲተገብሩት ማስገደድ የሚሉት ናቸው፡፡
የወያኔ ባለሶስት ጣት የምርጫ ስትራቴጂ በእርግጠኝነት እንከን ለሌለው የተጭበረበረ ምርጫ እንከንየለሽ የምርጫ ጨዋታ ዕቅድ ነው፡፡ አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ እንከንየለሽ የሸፍጥ የምርጫ ጨዋታ ህግ መጽሐፍ እ.ኤ.አ በ2010 ጽፎ ተግባራዊ አድርጓል፡፡ በዚህም መሰረት የእርሱ ፓርቲ እንከንየለሹን ምርጫ 99.6 በመቶ የፓርላማ መቀመጫዎችን በማግኘት አሸናፊነቱን አረጋግጧል፡፡ ከዚህ የበለጠ እንከንየለሽ የምርጫ ውጤት ማግኘት ሰብአዊነት ነውን? (አሁን በህይወት የሌለው ሳዳም ሁሴን ብቻ ነው እ.ኤ.አ በ2002 በተካሄደው አገር አቀፍ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከ11,445,638 ድምጽ ሰጭዎች መቶ በመቶ ድምጽ በማግኘት እከንየለሽ የድምጽ ውጤት በማግኘት በመፎከር ላይ የነበረው፡፡) የሸክስፒርን አባባል በመዋስ፣ የመለስ ሙት መንፈስ እ.ኤ.አ በ2015 በሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ላይ ለማጥላት “በጨላማው የሲኦል ቦታ ላይ እንደ እሬሳ ሳጥን“ ትንጠለጠላለች፡፡
ስለህዝቦች አገዛዝ/አስተዳደር ሳይሆን ህዝቦችን ለመግዛት ያፈጠጠ ምርጫ 
የበከተ አስተሳሰብን በመያዝ እና  እና የሞራል ስብዕና በሌላው መልኩ እ.ኤ.አ በ2014 የኃይለማርያም አለቆች ከእርሳቸው በስተጀርባ ሆነው እንከንየለሽ ተቋማዊ ሂደት፣ ህጎችን እና ደንቦችን በመጠቀም ተግባራዊ አድርገው ምርጫ ማሸነፍ እንዳለባቸው ብቻ አይደለም እምነታቸው ሆኖም ግን ኢትዮጵያን ለዘላለም ለመግዛት ባላቸው መብት የኢትዮጵያ ህዝቦች እንከንየለሽ ገዥዎች መሆናቸውን ለማረጋገጥ ጭምር እንጅ፡፡ በእነርሱ እና በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አስተሳሰብ በቀጣይ ኢትዮጵያን የሚገዛት ማን ነው የሚለው ከጥያቄ ውሰጥ የሚገባ ጉዳይ አይደለም፡፡ ይኸ ጉዳይ ለውይይት የሚቀርብ አይደለም፣ የሚያከራክርም አይደለም፣ እናም ለድርድር የሚቀርብ አይደለም፡፡ በእርግጥ መለስ እ.ኤ.አ በ2010 በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ የተጎናጸፈውን የምርጫ ድል አስመልክቶ ባደረገው ንግግር እንዲህ የሚል ግለጽ መልዕክት አስተላለፎ ነበር፣
“…በዚህ ምርጫ የህዝቡን የምርጫ ድምጽ ድጋፍ ላላገኛችሁት እና ስኬታማ ላልሆናችሁት ፓርቲዎች በዚህ ፓርላማ ወንበር ይኑራችሁም አይኑራችሁም የህዝቡን ፍላጎት፣ የአገሪቱን ህገመንግስት እና ሌሎችን የአገሪቱን ህጎች እስካከበራችሁ ድረስ ከእናንተ ጋር በመቀራረብ እናንተን በታላላቅ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በማሳተፍ እየተመካከርን አብረን እንሰራለን” ነበር ያለው፡፡ የውሸት እና የሸፍጥ ፈጣጣ ንግግር!
በቀላል አነጋገር ማንም ቢሆን እ.ኤ.አ በ2015 የሚካሄደውን እንከንየለሽ የምርጫ ውጤት አልቀበልም የሚል ልቡ ያበጠበት ወጠጤ ካለ በኃይለኛው ጡንቻ የመደምሰስ አደጋ ይገጥመዋል፡፡ አራት ነጥብ! ሆኖም ግን ምንም የማይሉ ሆኖም ግን የተባሉትን ብቻ የሚቀበሉ ዓላማቢስ እና ስሜት አልባ በመሆን አንገታቸውን ደፍተው ጫማ የሚልሱ ወንዶች እና ሴቶች ከሆኑ ያለምንም ችግር የመሸለም ዕድልን እየተጎናጸፉ በታላላቅ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በማማከር እና እንዲያውም በማሳተፍ ይህችን በእድገት ጎዳና ላይ እንደ እሮኬት ጥይት በመምዘግዘግ ላይ ያለች ሀገር የበለጠ እንድትተኮስ ያደርጓታል፡፡ እንዲያውም ባለሁለት አሀዙ የኢኮኖሚ ዕድገት እጅግ በጣም ከመጦዙ የተነሳ ወደ ባለሶስት አሀዝ ሳይገባ ይቀራል ጎበዝ! ከዚህ በላይ በአገር እና በህዝብ ላይ ከመቀለድ የከፋ እና የከረፋ ከቶውኑ ምን ነገር ሊኖር ይችላል! እ.ኤ.አ በ2015 የሚካሄደውን እንከንየለሽ አገር አቀፍ ምርጫ ውጤት አልቀበልም የምትሉ ዕደለቢሶቹ ሁሉም የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች (ውይ! ለምስክርነት ካላችሁ ማለቴ ነው)፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አመራሮች ካላችሁ በምርጫው ወቅት አንድም እንደ አህያ ዱላውን ተቀበሉ አለያም ደግሞ በእስር ቤት ውሰጥ በመግባት እየማቀቃችሁ የአህያውን ኑሮ መኖር ነው የሚጠብቃችለሁ፡፡
ሌሎቹስ ስለኢትዮጵያመ ምርጫ ምን ያህል ያውቃሉ? 
እ.ኤ.አ ኦክቶበር 2009 “የ2010 የኢትዮጵያ ምርጫ እብድነት” በሚል ርዕስ የሚከተለውን ጥያቄ በማንሳት ትችት ጽፌ ነበር፣ “የፖሊስ መንግስት በተንሰራፋበት ሀገር ፍትሀዊ እና ነጻ ምርጫን ማካሄድ ይቻላልን?“ (ይህ ጥያቄ የፕሬዚዳንት ኦባማን የከንፈር ቀለሙን እና የዓሳማውን ጉድኝት የሚያመሳስል ቀላል የተመሳስሎ አቀራረብ ነው፡፡)
ያ ትችት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እ.ኤ.አ በ2001 ከኢትዮጵያ ከስልጣናቸው መንበራቸው እስከለለቀቁበት ድረስ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት የነበሩት ባቀረቡት የምርጫ ዘመቻ ዘገባ ላይ መሰረት ያደረገ ነበር፡፡ ዶ/ር ነጋሶ በምዕራብ ኢትዮጵያ የምትገኘውን ደምቢዶሎን ወክለው ለተወካዮች ምክር ቤት ለመወዳደር ለምርጫ ቅስቀሳ በተንቀሳቀሱበት ወቅት በገዥው ፓርቲ የበታች አካላት ልክ የድሮዎቹ የኮሙኒስት ፍልስፍናን ሲያራምዱ የነበሩ አገሮች ሲያደርጉት እደነበረው ሁሉ ህዝቡን አስጨንቀው በመያዝ የአዛዥ እና የቁጥጥር ስርዓት/Command and Control በመዘርጋት ሲያደርጉት የነበረውን የአፈና አሰራር ነው፡፡ እርሳቸውም ተዘዋውረው በተመለከቱት መሰረት በደምቢዶሎ የገዥው ፓርቲ የታችኛው እርከን ድርጅቶች የደህንነት፣ የፖሊስ እና ሌሎች በታችኛው የስልጣን መዋቅር ላይ ያሉት የሲቪል ማህበረሰብ መሰል ድርጅቶችን ሁሉ ሳይቀር በቁጥጥር ስር በማዋል አንድ ወጥ የሆነ የቁጥጥር መዋቀር በዞኖች፣ በከተሞች፣ በወረዳዎች፣ በመንደሮች፣ በጎጦች እና በቤቶች ሳይቀር ተጠርንፈው የተያዙ መሆናቸውን ግልጽ አድርገው ነበር፡፡
ዶ/ር ነጋሶ የመረጃ ሰጭዎች፣ የወኪሎች እና የሚስጥር ፖሊስ መሰል አደረጃጀቶች ሆነው እነዚህም የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን ለማሸማቀቅ፣ ለማስፈራራት፣ የስለላ መረጃ ለመሰብሰብ እና ተቃዋሚዎችን በማዳካም ሰርስሮ ለመግባት የተዋቀሩ አደረጃጀቶች እንደነበሩ እጀ እረጅም በመሆን ህሉን አድራጊ ፈጣሪ እንደነበሩ ግልጽ አድርገው ነበር፡፡ በደምቢዶሎ በፖለቲካ ፓርቲው እና በህዝብ ደህንነቶች መካከል ምንም ዓይነት የስራ ክፍፍል ልዩነት የለም በማለት ሲሞግቱ ነበር፡፡ ሁለቱም በአንድ የፖለቲካ ጥላ ስር የተዋቀሩ እና የአካባበኒውን የፖለቲካ እና የማህበራዊ ሁነት በጅምላ የተቆጣጠሩ እና የበላይነትን የያዙ ነበሩ ብለዋል፡፡ የመንግስት ሰራተኞች፣ አርሶ አደሮች፣ የአካባቢው ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የአነስተኛ ብድር እና ቁጠባ ድርጅቶች እና ሌሎችም በግዳጅ በሚስጥራዊው የፓርቲ መዋቅር ስር እንዲሆኑ ይገደዳሉ፡፡ የቁጥጥር ስርዓቱ መጥበቅ ሁሉን ነገር የሚያሽመደምድ ነበር በማለት ዶ/ር ነጋሶ እንዲህ በማለት ጽፈው ነበር፣ “እያንዳንዱ ቤተሰብ በየዕለቱ ወደ ቤቱ የሚመጡትን እንግዶች እና ጎብኝዎች የመጡበትን ምክንያት፣ ምን ያህል ጊዜ እንደሚቆዩ፣ በቆይታቸው ጊዜ ምን እንደተናገሩ እና እዳደረጉ እንዲሁም በምን ስራ ላይ እንደቆዩ ዘገባ ማቅረብ ይጠበቅበታ”:: እንግዲህ ያ ነበር የመለስ የደህንነት ዋስትና በመሆን በ2010 እንከንየለሽ ምርጫ በማካሄድ 99.6 በመቶ ድምጽ በማግኘት የቅጥፈት የድል ከበሮ ሲደልቅ የነበረው፡፡ አሁን ከኃይለማርያም በስተጀርባ ያሉት ስምየሾች፣ አረመኔዎች እና ራዕይየለሾች በተመሳሳይ መልኩ እንደገና በ2015 ለሚደረገው ምርጫም ተመሳሳዩን የሸፍጥ ስራ ለመስራት እና ለማግኘት ደፋ ቀና ይላሉ፡፡
እ.ኤ.አ በ2010 በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ የምርጫ ውጤት ላይ ትችት በማቅረብ ፕሮፌሰር ቶቢያስ ሐግማን የተመለከቱትን እንደሚከተለው አስፍረዋል፡፡ “የኢትዮጵያ መንግስት እ.ኤ.አ በ2005 በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ውርደትን ባከናነበ መልኩ ሽንፈትን ከተጎነጨ ወዲህ አ.ኤ.አ በ2010 በተደረገው አገር አቀፍ ምርጫ መንግስት የመጨረሻ የፖለቲካ ስተራቴጂ ነድፎ የገባበት ነው፡፡ ይህ የአካሄድ እስትራቴጂ ዱላ እና ካሮትን ሁለቱንም አካትቶ የያዘ ነበር፡፡ ዱላው የሚያካትተው ማስፈራራትን፣ ማሸማቀቅን እና የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን እና የእነርሱ ደጋፊ ይሆናሉ ብለው የሚያምኑባቸውን በቁጥጥር ስር እያዋሉ ወደ እስር ቤት መወረወወር ሲሆን ካሮቱ የሚያካትታቸው ደግሞ ገዥው ፓርቲ አዲስ የፓርቲ አባላትን በገፍ መመልመል እና አዲስ የትንታኔ ዘገባ እንደሚጠቁመው ጠንካራ የተቃዋሚ አባላት በሚገኙባቸው ወረዳዎች በቀጥታ ከፌዴራል ወደ ወረዳዎቹ ገንዘብ እንዲላክ በማድረግ በጣም ጠንካራ የሆኑትን በገንዘብ መደለል እና በገንዘብ የምርጫ ድምጽ በመግዛት ዓላማቸውን ማሳካት ነበር… በምርጫ 2010 የተገኘው 99.6 በመቶ የምርጫ ድምጽ ውጤት ሲታይ ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ ለህዝብ አስተዳደር ሳይሆን ህዝቡን ለመግዛት የሚያመላክት ጠንካራ ምልክት ነው… ከ20 ዓመታት በላይ በስልጣን ላይ ከቆየ በኋላ የኢትዮጵያ ህዝቦቸች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) በፖለቲካ ውክልናው እና በውሳኔ ሰጭነቱ ህጋዊነትን ያልተላበሰ አድራጊ ፈጣሪ ጠቅላይ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲ ማለት ምን ማለት እንደሆነም በእራሱ አረዳድ እና ዓላማ ጠቅልሎ የያዘ ህጋዊነትን ያልተላበሰ ድርጅት ነው፡፡”
የፕሮፌሰር ሄግማን ምልከታዎች በተጨማሪም የወያኔ አመራሮች (እና የእነርሱ ጋሻ ጃግሬዎች) በእብሪተኝነት እና ሊለወጥ በማይችል ቀኖናዊ አመለካከት ወጥመድ ውስጥ የተያዙ በመሆናቸው ምክንያት እድሜልካቸውን ለመግዛት ሀሳብ አላቸው፡፡ ከዚህ አንጻር በኢትዮጵያ ምርጫ ማካሄድ ምንም ዓይነት እርባና የሌለው እና ከንቱ ነገር መሆኑን ፕሮፌሰሩ አጽንኦ በመስጠት አስቀምጠውታል፡፡ የምልከታቸውን ተጨባጭነት ይበልጥ ለማረጋገጥ እንዲህ ይላሉ፣ “ይህ ሁኔታ ኢህአዴግ እራሱን በሚያይበት መነጽር ላይ በግልጽ ሲንጸባረቅ ይታያል – በስም እራሱን አውራ ፓርቲ/Vanguard party እና የመንግስትነት ስልጣንን ጨብጨ የመምራት መብት የእኔ መብት ሆኖ ልማት ማለት ምን ማለት እደሆነ እና ዴሞክራሲ እንዴት መደራጀት እና መዋቀር እንዳለበት የምወስነው እኔ ነኝ፡፡ ስለሆነም ማንም ይሁን ማን ከኢህአዴግ አመለካከት ውጭ የሆነ ሁሉ ጸረ ልማት ወይም ደግሞ ጸረ ሰላም ነው፣ እናም ማንም ማን ይሁን የእርሱን ፖሊሲ የሚቃወም ሁሉ ጸረ መንግስት ነው“ በማለት የድርጅቱን (የጠቅላዩን እና ዘላለማዊ ገዥውን) ከንቱነት በማያሻማ መልኩ አስቀምጠውታል፡፡
.. 2015 በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ምን ያህል አውቃለሁ?
በ2015 በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ እኔ የማውቀው ይልቁንም የበለጠ የተወሳሰበ ነገር ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ በርካታ ጥያቄዎችን እጠይቃለሁ፣ እነዚህም ለእኔ የሚታወቁ ታዋቂዎች፣ ታዋቂ የማይታወቁዎች፣ እና የማይታወቁ የማይታዎቁዎች ናቸው፡፡ ይቅርታ አድርጉልኝ አንዳንድ ጊዜ እንቆቅልሽ ማውራት ይቀናቸው እንደነበሩት እንደ ቀድሞው የዩኤስ አሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ዶን ሩምፌልድ ዓይነት አቀራረብ ተከትየ ከሆነ፡፡ ዶን እንዲህ ብለው ነበር፣ “የምናውቃቸው የሚታወቁ ነገሮች አሉ፣ እንደዚሁም የምናውቃቸው የማይታወቁ ነገሮች አሉ፣ ይህም ማለት የማናውቃቸው ጥቂት ነገሮች አሉ፡፡ ሆኖም ግን የማናውቃቸው የማይታወቁ ነገሮች አሉ፣የማይታወቁ እና እኛም የማናውቃቸው፡፡“
ሙሉ በሙሉ ግልጽ ላድርገው፡፡ በእርግጠኝነት ጥቂት ነገር አውቃለሁ፡፡ የወያኔ ገዥ አካል እ.ኤ.አ በ2015 የሚካሄደውን አገር አቀፍ ምርጫ እንደ ቁማር ጨዋታ ሻጥር ይሰራበታል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ የምርጫው ዕለት የድምጽ ቆጠራ ገና ሳይጠናቀቅ እና የቆጠራ ጣቢያዎች ገና ሳይዘጉ የወያኔ ገዥ አካል በዝረራ አሸንፎ ድልን እንደተቀዳጀ በማስመሰል በህዝብ ግብር በሚተዳደረው መገናኛ ብዙሀን ማናፋቱን ይቀጥላል፡፡ ይኸ እንግዲህ ታዋቂው የማውቀው ነገር ነው፣ ምንም ዓይነት ሊያስረዳኝ የሚችል ሌላ ጭንቅላት አያስፈልገኝም፡፡
ሆኖም ግን የሚታወቁ የማላውቃቸው ነገሮች አሉ፡፡ ይህም ማለት እ.ኤ.አ በ2015 በሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ የወያኔ ገዥ አካል ቢያንስ በ99.6 በመቶ ያሸንፋል፣ ሆኖም ግን ይህ እንደ እስስት ተለዋወጭ የሆነው ገዥ አካል በ99.7፣ በ99.9፣ በ100 ወይም ደግሞ በ110 በመቶ ለማሸነፍ ዕቅድ ይዞ ይሆናል (ይህም እንግዲህ ከ2010 ጀምሮ የሞቱ ድምጽ ሰጭዎችን ቆጥረው ማለት ነው)፡፡ ሆኖም ግን በ2015 የሚደረገው ምርጫ የመራጮች ድምጽ ውጤት ከ99.6 በመቶ ያነሰ የድል ውጤት ተመዝግቦ ከሆነ መለስ ከመቃብር ውስጥ ሆኖ ለዚህ የሸፍጥ ምርጫ ስኬታማነት ተንቀሳቅሶ ሊሆን ስለሚችል የማይታወቅ የማላውቀው ነገር መሆኑ ነው፡፡
ለእኔ እ.ኤ.አ በ2010 በተደረገው አገር አቀፍ ምርጫ የወያኔ ገዥ አካል 99.6 በመቶ የመራጮች ድምጽ ውጤት አመጣሁ ብሎ የድል ከበሮ ሲደልቅ ፕሬዚዳንት ኦባማ በውስጠ ታዋቂነት ይህንን ተቀብለው ቡራኬ በመስጠት ማጽደቅ መቻላቸው የሚታወቀው የማውቀው ነገር ነው፡፡ ፕሬዚዳንቱ ለዚህ ጉዳይ ጆሮዳባ ልበስ፣ አላየሁም አልሰማሁም ነው ያሉት፡፡ (ሆኖም ግን እ.ኤ.አ በ2013 በዚምባብዌ በተደረገው አገር አቀፍ ምርጫ ሮበርት ሙጋቤ የፕሬዚዳንትነት ወንበሩን በ61 በመቶ ድምጽ በማግኘት አሸንፊያለሁ ብለው ድንፋታ ሲያሰሙ ፕሬዚዳንት ኦባማ ለወያኔው ገዥ አካል እንዳደረጉት ሁሉ በዝምታ አላለፉም፡፡) እንዲያውም እንደህ ነበር ያሉት፣ “ዚምባብዌያውያን/ት አዲስ ህገመንግስት አላቸው፡፡ ኢኮኖሚው በማገገም ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ወደፊት በእድገት የመገስገስ ዕድሉ ይኖራል፣ ሆኖም ግን ይህ ተፈጻሚነት ሊኖረው የሚችለው ነጻ፣ ፍትሀዊ እና ሰላማዊ ምርጫ ሲካሄድ ብቻ ሲሆን በዚህም መሰረት ዚምባብዌያውያን/ት የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውን እራሳቸው ምንም ዓይነት የማስፈራራት ፍርሀት እና የብቀላ እርምጃ ሳይወሰድባቸው ሲወስኑ ነው፡፡ 61 በመቶ የመራጮች ድምጽ በማግኘት አሸናፊ የሆነ ምርጫ ነጻ እና ፍትሀዊ አይደለም፣ ስለሆነ ህዝባዊ ውግዘት ሊደርስበት ይገባል“ ነበር ያሉት፡፡ ሆኖም ግን 99.6 በመቶ የመራጮችን ድምጽ በማግኘት አሸናፊ የሆነ ምርጫ እንደ ክቡር ፕሬዚዳንቱ መንታ ምላስ ሁኔታ ነጻ እና ፍትሀዊ ነው፣ እናም ታላቅ የሆነ የግል ሙገሳ ያስፈልገዋል!
ፕሬዚዳንት ኦባማ እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ስለምርጫው ጥቂት የማውቀው ነገር አለ ሲሉ የማይታወቀው እኔም የማላውቀው ነገር ማለት ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ምናልባት ፕሬዚዳንቱ የሚያውቁት ሆኖም ግን ማንም ኢትዮጵያዊ የማያውቀው ነገር ሊኖር ይችላል፡፡
እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ በሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ የተለያዩ የህወሀት ተስፈንጣሪ ቡድኖች የጠቅላይ ሚኒስትርነቱ ቦታ ለእኔ ይገባል፣ ለእኔ ይገባል በሚል የንግስና ጦርነት ለማካሄድ ዝግጅት ሊያደርጉ የሚችሉበት የማይታወቅ እኔም የማላውቀው ነገር ሊሆን ይችላል፡፡ ከኢኮኖሚያዊ ጥቅም አንጻር የተለያዩ የህወሀት ተስፈንጣሪ ቡድኖች አሮጌ ብር በማጣበቂያ ታሽጎ አንድ እንደሚሆነው ሁሉ እነርሱም ለጥቅም ሲሉ ብቻ አንድ ሊሁኑ የሚችሉበት የማይታወቅ እኔም የማላውቀው ነገር ሊኖር ይችላል፡፡ ሆኖም ግን የሚታወቅ እና እኔም የማውቀው ነገር አለ፣ ይኸውም የምርጫ ዘራፊዎች የሚከባበሩበት እና የማይከባበሩበት ያልተጻፈ ህግ አለ፣ እርሱም፣ “በምርጫ ወቅት አንድ ዘራፊ በሌላው ዘራፊ የምርጫ ጓደኛው ላይ ጦርነት አይከፍትም፣ ምክንያቱም በምርጫ ጦርነት የሚያሸንፉ የምርጫ ዘራፊዎች የሉምና፡፡“ ስለወያኔ ውስጣዊ ባህሪያት እና አሰራር በርካታ የማይታወቁ እና የማናውቃቸው ነገሮች አሉ፡፡ አጋጣሚ ሆኖ ስለወያኔ የማይታወቁ የማናውቃቸውን የሚያውቁ ንግግር አያደርጉም፣ እናም ንግግር የሚያደርጉት ስለወያኔ የማይታወቁትን የማናውቃቸውን አያውቁም፡፡ ኦ! በጣም አደናጋሪ ነገር ነው!
የነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫ ትክክለኛ ትርጉም እና ተሞክሮ፤
ምርጫዎች እና ምርጫዎች አሉ፡፡ በሸፍጥ የተሞሉ እና የተጭበረበሩ ምርጫዎች እራሳቸው ማለት ናቸው፡፡ አንድ ምርጫ ነጻ እና ፍትሀዊ ነው ወይም አይደለም “የተቋማዊ የአሰራር ሂደቱ፣ ህጎቻችን እና ደንቦቻችን እንከንየለሾች ናቸው“ ብሎ በመወሰን የማወጅ ያህል አይደለም፣ ችግሩ እንከንየለሽ የተቋማዊ የአሰራር ሂደት፣ ህጎች እና ደንቦች ያለመኖር አይደለም፣ ይልቁንም እነዚህ እንከንየለሽ ተቋማዊ የአሰራር ሂደቶች፣ ህጎች እና ደንቦች  ተፈጻሚነት የማይኖራቸው እንከን በእንከን በተሞሉ ሰዎች ስር በመሆናቸው ብቻ ነው፡፡ ችግሩ ያለው እነዚህን እንከንየለሽ ህጎች በሚጽፉት ሰዎች እጅ እና በትክክል ቅን ልቦና ኖሯቸው ወደተግባር አምጥተው በቅንነት መተግበር በማይችሉ እንከን በእንከከኖች ነው፡፡ ከሁሉም በላይ እንከን በእንከን የተሞሉ ሰዎች እንዴት እንከንየለሽ የአሰራር ሂደቶችን፣ ህግችን እና ደንቦችን ያወጣሉ? እነርሱ እራሳቸውን እንከንየለሾች ነን ብለው የሚያምኑ በቀላሉ ነገሮችን የመረዳት ወይም ደግሞ የግንዛቤ ችግር ያለባቸው ናቸው፣ እናም ያ ዓይነት አመለካከት ያላቸው አጠቃላይ የጅምላ እንከን በእንከን ቁልሎች ናቸው፡፡  ከኃይለማርያም ደሳለኝ በስተጀርባ ያሉት ኃይሎች እንከን በእንከን የሆነችውን ኢትዮጵያ ለመግዛት ከላይ ተቀብተው የመጡ እና በክልል፣ በሙስና እና የጅምላ ሰብአዊ መብትን እየጣሱ በእነርሱ የእንከንየለሽ መስፈርት ለማድረስ እየዳከሩ ያሉ ለመሆናቸው በእርግጠኝነት እምነቱ አለኝ፡፡
በእርግጥ በኢትዮጵያ እንከንየለሽ ደንቦችን፣ ህጎችን እና ሂደቶችን በማውጣት ብቻ እንከንየለሽ ምርጫ ይካሄዳል ብሎ የሚጠብቅ ሰው የለም፡፡ ነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫ ጥቂት እንከኖች ያሉበት፣ ቁስሎች እና ህጸጾች መኖራቸው ተፈጥሯቂ ነው፡፡ እንደዚህ ያሉት ምርጫዎች የመከሰታቸው ሁኔታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስምምነት የተደረሰባቸው መስፍርቶች እና መርሆዎች ያሉ ሲሆን መፍትሄዎችም ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች መክፈት እና ማስፋት፣ የተቃዋሚ አባላትን ማስፈራራት እና ማሸማቀቅ ማስወገድ፣ በሲቪል ማህበረሰቡ ላይ ያለውን የቁጥጥር ደረጃ ማላላት እና የነጻውን ፕሬስ መብት በማረጋገጥ ለዜጎች መረጃ እንዲሰጥ እና ዘገባ እንዲያቀርብ መፍቀድ ናቸው፡፡
ፍትሀዊ እና ነጻ ምርጫዎች ህዝቡ በዕለቱ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመሄድ የምርጫ ካርዱን ጥሎ በመምጣቱ ብቻ የሚከሰቱ አይደሉም፡፡ ይልቁንም ከምርጫው ዕለት በፊት የመከወኑ ነገሮች ናቸው፡፡ ፕሬዚዳንት አቦማ ጋና ላይ እንደተናገሩት፣ “ይህ በአጠቃላይ ምርጫ ከማካሄድ በላይ ነው፡፡ እንደዚሁም ደግሞ በምርጫዎች መካከል ምን ተከናወነ የሚለውም መታየት አለበት“ ነበር ያሉት፡፡ ከሁሉም በላይ በመጀመሪያ ነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫ ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው የህግ የበላይነት ባለበት እና መሰረታዊ የሆኑ የሰብአዊ መብቶች በተከበሩበት ሁኔታ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህግመንግስት “የሀገሪቱ የህጎች ሁሉ የበላይ” ለድምጽ ሰጭዎች እና ለዕጩዎች (በአጠቃላይም ለዜጎች) ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብትን ያጎናጽፋል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ፖለቲካዊ የሆኑ መልዕክቶች እና መረጃዎችን ከምርጫው በፊት እና ከድህረ ምርጫ በኋላ ወደ ህዝብ  ለማሰራጨት እና መረጃ ለመለዋወጥ የሚያስችለውን የፕሬስ ነጻነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ በህገመንግስቱ የማይገዙት ለምንድን ነው?
ህገመንግስቱ ለሁሉም ድምጽ ሰጭዎች፣ ፓርቲዎች እና እጩ ተወዳዳሪዎች፣ ነጻ፣ ከማንም ጋር ያልወገነ የምርጫ ሂደቱን የሚያስፈጽም የምርጫ ቦርድ እንዲኖር ዋስትና ይሰጣል፡፡ በዜጎች የፖለቲካ ፓርቲዎችን እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ለመመስረት በሚያደርጉት ጥረት የመደራጀት እና የመሰብሰብ መብት ላይ በዘፈቀደ የሚደረግ ጣልቃገብነት መኖር የለበትም፡፡ እንደዚሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰላማዊ ሰልፍ እና የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ለማድረግ ሲፈልጉ ያለምንም ችግር በነጻ መንቀሳቀስ እንዲችሉ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡  ዜጎች የፖለቲካ አመለካከታቸውን በነጻ የማራመድ እና ከማንኛውም ተጽእኖ ነጻ ሆነው መግለጽ እንዲችሉ መብታቸው ሊጠበቅ ይገባል፡፡ ዜጎች መረጃ የመፈለግ፣ የመቀበል እና የማካፈል መብታቸው ሊረጋገጥ ይገባል፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ የዘመቻ ቅስቀሳ ለማድረግ እና ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ከገዥው ፓርቲ ጋር ጭምር እኩል በሆነ መልኩ የመንቀሳቀስ መብታቸው ሊጠበቅ ይገባል፡፡
የፖለቲካ አመለከካከታቸውን ለማራመድ እና በህዝብ ዘንድ ለማስረጽ እንዲችሉ ማንኛውም እጩ ተመራጭ ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ለሚዲያ በተለይም ለብዙሀን መገናኛ እኩል እድል ሊያገኙ ይገባል፡፡ ከምርጫ እና ከፖለቲካ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ መልኩ የሚነሱ ውዝግቦችን በሰላማዊ መልኩ ለመዳኘት እንዲቻል ነጻ እና ከማንም ያልወገኑ ተቋማት ያስፈልጋሉ፡፡ የህገመንግስቱን ትዕዛዛት ለምን አይከተሉም?
የተቃዋሚ ፓርቲ እጩዎች እና ፓርቲዎች ለህዝብ ቀርበው ሀሳቦቻቸውን እና ፕሮግራሞቻቸውን ሊያስረዱ የሚቸችሉበት መንገድ ሊቀየስ ይገባል፡፡ ገዥው ፓርቲ ፖሊስን፣ ወታደሩን፣ የፍትህ አካላቱን፣ የመንግስት ሰራተኛውን፣ የምርጫ አስፈጻሚ ባለስልጣኖችን ከህግ አግባብ ውጭ ወገንተኝነት እንዲያሳዩ እና እራሱ እንዳይጠቀምባቸው ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ማድረግ እና መረጋገጥ አለበት፡፡ የመንግስት ገንዘብ እና የማስፈጸሚያ ቁሳቁሶች በምንም ዓይነት መንገድ ለፓርቲ ስራ ገዥውን ፓርቲ ጨምሮ መዋል የለባቸውም፡፡ ጥብቅ በሆነ መልኩ መከልከል አለባቸው፡፡ የምርጫ ሂደቱ ምንም ዓይነት ችግር የሌለበት የመራጮች ምዝገባ፣ ሊደረስባቸው የሚገባ የምርጫ ቦታዎች፣ የምርጫ አስፈጻሚ ኃላፊዎችን ክብር ያረጋገጠ አያያዝ ማድረግን፣ ለሁሉም ክፍት የሆነ እና ግልጽነትን የተላበሰ የመራጮች ድምጽ ቆጠራ እና የማረጋገጥ ስራ ሂደት፣ ምርጫዎችን በሰለጠነ እና ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ነጻ በሆኑ ኃላፊዎች ታዛቢነት እንዲኖር ማድረግ እና የምርጫ ማጭበርበር ያለመኖሩ መረጋገጥ አለበት፡፡
እ.ኤ.አ በ2010 በኢትዮጵያ ለተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ የአውሮፓ የምርጫ ታዛቢ ቡድን የመጨረሻ ዘገባ፣
የምርጫው ሂደት በተለይም የሂደቱን ግልጽነት እና ለሁሉም ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች እኩል ምህዳር ባለመስጠቱ ዓለም አቀፍ የምርጫ መስፈርትን አያሟላም፡፡ የበለጠ ፍትሀዊ እና ወካይነት ያለው የምርጫ ሂደት እንዲኖረው ተደረጉት ጥረቶች አናሳ ሆነው ተገኝተዋል…በመሆኑም ሙሉ፣ አድሎአዊ ያልሆነ እና መሰረታዊ የሆኑ መብቶችን ለመጠቀም ባለመቻሉ የምርጫው ሂደት በችግር ተተብትቧል… የገዥው ፓርቲ በመላ አገሪቱ ባሉ የምርጫ ጣቢያዎች ከመገኘቱ አንጻር ሲገመገም በተለይም የገጠሩ አካባቢ 80 በመቶ የሚሆነውን ህዝብ የሚሸፍነው የህብረተሰብ አካል የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተወካዮች እና ተወዳዳሪዎች አልነበሩም፡፡ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት በተለይም የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ባካተተ መልኩ የመሰብሰብ ነጻነቶች፣ ሀሳን በነጻ የመግለጽ፣ በነጻ የመንቀሳቀስ መብቶች ወጥ በሆነ መልክ አልተከበሩም…በመንግስት ቁጥጥር ስር ያለው የብዙሀን መገናኛ ለሁሉም እኩል በሆነ መልኩ ሽፋን አልሰጠም፣ በተለይም ለገዥው ፓርቲ ከ50 በመቶ በላይ የህትመት እና የብሮድካስት ሽፋን ሰጥቷል…በብዙዎቹ የአገሪቱ ዝቅተኛ የመንግስት አስተዳደራዊ መዋቅሮች ዘንድ በገዥው ፓርቲ እና በመንግስት መዋቅር መካከል የጠራ ልዩነት አልነበረም፡፡ የአውሮፓ የምርጫ ታዛቢ ቡድን በቀጥታ የመንግስት ሀብቶች ለገዥው አካል የምርጫ ዘመቻ ቅስቀሳ አገልግሎት መዋላቸውን አረጋግጧል፡፡ በስልጣን ላይ ያለው ገዥው ፓርቲ በግልጽ ጠቀሜታ ያለው መሆኑ በግልጽ የሚታይ ቢሆንም የምርጫ ቡድኑ የ2010ሩ አገር አቀፍ ምርጫ በብዙ መልኩ የምርጫ ምህዳሩ ፍትሀዊ አልነበረም፣ በብዙ የምርጫ ጣቢያዎች በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ገዥው ፓርቲ ያደላ ነበር…
አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ የአውሮፓ ህብረት የታዛቢዎችን ቡድን የምርጫ ዘገባ “ለምንም የማይውል ወደ ቆሻሻ ቅርጫት መጣል ያለበት“ በማለት በአደባባይ አጣጥሎታል፡፡ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “የምርጫ ዘገባው ስለእኛ ምርጫ አይደለም፡፡ ይኸ ጉዳይ በገዥው ፓርቲያችን መጠናከር ደስተኞች ያልሆኑት የምዕራቡ ዓለም ኒዮሊበራሎች አመለካከት ነው፡፡ ማንም ወረቀት እና ብዕር የያዘ ሰው የፈለገውን ነገር መሞነጫጨር ይችላል፡፡“ በእርግጥ መለስ በፖለቲካ መድረክ ላይ እንደዚህ ያለ አስቀያሚ ቋንቋ ማስተላለፍ መቻሉ አፈታሪክ ነበር፡፡ መለስ በአፍሪካ አህጉር ማንንም የፖለቲካ ሰው መሳደብ፣ የጭቃ ጅራፉን ማጮህ፣ መበጥበጥ፣ መዘለፍ፣ ጥላሸት ሲቀባ የቆየ ሰው ነበር፡፡ መለስ የአውሮፓ ህብረት የታዛቢዎች ቡድን የምርጫ ዘገባን “በውሸት ቁልል የታጨቀ“ ብሎታል፡፡
ፕሬዚዳንት ኦባማ ስለ2015 ምርጫ ማወቅ እና ማድረግ ያለባቸው ነገሮች፣
ፕሬዚዳንት ኦባማ እያወቁ ያላወቁ በመምሰል የሚያደርጉትን ትተው የምርጫ 2010 ስህተት በ2015ም እንዳይደገም ለመከላከል ማወቅ እና ማድረግ የሚኖርባቸው ጥቂት ነገሮች እንደሚከተለው ቀርበዋል፣
ቅድመ ምርጫ ከባቢ፡ የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን በ2010 እንደተመለከተው “ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻዎቻቸውን ነጻ እና ለሁሉም እኩል በሆነ የምርጫ ምህዳር ሜዳ ላይ የመወዳደር መብት እንዳለቸው ህጉ ይፈቅዳል”፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ የወያኔ ገዥ አካል የፖሊስ መንግስት ሆኖ የቀጠለ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከምርጫው በፊት በሚኖሩት ወራት ሰላማዊ ሰልፎች ለማካሄድ እና በአገሪቱ በሙሉ የፖለቲካ ከባቢ አየሩ ከማስፈራራት እና ከማሸማቀቅ ነጻ በመሆን እኩል የምርጫ ጨዋታ ምህዳር እንዲኖር ያላቸውን የፕሬዚዳንትነት ስልጣን ተጠቅመው እውን እንዲሆን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡
የመንግስት ሀብትን መጠቀም፡ ለአንድ ለፖለቲካ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ስራ በሚል የህዝብን ወይም የመንግስት ሀበት መጠቀም በህግ የተከለከለ ነው፣ ሆኖም ግን በ2010 በተካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ የአውሮፓ የምርጫ የታዛቢዎች ቡድን እንደዚህ ያሉ ሀብቶች በስፋት በስራ ላይ ውለው እንደነበር ምስክርነቱን ሰጥተቷል (ተሽከርካሪዎች፣ በስራ ላይ ያሉ የመንግስት ሰራተኞች ለገዥው ፓርቲ ለምርጫ ቅስቀሳ መሰማራት፣ በየአካባቢው ያሉ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ለምርጫ ቅስቀሳ ማዋል፣ ወዘተ) ፕሬዚዳት ኦባማ የህወሀት ገዥ አካል የመንግስት ሀብቶችን እና ተቋማትን ለእራሱ የፖለቲካ ስራ የሚጠቀምበት መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ እንደዚህ ያሉ የተሳሳቱ አሰራሮች ሊወገዱ እንደሚገባ ፕሬዚዳንቱ ጥረታቸውን ሊያደርጉ ይገባል፡፡
የሜዲያ ከባቢ፡ የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ተዛቢ ቡድን በ2010 በደረሰበት ድምዳሜ መሰረት በመንግስት በሞኖፖል የተያዘው የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት በአገሪቱ ያለውን ብቸኛ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቆጣጥሮታል፡፡ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ ይደረጋል፣ እንደዚሁም አንዳንድ በዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን የሚንቀሳቀሱ ድረ ገጾች ይሰለላሉ፡፡ የወያኔ አገዛዝ በአገሪቱ የሚገኙ ሁሉንም ነጻ ጋዜጦችን እና መጽሔቶችን የዘጋ መሆኑን፣ እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎትን መዝጋቱን መቀጠሉን እና የሳቴላይት እና የሬዲዮ ስርጭቶችን በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ወጭ እያደረገ እያፈነ መሆኑን ፕሬዚዳንት ኦባማ ሊያውቁት ይገባል፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ ያላቸውን ስልጣን በመጠቀም ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ እስከ ምርጫው ዕለት ድረስ በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉት ሚዲያዎች እኩል በሆነ መልክ እንዲያገልግሉ ብቻ ሳይሆን ጋዜጠኞች እንዲፈቱ እና ሜዲያው በነጻ እንዲያገለግል እና ሁሉን ዓይነት መረጃ ማቅረብ እንዲችል እንዲያደርጉ፡፡
ሲቪል ማህበረሰብ፡ የአውሮፓ የምርጫ ታዛቢ ቡድን በ2010 ምርጫ ዘገባው የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በበጎ አድራጎት እና ማህበራት ቀያጅ አዋጅ ምክንያት የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በምርጫ ሂደቱ ስራ በእጅጉ ስራቸው ተደናቅ ፎነበር፡፡ ይህ ህግ ከ10 በመቶ በላይ የሚሆነውን ገንዘብ ከውጭ ምንጭ የሚያገኙ ከሆነ የአገር ውስጥ ድርጅቶች እንዲባሉ ተደረገ፡፡ በሀገር ውስጥ ያሉ ደርጅቶች ብቻ ናቸው በሰብአዊ መብት እና በዴሞክራሲ ላይ መስራት የሚፈቀድላቸው፡፡       
ከአንድ ሳምንት ገደማ አካባቢ በኒዮርክ ከተማ በክሊንተን ግሎባል ኢኒሼቴቭ ባራክ ኦባማ እንዲህ የሚል ንግግር አሰምተው ነበር፣ “የሲቪል ማህበረሰቡ መሪዎች ብቻ ናቸው በብዙ መልኩ ዘለቄታዊነት ያለው ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉት፡፡ ምክያቱም አባባሉ ሲነገር በነበረበት ጊዜ በጣም ጠቃሚው ርዕስ “ፕሬዚዳንት” ወይም “ጠቅላይ ሚኒስትር” አይደለም፣ በጣም ጠቃሚው ርዕስ “ዜግነት”… ዜጎች ሲቪል ማህበረሰብ ለምን በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ያስታውሰናል፡፡ ህዝቦች ሀሳባቸውን በነጻ መግለጽ ሲችሉ እና መሪዎቻቸው ተጠያቂ እንዲሆኑ ሲደረጉ መንግስት መልስ ሰጭ እና ውጤታማ ይሆናል፡፡“ ፕሬዚዳንት ኦባማ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት ተብሎ የታወጀውን ቀያጅ አዋጅ እንዲወገድ ወይም ደግሞ ጠቃሚነት ያለው ማሻሻያ እንዲደረግበት ጥረት እንዲያደርጉ በአጽንኦ እጠይቀዎታሉ፡፡ የሲቪል ማህበረሰቡ ለዴሞክራሲያዊ ሂደቱ ዋናው እምብርት በመሆኑ ላይ ሙሉ እምነት ስላላቸው ፕሬዚዳንት ኦባማ ያላቸውን ኃላፊነት ተጠቅመው የ2015 አገር አቀፍ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት የሲቪል ማህበረሰቡ ስራውን እንዲጀምሩ እና ነጻ ሆኖ እንዲሰራ እንዲደረግ እንዲያደርጉልን፡፡
የፕሬዚዳንት ኦባማ ኃይል ምንድን ነው? የእርዳታ ገንዘብ፡፡ በጥረት የተገኘ የአሜሪካ የዶላር  ግብር ከፋይ ህዝብ፣ አፍሪካውያንን/ትን በመርዳት ሰበብ የአሜሪካንን ዶላር ለአፍሪካ አምባገነኖች መስጠት ሆኖም ግን የአፍሪካ አምባገነኖችን የሂሳብ አካውንት ማቆም፣ የእርዳታ ገንዘብ ይናገራል፣ እናም በወያኔ ደንቆሮ አለቆች አንደበት በከፍተኛ ደረጃ ይሰማል፡፡ ዳምቢሳ ሞዮ በመጽሐፏ ላይ የሞተ እርዳታ/Dead Aid ብላ ባሰፈረችው መሰረት የወያኔ ገዥ አካል 97 በመቶ የሚሆነውን በጀት የሚያገኘው ከውጭ እርዳታ ነው፡፡ በቀላል አነጋገር የወያኔ ገዥ አካል ከአሜሪካ ጠንካራ ሰራተኛ ግብር ከፋዮች የሚሰበሰብ እርዳታ እስካላገኘ ድረስ ለአንዲት ቀን እንኳ መቆየት እንደማይችል እና ህልውና እንደሌለው ግልጽ ሊሆን ይገባል፡፡ ፕሬዚዳት ኦባማ ዓመታዊውን የደህንነት እርዳታ ለለማኞቹ የወያኔ ተመጽዋቾች ለመስጠት እጅዎን ሲዘረጉ እ.ኤ.አ በ2009 በጋና አክራ ለአፍሪካውያን/ት ምን የሚል ንግግር አድርገው እንደነበር ያስታውሱ፡፡ 
ልማት በመልካም አስተዳደር ላይ የሚወሰን ነው፡፡ የእራሳቸውን ህዝቦች ፍላጎት የሚያከብሩ፣ በስምምነት የሚገዙ እና በጭቆና የማይገዙ መንግስታት በጣም ሀብታሞች ናቸው፣ የተረጋጉ ናቸው እናም ከሌሎች የዚህ ዓይነት ባህሪያት ከሌላቸው መንግስታት የበለጠ ስኬታማ ናቸው፡፡ መንግስታት የህዝቡን ሀብት እየመዘበሩ የእራሳቸውን ኪስ የሚያዳብሩ ከሆነ ማንም አገር ቢሆን ሀብት ሊፈጥር አይችልም፡፡ የህግ የበላይነት ቦታውን ለጨካኝነት እና ባርነት የሚለቅ ከሆነ በዚህ ዓይነት ማህበረሰብ ውስጥ መኖር የሚፈልግ የለም፡፡ ያ ዴሞክራሲ አይደለም፣ ይልቁንም ያ አምባገነናዊነት ነው፡፡ እናም በአሁኑ ጊዜ የዚያ ዓይነት መንግስት መወገጃው ጊዜው አሁን ነው…
2015 የኢትዮጵያ ምርጫ ከነፋስ ጋር አብሮ ይሄዳል፣
እ.ኤ.አ በአስራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አራት ኦር ዌል እንዲህ ብለው ጽፈው ነበር፣ “የወደፊቱን ስዕል የምትፈልግ ከሆነ በሰው ፊት ላይ ለዘላለም ማህተም የተደረገ የቦት ጫማ በህሊናህ ውስጥ አስብ፡፡“ የ2015ን የኢትዮጵያን ምርጫ ስዕል ለማየት ከፈለግህ በጠራራ ጸሐይ በቀን ብርሀን የተሰረቀን የምርጫ ውጤት እና በምርጫ ቦት የምርጫ ሌቦችን እና ዘራፊዎችን የሚያባርሩትን ፊቶች፣ ግን ለብዙ ጊዜ አይቆይም፣ ግን በጣም ለረዥም ጊዜ አይቆይም፡፡
በ2015 በኢትዮጵያ ስለሚደረገው ምርጫ የፕሬዚዳንት ኦባማ ንግግር “ባዶ ነፋስ” ነው፣ (“የውሸት ቁልሎች” ከመለስ ዜናዊ ዘለፋ በመጥቀስ) ውሸትን እውነት የሚያስመስል ፖለቲካዊ ቋንቋ፡፡ ታሪክ ብዙ ነገሮች “ከነፋስ ጋር እንደሚሄዱ” ያሳያል፡፡ “እርሱ የእራሱን ቤት የሚያስቸግር ነፋስን ይወርሳል፡ እናም ቂል የብልህ አሽከር ይሆናል የሚለውን ሁላችንም ልናውቀው ይገባል”፡፡ አሁን በህይወት የሌለው መለስ እና የእርሱ ደቀመዝሙሮች በአሁኑ ጊዜ አስቸጋሪ በሆነ መልኩ የኢትዮጵያን ቤት በማስቸገር ላይ ይገኛሉ፣ እናም ነፋስን ይዘግናሉ! አውሎ ነፋስም በቅስፈት ይዞዋቸው ይሄዳል።
በ2015 በኢትዮጵያ ምርጫ አለ፡፡ ምርጫው ሰዎችን እንዴት በብር መግዛት እንደሚቻል ነው፣ እናም ስለሰዎች አስተዳደር አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ በ2015 ምርጫ አይኖርም፣ ሆኖም ግን ሸፍጥ ለመስራት የሚቆይ ምርጫ አለ፡፡ 
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ጥቅምት 15 ቀን 2007 .