Thursday, November 6, 2014

ሰመጉ በቅርቡ በጋምቤላ ተከስቶ በነበረው ግጭት የሞቱ ሰዎችን ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ

November 6,2014
ሰመጉ በግጭቱ መነሻ ዙሪያ የተናገረው ነገር ባይኖርም፣ በተለያዩ አካባቢዎች የብሄረሰቦች ግችት እየተስፋፋ ቢመጣም መንግስት ይህን አሳሳቢ ጉዳይ በዘላቂነት ለመፍታት እያደረገ ያለው ጥረት ከችግሩ ክብደትና እየደረሰ ካለው ጉዳት አንጻር ሲታይ ጨርሶ የሚመጣጠን አይደለም ብሎአል። መንግስት ተመሳሳይ ግጭቶች እንዳይፈጠሩ ዘላቂ መፍትሄ ማበጀት ለነገ የማይባል አንገብጋቢ ጉዳይ ነው የሚለው ሰመጉ፣ በመዠንገር ዞን ለተፈጠረው ሰብአዊ እልቂትና መንስኤ የሆኑ ምክንያቶችንና ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ግልሰቦችንና ቡድኖችን አጣርቶ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል። 

ሰመጉ ባወጣው መግለጫ ላይ መንግስት የሰጠው አስተያየት የለም። መኢአድ የተገደሉ ዜጎችን ቁጥር በመቶዎች የሚቆጠር መሆኑን ሲገልጽ፣ ኢሳት በበኩሉ ምንጮችን ዋቢ በማድረግ ከ50 በላይ ዜጎች መገደላቸውን ዘግቦ ነበር።

No comments: