Sunday, November 2, 2014

የወላይታ ዞን የአንድነት አመራሮች በመንግስት ሀይሎች ከባድ ድብደባ ተፈፀመባቸው

November 2,2014

(ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ) የወላይታ ዞን የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ማሞ ገሞ እና የዞኑ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ወኖ በዳሳ ትላንት ጥቅምት 22 ቀን 2007 ዓ.ም ከቀኑ በ 8 ሰዓት ከስብሰባ ወጥተው በወላይታ ሶዶ ከተማ በአንድ ሆቴል ውስጥ እያሉ በከተማው የፖሊስ አዛዥ መመሪያ በመንግስት ሀይሎች “እኛ ሀገር እመራን እናንተ ትቃወሙናላችሁ እናንተን እናጠፋቹሀለን” በማለት ከባድ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ለፍኖተ ነፃነት አስታወቀ፡፡ አመራሮቹ በድብደባው ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ታውቋል፡፡
UDJ
በድብደባው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው አቶ ወኖ በዳሳ ራሳቸውን ስተው በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል ቢወሰዱም እስካሁን እንዳላገገሙ እና የዞኑ የአንድነት ሰብሳቢ አቶ ማሞ ገሞ ህክምና አግኝተው ከወጡ በኋላም በከተማው ደህንነቶች ክትትልና ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝም ታውቋል፡፡
የወላይታ ዞን የአንድነት አመራሮች ላይ ድብደባ እንዲደርስ መመሪያ የሰጡት የከተማው የፖሊስ አዛዥ በአቶ ወኖ ላይ በደረሰው ከባድ ጉዳት ተደናግጠው በአምቡላንስ እንዲወሰዱ ካደረጉ በኋላ የዞኑ የአንድነት ሰብሳቢ አቶ ማሞ ገሞ “በአንድም ሚዲያ ስለሁኔታው እንዳይናገሩ” በሚል ክትትል እያስደረጉባቸው ያገኛል፡፡

No comments: