Friday, May 22, 2015

የወያኔን የይስሙላ ምርጫ አስመልክቶ ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢትዮጵያ ህዝብ የተላለፈ ጥሪ

May 22, 2015
የተከበራችሁ እናቶቼና አባቶቼ፤ እህቶቼና ወንድሞቼ እንዲሁም ልጆቼ የምትሆኑ ወጣቶች!!
dr-berhanu-Negaአገራችን የምትገኝበትን አስጨናቂ ሁኔታ ሁላችንም እንረዳለን። የህወሓት/ኢሕአዴግ ፋሽስቶች ቡድን እየገረፈ፣ እያሰረና እየገደለ በካርዳችሁ መርጣችሁ የምርጫ ድግሴን ካላሞቃችሁልኝ እያለ ነው። እንኳንስ ዛሬ ታዛቢ በሌለበት፤ ታዛቢ እያለም እንኳን ወያኔ የሕዝብን ድምጽ በትክክል ቆጥሮ አያውቅም። ወያኔ ለህዝብ ድምጽ ምንም ደንታ የሌለው የኋላቀር ወሮበሎች ቡድን ነው::
ለስንት አስርት ዓመታት ለወያኔ ባርነት እንገብራለን? ለሀያ አስምስት ዓመታት ተገዛን፣ ተገደልን፣ ተቀጠቀጥን፣ ታሰርን፣ ተሰቃየን፣ ልጆቻችን በአገራቸው ተስፋ ቆርጠው ሲሰደዱ በበረሀ ንዳድ አለቁ፤ በባህር ሰጥመው ቀሩ፤ በባዕዳን አረመኔዎች እንደከብት ታረዱ፤ ቤንዚን ተርከፍክፎባቸው ተቃጠሉ። ሀይማኖታችን ተዋረደ፤ ባህላችን ረከሰ፤ ታሪካችን ተናቀ። በልማት ስም ወልደን ከከበድንበት ተፈናቀልን፤ አገራችን አደገች እያለ ሕዝብ በኑሮ ውድነት ተሰቃየ። በልቶ ማደር ብርቅ ነው። እንደሙጫ የሚያጣብቀንን ማህበረሰባዊ ትስስር በስልጣን ለመቆየትና ህብረተሰቡን ለመዝረፍ ሲል ሆን ብሎ እያፈራረሰው ነው:: ይኽ ሁሉ አይበቃንምን? ይኸ ሁሉ አይመረንምን?
ወላጆቼ፣ እህት ወንድሞቼ!ውርደት ይብቃን። የተረገጥንና የተገደልን አንሶን ፍጹም ማንንም ሊያሞኝ በማይችል የለበጣ ምርጫ ወደን የተረገጥን፤ ፈልገን የተገዛን ለማስመሰል ወያኔ የሚያደርገውን ሩጫ እናክሽፈው:: ከፊታችን ያለውን ምርጫ ባለመሳተፍ ምሬታችንን እንግለጽ።
ዛሬ በግሌ እና በአርበኞች ግንቦት 7፡ የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ስም ጥሪዬን አቀርባለሁ። በዚህ ምርጫ አትሳተፉ። የምርጫ ካርዳችሁን ቀዳችሁ ጣሉት። እናምርር። ካላመረርን ለውጥ ሊመጣ አይችልም። ይልቅስ ለማይቀረው የመጨረሻው ትግል ራሳችንን እናዘጋጅ::
አርበኞች ግንቦት 7፣ ከትግራይ፣ ከኦሮሞ፣ ከአፋር፣ ከኦጋዴን፣ ከጋምቤላ፣ ከቤሻንጉል ድርጅቶች ጋር ትብብር በመፍጠር የአገር አድን ኃይል በመገንባት ላይ ነው። እኛ ልጆችህ በብሔርም ሆነ በሀይማኖት አንከፋፈልም። ከትግራይ እስከ ኦጋዴን፤ ከአፋር እስከ ጋምቤላ ሁሉንም የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ያካተተ ስብስብ ፈጥረን በኅብረት አገዛዙን እየታገልን ነው። ይህ ትግል ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ ትግል ነው። የትግሉም ባለቤት የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ነው። ክርስቲያን ሙስሊም፤ ወንድ ሴት፤ ወጣት አረጋዊ ሳንል፤ በብሔርም ሆና በቋንቋ ሳንከፋፈል ሁላችንም ይህን አስከፊ ሥርዓት በቃህ እንበለው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ!
ይህንን የውሸት ምርጫ ባለመሳተፍ ለለውጥ ያለህን ዝግጁነት አሳይ! ደግሜ እለዋለሁ – የምርጫ ካርድህን ቅደድ!!!
የጦርና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ሆይ!
እናንተ የሕዝብ አካላት ናችሁ። በወገኖቻችሁ ላይ አትተኩሱ። ይልቁንስ አፈሙዛችሁን አገራችንን ለውርደት በዳረገውና በሙስና በተጨማለቀው ዘራፊው የህወሓት አገዛዝ ላይ አዙሩት። ታሪካችሁን ከምታበላሹ፤ ታሪክ ሥሩ። ለራሳችሁ፣ ለቤተሰቦቻችሁ፣ ለልጆቻችሁ እና ለሕዝብ የሚጠቅም አገርና መንግሥት እንዲኖረን የእናንተ የግልም ሆነ የጋራ ተነሳሽነት ወሳኝ ነው። ወያኔ ህዝቡን የሚዘርፈው በእናንተ ትከሻ ላይ ቆሞ እንደሆነ ላንዳፍታም አትርሱት:: እንደመላው ህብረተሰብ እናንተም በነጻነትና በኩራት የምትኖሩበት ሀገር እንደምትሹ አልጠራጠርም:: ስለዚህም ይህን የህወሓት የውሸት ምርጫ ተቃወሙ። ዛሬውኑ ነፃነትና ፍትህ ከጠማው ወገናችሁ ጎን ቁሙ።
የኢትዮጵያ ወጣቶች፤ ትግላችን እስከ ነፃነት ድረስ ይቀጥላል። ነፃነታችንን በእርግጠኝነት በትግላችን እንቀዳጃለን። የምትወዷት፣ የምትኮሩባት አገር – ኢትዮጵያ – ትኖረናለች። ለዚህ ግን ዛሬ ተደራጅተን፣ ፀንተን መታገል የሁላችንም ኃላፊነት ነው። ዛሬ ሁላችንም በፍላጎትና በመንፈስ የተገናኘን ነንና ሁሉም በያለበት ትግሉን ያጧጡፍ። ውጤቱ ቀድሞ በታወቀው በዚህ ምርጫ አለመሳተፍ ለትግሉ ያለንን ቁርጠኝነት ማሳያ ነውና ለውሸት ምርጫ ያለን የመረረ ተቃውሞ በምርጫው ባለመሳተፍ እናሳይ።
ነፃ እንወጣለን!
የኢትዮጵያ ሕዝብ የነፃነቱ ባለቤት ይሆናል!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

Thursday, May 21, 2015

ለውጤታማ ድል፤ ተግባራዊ ትብብር!

May 21, 2015
def-thumbበመርህ ላይ በተመሠረተ ትብብር ወያኔን በጋራ ታግሎ ማሸነፍ እና በየደረጃው የሚገኝ የመንግሥት ስልጣን ነፃ፣ ፍትሀዊና ተዓማኒን በሆነ የሕዝብ ምርጫ ብቻ የሚያዝበት የፓለቲካ ሥርዓት መገንባት የአርበኞች ግንቦት 7፡ የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ተልዕኮ ነው። በዚህም መሠረት አርበኞች ግንቦት 7፣ በተግባራዊ እንቅስቃሴ ላይ ከሚገኙት ከትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ ከጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ፣ ከቤንሻንጉል ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ እና ከአማራ ዴሞክራሲ ኃይል ንቅናቄ ጋር በመርህ ላይ በተመሠረተ ትብብር በጋራ ለመታገል የሚያስችለውን ስምምነት ላይ እየደረሰ ነው።
ይህ የትብብር ጥረት ብዙ ጉዳዮችን ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ የኢትዮጵያን ሕዝብ ጠንካራ ድጋፍ ይሻል።
  1. ህወሓትን ከስልጣን የማባረር ኃላፊነት የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ኃላፊነት ነው። ይህ ትልቅ ኃላፊነት በአንድ ወይም በጥቂት ድርጅቶች ላይ መጣል የለበትም። ይህ ትብብር ይህንን የጋራ ኃላፊነትን በጋራ ለመወጣት የተደረገ በዓይነቱ አዲስ የሆነ ተግባራዊ ትብብር ነው።
  2. ህወሓት በትግራይ ውስጥ መቶ በመቶ ተቀባይነት ያለው አስመስሎ ፕሮፖጋንዳ ሲነዛ ቆይቷል። ህወሓት፣ የትግራይና የአማራ ሕዝብ በጠላትነት እንዲተያዩ፤ የትግራይ ሕዝብ ራሱን ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጥሎ እንዲያይ የረዥም ግዜ እቅድ አውጥቶ ተግባራዊ እያደረገ ነው። ይህን እኩይ ሴራ ማክሸፍ የምንችለው በፀረ-ወያኔ ተግባራዊ ትግል በጋራ ስንቆም ነው። ይህ ትብብር ለአገራችን አንድነትና ዘላቂ ሰላም ወሳኝ የሆነው በፀረ ህወሓት አቋሙ የጠነከረ የትግራይ ሕዝብ እንዲኖር ወሳኝ ሚና ይኖረናል ብለን እናምናለን።
  3. በአሁኑ ሰዓት የህወሓት አገዛዝ የቆመው ዘረኛ በሆነ መንገድ ባደራጀው ጦር፣ በስለላ ድርጅቱ እና ኃያላን መንግሥታት ለጥቅማቸው ሲሉ በሚያደርጉለት ሁለተናዊ ድጋፍ ነው። እነዚህ ህወሓትን ደግፈው የያዙ ኃይሎች ጠባቸው ከመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር መሆኑን በተግባር የምናሳያቸው ተግባርን መሠረት ያደረገ ጠንካራ ኅብረት ፈጥረን ስንገኝ ነው።
  4. ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ነባራዊ ማኅበራዊ ሀቅ ምክንያት ከፓለቲካ አመለካከት ይልቅ በወል ማንነት ላይ የተመሠረቱ ድርጅቶች የሚበዙበት ሆኗል። የኢትዮጵያን ችግር ለመፍታት ሁለቱን አመለካከቶች መሠረት አድርገው በተደራጁ ድርጅቶች መካከል ትብብር መፍጠር ወሳኝ ነው።
አርበኞች ግንቦት 7፣ ከላይ በአጭሩ በተዘረዘሩት ምክንያቶች እየተፈጠረ ያለው ትብብር የኢትዮጵያን የፓለቲካ መልካምድር ወደተሻለ ሁኔታ ለመቀየር የራሱ አስተዋጽዖ ይኖረዋል የሚል እምነት አለው። በዚህም ምክንያት መጠናቀቅ የሚገባቸው ነገሮች ተጠናቀው ትብብሩ በይፋ እንዲመሠረት የበኩሉን ጥረት ያደርጋል።
ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች ሳቢያ የትብብር አድማሳችን ከዚህም መስፋት አለበት ብሎ አርበኞች ግንቦት 7 ያምናል። ስለሆነም፣ በተለያዩ ምክንያቶች ለጊዜው የትብብር ማዕቀፍ ውስጥ ያልገቡ የፓለቲካ ድርጅቶች ወደ ትብብሩ እንዲመጡ፤ ለሀገራችን እና ለሕዝብ በጋራ መሥራት በምንችላቸው ጉዳዮች ላይ እንድመክር ጥሪውን ያስተላልፋል። በመመካከር ህወሓትን ማስወገድ ብቻ ሳይሆን ለሁላችን የሚበጅ የተሻለ ሥርዓት በአገራችን ላይ እንዲመሠረት መሠረት መጣል እንችላለን ብሎ አርበኞች ግንቦት 7 በጽኑ ያምናል። ስለሆነም እንነጋገር፤ ለሁላችን የሚበጀንን መንገድ በጋራ እንፈልግ፤ የህወሓት ፋሽስታዊ አገዛዝን በጋራ እንታገል፤ ከራሷ ጋር የታረቀች አገር ጥንስስ እኛው ውስጥ እንፍጠር ይላል።
ለውጤታማ ትግል እንተባበር!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Monday, May 18, 2015

ካድሬዎች የምርጫ ካርድ ላይ ንብን እየለጠፉ ለመራጩ እያደሉ ነው

May 18,2015
በጋሞጎፋ ዞን ቁጫና ቦርዳ ወረዳዎች የደኢህዴን/ኢህአዴግ ካድሬዎች የህዝቡን ካርድ እየተቀበሉ የምርጫ ካርዱ ላይ የንብን ምልክት በስቴፕለር በማያያዝ ኢህአዴግን እንዲመርጡ እያስገደዱ እንደሚገኙ በጋጎፋ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ አቶ ወንድሙ መኩሪያ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ካድሬዎቹ ህዝቡን 1ለ5 በማደራጀት የንብ ምልክት የተለጠፈበት ካርድ በማደል ‹‹የምትመርጡት ኢህአዴግን ነው›› እያሉ እያስገደዱ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
የዞኑ፣ የወረዳውና የየ ምርጫ ክልሉ ምርጫ አስፈጻሚዎች ካድሬዎቹ የንብ ምክትን የምርጫ ካርዱ ላይ እያያያዙ ኢህአዴግን እንዲመርጡ እያስገደዱ መሆኑን ቢያውቁም ምንም እርምጃ እየወሰዱ አይደለም ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል በጋሞጎፋ ዞን ቦረዳ ወረዳ ሰማያዊ ፓርቲ እሁድና ቅዳሜን ‹‹የገበያ ቀን ስለሆነ›› በሚል ቅስቀሳ እንዳያደርግ መከልከሉን አስተባባሪው ገልጸዋል፡፡ ‹‹የምርጫ ህጉ የሚለው ቅስቀሳ መደረግ ያለበት ከገበያ 500 ሜትር ርቆ ነው እንጅ በገበያ ቀን ቅስቀሳ አይደረግም አይልም፡፡ እኛን ግን ገበያ በሌለባቸው ቦታዎች ሁሉ እሁድና ቅዳሜ ቅስቀሳ እንዳናደርግ ከልክለውናል›› ብለዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ቅስቀሳ እንዳያደርግ እየከለከሉ የሚገኙት የቦረዳ ወረዳ የፀጥታ አስተዳደር ኃላፊ አቶ ማርካ ማዶ እና የወረዳው ፖሊስ አዛዥ መቶ አለቃ ታምራት ናቸው ብለዋል፡፡

Sunday, May 17, 2015

" ኢህአዴግ ጠመንጃና ምርጫ ቦርድን እንደ ምርኩዝ ይዞ ነው የሚንቀሳቀሰው፡፡ "

May 17,2015
ዶ/ር መረራ ጉዲና
Minilik Salsawi's photo.
በየቦታው ትንንሽ ጦርነት የሚመስሉ ነገሮች ነበሩ፡፡ የኛ ቅስቀሳ በተሳካ ቁጥር የእነሱ ብስጭት ይግል ነበር፡፡ ካድሬው ለሆዱ፣ መንግስት ለስልጣኑ በሚገባ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ይሄ አመላካች ነው፡፡ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ግን ካድሬው ሽጉጥ ታጥቆ፣ ጠመንጃ ይዞ እገባለሁ አትገባም የሚል ግብግብ እስከመፈጠር ደርሷል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ መኪናዎቻችን እንዳይንቀሳቀሱ ተደርገው ተወዳዳሪ እጩዎቻችን ሳይቀሩ ተደብድበዋል፡፡ በአባላቶቻችን ላይ እስር፣ ድብደባና ወከባ ተጠናክሮ ቀጥሏል:: በዘንድሮ ምርጫም ኦሮምያ ላይ እናሸንፋለን ብለዋል - ዶ/ር መረራ፡፡
በኦሮሚያ ብዙ አካባቢዎች ሰፋፊ ህዝባዊ ስብሰባዎችን አካሂደናል፡፡ ባኮ፣ አምቦ፣ ጀልዱ፣ ጊንጪ የመሳሰሉት አካባቢዎች እኔ የተገኘሁባቸው ህዝባዊ ስብሰባዎች ተደርገዋል፡፡ በየስብሰባው ከ60ሺህ በላይ የሚገመት ህዝብ ነው ድጋፉን ሲገልፅልን የነበረው፡፡ በተለይ የወጣቱ ድጋፍ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ነው፡፡ “ከዚህ በኋላ የፀረ-ዲሞክራሲ አገዛዝ ይብቃን” የሚሉ ህብረ ዝማሬዎችን እያሰማ ነው ህዝቡ በየስብሰባው ላይ ሲታደም የነበረው፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ሲታዩ ቅስቀሳው ስኬታማ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ክልሉን እያስተዳደረ ያለው ኦህዴድ፣ በዚህ መልኩ ወጣቱ ለኛ ድጋፍ ይሰጣል ብሎ የገመተ አይመስለንም። አሁን ታዲያ የድንጋጤ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው፡፡ በአርሲ፣ በባሌ፣ በሃረርጌ፣ በባሌ እና በሸዋ አካባቢዎች አባሎቻችንን ማሰር፣ መደብደብና ማዋከብ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ የቅስቀሳ መኪናዎቻችንን መስተዋቶች በድንጋይ የመስበር፣ መኪኖችን በቡና ቤቶች አካባቢ ማሳደር እንዳንችል የማድረግ ሁኔታዎች በስፋት ተስተውለዋል፡፡ ብለዋል - ዶ/ር መረራ፡፡
በሁሉም የኦሮሚያ ዞኖችና አካባቢዎች ተመሳሳይ የሆነ አቀባበል ከህዝቡ አግኝተናል፡፡ በአጠቃላይ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በትግራይ እና በአዲስ አበባ በምርጫው እንወዳደራለን፡፡ በሁሉም ላይ ቦታ ሰፊ አቀባበል ያገኘን ቢሆንም በተለይ ኦሮሚያ ላይ ኢህአዴግ ምርጫውን ካላጭበረበረ በቀር የሚያሸንፍበት መንገድ የለውም፡፡ እኛ ሁለት ነገር ነው የምንጠብቀው፡፡ አንደኛ ኢህአዴግ ካላጭበረበረ በቀር ኦሮሚያ ላይ አያሸንፈንም፣ ሁለተኛ ደግሞ ፖለቲካውን በሚገባ እንዳሸነፍን አሳይተናል፡፡ ሰፊ ድጋፍ እንዳለን አስመስክረናል፡፡ በየትኛውም ሚዛን ከኦህዴድ እንደምንሻል አሳይተናል፡፡ በዚህ ተደናግጠው እኔ በምወዳደርበት አካባቢ ኦህዴዶች ህዝቡን በሬ አርደው ማብላት ሁሉ ጀምረዋል፡፡ የክልሉ ካድሬዎች አሁን አምቦ ከትመዋል፡፡ ሥራ ላይ ናቸው ማለት ነው፡፡ ኦህዴድና ህዝቡ ከተለያየ ቆይቷል፡፡ ያው በኢህአዴግ ጃንጥላና ጠመንጃ ስር ነው የሚንቀሳቀሰው፡፡ እነሱም እንደማያሸንፉ ያውቃሉ። እኛ በ97 እኮ አሳይተናቸዋል፡፡ በወቅቱ እነ አባዱላን ያሸነፉት እኮ የ6ኛ እና 7ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ ኦህዴድ በኦሮሚያ ሊሸነፍ እንደሚችል በ97 ምርጫ ነው ያረጋገጥነው፡፡ ብለዋል - ዶ/ር መረራ፡፡
“መድረክ” አብላጫ ድምፅ ካገኘ ጥምር መንግስት ይመሰርታል:: እኛ በፕሮግራማችን ላይ በግልፅ አስቀምጠናል። በሽግግሩ ጊዜ ጥምር መንግስት ያስፈልጋል ብለናል። ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር፣ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ለማካሄድና ለመሳሰሉት ዲሞክራሲያዊ ሂደቶች መልክ ማስያዣ ይሆን ዘንድ የብሄራዊ አንድነት መንግስት ያስፈልጋል፡፡ ከማን ጋር ይመስረት የሚለው በድርድር የሚከናወን ይሆናል፤ ነገር ግን አግላይ ፖለቲካ ውስጥ አንገባም፡፡አንድ ፓርቲ ሌላውን አግልሎ ኢትዮጵያን መንግስተ ሰማያት ያደርሳል የሚሉ ካሉ ወይ የፖለቲካ ሳይንስ ያልገባቸው ወይም እስከቻልን ድረስ በፈላጭ ቆራጭነት ረግጠን እንግዛ የሚሉ ናቸው፡፡ በተረፈ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲ ለማምጣት መታለፍ ያለበት አንዱ ሂደት የብሄራዊ አንድነት መንግስት ማቋቋም ነው። ብለዋል - ዶ/ር መረራ፡፡
በአጭሩ የኢትዮጵያ መንግስት ደጋግሞ እንዲያስብበት የምመክረው ምርጫውን እንዳያጭበረብር ነው፤ ውጤቱ የፈለገ ይሁን፡፡ ምርጫን አጭበርብሮ አሸንፌያለሁ የማለት ጊዜ ማብቃቱን ማወቅ አለበት። ያንን ካላደረገ ሃገሪቷንና ህዝቦቿን ለበለጠ ተስፋ መቁረጥ ነው የሚዳርገው፤ ይሄ በተግባር እየታየ ነው። ወጣቱ ከቀይ ባህር እስከ ሜዲትራኒያን ድረስ የባህር ሲሳይ የሚሆነውና በረሃ ውስጥ እንደዚያ የሚታረደው፣ ደቡብ አፍሪካ እንደዚያ የሚቃጠለው በሃገሩ ተስፋ ስላጣ ነው፡፡ ኢህአዴግ በጠራው ሰልፍ ላይ እንኳ “የስደት ዘመን ይብቃ” ብሎ ከፖሊስ ጋር እንዴት እንደተጋጨ ተመልክተናል፡፡ አጥፍቶ የመጥፋት ፖለቲካ ይብቃ! የኢህአዴግ ባለስልጣናት ደጋግመው ያስቡበት። ህዝቡንም ወጣቱንም ተስፋ ማስቆረጥ ለማንም አይጠቅምም፡፡ በተለይ ወጣቱ በሃገሬ የተሻለ ሥራ አገኛለሁ የሚል ተስፋ ሊያድርበት ይገባል፡፡ ይሄንን ወጣት ተስፋ ማስቆረጥ ለሁላችንም አይበጅም፡፡ ብለዋል - ዶ/ር መረራ፡፡

Thursday, May 14, 2015

በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ላይ ዘለፋ አዘል ግምገማ ተካሄደ

May 13,2015

ኢሳት ዜና :- ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በሰብሳቢነት የሚመሩት  ኢህአዴግ፣  ከፍተኛ የግንባሩንና የመንግስት አመራሮችን በመገምገም ለሚቀጥሉት አምስት አመታት የመንግስት ስልጣን የሚይዙትንና ድርጅቱን የሚመሩትን ሲመርጥ ከርሟል። ሁሉም የኢህአዴግ ከፍተኛ ሹሞች የተገመገሙ ሲሆን፣ የመንግስት ስልጣን ያልያዙ ነገር ግን በግንባሩ ውስጥ ያገለገሉ ነባር ታጋዮችም በግምገማው ተሳትፈዋል። አቶ ሃይለማርያም ግምገማውን በሰብሳቢነት ሲመሩ ቆይተው፣ የመጨረሻው ተገምጋሚ ራሳቸው ሆነዋል። በጠ/ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ላይ የተደረገው ግምገማ አንድ ሙሉ ቀን የወሰደ ሲሆን፣ ከምሽቱ ሶስት ሰአት ላይ መጠናቀቁን ምንጮች ገልጸዋል። አቶ ሃይለማርያም ብዙዎችን የግምገማ ነጥቦች ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆናቸው ለግምገማው መራዘም ምክንያት ሆኗል።
ሁሉም ባለስልጣናት  የሚገመገሙባቸው ነጥቦች ተመሳሳይነት አላቸው።  አስተያየቶች የሚሰጡትም በእነዚህ ነጥቦች ዙሪያ ነው። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ  በቅድሚያ ራሳቸውን የሄሱ ሲሆን፣ እንዲህ ብለዋል ” ጥራት ያለው እቅድ አዘጋጅቶ በማከናወን ረገድ ፣ ራስን በንባብ ለማብቃት ጥረት በማድረግ ላይ እንዲሁም የለውጥ ትግበራ ላይ ችግሮች አሉብኝ” ። ነገር ግን “ስራን ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በመፈጸም፣ ስራን በተሟላና ጥብቅ ስነምግባር በመፈጸም፣ ለስራ የተሰጠኝን መሳሪያዎች በእኔ ባይነት ስሜት በመጠቀምና በመጠበቅ እንዲሁም በፖሊሲ አፈጻጸም ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ በኩል  ችግሮች የሉብኝም” ብለዋል። ኪራይ ሰብሳቢነትን በመታገል በኩል በከፊል ችግሮች አሉብኝ ሲሉ አክለዋል።
ከቃለ ጉባኤው ለመረዳት እንደሚቻለው የመጀመሪያውን ሂስ ያቀረቡት ነባሩ የህወሃት ታጋይና የጠ/ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ አርከበ እቁባይ ናቸው። አቶ አርከበ ” የተጠራቀሙ ችግሮችን በመፍታት በኩል ችግሮች አሉብህ፣  ካቢኔህ ውስጥ ያለውን  የጥራት ችግርም በደንብ አላየኸውም፤ ለሃገሪቱ አመራር ቶሎ ምላሽ አትሰጥም፤ ‘እኔ የሚመስለኝ እንዲህ ነው’ ከማለት ውጭ፣ ቆፍጣና የሆነ አመራር አትሰጥም፤ ስራዎች ሁሉ ከሌላው አካል እንዲመጣልህም ትጠብቃለህ፣ ብዙውን ጊዜ በቅጻቅጾች ላይ አትኩረህ አይሃለሁ፤ ከብሄራዊ ደህንነት እና የቴክኖሎጂ ቁርኝት ጋር ያለውን ችግር ቁጭ ብለህ አለመፍታትህ ውዝግቡ እስካሁን እንዲቆይ አድርጎታል” ሲሉ ሂስ ሰንዝረዋል።
ሌላው የህወሃት አባል አቶ አስመላሽ ወ/ስላሴ ደግሞ  ” ስልጣንን ጠቅልሎ የመያዝ ነገር አለ፤ ስዎችን እርስ በርስ የማጋጨት ነገርም አለ፣ ለአማካሪዎችህ ‘እሱ ምን ሰርቶ ነው’ ትላለህ፣ በፖሊሲና እና ስትራቴጂ ላይ አዲስ የፈጠርኸው ቋንቋም የለም፣ ፓርላማው በአንተ
ጊዜ አዲስ ቃላትን እንኳ አለመደም፣ ይህም ከንባብ  የመጣ ችግር ነው፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን በመደገፍ ፤ ሃሳብን በመቀበል ረገድ ችግር አለብህ፣ ገንቢ ሃሳብም በመስጠት ላይ ችግር ይታያል”” ብለዋል። አቶ ሃይለማርያምን እጅግ ያበሳጫቸው የአፋር ክልል ፕሬዚዳንት አቶ እስማኤል አሊሴሮ ያቀረቡት ትችት መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ።በቃለ ጉባኤው ላይ ሰፍሮ እንደሚታየው  አቶ አሊሴሮ ” ተግባብቶ መስራት ላይ ችግር አለ፣ ከክልሎች ጋር ያለው ግንኙነት እንዲሻሻል
የእሱ አስተዋጽኦ የለበትም፣ ያልተጻፉ ህጎች ይወጣሉ፤ ከክልሎች  ጋር ሳትነጋገር ከምክትሎች ጋር የኮሚኒኬሽንን ስልጣን በመጋፋት የህዝብ አስተያየት ትሰበስባለህ፤ ሰዎች ነጻ ሆነው እንዲሰሩ አለማድረግ፤ ገፍቶ ሄዶ ችግሮችን አለመፍታት፣ በአማራና አፋር፣ በትግራይና አፋር ድንበሮች ያለውን ውዝግብ ተጋፍቶ ችግሮችን ለመፍታት አለመቻል፣ ጥሩነትን ወይም በጎነትን አለማበረታታት፣ አንዳንድ ሚኒስትሮች ቤተመንግስት እንዳይገቡ መከልከል፤ እቅድ ከማውጣት ጀምሮ በፖለቲካ ላይ ለውጥ ለማምጣት ስትጥር አለመታየት” የሚሉ ትችቶችን በንባብ አሰምተዋል።
አቶ ሃይለማርያም ይህን ጽሁፍ ያዘጋጀውንና እንዲቀርብ ያደረገውን ሰው አውቀዋለሁ በማለታቸው ከፍተኛ ውዝግብ ተፈጥሮ ነበር፣ እንደምንጮች መረጃ። ወ/ሮ ሙፈሪያት ከሚል ባቀረቡት ሂስ ደግሞ ” በመንግስት በጀት እና ፋይናንስ እገዛ ማድረግ እና  ስራ እንዲሰራ መደገፍ ሲኖርብህ አትገድፍም፤ የመከላከያ ገንዘብ አወጣጥን በተመለከተ በከፊል በኦዲተር እንዲጣራ ከተስማማህ በሁዋላ ፣ በግልህ ሽረህ በእኔ ላይ ዛቻ እንዲደርስብኝ አስደርገሃል። ቤተመንግስቱን ኦዲት ለማድረግ በኦዲተርነት ሰርቶ የማያውቅ ሰው ተመድቧልና አይሆንም ስል፣ ‘ሂጂ ስራሽን ስሪ ዛሬ ችሎ ሊሆን ይችላል’ ተብያለሁ፣ ይሄ ስራ እንዲሰራ አለመፈለግ ነው። ለለውጥም ዝግጁ አይደለህም። በረከት ሰብስቦን ሁሉም ስህተቱን ሲቀበል አንተ አልተቀበልህም፣ ይሄ ለለውጥ አለመዘጋጀትህን ያሳያል።” ብለዋል።
ወ/ሮ ሙፍሪያት  ” ከቢሮ ስነምግባር አንጻርም ችግሮች አሉ ይላሉ። ወደ ውጭ አገር በሚደረግ ጉዞ ላይ አድልዎ መኖሩን ራሳቸውን በምሳሌነት በማቅረብ ተናግረዋል። ” በግል ‘ አንቺ ተጽኖ ፈጣሪ አይደለሽም ፣ ደቡብ አንቺን ከሚወክል ቢቀር ይሻል ነበር’” ተብያለሁ የሚሉት ወ/ሮ ሙፈሪያት፣  ወደ አውሮፓና ግብጽ ለሚደረገው የዲፕሎማሲ ጉዞ አስቀርቶኝ ወደ አዋሳ ልኮኛል ብለዋል። ዋናው ኦዲተር በአግባቡ እየሰራ አለመሆኑን ስናገርም ሙፈሪያት ስራ አትሰራም ብለኸኛል። ከካሱ ኢላላና ከሽፈራው ጋር ተጋጭቼ አንድም ቀን ችግሩን ለመፍታት አልሞከርክም፤ የሰው ስም ታጠፋለህ፣ ትለማመናለህ”” ሲሉ የሰላ ትችት አቅርበዋል። ወርቅነህ ገበየሁ ደግሞ ”   ቆራጥ አመራር በመስጠት በኩል መሰራታዊ ክፍተቶች አሉብህ” ያሉዋቸው ሲሆን፣  የፌደራል ፖሊስ ራሱ ተሟሙቶ ካልሰራ በስተቀር ሃይለማርያም አያግዘውም ሲሉ አክለዋል። “አፋጣኝ መልስ መስጠት ላይ ችግር አለ። የፌደራል ፖሊስ
ኮሚሽነር በነበርኩበት ዘመን፣ ህዳር 23 ሶማሊ በነብርኩበት ጊዜ በተደጋጋሚ ደውየ ‘ ስብሰባ ላይ ነኝ’ በሚል አልመለስክልኝም፤ ይዘነው የመጣነውን ፕሮግራም ጠፍቶብኝ ከደህንነቶች ጋር ስጨቃጨቅ ውዬ ፣ ተሰድቤ በበነጋታው ችግሩን ስነግርህ ልትፈታው አልቻልክም። የፌደራል ፖሊስ ከደህንነት ክፍሉ ጋር ያለው ግንኙነት የደከመ ነው። ጋምቤላ ላይ ያሉ ተዋጊዎችን እናጥፋቸው አሁንም ሶማሊና አማራ ክልል  ያሉ አማጽያንን እናጥፋ ስልህ የደህንነት ክፍሉና ጸጋየ በርሄ ይዘውታል ብለኸኛል። ጅጅጋ በተፈጠረው ነገር አራት ጊዜ ደውየ ምላሽ ሳጣ ለሳሞራ ደወልኩ፣ እናም ‘ ለእኔ ከማሳወቅ ይልቅ ከጦሩ ጋ መንጠንጠል ይወዳል’ አልከኝ። ኢንሳ፣ ኢሳያስ ክፍል ስንሄድ ‘ሁሉንም ነገር እንዳታደርጉ ተብለናል’ እንባላለን። ከሁሉም የደህንነት ክፍሎች ጋር ፊትና ሁዋላ ሆነን እያለ በግዴለሽነት ችግሩን አልፈታሃውም” ሲሉ ጠንካራ ነቀፌታ አቅርበዋል። ነባሩ የህወሃት ታጋይ አቶ ስብሃት ነጋ በበኩላቸው ” ሃይለማርያም ቸልተኝነት ያበዛል፣ በጣም ችላ ይላል፤ ስራዎችን ይገፋል። የሚያውቃቸውን ክህሎት፣ ካለው ሃላፊነት አንጻር ለሌሎች ላማካፈል አይጥርም፤ ያለመጋጨት ነገር አለ። ሚኒስትሮች ‘በፍላጎት እንዳንሰራ ከሚያደርጉን ነገሮች አንዱ ስልጠናዎችን ስናገኝ  ስለሚያሳልፍብን ነው’ እያሉ ስሞታ ያቀርባሉ። በስራ ስምሪት ወቅት በምትፈልጋቸው ስራዎች ላይ ራስህ ሰው ትመድባለህ። በረከት ላይ ትለጠፋለህ።” ብለዋል።
ሌላው ነባር ታጋይ አባይ ጸሃየ ደግሞ ” ሚኒስትሮች ሃላፊነት ተስምቷቸው የሚሰሩ አይመስለውም፤ ድጋፍ የማይሆን ክትትል ያበዛል፣ ሰራተኞችን በጣም ይንቃል። ከፍተኛ ሃላፊዎች ቢታመሙም የታመሙ አይመስልህም። ስራን ያላገናዘበ ሞራልን የሚነካ የሚያስፈራራ ደብዳቤ ለአራት ሚኒስትሮች ሰጥተሃል።” ሲሉ ሂሰዋቸዋል። የብአዴኑ ሊ/መንበርና ምክትል ጠ/ሚኒስትሩ በፊናቸው ” ከህዝብ ወገንተኝነት ጋር በተያያዘ፣ አሁንም ቢሆን፣ ሁሉም እምነቶች በእኩል መስተናገድ ሲገባቸው ለፕሮቴስታንት ሃይማኖት ማዳለት እንዳለ ተገንዝቤአለሁ፤ ስራን በቁጭት ትሰራለህ ብየ አላስብም፣ የመሪነቱን እንዳልታማ እንጅ ለስራው ተቆርቁሮ የሚሰራ አይመስለኝም።  አስተያየት ሲሰጥ ተቀብሎ ለማሻሻል ከመጣር ይልቅ ሃሳቡ ጥሩ ነው ብሎ የመግፋት ነገር አለ፤ ከደህንነት ክፍሉና ከጠባቂዎችህ ጋር ያለህ ግንኙነትም የደከመነ ነው” ብለዋል።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ወ/ሮ ሮማን ገብረስላሴ ደግሞ ” ፈጣን ምላሽ መስጠት ላይ፣  ስብሰባ ከገባህ በምንም መንገድ መልስ አትሰጥም፣ ስራን ከፋፍሎ ያለመስጠት ነገር አለ። በሰው ላይ እምነት የማጣት ነገር አለ። ችግርን ወደ መድረክ አምጥቶ ከመፍታት ይልቅ ወደ ዝምታ ታመራለህ። ” ብለዋቸዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ የብአዴኑ አቶ አህመድ አብተው በበኩላቸው ” ታዳላለህ፣ የአቶ አዲሱ ለገሰን ስልጠና እንዳላገኝ ተከልክያለሁ፣ በአንተ አመራር ጥሩ ስራ መስራትና ጥሩ ስነምግባር ማሳየት የመብት መጣስን ያመጣል፣ በጣም ሃይለኛ ተንኮል አለብህ፤ በአንድ ስብሰባ ላይ ‘አማራ አይቀበልህም’ ብለህ ከብሄሬ ጋር ልታጋጨኝ ሞከረሃል። በኢንዱስትሪ ዘርፍ ያሉ ሌሎች ስራዎችን ትተሃቸዋል ስልህ ‘ ስለሌሎች አያገባህም፤ እኔ ጠ/ሚኒስትር ነኝ’ አልከኝ። ለመማር እንኳ ዝግጁ አይደለህም። እኔ እየተማርኩ መሆኔን እያወቅ ከፈቃድ አሰጣት ጋር አድልዎ ታደርጋለህ። ከጓደኞችህ ጋር በመሆን ‘አህመድ አገሪቱን በእንዱስትሪ ጭስ አፈናት ‘ ብለህ አፌዝክብኝ፤ ሰራተኛ ምንም አይመስልህም። ሞራል ትነካለህ፣ ሞራል አትጠብቅም፣ አስተካክል።” ብለዋል።
ሌላው ትችት አቅራቢ የደህዴኑ የኮምኒኬሽን ሚኒስትሩ አቶ ሬድዋን ሁሴን ናቸው። አቶ ሬድዋን ” ገንቢ አስተያየት መስጠትን በተመለከተ ፣ ብዙ ጊዜ አንድ ፕሮግራም አስቤ እጠይቅሃለሁ። ነገ ዛሬ እያልህ ሃሳብ አትሰጠኝም። አመራር ተቆራርጦ ይሰጣል። በወኔና በእልህ ሂ ደቱን ለመለወጥ የሚደረገው ጥረት አናሳ ነው። ከእኔ ጋር በጥሩ ሁኔታ እያወራ ፣ ከሌላ ሰው ጋር ስለእኔ ሌላ ነገር ነው የሚናገረው፤ ለበረከት ‘እሱና ሽመልስ ልዩ ተልእኮ ያላቸው ሰዎች ናቸው፣ ልቆጣጠራቸው አልቻልኩም’ ብሎ ነግሮታል። ለእኔ አልነገርከኝም። የአመራር መስፈርቶችን ታሟላለህ አልልም።” የሚል ትችት አቅርበዋል።
አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በቀረቡባቸው ሂሶች ላይ መልስ ሰጥተዋል። “መሻሻል ያለባቸውን አሻሽላለሁ” ብለዋል። “ብዙውን ስራ እራሴ እሰራለሁ በሚል ለመስራት ስለምሞክር ነው ክፍተቶች የተፈጠሩት” የሚሉት አቶ ሃይለማርያም፣  “ስራውን ጠቅልሎ ይዟል ለሚባለው ግን የሚገባኝን ይዣለሁ ብየ ነው የማስበው” ብለዋል።  ሰዎችን ማጋጨት ለተባለው  “እኔ ሰዎችን በማጋጨት ምን ላገኝ? ችግር ያለበትን ሰው ችግር አለበት ፣ ጥሩውንም ጥሩ ነው” እላለሁ። ሲሉ ተከራክርዋል። “ሶማሊና አማራ፣ ትግራይ አፋር ላይ የተነሳው ችግር ከአሰራር ጋር በተያያዘ የመጣ ችግር መሆኑን የገለጹት አቶ ሃይለማርያም፣ በሙፍሪያት ለተነሳው ቅሬታም ” ሙፈሪያትና ሽፈራውን ለማስማማት ሁለቱም ጋር ችግር አለ፤ አባይ እንዲፈታው ነግሬዋለሁ፡፡ ብለዋል””
“ስንሰራ ከፖለቲካ ጋር አስተሳስረን እንስራ ነው ያልኩት እንጅ ስራን አልከለከልኩም የሚሉት አቶ ሃይለማርያም በአቶ አህመድ  በአቶ አህመድ ለቀረበባቸው አስተያየት ደግሞ ” ፊት ለፊት ለራስህን ነው የነገርኩህ፣ ለሌላ ሰው በቀልድ መሃል ላወራ እችላለሁ።” ሲሉ በመካድና ባለመካድ መሃል ሆነው መልሰዋል። “ለውጭ ጉዞ ታዳላለህ የተባለውን በአሰራራችን መሰረት ብናየው ጥሩ ነው ” ያሉት አቶ ሃይለማርያም፣ “እገሌ ከገሌ የሚባል ሳይሆን የስራውን አዋጭነት አይተን ነው  ሰዎችን የምንመድበው ሲሉ አክለዋል። “ሰው ሲጋጭ ደስ ይልሃል የተባለውን አልቀበለውም” ብለዋል።   “ስራ ሲሰራ በግድ መሆን ባለበት ቀን ሊሰራ አይችልም፤ ችግሮች አሉ።  የደረሰንን ስልጠና አዳርሰናል፣ ማንንም የምነካ ሰው አይደለሁም፤ ማንንም አልንቅም” ሲሉ ራሳቸውን ለመከላከል ሞክረዋል።
“እምነትን በተመለከተም በእኔ እምነት ሁሉንም እኩል እያስኬዱ ነው ” አቶ ሃይለማርያም፣  የሙስሊሙንም የክርስቲያኑንም ችግሮች እኩል አያለሁ፣ ያለሁት ፖለቲካ ላይ ነው። ብለዋል። በአቶ ስብሃት ለቀረበባቸው ሂስ ደግሞ ” ስብሃት በጣም ይጮሃል፣ እንዳሞራ ሁሉ ይዞረኛል፣ እዚህ ሳወያይ ሁሉ በጣም ይጮሃል፣ አለቃ መሆን ችግር ነው ብየ ዝም አልሁ። ንግግር ከመልክ ያምራል ይባላልና የተሳሳትኩት ነገር ካለ አርማለሁ።በአባባል ክፈተት ካለ ይቅርታ እጠይቃለሁ። በማለት በአቶ ስብሃት ላይ ያላቸውን ቅሬታ ገልጸዋል። አቶ ሃይለማርያም የቀረበባቸውን ሂስ ቢቀበሉም ሌሎች አባሎቻቸው ግን በሂስ አቀባበላቸው ላይ የሰላ ትችት ከመሰንዘር አላገዳቸውም። የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ በከር ሻሌ ዱሌ ” ሃይለማርያም አሁንም ለመማር አልተዘጋጀህም፣ ሰው ከሁለት ነገሮች አያመልጥም፣ ከፈጣሪና ከህሊናው።  ቀኑን ሙሉ በውይይት ፈጅተን የተሰጠን ምላሽ አልተመቸኝም”ያሉ ሲሆን፣  የአካባቢ ጥበቃና የደን ሚኒስትር አቶ በለጠ ታፈረ ደስታ በበኩላቸው “አብዛኛውን ገፍቶታል፣ ወደውስጡ አላስጠጋውም፣ ሁሉን ከተከላከለ በሁዋላ አስተካክላለሁ ብሎአል ” ብለዋል።
ዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል ደግሞ  ” ከፊሎችን አልነካሃቸውም ፣ መኮርኮምም አይቸብሃለሁ፤ ይሄ ከአንድ የአገር አመራር አይጠብቅም” ያሉ ሲሆን፣ ወ/ሮ አስቴር ማሞ  ደግሞ ” አቀባበሉ ላይ ዞሮ ዞሮ ላንተ ነው የሚጠቅምህ፣ እዚህ አገር ላይ የሆነ አሻራ ብታሳርፍ ያንተ ስም ነው የሚነሳው ፣ ፍቅርንና የመተባበር መንፈስን ብትዘራ ጥሩ ነው።” ብለው ምክር ለግሰዋቸዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሃኖም ደግሞ ” ሁሉንም ጥያቄዎች ሳያቸው በወቅቱ መፈታት ይችሉ ነበር። ነገ የተሻለ አማራጭ እንዲኖረን እነዚህን ወስደህ ማረም አለብህ። የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ አመራር ማሰሩን በተመለከተ ትእዛዙ የመጣው ከላይ ነው። ባይሰራው ኖሮ ነበር የምጠይቀው” በማለት ውሳኔ የሚወስን ሌላ ሃይል እንዳለ ፍንጭ ሰጥተዋል። አቶ ደሴ ዳልኬ ደግሞ ” በከፍተኛ አመራሩ ውስጥ ያለው መሰረታዊ ችግር ምንድነው የሚለውን ለይቶ የመፍታት ነገር ቢጠናከር” የሚል ሃሳብ ሲሰነዝሩ፣  አቶ አረከበ እቁባይ  የአቶ ደሴን ሃሳብ በመደገፍ  ” ጠንካራ ጎኑ እንዳለ ሆኖ መስተካከል ካለበት ነገር አንዱ ነገሮችን ጠቅልሎ መያዝ ላይ ነው። በአሰራራችን መሰረት ሚኒስትሩ የራሱን ስራ ፣ የክልል አመራሮችም ያራሳቸውን ስራ መስራት አለባቸው። ያንን ማስተካከል ያለብህ ይመስለኛል።” ብለዋል።
አቶ በረከት ስምኦን በበኩላቸው “ቸልተኛ መሆንህና በችግሮች ልክ ቶሎ ምላሽ አለመስጠትህ በተለይ ከራሱ ጠባቂዎችና ከቤተመንግስት ደህንነቶች ጋር እንደፈለገ እንዲጨፈርብን አድርጎናል። እዚህ ላይ  ብታስተካክል ጥሩ ነው። ሌሎችን ጉዳዮች በተመለከተ ራሱ ባለቤቱ ነው መሙላትና መጨነቅ ያለበት” ሲሉ የድጋፍ አይሉት የተቃውሞ አስተያየት ሰጥተዋል። አቶ ሃይለማርያምም በመጨረሻ የቀረበባቸውን ሂስ እንደሚያስተካክሉ ተናግረው ግምገማው አብቅቷል።   አቶ ሃይለማርያም የ ቢ ደረጃ ማግኘታቸውን ከቃለጉባኤው ግምገማ  ውጤት ያሳያል።

Monday, May 11, 2015

መንግስት ከ‹‹ሁከትና ብጥብጥ›› ጋር በተያያዘ የያዛቸው የሰማያዊ አባላት ላይ ክስ መሰረተ

May 11,2015
∙ተከሳሾች ዋስትና ተከልክለዋል
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም ራሱ በጠራው ሰልፍ ላይ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳትና በማስተባበር›› አስሯቸው የቆዩ ሰዎች ላይ ክስ መሰረተ፡፡ በፌደራል አቃቤ ህግ ከሳሽነት ክሱ የተመሰረተባቸው ሦስት የሰማያዊ አባላትና አንድ ሌላ ግለሰብ ሲሆኑ፣ ተከሳሾች ዛሬ ግንቦት 3/2007 ዓ.ም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መናገሻ ምድብ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል፡፡
በእነ ማትያስ መኩሪያ የክስ መዝገብ የተካተቱት ተከሳሾች ማቲያስ መኩሪያ፣ መሳይ ደጉሰው፣ ብሌን መስፍን እና ተዋቸው ዳምጤ ሲሆኑ፣ የክሱ ይዘትም በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32(1)(ሀ) እና 487(ሀ) እንዲሁም 490(3) የተመለከተውን በመተላለፍ መሆኑ ተገልጹዋል፡፡ 
ተከሳሾች መንግስት በጠራው ሰልፍ ላይ ህዝቡን የማነሳሳትና ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ሲናገሩ፣ ‹‹በፖሊስና በህዝብ ላይ ድንጋይ በመወርወር ረብሻና ሁከት፣ ብጥብጥ እንዲነሳና ሰልፉ እንዲታወክ በማድረጋቸው በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን›› እንደተከሰሱ ተመልክቷል፡፡
ሁሉም ተከሳሾች ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብታቸውን እንዲያስጠብቅላቸው የጠየቁ ቢሆንም፣ አቃቤ ህግ ‹‹ተከሳሾቹ የምርጫ ወቅትን በተመለከተ ቀጣይ ሰልፎች ሊደረጉ ስለሚችሉ ሰልፎች ላይ ሊሳተፉ ይችላሉ…›› በማለት ባቀረበው ‹መከራከሪያ› ዋስትና ሊከለከሉ ችለዋል፡፡ በዚህም ተከሳሾቹ 11 ቀናት ቀጠሮ ተሰጥቶባቸው ወደ ቂሊንጦና ቃሊቲ እንዲወርዱ ታዝዟል፡፡ 
በሌላ ዜና ባለፈው አርብ ክስ ተመስርቶበት የ6000 ብር ዋስትና ተጠይቆበት በዛሬው ዕለት ብሩ ተከፍሎ ከእስር እንዲለቀቅ ተደርጎ የነበረው የሰማያዊ አባል ወጣት ቴዎድሮስ አስፋው ከእስር እንደወጣ ሲቪል በለበሱ ሰዎች ታፍኖ ወደ ሶስተኛ ፖሊስ መወሰዱ ታውቋል፡፡ ወላጅ እናቱ ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ሄደው ልጃቸው እዚያ ስለመኖሩ ቢነገራቸውም ለሶስት ቀናት ያህል ግን ሊያዩት እንደማይችሉ እንደገለጹላቸው ተናግረዋል፡፡

Sunday, May 10, 2015

የሰማያዊ ፓርቲን የገንዘብ ምንጭ ለማወቅ ምርመራ ተጀመረ

May 10,2015
‹‹በፋይናንስ ግኝታችን ጥያቄ ሊነሳ አይገባም›› ሰማያዊ ፓርቲ

በኢትዮጵያ ፖለቲካ አነጋጋሪ ሆኖ ብቅ ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ለ2007 ዓ.ም. ምርጫ ይፋ ያደረገው የበጀት መጠን ‹‹ከፍተኛ መሆን››፣ የውጭ ፋይናንሰሮች እጅ አለበት የሚል ጥርጣሬ በማስነሳቱ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑ ተጠቆመ፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ለዘንድሮ ምርጫ 92 ሚሊዮን ብር በጀት እንደያዘ ካስታወቀ በኋላ፣ ከሚያነሳቸው ፖለቲካዊ አጀንዳዎች በተጨማሪ የያዘው በጀት መጠን የወቅቱ መነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ ሆኗል፡፡

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ መንግሥት ሰማያዊ ፓርቲ ለምርጫው በያዘው በጀት መጠን ላይ ጥርጣሬ አለው፡፡

‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ይህንን ገንዘብ ሊያመነጭ የሚችልበት መንገድ የለውም፡፡ ምክንያቱም በግልጽ እንደሚታወቀው ኮንሰርት አላዘጋጀም፡፡ ከባለሀብቶች የተዋጣ ገንዘብ የለም፡፡ ምርጫ ቦርድ የመደበለት ገንዘብም ይታወቃል፤›› ያሉት አቶ ሬድዋን፣ ‹‹አባላቱ ይህንን ገንዘብ ሊያዋጡ የሚችሉ ቱጃሮች አይደሉም፡፡ በቁጥርም አነስተኛ ናቸው፤›› በማለት ገንዘቡ ሕጋዊ መሠረት የለውም የሚል ትንታኔ ይሰጣሉ፡፡

አቶ ሬድዋን እንደሚሉት፣ ሰማያዊ ፓርቲ 92 ሚሊዮን ብር በጀት ይዣለሁ በማለት በይፋ ሲያውጅ የማይነጥፍ የሀብት ምንጭ  አለው ማለት ነው፡፡ ይህ የሀብት ምንጭ ደግሞ በእርግጠኝነት ሕገወጥ ነው በማለት በገንዘቡ ጤናማነት ላይ መንግሥት ያለውን ጥርጣሬ አስገንዝበዋል፡፡

በዋናነት የመንግሥት ጥርጣሬ ትኩረት የሚያደርገው ሰማያዊ ፓርቲ ይህንን ገንዘብ፣ በተለያዩ አገሮች ከሚገኙ ሕጋዊነት ከሌላቸው አካላት ፈሰስ ተደርጎ ሊሆን ይችላል የሚል ነው፡፡

አቶ ሬድዋን የአገሪቱ የባንክ ሥርዓት የዚህ ዓይነት የገንዘብ ዝውውሮችን ለመቆጣጠር ያን ያህል የዳበረ አሠራር ያለው አይደለም ይላሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ያለመፈተሽ መብት ባላቸው ሰዎች አማካይነት የሚገባ ገንዘብ ይኖራል በማለት ያክላሉ፡፡

መንግሥት እነዚህን ምልክቶች ማስተዋሉን የሚናገሩት አቶ ሬድዋን፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ምርመራ እያካሄዱ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

በተለይ ከፓርቲዎቹ ጋር በተያያዘ በሕግ ኃላፊነት የተሰጠው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ለፓርቲዎች ያከፋፈለውን በጀትና ለምርጫ የወጣውን ሒሳብ ኦዲት በሚያደርግበት ወቅት ሊታወቅ የሚችል እውነታ መሆኑን እየገለጸ ነው፡፡

ለገዥው ፓርቲ መሪዎች ያስደነቀው ግን ከተመሠረተ ሦስት ዓመታት ብቻ ያስቆጠረው ሰማያዊ ፓርቲ፣ ለዘንድሮ ምርጫ 92 ሚሊዮን ብር መያዙ ብቻ ሳይሆን፣ ይህ ገንዘብ ኢሕአዴግ ከያዘው በጀት መብለጡ ነው፡፡

የኢሕአዴግ የሕዝብና የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደስታ ተስፋው ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ሰማያዊ ፓርቲ የያዘው በጀት ኢሕአዴግ ከያዘው በጀት ጋር ሲነፃፀር እጅግ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ኢሕአዴግ በ2002 ዓ.ም. ምርጫ 23 ሚሊዮን ብር በጀት የመደበ መሆኑን፣ በ2007 ዓ.ም. ምርጫ የያዘው በጀትም ከ23 ሚሊዮን ብር እንደማይበልጥ የኢሕአዴግ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ በዚህ ሐሳብ አይስማሙም፡፡ ምክንያቱም ሰማያዊ ፓርቲ ይህንን በጀት የያዘው በግንቦት 2007 ዓ.ም. ምርጫ ከያዘው ግብ አኳያ ነው፡፡ እሳቸው እንደሚሉት፣ ፓርቲው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 500 ዕጩዎችን ለምርጫ አቅርቦ 380 መቀመጫ በማሸነፍ ከገዥው ፓርቲ ሥልጣን ለመረከብ ግብ አስቀምጧል፡፡ ነገር ግን 200 ዕጩዎች ከምርጫ ውድድር ውጪ በመሆናቸውና በአንዳንድ አካባቢዎች የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ባለመቻሉ፣ የተያዘውን በጀት ለመጠቀም አለመቻሉን አቶ ዮናታን ተናግረዋል፡፡

‹‹እየተደረገብን ባለው ተፅዕኖ የተያዘውን በጀት ለመጠቀም አልተቻለም፤›› ያሉት አቶ ዮናታን ጨምረው እንደገለጹት፣ ይህንን በጀት ፓርቲያቸው የቀረፀው ማንኛውም ባለበጀት መሥሪያ ቤት ለሚያካሂደው ሥራ የሚያስፈልገውን በጀት እንደሚያዘጋጀው ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ከዚህ አንፃር የተለያዩ ቲሸርቶችን በመሸጥ፣ ከአባላት ከሚገኝ መዋጮ፣ የፓርቲውን ዓላማ ከሚደግፉ ባለሀብቶች፣ አውሮፓና ከሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ ደጋፊዎች ይህንን ገንዘብ ማሰባሰቡን ገልጸዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 800 ሺሕ ብር ያገኘ መሆኑንም አቶ ዮናታን ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

‹‹በፋይናንስ ግኝታችን ጥያቄ ሊነሳ አይገባም፡፡ በውስጥና በውጭ ኦዲት ሒሳቡ በሚመረመርበት ወቅት በግልጽ ይታወቃል፤›› ሲሉ አቶ ዮናታን ከፓርቲያቸው ላይ የተሰነዘረው ክስ መሠረተ ቢስ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

ምንጭ ሪፖርተር

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ አዲስ ድህረ ገጽ መልቀቁን ከድርጅቱ ጽ/ቤት ለማወቅ ተችሎል

May 9,2015
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ባለፉት ወራቶች ውህደት ከፈጸመ በሆላ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተስፋ የጣሉበት ሲሆን፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ በአካባቢው መፈጠሩና ውጥረት መከሰቱ የሚታወቅ ሲሆን ብዙዎቹ የድል ሽታ መፍጠሩን ይስማሙበታል። ወያኔ በምንም ታምር በሰላማዊ መንገድ ከስልጣን እንደማይወርድ እና በስልጣኑ የመጡበትን ሁሉ መግደል ወይም ማሰር እና ማሰደድ ላይ ያተኮረው የህወሃት ድርጅትን ብቸኛው መንገድ በሁለገብ ትግል ማስወገድ ተገቢ መሆኑን አሁን ያለው ሁኔታ የሚመሰክር መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይስማሙበታል።
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ይህን ትግል ከግብ ለማድረስ የጀመረውን እንቅስቃሴ በማጠነከር ረገድ ስራውን እየሰራ ሲሆን በቅርቡ በርካታ ወጣቶችና የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ድርጅቱን መቀላቀላቸው ይታወቃል።
አዲሱ ድህረ ገጽ www.patriotg7.org ነው። እለታዊ ዜናዎችንና መረጃዎችን ዌብሳይቱን በመጎብኘት ሊያገኙ ይችላሉ።
EPPF-G7-header

www.patriotg7.org

Saturday, May 9, 2015

ወያኔ ሕዝብን አዘናግቶ በህዝብ ልጆች ላይ ከፍተኛ የሞራል ድቀት የሚያስክትል ተጨማሪ ወንጀሎችን ሊሰራ አቅዷል

May 9,2015
ወያኔ ሕዝብን አዘናግቶ በህዝብ ልጆች ላይ ከፍተኛ የሞራል ድቀት የሚያስክትል ተጨማሪ ወንጀሎችን ሊሰራ ስላቀደ በአስቸኳይ በአንድነት ተቀናጅተን ይህንን እኩይ ስርአት ልናስወግድ ይገባል::ከመቼውም ጊዜ በላይ እርስ በርስ መግባባትና መስማማት ያለብን አስቸኳይ ሰዓት ላይ ነን፡፡ምርጫውን ተከትሎ የሚወለደው ሕዝባዊ አመጽ ያስደነገጠው ወያኔ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ ዞን ዘጠኝ ጦማሪያንን እና ጋዜጠኞችን የመፍታት እቅድ አለ የሚል ወያኔያዊ ፕሮፓጋንዳ ለማዘናጊያ/ለስልጣን ማስረዘሚያ እየረጨ ይገኛል:: ወያኔ ያልገባ ነገር ቢኖር ሕዝቡ የሚያደርገው ትግል ለለውጥ እንጂ እስረኞች ሲፈቱ ተሰብስቦ ሊቀመጥ አይደለም:;እስረኞቹ ራሳቸው የታሰሩት ለሕዝቦች ነጻነት እና መብት ሲታገሉ መሆኑን ማናችንም የምናውቀው ወያኔንም ሆዱን የቆረጠው ይህ መሆኑ እሙን ነው::

መንግስት ከሕዝብ ሳይግባባ ሲቀር ሕዝብ ከሕዝብ ጋር እንዳይግባባ የማይቆፍረው ጉድጓድ የለም::በሃይማኖት በዘር በአስተሳሰብ ወዘተ እክይ ስራዎችን ተግቶ በመስራት ጥላቻን መዝራት የአምባገነኖች አንዱ ባህሪ ነው::ይህ ባህሪ በ አሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ለማንቀሳቀስ ቢፈለግም ያለው ጨቋኝ ስርአት አልተሳካለትም::ሕዝብን እያባሉ በማደናገሪያ አሉባልታ እየረጩ እያረጋጉ እያዘናጉ አፍዝዞ መግደል..ይህ ወያኔያዊ ስልት ተነቅቷል::የተነቃበት ወያኔያዊ ስልት በመሆኑ ሕዝቡ በፍጹም በነጻነቱ እና በመብቱ ላይ እንደማይደራደር በተግባር የሚያስመሰክርበት ጊዜያት ቀርበዋል::የህዝብ የትግል ውጤት በግፍ የታሰሩ ንጹሃንን ነጻ ያወጣል:: በግፍ የተሰደዱትን ወደ ሃገር ቤት ይመልሳል::ፍትህ ላጡት ብርሃን ይሆናል::የህዝብ የትግል ውጤት…..

ያለንበት ሰዓት ላወቀው ይሁን ላላወቀው በእርስ በእርስ መግባባት እና መስማማት ላይ ተመስርተን በመቻቻል በአንድነት የምንቆምበት ሰአት ነው::ለወያኔ የማደናበሪያ እና የማዘናጊያ ስልቶች ሳንታለል ለነጻነት እና ለመብት የምናደርገውን ትግል በመሃል አገር ይሁን በዳር አገር ላይ ጠንክረን ልንገፋበት ግድ የሚለን አስረአንደኛው ሰአት ላይ መድረሳችንን ልንረዳ ይገባል::

ፍትህን አጥተው የሚገላቱ የሃይማኖት አባቶች እና ምሁራን የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት ጦማርያን እና ጋዜጠኞች በጅምላ ታፍሰው ብየማጎሪያ ካምፑ የተከማቹ ወገኖቻችን ሁሉ የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ ያሉበት እቅት ላይ መሆናችንን ማወቅ ሲገባን ለኛ ነጻነት እና መብት መከበር ትግሉን ጀምረው የተሰዉ ኢትዮጵያውያንም ደም እየጮኽ ነው::ፍትህ አጥተው በየእስር ቤቱ የሚገላቱ ወገኖቻችን ቀጠሮ መርዘሙ በራሱ ከካንጋሮ ፍርድ ቤት ውሳኔ አለመሰጠቱ በራሱ ሊያሳየን የሚችለው ነገር ቢኖር ምርጫውን በጁ ካደረገ በኋላ ወያኔ አዘናግቶና ተረጋግቶ በህዝብ ልጆች ላይ ከፍተኛ የሆነ የሞራል ድቀት ሊያስከትል የሚችል ተጨማሪ ወንጀል ለመስራት ማቀዱን ስለሆነ ጠንክረን በመታገል ይህንን ስር አት ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ልናሰወግድ ይገባል::‪
#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Thursday, May 7, 2015

ገዥው ፓርቲ ኦሮሚያ ውስጥ ምርጫውን ጀምሮታል ተባለ

May 7 ,2015
ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ገዥው ፓርቲ ምርጫውን ከአሁኑ እንደጀመረው ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች ካድሬዎች መራጮችን በጋንታ፣ በሴልና በኔትወርክ እያደራጁ ‹‹ኦህዴድ/ኢህአዴግን መርጫለሁ›› በሚል እያስፈረሙና ፎርም እያስሞሉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በጋንታ፣ በሴልና በኔትወርክ ተደራጅተው ‹‹ኦህዴድን መርጠናል›› ብለው እንዲፈርሙ የተደረጉ ዜጎች ፎርሙን ከሞሉበት ቀን ጀምሮ የምርጫ ካርዳቸውን ለጋንታ፣ ሴልና ኔትወርክ መሪዎቻቸው እንደሚሰጡ ታውቋል፡፡ የጋንታ፣ የሴልና የኔትወርክ መሪዎችም ኢህአዴግን ከአሁኑ መርጠዋል ተብለው የተደራጁ ዜጎችን ስምና የምርጫ ካርድም ለኦህዴድ/ኢህአዴግ ከፍተኛ ካድሬዎች እንደሚሰጡ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡
ካድሬዎች ግንቦት 16 ቀን በፊት የምርጫ ካርዳቸውን ለጋንታ፣ ለሴልና ለኔትወርክ መሪዎች የሚሰጡትን ዜጎች ቤት ለቤት እየዞሩ እያስፈረሙ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ በጋንታ፣ ሴልና ኔትወርክ ተደራጅተው ኦህዴድ/ኢህአዴግን ከአሁኑ እንደመረጡ በፊርማቸው አረጋግጠዋል የተባሉት ዜጎች ግንቦት 16/2007 ዓ.ም በሚደረገው ምርጫ እንደማይሳተፉ የታወቀ ሲሆን አብዛኛዎቹ በግዳጅና በማስፈራሪያ እየሞሉ እንደሚገኙ ተገልጾአል፡፡
የጋንታ፣ የሴልና የኔትወርክ እንዲሁም የመራጮች ስምና ፊርማቸው እየሰፈረበት ከግንቦት 16 በፊት እንደመረጡ ተደርጎ ዜጎች እንዲሞሉት የሚደረገውና ከስር የሚታየው ቅጽ ካድሬዎች በአርሲ ዞን በቆጅ ወረዳ ቤት ለቤት ሲያስሞሉ የተገኘ ነው፡፡

Wednesday, May 6, 2015

የኢህአዴግ መሰረተ ልማት ግንባታ ለፖለቲካ ፍጆታ እንጂ ለህዝብ ጥቅም ሲውል አልታየም!!

May 6,2015

amh editorail
በማንኛውም አገር የመሰረተ ልማት ግንባታ ወሳኝ ነው። ነገር ግን የሚሰሩት ግንባታዎች ለፖለቲካዊ ጥቅምና ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ተብሎ የሚሰሩና የህብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ የማይለውጡ ከሆኑ ግን መሰረተ ልማት ብሎ ከመጥራት ይልቅ የሙስና እና የብልሹ አሰራር መሰረተ ተብሎ ቢገለፅ ይቀላል።
የአንድ አገር መሰረተ ልማት የህብረተሰቡን የኢኮኖሚ እድገት ወደ ተሻለ ደረጃ የሚያደርስ፤ በህዝቡ ውስጥ ያለው የኑሮ ሁኔታ ልዩነት የሚያጠብና ሁሉም ዜጎች እኩል ሆነው ለመኖር የሚያስችል መሆን ይኖርበታል።
ባሁኑ ግዜ በኢህአዴግ አመራር አገራችን እየተካሄደ ያለው የመሰረተ ልማት ግንባታ። የሁሉንም ከተሞች እድገት በእኩል የማሳደግ ፋላጎት ሳይሆን ለአንዳንድ ከተሞች ብቻ ልዩ ትኩረት የሚያደርግና በቂ ዝግጅት ሳይደረግበት ግብታዊ በሆነ መንገድ ፖለቲካዊ ጥቅም ለማስገኘት ብቻ ተብሎ የሚካሄድ የግንባታ ስራ በመሆኑ እስካሁን ድረስ አመርቂ የሆነ ውጤት ማምጣት አልቻለም።
በሌላ በኩል ትኩረት ሊደረግበት የሚገባው የመሰረተ ልማት ሁኔታ። የህዝቡ ብዛት ግምት ውስጥ ያስገባ እንዲሆን ማደረግ ነው፣ የሚገነባው የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ከህዝቡ ብዛት የሚመጣጠን ካልሆነ ፋይዳ ሊኖረው አይችልም ብቻ ሳይሆን የአገሪቱ ግንባታዎች በረጅም ግዜ ታይተው የሚሰሩና የሚፈጸሙ ካልሆኑ የህብረተሰቡን ፍላጎት ሟሟላትም አይችሉም። በተለይ ያገራችን ህዝብ ከ 20 እና 30 ዓመት በኋላ በእጥፍ ማደግ እንደሚችል ግምት ውስጥ በማስገባት የሚካሄድ የልማት ሁኔታ ከሌለና ከግዜው ጋር እድገት እያረጋገጠ የሚጓዝ መሰረተ ልማት መሆን ካልቻለ ችግሩ አደገኛ ነው የሚሆነው።
ከዚህ በመነሳት የኢህአዴግ ስርዓት በተለይ በከተሞቻችን ውስጥ የመኖሪያ ቤት ግንባታና የመንገድ ስራዎችን በተመለከተ ከተሰሩ በኋላ አስፈላጊውን አገልግሎት ሳይሰጡ ስለሚበላሹ የከተሞቹ ዘመናዊነት መበላሸታቸውን ሳይበቃ ያለ በቂ ጥናትና ክትትል የተሰሩትን መሰረተ ልማቶች እንደገና ለመጠገን እጅግ በርካታ ወጪ ስለሚደረግላቸው ለሌላ ግንባታ መሆን የሚገባውን ያገር ሃብት ተገቢ ባልሆነ መንገድ ሲባክን ማየት የተለመደ አሰራር ሆኗል።
ከተሞቻችን ማደግ ከሚገባቸውን እድገትና ስልጣኔ አኳያ ሲታይ ምንም እንኳን እጅግ በርካታ ወጪ የሚጠይቅ ቢሆንም በቂ ዝግጅት ተሰጥቶት በሰለጠነና ዘመናዊ በሆነ መንገድ መሰራት ሲገባቸው ለከተሞቹ ቀጣይ እድገት ግምት በማያስገባና በሚያበላሽ መንገድ እየተካሄደ በመሆኑ የመሰረተ ልማት ግንባታው ለወደፊቱ ትልቅ ጉዳት ማስከተል እንደሚችል የሚያጠራጥር አይደለም።
ለማጠቃለል የኢህአዴግ ስርዓት የሚያካሂደው የመሰረተ ልማት ግንባታ ባለሙያዎች የተደገፉ ባለመሆናቸውና። ሁሉም የግንባታ ስራዎች በቂ ሞያ በሌላቸው የስርዓቱ አገልጋዮች እየተመራ በመሆኑ አጥጋቢ ውጤት ማግኘት አልተቻለም እየታየ ያለው የግንባታ ሁኔታም ቢሆን የህዝቡና የአገሪቱን ጥቅም ለማስከበር ታስቦ ሳይሆን የስርዓቱን ፖለቲካዊ ስልጣን ለማቆየት ታስቦ እየተካሄደ ያለ መሆኑንና በህዝቡም ላይ የመጣ አንዳችም ለውጥ እንደሌለ ማወቅ ያስፈልጋል።
ዴምህት

የቁልቁለቱን ጉዞ እናስቁም፤ ውርደት ይብቃን!!!

May 6,2015
pg7-logoየህወሓት አገዛዝ ፋሽስታዊ ባህርያት እያደር መረን እያጣ፤ ነውረኛ እየሆነ መጥቷል። በአሳለፍነው ሣምንት ብቻ እንኳን አስነዋሪ ይዘት ያላቸው ሁለት ፋሽስታዊ ክስተቶችን አስተውለናል።
አንዱ በምርመራ ስም በታሳሪዎች ላይ የሚደረገው አሳፋሪ ሰቆቃ ነው። በገላቸው በሚያፌዙና በሚሳለቁ ተቃራኒ ፆታ መርማሪዎች ፊት ለሰዓታት ተመርማሪዎች ራቁታቸውን እንዲሆኑ የሚደረግበት እና እየተፌዘባቸው የሚደበደቡበት ሥርዓት መኖሩ የጉዳቱ ሰለባዎች ይፋ ሲያወጡ እፍረቱ ለመርማሪዎቹ ብቻ ሳይሆን ይህንን ጉድ ተሸክመን ለኖርነው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ነው። በተለይም ደግሞ እንዲህ ዓይነት ክብረነክ ሰቆቃ በሴቶች ላይ እየተፈፀመ መሆኑን ስንሰማ አገራዊ ውርደቱ ያሸማቅቀናል። እንዲህ ዓይነቶችን በሰው ስቃይና እፍረት የሚዝናኑ ጉዶችን ተሸክመን የምኖር መሆናችን ሁላችንን ያዋርደናል። ይህንን አስነዋሪ “የምርመራ ዘዴ” ያጋለጡት የዞን 9 ብሎገሮች፣ ጋዜጠኞችና ፓለቲከኞች ክብርና ሞገስ የሚገባቸው ጀግኖች ሲሆኑ የተዋረዱት እነሱ ሳይሆኑ እኛ ኢትዮጵያዊያን መሆናችን ሊሰማንና “ውርደት በቃ” ልንል ይገባናል።
ሁለተኛው አሳፋሪ ድርጊት ደግሞ ወገኖቻችንን በግፍ ባረደው አይሲስ በተሰኘው አሸባሪ ድርጅት ላይ የህወሓት አገዛዝ የተለሳለሰ አቋም ወስዷል ብለው ራሱ ህወሓት በጠራው ሰልፍ ላይ ተቃውሞዓቸውን ባሰሙ ወጣቶች ላይ አገዛዙ የወሰደው የኃይል እርምጃና ከዚያም ወዲህ እየተደረገ ያለው ነገር ነው። አገዛዙ ለፕሮፖጋንዳው ይጠቅመኛል ብሎ በጠራው ሰልፍ ወጥተው ተቃውሞዓቸውን የገለፁ ወጣቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተደብድበዋል፤ በጅምላ ወደ እስር ቤቶች ተግዘዋል። የአገዛዙ ካድሬዎች ወገኖቻችንን የፈጀውን አይሲስን በመቃወም ፋንታ የራሱ የህወሓትን ውል አልባ ህግ አክብረው በመንቀሳቀስ ላይ ያሉትን ሰማያዊ ፓርቲ፣ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን እና አረና ፓርቲን እየወነጀሉ መሆኑ አጅግ አሳፋሪ ነገር ነው። የአይሲስን አረመኔአዊ ድርጊት ከኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ጋር ለማገናኘት በህወሓት የደህንነት ቢሮ አማካይነት እንቅስቃሴ መጀመሩ እየተሰማ ነው። ለወጣቱ በብዛት መሰደድ በምክንያትነት የሚያቀርቡት ደላሎችን መሆኑ አላዋቂነት ሳይሆን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ቅራኔው በኢትዮጵያዊያን መካከል እርስ በርስ እንዲሆን ያለመ መሠሪነት ነው። ከዚህም አልፎ የትግራይ ወጣቶችን ነጥሎ በመሰብሰብ “ትምክህተኞች ሊበሉህ ነውና ታጥቀህ ሳይቀድሙህ ቅደም” እያሉ መቀስቀስ በመንግሥት ደረጃ የእርስ በርስ እልቂትን ከማደራጀት ተለይቶ አይታይም። የሥርዓቱ ይሉኝታ ቢስነት የደረሰበት ዝቅጠት ገላጭ ከሆኑ ነገሮች አንዱ “እስከምርጫ መጨረሻ ድረስ ልጆቻችሁን አስረን እናቆይላችሁ” እያሉ ወላጆችን እስከመጠየቅ መድፈራቸው ነው።
ከላይ በአጭሩ የተዘረዘሩት ኩነቶች የሚያረጋግጡት ህወሓት የተማከለ አመራር አጥተው መንገድ የጠፋቸው፤ ሆኖም ግን እጃቸው ውስጥ የገባው ስልጣንና ሀብት ላለማጣት ምንም ነገር ከማድረግ የማይመለሱ አውሬዎች ስብስብ መሆኑ ነው። እንዲህ ዓይነቱን የአውሬዎች ስብስብ የሚገዛው የህግም ሆነ የሥነ-ምግባር ገደብ የለም። ህወሓት እስር በርሳችንን አባልቶ አገራችንንና ሕዝቧን ወደ ማንወጣው አዘቅት ከመክተቱ በፊት ራሱ ህወሓትን ማስወገድ እና በምትኩት ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን መገንባት የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው። ይህ ካላደረግን አሁን በወህኒ ቤቶች የሚደረገው ዜጎችን ልብስን አስወልቆ የማዋረድ አስነዋሪ ተግባር ነገ በአደባባዮች የማይደረግ ስለመሆኑ ምንም ማረጋገጫ የለንም። ይህ ትውልድ ኃላፊነቱ ካልተወጣ ህግን አክብረው ከአገዛዙ የተለየ ሀሳብ እናራምዳለን የሚሉ ወገኖቻችን በሙሉ አደጋ ውስጥ ናቸው። በህወሓት መሠሪ ተግባራት ሳቢያ በክርስትናና እስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን መካከል ያለው መግባባት እንዲሻክር እየተደረገ ነው። ዜጎችን በማዋረድ የሚደሰት አገዛዝና ለመዋረድ የፈቀደ ሕዝብ እስካለ ድረስ የቁልቁለቱ ጉዞ መጨረሻ የለውም። ይህንን ማስቆም ያለብን እኛ ሁላንችንም ነን። በአደባባይ መደራጀት ሲከለከል በምስጢር መደራጀትን መልመድ የኛ ኃላፊነት ነው። የኢትዮጵያ አርበኞች ድል መታሰቢያ በዓልን ስናከብር ከቀደምቶቻችን ልንወርስ ከሚገቡን እሴቶች አንዱ ለክብራችን ዋጋ መክፈል ያለብን መሆኑን ጭምር ነው። የኢትዮጵያዊያን ክብር በወያኔ ሲዋረድ እያየን ዝምታን ከመረጥን ከዚህም የባሰ እንዲመጣ መፍቀዳችንን እንወቀው።
አርበኞች ግንቦት 7:የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የዜጎችና የአገር ውርደት ይብቃ! በተባበረ ክንድ ህወሓት ይወገድ፤ በምትኩም ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመመሥረት መሠረት እንጣል፤ ይህንን ታላቅ ኃላፊነት ለመወጣት በኅብረት እንነሳ ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!

የዜጎች ከፍተኛ ጭፍጨፋ በመተማ

May 6,2015
ሰሜን ጎንደር ዞን በመተማ ከተማ፣ በሕግ ወጥ መንገድ የተሰሩ ቤቶች ናቸው ያሏቸውን ቤቶች ለማፍረስ በሚሞክሩበት ጊዜ፣ ከነዋሪው በተነሳዉ ተቃዉሞ ምክንያት በተፈጠረው ግጭት፣ የሕወሃት ታጣቂዎች ሁለት ነዋሪዎችን ሲገድሉ፣ ሶስት ለሞት የሚያደርስ ከፈተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከአምሳ በላይ የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል።
በአምቦ፣ በባህር ዳር በመሳሰሉት ቦታዎች እንደታየው ዜጎች በሕወሃት ታጣቂዎች ጥይት እንደ ቅጠል እየረገፉ ነው። ህወሃት ከሕዝብ የሚነሱትን መሰረታዊ የፍትህ፣ የዴሞክራሲና የለዉጥ ጥያቄዎች፣ በሃያ አንደኛ ክፍል ዘመን እንዳሉ ድርጅቶ ዘመናዊና ስልጣኔ በተሞላበት መልኩ ማስተናገድ ሲገባው፣ በስድሳዎች ጊዜ እንደነበረው መግደል፣ ማረድና ፣ ዜጎችን እንደ እንስሳ መደብደቡን በመምረጥ የጫካን ኋላ ቀር ፖለቲካ እያራመደ መሆኑ በድጋሚ ዛሬ ደግሞ በመተማ ተመስክሯል።
ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት ከደርቡሽ ጋር በተደረገ ትንቅንቅ አጼ ዮሐንስን ጨመሮ በርካቶች ደማቸውን ያፈሰሱባት መተማ፣ ዛሬ ከዉጭ ወራሪዎች ሳይሆን፣ ከሕወሃቶች በተተኮሰ ጥይት የልጆቿ ደም እየተረጨባት ይገኛል።
መተማ ዛሬ ይሄንን ትመስል ነበር።
 የሚሊዮኖች ድምጽ
metema 3
metema 2
metema

Monday, May 4, 2015

Human Rights Watch Report 2015: Ethiopia

May 3,2015


Internet café in Lalibela, Amhara Region, Ethiopia. © 2010 Hemis.fr/AFP Photo

Hopes that Ethiopia’s government would ease its crackdown on dissent ahead of the May 2015 elections were dashed in 2014.

Instead the government continued to use arbitrary arrests and prosecutions to silence journalists, bloggers, protesters, and supporters of opposition political parties; police responded to peaceful protests with excessive force; and there was no indication of any government willingness to amend repressive legislation that was increasingly condemned for violating international standards, including at Ethiopia’s Universal Periodic Review at the United Nations Human Rights Council.


Freedom of Peaceful Assembly

Security forces have harassed and detained leaders and supporters of Ethiopian opposition parties. In July, leaders of the Semawayi (“Blue”) Party, the Unity for Democracy and Justice (UDJ), and the Arena Tigray Party were arrested.  At time of writing, they had not been charged but remained in detention.

The Semawayi Party’s attempts to hold protests were regularly blocked in 2014.  Its applications to hold demonstrations were denied at least three times and organizers were arrested. Over the course of the year, authorities repeatedly harassed, threatened, and detained party leaders.

In June, Andargachew Tsige, a British citizen and secretary general of the Ginbot 7 organization, a group banned for advocating armed overthrow of the government, was deported to Ethiopia from Yemen while in transit. The transfer violated international law prohibitions against sending someone to a country where they are likely to face torture or other mistreatment. Tsige had twice been sentenced to death in absentia for his involvement with Ginbot 7.  He was detained incommunicado in Ethiopia without access to family members, legal counsel, or United Kingdom consular officials for more than six weeks. He remains in detention in an unknown location.

Protests by members of some Muslim communities against perceived government interference in their religious affairs continued in 2014, albeit with less frequency. As in 2013, these protests were met by excessive force and arbitrary arrests from security forces. The trials continue of the 29 protest leaders who were arrested and charged under the Anti-Terrorism Proclamation in July 2012.

In April and May, protests erupted in towns throughout the region of Oromia against the planned expansion of Addis Ababa’s municipal boundary into Oromia. Security personnel used excessive force, including live ammunition, against protesters in several cities. At least several dozen people were confirmed dead and hundreds were arrested. Many of them remain in custody without charge.

Restrictions on human rights monitoring and on independent media make it difficult to ascertain the precise extent of casualties and arrests. Foreign journalists who attempted to reach the demonstrations were turned away or detained by security personnel. Ethnic Oromos make up approximately 45 percent of Ethiopia’s population and are often arbitrarily arrested and accused of belonging to the banned Oromo Liberation Front (OLF).

Freedom of Association

The Charities and Societies Proclamation (CSO law), enacted in 2009, has severely curtailed the ability of independent nongovernmental organizations to work on human rights. The law bars work on human rights, good governance, conflict resolution, and advocacy on the rights of women, children and people with disabilities if organizations receive more than 10 percent of their funds from foreign sources. The law was more rigorously enforced in 2014.

In March, Ethiopia was approved for membership in the Extractive Industries Transparency Initiative (EITI), which promotes transparency on oil, gas, and mining revenues, despite the requirement for candidate countries to make a commitment to meaningful participation of independent groups in public debate on natural resource management. Ethiopia’s previous application was denied in 2010 based on concerns over the CSO law.

Freedom of Expression

Media remain under a government stranglehold, with many journalists having to choose between self-censorship, harassment and arrest, or exile. In 2014, dozens of journalists and bloggers fled the country following threats. In August 2014, the owners of six private newspapers were charged following a lengthy campaign of threats and harassment against their publications. According to the Committee to Protect Journalists, Ethiopia is one of three countries in the world with the highest number of journalists in exile.

Since 2009, the Anti-Terrorism Proclamation has been used to target political opponents, stifle dissent, and silence journalists. In July, Ethiopia charged 10 bloggers and journalists known as the Zone 9 Collective under the Anti-Terrorism Proclamation after they spent over 80 days in pre-charge detention.  The charges included having links to banned opposition groups and trying to violently overthrow the government. The bloggers regularly wrote about current events in Ethiopia. Among the evidence cited was attending a digital security training course in Kenya and the use of “security in-a-box”--a publicly available training tool used by advocates and human rights defenders. Due process concerns have marred the court proceedings.

Other journalists convicted under the Anti-Terrorism Proclamation-including Eskinder Nega, Reeyot Alemu, and Woubshet Taye-remain in prison.

The government continues to block even mildly critical web pages and blogs. The majority of opposition media websites are blocked and media outlets regularly limit their criticism of government in order to be able to work in the country.

The government regularly monitors and records telephone calls, particularly international calls, among family members and friends. Such recordings are often played during interrogations in which detainees are accused of belonging to banned organizations. Mobile networks have been shut down during peaceful protests and protesters’ locations identified using information from their mobile phones. The government has monitored digital communications using highly intrusive spyware that monitors all activity on an individual’s computer, including logging of keystrokes and recording of skype calls. The government’s monopoly over all mobile and Internet services through its sole, state-owned telecom operator, Ethio Telecom, facilitates abuse of surveillance powers.

Abuses of Migrant Workers

Hundreds of thousands of Ethiopians continue to pursue economic opportunities in Saudi Arabia, Yemen, Bahrain, and other Gulf countries, risking mistreatment from human traffickers along the migration routes. In Yemen, migrants have been taken captive by traffickers in order to extort large sums of money from their family members. In late 2013 and early 2014, hundreds of thousands of migrant workers, mainly Ethiopians, were detained and deported from Saudi Arabia to Ethiopia. Saudi security forces and civilians attacked Ethiopians, prompting restrictions on migration to certain countries.

Forced Displacement

Both the government of Ethiopia and the donor community failed to adequately investigate allegations of abuses associated with Ethiopia’s “villagization program.” Under this program, 1.5 million rural people were planned to be relocated, ostensibly to improve their access to basic services. Some relocations during the program’s first year in Gambella region were accompanied by violence, including beatings, arbitrary arrests, and insufficient consultation and compensation.

A 2013 complaint to the World Bank’s Inspection Panel from Ethiopian refugees, the institution’s independent accountability mechanism, continues to be investigated. Ethiopian refugees alleged that the bank violated its own policies on indigenous people and involuntary resettlement in the manner a national program was implemented in Gambella. In July, a UK court ruled that allegations that the UK Department for International Development (DFID) did not adequately assess evidence of human rights violations in the villagization program deserved a full judicial review. The judicial review had yet to be heard at time of writing.

Ethiopia is continuing to develop sugar plantations in the Lower Omo Valley, clearing 245,000 hectares of land that is home to 200,000 indigenous people. Indigenous people continue to be displaced without appropriate consultation or compensation. Households have found their grazing land cleared to make way for state-run sugar plantations, and access to the Omo River, used for growing food, restricted. Individuals who have questioned the development plans face arrest and harassment. Local and foreign journalists have been restricted from accessing the Omo Valley to cover these issues.

LGBT Rights

Ethiopia’s criminal code punishes consensual adult same-sex relations with up to 15 years in prison. In March, Ethiopia’s lawmakers proposed legislation that would make same-sex conduct a non-pardonable offense, thereby ensuring that LGBT people convicted under the law could not be granted early leave from prison. However, in April the government dropped the proposed legislation.

Ethiopia came for Universal Periodic Review in May 2014, and they rejected all recommendations to decriminalize same-sex conduct and to take measures to combat discrimination based on sexual orientation.

Key International Actors

Ethiopia continues to enjoy unquestioned support from foreign donors and most of its regional neighbors, based on its role as host of the A frican Union (AU); its contribution to UN peacekeeping, security and aid partnerships with Western countries; and its stated progress on development indicators.

Its relations with Egypt are strained due to Ethiopia’s construction of the Grand Renaissance Dam, which will divert water from the Nile and is due to be completed in 2018. In 2014, Ethiopia negotiated between warring parties in South Sudan, and its troops maintained calm in the disputed Abyei Region. Ethiopia continues to deploy its troops inside Somalia; they were included in the AU mission as of January.

Ethiopia is one of the largest recipients of donor aid in Africa, receiving almost US$4 billion in 2014, which amounted to approximately 45 percent of its budget. Donors remain muted in their criticism of Ethiopia’s human rights record and took little meaningful action to investigate allegations of abuses. Donors, including the World Bank, have yet to take the necessary measures to ensure that their development aid does not contribute to or exacerbate human rights problems in Ethiopia.

Ethiopia rejected recommendations to amend the CSO law and the Anti-Terrorism Proclamation that several countries made during the examination of its rights record under the Universal Periodic Review in May.
SOURCE  http://www.hrw.org/world-report/2015/country-chapters/ethiopia

Sunday, May 3, 2015

በአገራችን ላይ የመልካም አስተዳደርና የህግ የበላይነት አልተረጋገጠም!!

May 2,2015
in our country amharic
በአገራችን የመልካም አስተዳደርና የህግ የበላይነት መከበር ባለመቻሉ ምክንያት ህዝባችን ከድህነት፤ ከስደትና ኋላ ቀርነት መውጣት አልቻለም ብቻ ሳይሆን እኩል የመብቱ ተጠቃሚ ሳይሆን ቀርቶ ውስን ባለስልጣናት ተንደላቅቀው የሚኖሩበት አብዛኛው ደግሞ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥሮ በላዩ ላይ በደል እየተፈፀመበት እንዲኖር ተፈርዶበታል፣
ይህ ካለፉት ገዢዎች የጀመረውና አሁንም ቢሆን በከፋ መልኩ እየቀጠለ ያለውን የመልካም አስተዳደርና የህግ የበላይነት ያለመከበር ሁኔታ በህዝባችን ላይ እያደረሰው ያለው ወደር የለሽ ችግር ባሁኑ ግዜ የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ እያስከተለ መሆኑ ይታወቃል፣
የኢትዮጵያ ህዝብ አገሩ ውስጥ እንዳይኖር፤ ተምሮ እድገት እንዳያሳይና ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቱ ተከብሮለት ነፃ ሆኖ እንዳይንቀሳቀስ፤ ነጋ ጠባ ካገሩ እየተሰደደ በሰው አገር እንዲኖርና እንዲዋረድ እያስገደደው ያለ ዋናው ምክንያት እትብቱ የተቀበረባትን ቀየውን አስጠልቶት ሳይሆን ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው መብቱ መከበር ስላልቻለና ባገሩ ውስጥ የህግ የበላይነት ተከብሮ በእኩል ተጠቃሚ ሆኖ መኖር ስላልቻለ ብቻ ነው፣
የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት በተለይ በትረ ስልጣኑ ከተቆጣጠረበት ዕለት ጀምሮ። ሁሉም የዴሞክራሲ መብቶች እንደተሻሻሉ አድርጎ ቢናገርም። በተጨባጭ መሬት ላይ እየታየ ያለው እውነታ ግን ከሚባለው በእጅጉ የተለየ ነው፣ ይህንኑ ትልቅ አርእስት እንደ መከራከርያ ተደርጎ ባለፈው ሳምንት በተቃዋሚ ድርጅቶችና በኢህአዴግ መንግስት የተካሄደውን ክርክር ሁሉም ያገሬው ህዝብ እንደተከታተለው። በተለይ በኢህአዴግ ባለስልጣኖች የተሰጠው መልስና አስተያየት እጅግ የሚያሳፍር እንደነበር ተከታትለናል፣
  • ዛሬ በሁሉም ያገራችን ከተሞች ንፁሕ የሚጠጣ ውሃ፤ የመብራት ኃይል አገልግሎት፤ በጋና ክረምት የሚያገናኝ መንገድና ሌሎች መሰረታውያን ነገሮችን ስላልተሟላለት በተከታታይ ብሶቱን እያሰማ ይገኛል፣
  • ዛሬ ባገራችን ውስጥ የኢህአዴግ ስርዓት በፈጠረው የጎሳና የሃይማኖት ልዩነት። ህዝቡ ራስ በራሱ የሚጋጭበትና የማይተማመንበት ሁኔታ ላይ ይገኛል፤
  • ዛሬ። በማንኛቸውም መስሪያ ቤቶች የሚገኙ ባለስልጣኖች። ለስርዓቱ ባላቸው ቅርበት እንጂ በብቃታቸው ተመዝነው ስለ ማይመደቡ። ተጠያቂነት፤ ግልፅነትና ፍትሃዊነት ያለው አሰራር ባለመኖሩ ምክንያት ህዝቡ አቤቱውን እያቀረበ ይገኛል፣
  • ዛሬ። በአለማችን ከሚገኙ አገሮች። ኢትዮጵያ በብልሹ አሰራራቸው ከሚታወቁ አገሮች ከመጨረሻዎቹ በ6 ተርታ ላይ ተቐምጣ። ህዛቧ ወገናዊነት በተጠናወተው ብልሹ አሰራር እየተሰቃየ ይገኛል፣ ባገራችን ውስጥ እነዚህና የመሳሰሉት ከፍተኛ ችግሮች ከመጠን በላይ ተደቅነውና ተስፋፍተው ባሉበት ባሁኑ ግዜ። በየትኛው መመዘኛ ነው ኢህእዴግ ባገራችን ውስጥ መልካም አስተዳደርና የህግ የበላይነት አረጋግጫለሁ እያለ መናገር የሚችለው?
ወደደም ጠላም ይህ ስርዓት ህዝቡን ለማደናገር ብሎ በመልካም አስተዳደርና የህግ የበላይነት በማስፈን ላይ ብዙ ርቀት እንደሄደ አስመስሎ ቢገልፅም።-
  • በግብር አከፋፈል ላይ ፍትሃዊ ያለመሆን፤
  • በበጀት አመዳደብና ቁጥጥር ስርዓት ላይ ከዜሮ በታች መሆን፤
  • እስከታች ወርዶ ከህዝቡ ጋር ተመካክረሮ ያለ መስራት፤
  • ሁሉንም ያገራችን አካባቢዎች በእኩል በማሳደግና ፍትሃዊ በሆነ የተጠቃሚነት ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ያለመሆኑ፤
  • ፈጣን ውሳኔ ያለመስጠትና በወገናዊነትና በአድልዎ የሚፈጸሙ ተግባራት እጅግ የተስፋፉ መሆናቸው እንጂ። ስርኣቱ ለፖለቲካ ፍጆታ ብሎ እንደሚቀሰቅሰው እንዳልሆነና አጠቃላይ ያገራችን ሁኔታ ከኢትዮጵያ ህዝብና ከዓለም ማሀበረሰብ የተደበቀ ነገር እንዳልሆነ ይታወቃል፣
  • ከዴምህት የተወሰደ

Friday, May 1, 2015

Detail of Rights Violation on Zone9 Bloggers and Journalists

May 1, 2015
Ethiopia Human Rights Project
It is now solid one year since the arrest of Zone9 blogger and journalists. there had been 27 court hearings, 86 days of interrogation at the notorious “Meakelawi” interrogation center before they moved to their current detention place in “Kality” and “Kilinto”. during their stay they faced many rights violation. this rights violation had also been reported for the united nations working group for arbitrary detention.
On the commemoration of their arrest the summary of the rights violation was made public for readers and followers of the case of for the last one year. attached is the summary of the rights violation.
Violation on Zone9 Bloggers


የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ሆቴ የሺሻ ማጨሻ ሆነ

May 1,2015
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ያስገነባው እና ዘመናዊ ተብሎ የሚጠራቅ ቀነኒሳ ሆቴል በሺሻ ማጨስ የተለከፉ ወጣቶች መጠራቀሚያ እና ጥራቱን ያልጠበቀ ስራ በመስራት የሚታወቅ ሆቴል ሆⶈል ። በአዲስ አበባ ከተማ ወጣት ሴቶች ከተለያዩ ጓደኞቻቸው ጋር የሚቀጣጠሩበት ዋነኛ መድረክ የሆነው ሺሻ ወይንም ሁካ ማጨሻ ስፍራዎች ሲሆኑ ፣በአሁን ሰአት ግን ይህ ሆቴል የሆቴሎች አስተዳደር ድርጅት እና የአዲስ አበባ ስራ እና ከተማ ልማት ቢሮ የሰጠውን፡ሕጝ፡ጥሶ የሺሻ ማጨሻ ሱቅ ማድረጉ በጣም አሳፋሪ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገልጸዋል ።
ቀነኒሳ በቀለ ሆቴሉን ካሰራ በሁዋላ የፊት ለፊት ገጹን የስሙን ጽሁፍ በቻይንኛ ማሰራቱ በሃገሩ ቋንቋ እና በማንነቱ የማይኮራ ነው ሲባል የተወቀሰ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ፣በሌላም በኩል ከፍተኛውን ስራ የሰሩት ቻይናዎች ሲሆኖ ጫና አሳድረውበት ነው ሲሉ ገልጸዋል ;በሌላም በኩል በአማካሪው ግፊት ነው የቻይንኛ ቋንቋ የመሰለ ፊደል ሊጠቀም የቻለው ሲሉም 

በተለይም እንደ አትሌት ቀነኒሳ አይነት የስፖርት ቤተሰብ የሆነ ሰው እና በህዝብ ዘንድ በስራው ገናናነትን ያተረፈው ድንቅ አትሌት ወጣቶችን ከእንደዚህ አይነት ድርጊት እንዲቆጠቡ መምከር ሲገባው በእራሱ ባሰራው ህንጻ ላይ ታዳጊ ወጣቶች እንዲበላሹ መጋበዙ አሳፋሪ እና ከእሱ ስራ እና ክብር የማይጠበቅ ነው ሲሉ ወርፈውታል ።
በሌላም በኩል ሆቴሉ የሚያቀርባቸው አግልግሎቶች ውስጥ ማናቸውም ከሁካ ወይንም ሺሻ ጋር የሚቀርቡ መጠጦችም፡ምግቦች ዋጋቸው የናረ ከመሆኑም በላይ መንግስት ያለቀረጥ የሚነግዱትን እንደሚያስር እና እንደሚቀጣ ሁሉ የአትሌት ቀነኒሳ ስራ ከማናቸውም ሆቴሎች ደረጃ በላይ ውድ መሆናቸው በላይም የመንግስት አስተዳደር ዝምታውን መምረጡ ተገቢ አይደለም ሲሉ አክለው ገልጸዋል ።
ሆኖም ግን በዚህ የሺሻ መሸጫ መደብር የሆነው የቀነኒሳ ሆቴል ውስጥ፡ባለ፡ስልጣናት እና የባለስልጣናት ልጆች ጊዜ ማሳለፊያቸው እና መዋያቸውንም ዘጋቢያችን ወይዘሪት ኢትዮጵያ ከስፍራው ገልጻለች ። ማለዳ ታይምስ

ሊቢያ ውስጥ አይ ኤስ በተባለው አሸባሪ ቡድን መንግስት ፈጣን ግብረ መልስ መስጠት አለበት በማለት የጠየቁ የሰራዊት አዛዦች እየታሰሩ ነው

May 1,2015
7th mekenayzid አይ ኤስ በተባለው አሸባሪ ቡድን በዜጎች ላይ የተፈፀመውን ግፍ የተሞላበት ግድያ መንግስት ፈጣን ግብረ መልስ መስጠት አለበት በማለት የጠየቁ የሰራዊት አዛዦች እየታሰሩ መሆናቸውን ምንጮች ገለፁ፣የደረሰን መረጃ እንደሚያመልክተው- የምዕራብ እዝ 7ኛ ሜካናይዝድ የሬጅመንት ምክትል አዛዥ ሻለቃ ሙሉአለም የተባለ መኮነን የኢህአዴግ ገዥው መንግስት በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ እንዲሁም በየመን በኢትዮጵያውያን ዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ላለው አስቃቂ ግፍ መንግስት ፈጣን ግብረ መልስ መስጠት አለበት ብሎ ስለጠየቀ ብቻ ፀረ ሰላም ነህ ተብሎ ባህር ዳር መኮድ በተባለ ቦታ እንደታሰረ ምንጮቻችን አስታወቁ፣
ስርዓቱ በአይ ኤስ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ፍላጎት ስለሌለው የዜጎቻችንን ደም መመለስ አለብን የሚል ጥያቄ ለሚያነሱ ሰዎች እንደ ጠላት እያዬ ወደ እስር ቤት እያስገባቸው እንደሚገኝ የገለፀው ይህ መረጃ የመከላከያ ሰራዊትም በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ላለው የሚያሳዝን ተግባር ዋነኛ ተጠያቂው በስልጣን ላይ ያለው የኢህአዴግ ስርዓት መሆኑን በተደጋጋሚ እየገለፁ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ያደረሱን መረጃ ገልጿል፣
ምንጭ-ዴምህት

የማዕከላዊ እዝ ከፍተኛ ሃላፊዎች የሰራዊት ክህደት እየጨመረ መምጣቱ ታወቀ

May 1,2015
mekononoch serawitየማዕከላዊ እዝ  ከፍተኛ ሃላፊዎች የሰራዊት ክህደት እየጨመረ መሄዱ ስላሳሰባቸው የእያንዳንዱን ወታደር ንብረት እየፈተሹ በርካታ ወታደሮችን ማሰራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣በምንጮቻችን መረጃ መሰረት የማዕከላዊ እዝ አመራሮች በየዕለቱ የሚከዳው የሰራዊት ቁጥር ስላሳሰባቸው ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓ/ም የእያንዳንዱን ወታደር የግል ንብረት ሲፈትሹ የዋሉ ሲሆን በፍተሻውም ከ180 በላይ የሚሆኑት የሲቪል መታወቂያ ካርድ ያላቸው ወታደሮች መገኘታቸውን አስረድቷል፣
ይህ የተገኘው የሲቪል መታወቂያ ካርድም ከትውልድ ቦታቸው በተለያዩ መንገዶች የተላከላቸው ሲሆን ሲቪል መስለው ስርዓቱን እየጣሉ ለመሸሽ እንዲያግዛቸው የተዘጋጀ መሆኑን የገለፀው መረጃው በዚህ የተነሳም አራት ነባር የሰራዊት አባላቶች ለ3 ወር እስራት ተወስኖባቸው በአዲ ኮኮብ እስር ቤት ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል፣
ምንጭ -ዴምህት