Sunday, May 3, 2015

በአገራችን ላይ የመልካም አስተዳደርና የህግ የበላይነት አልተረጋገጠም!!

May 2,2015
in our country amharic
በአገራችን የመልካም አስተዳደርና የህግ የበላይነት መከበር ባለመቻሉ ምክንያት ህዝባችን ከድህነት፤ ከስደትና ኋላ ቀርነት መውጣት አልቻለም ብቻ ሳይሆን እኩል የመብቱ ተጠቃሚ ሳይሆን ቀርቶ ውስን ባለስልጣናት ተንደላቅቀው የሚኖሩበት አብዛኛው ደግሞ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥሮ በላዩ ላይ በደል እየተፈፀመበት እንዲኖር ተፈርዶበታል፣
ይህ ካለፉት ገዢዎች የጀመረውና አሁንም ቢሆን በከፋ መልኩ እየቀጠለ ያለውን የመልካም አስተዳደርና የህግ የበላይነት ያለመከበር ሁኔታ በህዝባችን ላይ እያደረሰው ያለው ወደር የለሽ ችግር ባሁኑ ግዜ የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ እያስከተለ መሆኑ ይታወቃል፣
የኢትዮጵያ ህዝብ አገሩ ውስጥ እንዳይኖር፤ ተምሮ እድገት እንዳያሳይና ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቱ ተከብሮለት ነፃ ሆኖ እንዳይንቀሳቀስ፤ ነጋ ጠባ ካገሩ እየተሰደደ በሰው አገር እንዲኖርና እንዲዋረድ እያስገደደው ያለ ዋናው ምክንያት እትብቱ የተቀበረባትን ቀየውን አስጠልቶት ሳይሆን ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው መብቱ መከበር ስላልቻለና ባገሩ ውስጥ የህግ የበላይነት ተከብሮ በእኩል ተጠቃሚ ሆኖ መኖር ስላልቻለ ብቻ ነው፣
የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት በተለይ በትረ ስልጣኑ ከተቆጣጠረበት ዕለት ጀምሮ። ሁሉም የዴሞክራሲ መብቶች እንደተሻሻሉ አድርጎ ቢናገርም። በተጨባጭ መሬት ላይ እየታየ ያለው እውነታ ግን ከሚባለው በእጅጉ የተለየ ነው፣ ይህንኑ ትልቅ አርእስት እንደ መከራከርያ ተደርጎ ባለፈው ሳምንት በተቃዋሚ ድርጅቶችና በኢህአዴግ መንግስት የተካሄደውን ክርክር ሁሉም ያገሬው ህዝብ እንደተከታተለው። በተለይ በኢህአዴግ ባለስልጣኖች የተሰጠው መልስና አስተያየት እጅግ የሚያሳፍር እንደነበር ተከታትለናል፣
  • ዛሬ በሁሉም ያገራችን ከተሞች ንፁሕ የሚጠጣ ውሃ፤ የመብራት ኃይል አገልግሎት፤ በጋና ክረምት የሚያገናኝ መንገድና ሌሎች መሰረታውያን ነገሮችን ስላልተሟላለት በተከታታይ ብሶቱን እያሰማ ይገኛል፣
  • ዛሬ ባገራችን ውስጥ የኢህአዴግ ስርዓት በፈጠረው የጎሳና የሃይማኖት ልዩነት። ህዝቡ ራስ በራሱ የሚጋጭበትና የማይተማመንበት ሁኔታ ላይ ይገኛል፤
  • ዛሬ። በማንኛቸውም መስሪያ ቤቶች የሚገኙ ባለስልጣኖች። ለስርዓቱ ባላቸው ቅርበት እንጂ በብቃታቸው ተመዝነው ስለ ማይመደቡ። ተጠያቂነት፤ ግልፅነትና ፍትሃዊነት ያለው አሰራር ባለመኖሩ ምክንያት ህዝቡ አቤቱውን እያቀረበ ይገኛል፣
  • ዛሬ። በአለማችን ከሚገኙ አገሮች። ኢትዮጵያ በብልሹ አሰራራቸው ከሚታወቁ አገሮች ከመጨረሻዎቹ በ6 ተርታ ላይ ተቐምጣ። ህዛቧ ወገናዊነት በተጠናወተው ብልሹ አሰራር እየተሰቃየ ይገኛል፣ ባገራችን ውስጥ እነዚህና የመሳሰሉት ከፍተኛ ችግሮች ከመጠን በላይ ተደቅነውና ተስፋፍተው ባሉበት ባሁኑ ግዜ። በየትኛው መመዘኛ ነው ኢህእዴግ ባገራችን ውስጥ መልካም አስተዳደርና የህግ የበላይነት አረጋግጫለሁ እያለ መናገር የሚችለው?
ወደደም ጠላም ይህ ስርዓት ህዝቡን ለማደናገር ብሎ በመልካም አስተዳደርና የህግ የበላይነት በማስፈን ላይ ብዙ ርቀት እንደሄደ አስመስሎ ቢገልፅም።-
  • በግብር አከፋፈል ላይ ፍትሃዊ ያለመሆን፤
  • በበጀት አመዳደብና ቁጥጥር ስርዓት ላይ ከዜሮ በታች መሆን፤
  • እስከታች ወርዶ ከህዝቡ ጋር ተመካክረሮ ያለ መስራት፤
  • ሁሉንም ያገራችን አካባቢዎች በእኩል በማሳደግና ፍትሃዊ በሆነ የተጠቃሚነት ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ያለመሆኑ፤
  • ፈጣን ውሳኔ ያለመስጠትና በወገናዊነትና በአድልዎ የሚፈጸሙ ተግባራት እጅግ የተስፋፉ መሆናቸው እንጂ። ስርኣቱ ለፖለቲካ ፍጆታ ብሎ እንደሚቀሰቅሰው እንዳልሆነና አጠቃላይ ያገራችን ሁኔታ ከኢትዮጵያ ህዝብና ከዓለም ማሀበረሰብ የተደበቀ ነገር እንዳልሆነ ይታወቃል፣
  • ከዴምህት የተወሰደ

No comments: