Sunday, May 10, 2015

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ አዲስ ድህረ ገጽ መልቀቁን ከድርጅቱ ጽ/ቤት ለማወቅ ተችሎል

May 9,2015
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ባለፉት ወራቶች ውህደት ከፈጸመ በሆላ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተስፋ የጣሉበት ሲሆን፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ በአካባቢው መፈጠሩና ውጥረት መከሰቱ የሚታወቅ ሲሆን ብዙዎቹ የድል ሽታ መፍጠሩን ይስማሙበታል። ወያኔ በምንም ታምር በሰላማዊ መንገድ ከስልጣን እንደማይወርድ እና በስልጣኑ የመጡበትን ሁሉ መግደል ወይም ማሰር እና ማሰደድ ላይ ያተኮረው የህወሃት ድርጅትን ብቸኛው መንገድ በሁለገብ ትግል ማስወገድ ተገቢ መሆኑን አሁን ያለው ሁኔታ የሚመሰክር መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይስማሙበታል።
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ይህን ትግል ከግብ ለማድረስ የጀመረውን እንቅስቃሴ በማጠነከር ረገድ ስራውን እየሰራ ሲሆን በቅርቡ በርካታ ወጣቶችና የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ድርጅቱን መቀላቀላቸው ይታወቃል።
አዲሱ ድህረ ገጽ www.patriotg7.org ነው። እለታዊ ዜናዎችንና መረጃዎችን ዌብሳይቱን በመጎብኘት ሊያገኙ ይችላሉ።
EPPF-G7-header

www.patriotg7.org

No comments: