Sunday, November 24, 2013

“የኢትዮጵያ ህዝብ ለውጥ ፈልጓል፤ ግን ለውጡን የሚሸከምለት ፓርቲ ይፈልጋል”

“የኢትዮጵያ ህዝብ ለውጥ ፈልጓል፤  ግን ለውጡን የሚሸከምለት ፓርቲ ይፈልጋል”November 24/2013

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በቅርቡ ከአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ጋር ውህደት፣ ከሌሎች 10 ፓርቲዎች ጋር ቅንጅት ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ፓርቲው ከረጅም አመታት በኋላ የፕሬዚዳንት ለውጥም አድርጓል፡፡

 ከአዲሱ ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሃሪ ጋር ፓርቲው ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር እየፈጠረ ስላለው ውህደት እና ቅንጅት እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ፤ በፓርቲው ጽ/ቤት ተገኝቶ አነጋግሯቸዋል፡፡
ከ“መድረክ” ጋር ያለው ጥያቄ “አንድነት” ሊፈታው የሚገባው ነው ፓርቲያችን ግራ የተጋባ አይደለም መኢአድ በሀገሪቱ ካሉ ፓርቲዎች ጠንካራው ነው ህዝቡ እውነተኛውንና ውሸታሙን መለየት አለበት::
ከ“አንድነት” ፓርቲ ጋር ውህደት ለመፈፀም የጀመራችሁት ውይይት ምን ላይ ደረሰ? ውህደቱንስ በዚህን ወቅት መፈፀሙ ለምን አስፈለገ?
ህዝባችንን ካለበት ችግርና የሰብአዊ መብት ጥሰት ነፃ ለማውጣት የጋራ አላማ ያላቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች በአንድ ላይ መስራት ወሣኝነት አለው ብለን እናምናለን፡፡ ተለያይቶ ድምጽ ከመሻማት ይልቅ አንድ ላይ ሆኖ ሃብትንም ሆነ ሌላ ሌላውን አቀናጅቶ መንቀሳቀስ ጠቃሚ ነው፡፡ በህዝቡም ላይ በራስ መተማመንን ፈጥሮ ሃይል ያለው “ሊመራኝ የሚችል ፓርቲ አለኝ” ብሎ እንዲያምን አንድ መሆን ወሳኝ ነው ብለን እናምናለን፡፡ እኔ አሁን ባለው ደረጃ ማለት የምችለው፣ አንድነትና መኢአድ ለመዋሃድ ድርድር እያደረጉ ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ ግን መግለጫ ለመስጠት ያስቸግረኛል፡፡ ምክንያቱም ሂደቱ በራሱ ኮሚቴ የሚመራ ነው፡፡ ኮሚቴው ማንም ሰው በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ መስጠት አይችልም የሚል ፕሮቶኮል ፈርሟል፡፡ የየፓርቲዎቹ ባለስልጣናትም ሆኑ ተደራዳሪዎች መግለጫ መስጠት አይችሉም፡፡

 ከአንድነት ጋር ውይይት ጀምረናል ብላችኋል፣ አንድነት ደግሞ የመድረክ ግንባር አባል ነው፣ እናንተ ደግሞ መድረክን እንደማትፈልጉት በተደጋጋሚ ገልፃችኋል፡፡ ይሄ እንዴት ሊሆን ይችላል?

መኢአድ በኢትዮጵያ አንድነት ጥላ ስር ለመሄድ ከማይፈልጉ ፓርቲዎች ጋር በጋራ ለመንቀሳቀስ ይቸገራል፡፡ የመኢአድ አወቃቀሩም ሆነ አላማው ሁሉም ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ጥላ ስር መንቀሳቀስ አለባቸው የሚል ነው፡፡ በጐሣም ተደራጅተው በኢትዮጵያ ጥላ ስር ሆነን “አንዲት ሉአላዊት ኢትዮጵያ” በሚለው ስር አብረን እንሄዳለን ካሉ አብሮ ለመስራት ችግር የለውም፡፡

 ስለዚህ አንድነት በመድረክ ስር ሆኖ እንዴት ይሆናል የሚለው የራሱ የአንድነት ጉዳይ ነው፤ የመኢአድ ጉዳይ አይደለም፡፡ መኢአድ እና አንድነት እየተደራደሩ ነው፤ ሁለቱም ተመሳሳይ ፕሮግራም፣ አላማ፣ ደንብ ያላቸው ፓርቲዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ከመድረክ ጋር ያለውን ጥያቄ አንድነት ሊፈታው የሚገባው ጥያቄ ነው እንጂ የመኢአድ አይደለም፡፡ ይሄ የድርድሩም አካል ነው፡፡
ውህደቱን ስትፈጽሙ አመራሩስ እንዴት ነው የሚደራጀው?

እንግዲህ እንደነገርኩህ በዚህ ላይ መግለጫ ለመስጠት ያስቸግረኛል፡፡ ተደራዳሪዎች ስላሉ ይሄ ነው ብሎ ለማለት ፕሮቶኮሉ ያስረኛል፤ ነገር ግን ውህደት ከተካሄደ ውህደት የሚፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ ይፈፀማሉ ማለት ነው፡፡ ለዚህ ካለአመራሩ ይሄ ይሆናል ማለት አልችልም፡፡
መኢአድ ከሌሎች ፓርቲዎች የሚለየው በምንድነው?

ፓርቲያችን ተመሳሳይ ደንብ እና አላማ ካላቸው ፓርቲዎች የሚለይበት አንደኛ፣ ህብረ ብሔራዊ መሆኑ ነው፡፡ የመኢአድ እምነት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ፣ ጥላ ስር ሆኖ የእያንዳንዱ ዜጋ መብት ሲከበር፣ የሁሉም ዜጋ መብት ይከበራል ብሎ ያምናል እንጂ የአንድ ጐሣ መብት ሲከበር የጐሣው አባላት መብት ይከበራል ብሎ አያምንም። አሁን ለምሣሌ ገዢው ፓርቲ ውስጥ ያለው የብአዴን መብት ሲከበር፣ የእያንዳንዱ አማራ መብት ተከበረ ማለት አይደለም፡፡ የኦህዴድም በተመሳሳይ፤ ሌላው መኢአድ የሚመራው በሊበራል ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ነው፤ ይሄ ከሌላው የሚለየን ይመስለኛል። ሌላው የምንለይበት ፓርቲያችን ግዙፍ የሆነ አደረጃጀት ያለው ነው፡፡ በመላው ሃገሪቱ በሚገኘው እያንዳንዱ ቀበሌ መኢአድ አለ፡፡
በአራቱም ማዕዘናት ቢኬድ መኢአድ የሌለበት ቀበሌ የለም፡፡ እንዲሁም ፓርቲው የእያንዳንዱ ብሔር ጥንቅር ውጤት ነው፡፡
ምናልባት የብሔር ተዋጽኦው ሲነሣ እርስዎ ከሚሉት በተቃራኒ የአማራው ሚና የሚጐላበት እንዲያም ሲል አመራሩ እና ማዕከላዊ ኮሚቴው ለሰሜን ሸዋ አካባቢ ተወላጆች ብቻ የተሰጠ ነው የሚል ወቀሳ ይቀርብበታል…

እዚህ ላይ አሁን የመኢአድን አመራር ጥንቅር ያየህ እንደሆነ ከአማራው፣ ከጐፋው፣ ከወላይታው ያለበት ነው፡፡ ለምሣሌ የፓርቲውን ምክትል ተቀዳሚ ሊቀመንበር ብንወስድ ከጐፋ ነው፣ የመኢአድን የስራ አስፈፃሚ ብትወስድ ኦሮሞች አሉ፤ ለምሣሌ ብሩ ደሲሣ ከአሶሳ አለ፣ ገለቱ ኤጀርሣም አለ፡፡ ስለዚህ ይሄ የጠላት ወሬ ነው። መኢአድን ለማዳከም የሚነዛ አሉባልታ ነው። አማራው ከሌላው ብሔር የበለጠ በዚህ ፓርቲ ውስጥ ተሳትፎ የለውም፡፡ ለምሣሌ የአባላት ጥንቅርን የወሰድን እንደሆን በሰሜን ካለው አባል የበለጠ በደቡብ ነው ያለው፡፡ ከ39 በመቶ በላይ በደቡብ አካባቢ ያሉ ናቸው፡፡ ከሰሜን ሸዋ የመጡ ናቸው የሚባለው የሰሜን ሸዋ ህዝብ ወይም በዚያ የሚገኝ የአማራ ተወላጅ እንዳጋጣሚ ሆኖ አማራው ይገደል በነበረ ጊዜ ፕ/ር አስራት ፓርቲውን ይመሩ ነበር፡፡ ይህ ማለት ግን አመራሩ በጠቅላላ ከሰሜን ሸዋ ነበረ ለማለት አይቻልም። እሣቸው እንደ ፕሬዚዳንት ከሰሜን ሸዋ ይሁኑ እንጂ ከተለያዩ የአማራ ክፍሎች የተውጣጣ የስራ አስፈፃሚ መዋቅር ነበር፡፡ ፕ/ር አስራት፤ የመላው አማራ ህዝብ ድርጅትን ሲያቋቁሙ የአማራው ወይም የአንድ ብሔር ፓርቲ አድርገው ለማቋቋም አልነበረም ፍላጐታቸው፤ ነገር ግን ይገደልና ይሰደድ የነበረውን አማራ ከጥቃቱ ለመከላከል ያህል ያቋቋሙት ነው፡፡ በወቅቱ ለጊዜው አማራው ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እንከላከልና ኋላ ላይ ህብረ ብሔራዊ ሆኖ ሁሉንም ብሔሮች አሣትፎ ይቀጥል የሚል መርህ ነበራቸው፡፡ በዚህ መርህ አሁን ካለበት ደረጃ ደርሷል፡፡ አማራው በዚህ ውስጥ በምንም ሁኔታ የበላይነት የለውም፤ ይሄ የጠላት ወሬ ነው፡፡

 ከዚህ ቀደም ከመድረክ ጋር አብረን አንሰራም ብላችሁ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ 10 ፓርቲዎች ያሉበት ቅንጅት በመኢአድ ጉልህ ሚና እየተፈጠረ ነው ያለው፡፡ ከዚህ ፓርቲዎች አብዛኞቹ የጐሳ ፓርቲዎች ናቸው፡፡ ከመድረክ ጋር አብሮ አያስጉዘንም ያላችሁበት አጀንዳን ወደ ጐን ትታችሁ አሁን እንዴት ከነዚህ ፓርቲዎች ጋር ለመቀናጀት መረጣችሁ?

ትክክል ነው እነዚህ ድርጅቶች የጐሳ ናቸው። ኢህአዴግ ኢትዮጵያን በጐሳ ሲሸነሽን እነዚህ ፓርቲዎች በጐሳቸው… ተደራጅተው ነው፤ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ፓርቲዎቹ የጐሣ ቢሆኑም በኢትዮጵያ ጥላ ስር ሆነን እንታገላለን ያሉ ናቸው። ስለዚህ ፓርቲዎቹ በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር መሆንን የሚሹ ናቸው፡፡ የጐሣ/ብሔር/ ፖለቲካ እንደማያዋጣ አምናለሁ፤ በኢትዮጵያ ጥላ ስር ሆነን ከመኢአድ ጋር እንታገላለን ስላሉ ነው የተቀበልነው፡፡ እንግዲህ የነበሩት 33 ፓርቲዎች ናቸው፡፡ ከ33ቱ አብዛኞቹ በጐሣችን ብቻ ነው የምንታገለው ስላሉ አማራጫቸውን ይዘው ሄደዋል፡፡ በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር ሆነን እንታገላለን ያሉት መኢአድ እንዲያታግላቸው ወደዚህ መጥተዋል፡፡ እዚህ ላይ ግልጽ መሆን ያለበት ከመጡት ውስጥ 70 በመቶ የሚሆኑት የብሔር /ጐሣ/ ድርጅቶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ህብረ ብሔራዊ ናቸው፡፡

 ከመድረክ ስብስብ ጋር ያላችሁ መሠረታዊ ቅራኔ ምንድን ነው? ከስብስቡ ውስጥ በኢትዮጵያዊነት አያምኑም ብላችሁ የምትጠቅሷቸው ፓርቲዎች አሉ እንዴ?

በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር ካለማመን ባሻገርም በአንዳንድ ፖሊሲያችንም እኮ እንለያያለን፡፡ ለምሣሌ በመሬት ጉዳይ፤ መኢአድ መሬት የህዝብ ነው፤ መንግስት ሊያዝበት አይችልም ብሎ ነው የሚያምነው፡፡ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ጥሪት ሊኖረው ይገባል ብሎ ያምናል፡፡ ዜጐች መሬት ተከራይተው ሊኖሩ አይገባም፤ ይሄ የመኢአድ ፖሊሲ ነው፡፡ ነገር ግን የሌሎቹ የመድረክ አባላት ፕሮግራም በዚህ አያምንም፤ የኢህአዴግን ነው ይዘው የሚሄዱት፤ በነገራችን ላይ አንዳንዶቹ ኢህአዴግ ዲሞክራሲያዊ ስላልሆነ ነው እንጂ በፖሊሲ ደረጃ አንለይም ባይ ናቸው፡፡
መድረክ ውስጥ እንደዚያ የሚሉ ድርጅቶች አሉ?

አዎ! በሚገባ

 የአስሩን ፓርቲዎች ፖሊሲና ፕሮግራም ካስቀመጡልን ነጥቦች አንፃር በሚገባ መርምራችኋል ማለት ነው?

መቶ በመቶ በሚገባ አጥርተን መርምረናል፣ ፕሮግራማቸውን አንብበን እና ተናበን ነው ይሄን ያደረግነው፡፡
በ1997 ስለተፈጠረው ቅንጅት አመሰራረትና ውድቀት ብዙ ተብሏል፡፡ የአሁኑን ቅንጅት ከፈረሰው ቅንጅት ምንድን ነው የሚለየው?
ቅንጅት ስንል ያው ቅንጅት ነው፡፡ አይለያይም። እያንዳንዱ ፓርቲ የራሱን ህልውና ጠብቆ ነገር ግን የሚመጣው ችግርና አደጋ በአንድ ላይ እንታገላለን ብሎ የሚያምን ነው፡፡ ስለዚህ አንድ ላይ ተጨፍልቆ አንድ እንደመሆን አይታሰብም፡፡ በ1997ም እያንዳንዱ ፓርቲ በዚህ አይነት ሁኔታ ራሱን የቻለ ነበር፡፡

 ግን በአንድ ፕሮግራምና በአንድ የመወዳደሪያ ምልክት ነበር ለምርጫው የቀረበው…

ይሄም ልዩነት አይኖረውም፤ እንደዚያው ነው። ነገር ግን የአሁኑ በየክልሉ ያሉት ፓርቲዎች ቢሮ ካላቸው እንደ ግንኙነት መድረክነት ያገለግላል፤ በየክልሉ በቀላሉ ተደራሽ መሆን ይቻላል፡፡ ከዚያ በተረፈ ከ97 ዓ.ም ቅንጅት ልዩነት የለውም፡፡

 ወደ አንድነት ድርድሩ እንመለስና የ97 ቅንጅት ሲፈርስ መኢአድ ህልውናውን ጠብቆ ሲጓዝ “አንድነት” ደግሞ የመኢአድ አባላት የነበሩትን ጨምሮ በቅንጅቱ መፍረስ ቁጭት ባደረባቸው ፖለቲከኞች የተቋቋመ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ያን ጊዜ በአንድነት መጓዝ ያልቻላችሁ አካላት ዛሬ ምን ታይቷችሁ ነው አንድ ካልሆንን እያላችሁ ያለው?

መቼም አንድ ላይ ስትሠራ ትጋጫለህ ትኮራረፋለህ፣ የሃሣብ ልዩነት ይፈጠራል። እያንዳንዱ አመራር ልዩነት ይኖረዋል፡፡ ይሄ እንግዲህ ያለ ነው፡፡ ችግራችን ምንድነው ልዩነት ሲመጣ የግለሰቦች ፀብ ነው ነጥሮ የወጣው፤ ነገር ግን ይሄ መሆን የለበትም፡፡ ግለሰቡን ሣይሆን ከተቃወምንም ሃሳቡን ነው መቃወም ያለብን። ኢትዮጵያውያን የሚጐደለን ይሄ ይመስለኛል። ስለዚህ እንዳልከው አንድነትን የመሠረቱት ብዙዎቹ ሰዎች ከዚህ አኩርፈው የሄዱ ናቸው። ያኔ በተለያዩ ምክንያቶች ሄደዋል፡፡ አሁን ግን ከስህተቶቻችን ተምረን አብረን ጠንክረንና ተባብረን እንሠራለን። አንድ ጊዜ ተጣልተናልና መልሰን አብረን መስራት አንችልም የሚል እምነት አይኖረንም፡፡ እየተጋጨንም ዞረን ደግሞ ስህተታችንን አምነንና ተማምነን መስራት ምንም ማለት አይደለም፡፡ ለወደፊትም አለመግባባቶች ቢኖሩ በዚህ መልኩ እየተማመኑና እየተወያዩ መሄዱ ይቀጥላል የሚል እምነት ነው ያለኝ እና ከዚህ አንፃር ቢታይ መልካም ነው፡፡

 በየጊዜው ፓርቲዎች መድረክ፣ ትብብር፣ ህብረት፣ ቅንጅት እያሉ በጋራ እየተሰባሰቡ ሲወድቁ ሲነሱ የኢትዮጵያ ህዝብ ታዝቧል፡፡ መኢአድም የዚህ ሂደት አንዱ አካል ነው፡፡ ለወደፊትስ ፓርቲያችሁ በዚህ ሁኔታ እስከየት ድረስ ነው ሊጓዝ የሚችለው?

እንግዲህ ባለፉት 22 አመታት የፓርቲዎች ስብስብ አንድ ሲሆን ሲለው ደግሞ ሲፈርስ ኖሯል፡፡ እንደ እኔ አመለካከት ይሄ የሆነው ሁሉም ነገር በግለሰቦች ፍላጐት ላይ የተመሠረተ ስለነበረ ነው፡፡ ይሄ ኢትዮጵያንም ሆነ ዜጐቿን የጐዳ ትልቁ በደል ነው፡፡ አንዳንዱ የፓርቲ አመራር ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ቆሜያለሁ ካለ፣ ራሱን ለዚያ አላማ መሸጥ አለበት፡፡ ግቡ ወይም የሩቅ አላማው ኢትዮጵያውያንን ነፃ ማውጣት ወይም በኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ሠፍኖ ማየት መሆን አለበት። ግን በዚህች ሀገር እስካሁን ሲደረግ የቆየው እኔ ሊቀመንበር ካልሆንኩ፣ የኔ ፓርቲ የበላይ ካልሆነ ሲባል ነው፡፡ ከዚህ አንፃር አሁንም ቢሆን መኢአድ ሊያደርግ የሚችለው የጋራ ትግል አስፈላጊነትን ያምናል፤ ስለዚህ እስከቻለው ድረስ ከአላማው ጋር ከሚስማሙት ጋር አብሮ ይሠራል፡፡ ይህ መሆኑ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ አንደኛ ድምጽ አይሻሙም፤ በሁለተኛ ደረጃ በህዝቡ ላይ በራስ የመተማመን ስሜትን መፍጠር ይቻላል። አለኝታ የሚሆን ፓርቲ አለኝ ብሎ እንዲያምን ይገደዳል፡፡ ደካማና የተነጣጠለ ፓርቲ ሆነው ካያቸው ግን ህዝቡ እምነት ሊጥልባቸው ይቸገራል እና መኢአድ አሁንም| ተመሳሳይ ፕሮግራም ካላቸው ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስራት ቁርጠኛ ነው፤ ግን ይሄ የሚሆነው በቅንነት፣ በእውነተኛነት ኢትዮጵያን እያሰበ ከሚመጣ አካል ጋር ነው፡፡ ሸር ይዞ ከሚመጣ ጋር ግን ለመስራት ይቸገራል፡፡

 መኢአድ ራሱ አንዴ ሲቀናጅ፣ ሲዋሃድ፣ ሲተባበር ሲያሻው ደግሞ ቅንጅቱና ውህደቱን ሲያፈርስ የኖረ ፓርቲ ነው፤ አሁንም በዚህ አዙሪት ውስጥ መሆኑን ያዩ ወገኖች ፓርቲው ግራ የተጋባ ነው ሲሉም ይደመጣል…

ፓርቲያችን ግራ የተጋባ አይደለም፡፡ ግልጽ አላማ ግልጽ የሆነ ፕሮግራምና ደንብ ያለው ፓርቲ ነው። ፓርቲው ህብረ ብሔራዊ፣ ብዙ አባላትና ደጋፊዎች በውጭም በሀገር ውስጥም ያለው በመልካም አመራር የሚመራ ፓርቲ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን አምነው ከሚመጡ ፓርቲዎች ጋር ለመስራት መኢአድ ዝግጁ ነው፤ ነገር ግን የሚመጡትን ፓርቲዎች ለመምራት የሚሞክር ሳይሆን አብሮ የሚሰራ ነው፡፡

 በየክልሉ ያሉ ቢሮዎቻችሁ እየተዘጉባችሁ እንደሆነ ስትገልፁ ከርማችኋል፡፡ ከነዚህ ክልላዊ እና ጐሣዊ ፓርቲዎች ጋር ለመቀናጀት የወሰናችሁበት ሚስጥር ምናልባት ዳግም ለመጠናከር አስባችሁ ይሆን?

ይሄም ዝም ብሎ ግምታዊ አስተያየት ነው እንጂ ፓርቲው አሁን በየትም ቦታ ብትሄድ ቢሮ አለው ወይም መዋቅር አለው፡፡ እንደተባለው በተለያዩ ጫናዎች ምክንያት በተለይ የወረዳዎቹ ቢሮዎች ተዘግተው ነበር፡፡ ይሄ ደግሞ መኢአድን ብቻ ሣይሆን ሌሎችንም ጐድቷቸዋል፡፡ ስለዚህ አሁን መኢአድ በሃገሪቱ ካሉ ፓርቲዎች ጠንካራው ነው ብል ስህተት አይደለም። በሀገር ውስጥም በውጭም ያሉ ደጋፊዎቻችን ለፓርቲው መጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው። እዚህ ያለው አመራርም የተዘጉ ቢሮዎችን ለማስከፈት ጥረት እያደረገ ነው። እስከ 2007 ድረስ ሙሉ ለሙሉ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ቢሮ ይኖረናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ይህን ካልኹ፣ አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ፤ “አንድ ላይ ካልተባበራችሁ፣ ካልሠራችሁ ለትግሉ አስቸጋሪ ነው” በሚል ህብረት እንድንፈጥር እየጠየቀ ነው፡፡ ስለዚህ መኢአድ፤ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወደ አንድ መጥቶ፣ ጠንካራ ፖለቲካ ፓርቲ ተፈጥሮ፣ መወዳደር አለባቸው እንጂ መቶ ደካማ ፓርቲዎች ዝም ብለው መጮህ የለባቸውም የሚል እምነት አለው፡፡ ከዚህ አንፃር ነው እንጂ እኛ ድክመት ኖሮብን በእነሱ ለመሸፈን አይደለም፡፡ እነሱ ብዙም ይዘው የሚመጡት ነገር የለም፡፡

 መኢአድ ከሌላው የተሻለ ሰፊ ህዝባዊ መሠረት ካለውና አደረጃጀቱም ጠንካራ ከሆነ በምርጫ ወቅት ለምን ተፎካካሪ ሊሆን አልቻለም?
ፓርቲው እየታገለ ያለው እሱ ብቻ የስልጣን ባለቤት እንዲሆን አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን ባለቤት እንዲሆን ነው፡፡ እንደተባለው ፓርቲው ጠንካራ መሠረት ያለው ቢሆንም ከገዢው ፓርቲ የሚደርስበት ጫናም በዚያው ልክ የሰፋ ነው። አባላቱ ንብረታቸውን ይነጠቃሉ፣ ይታሰራሉ፣ ይደበደባሉ፤ ሰዎች የፓርቲው አባል ስለሆኑ ብቻ የተለየ ጥቃት ይደርስባቸዋል፡፡ እንደነዚህ አይነት ተጽእኖዎች ደግሞ ሊያራምዱ አይችሉም፡፡ በሌላ መንገድ ገዥው ፓርቲ የራሱን የደህንነት አባላት እና ካድሬዎች በየፓርቲዎቹ ውስጥ ሰግስጐ ያስገባል፡፡ በዚህም በፓርቲ ውስጥ መናወጥ ይፈጥርና የፓርቲውን አመራር ያዳክማል፡፡ ይሄ በማዕከል ብቻ ሳይሆን በዞንና በወረዳም ጭምር የሚደረግ ነው፡፡ እንደነዚህ አይነት ተጽእኖዎች ናቸው ከፍተኛ ችግር የፈጠሩት፡፡ ህዝቡም መወጣት ያለበትን ሃላፊነት መወጣት አለበት፡፡ እውነተኛውንና ውሸታሙን መለየት መቻል አለበት፤ ዳር ሆኖ መመልከቱ አይጠቅምም፡፡

 ተቃዋሚዎች ለመዳከማቸው ገዢውን ፓርቲ ተጠያቂ ያደርጋሉ፤ ገዥው ፓርቲ ደግሞ ጠንካራ ተቃዋሚዎች ባለመኖራቸው ሸክሜ በዝቷል እያለ ነው…

እዚህ ላይ ሁለት ነገር ነው የሚታየኝ፡፡ አንደኛ አቶ መለስም በህይወት በነበሩ ጊዜ የተናገሩት ነው፡፡ ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲ ቢመጣ ሩቅ መንገድ ሄደን እንቀበለዋለን ተብሎ ነበር፡፡ ነገር ግን ቅንጅት ተፈጥሮ ጠንካራ ፓርቲ ሲመጣ በጥይት ግንባሩን ነው ያሉት። ይሄ አባባል እንግዲህ ፖለቲከኞቻችን ለይስሙላ የሚጠቀሙት መሆኑን አረጋጋጭ ነው፡፡ “እንዳይበላ ግፋው እንዳያማህ ጥራው” አይነት ነገር ነው፡፡ አሁንም አቶ ኃይለማርያም የተናገሩትን ሰምቸዋለሁ “ሌሎቹ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሃላፊነትን መሸከም ስላልቻሉ የሃገሪቱ ሸክም ሁሉ ኢህአዴግ ላይ ወድቋል።
ተበራቱ” የሚል ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ኢህአዴግ ምንም አይነት ሃላፊነት ሊሸከም የሚችል ፓርቲ ነው ብዬ አላምንም፡፡ ለምን? የኢትዮጵያን ህዝብ ሰብአዊ መብት እየጣሰ ያለ ፓርቲ፣ ሃላፊነት እሸከማለሁ ቢል አይታመንም፡፡

 በሁለተኛ ደረጃ የኢትዮጵያን ህዝብ አዎንታ የተቀበለ ፓርቲ አይደለም፡፡ በሃይል፣ በመሳሪያ ስልጣን የያዘ ፓርቲ ነው፡፡ እኔ የማዝነው አቶ ኃይለ ማርያም በጣም ክርስቲያን ናቸው ይባላል፤ ግን በእዚህ አይነት ጉዳይ ላይ የሚናገሩት ነገር ከእምነታቸው ይቃረንብኛል፡፡ እነሱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ያቁሙና ከዚያ በኋላ ጠንካራ ተቃዋሚ ካጡ ይሄን ነገር ሊናገሩ ይችላሉ፡፡

 መኢአድን ጨምሮ ብዙዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በግለሰብ አውራዎች ላይ የተመሠረቱ ሆነው ይታያሉ። ከፕሮግራምና አላማቸው ይልቅ ፕሬዚዳንቶቻቸው ጐልተው ይወጣሉ፡፡ የሚሆነው ለምን ይመስልዎታል?

በእርግጥ ይሄ ነገር መሆን የሌለበት ነው፡፡ አመራር ብቻ አይደለም፤ አባላትም በሁሉም ነገር ላይ ተሣትፎአቸው መጠየቅ አለበት፡፡ የእነሱ ተሣትፎ ከሌለበት የኔ ነው የሚሉት ነገር ሊኖር አይችልም። በመጀመሪያ ደረጃ አባላቱ የኔ ነው ሊሉ የሚችሉት ፓርቲው አሣታፊ ሲሆን ነው፤ ስለዚህ እንደነዚህ አይነት ነገሮች በቀጣይ ሊታረሙ የሚገቡ ናቸው፡፡ አመራሩና አባላቱ የውስጥ እኩል ተሣትፎ ሊኖራቸው ይገባል። አንድ ሰው አንድ ፓርቲ ሊሆን አይገባም። የእከሌ ፓርቲ ሊባል አይገባም፡፡ መኢአድ ያንን ለማድረግ እየሰራ ነው፡፡ በአደረጃጀቱም ትልቁን ስልጣን የሚሰጠው ከታች ላለው ነው፡፡ የፓርቲ አመራሮች ራሳቸውን ለአባላቱ ተገዢ ካላደረጉ፣ ነገ ለሚመሩት የኢትዮጵያ ህዝብ ተገዢ ሊሆኑ አይችሉም።

 የ2007 ምርጫ እየተቃረበ ነው፡፡ መኢአድ ከምርጫው ምንድን ነው የሚጠብቀው?
እኛ ስራችንን እየሰራን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ አዎንታውን ከሰጠን ስልጣን ለመያዝ ከመጓዝ የሚያግደን ነገር የለም፣ ነገር ግን የመጫወቻ ሜዳው በትክክለኛው መንገድ ካልሄደ የኢትዮጵያን ህዝብ ልናማው አንችልም፡፡

 እኛንም ህዝቡ ሊያማን አይገባም፤ ማማት ያለበት ገዢውን ፓርቲ ነው፡፡ በጥይት በዱላ እየደበደበ አባላቶች እንዳይሳተፉ የሚያደርግ ከሆነ፣ በምርጫ ወቅት ካርድ እየሰረዘ አሽነፍኩ የሚል ከሆነ፣ በምርጫ ወቅት ታዛቢዎቻችንን እየደበደበ፣ በመድሃኒት እያሠከረ እያስተኛ የሚዘርፍ ከሆነ መታማት ያለበት ገዢው ፓርቲ ነው፡፡ መኢአድ በ2007፤ መቶ በመቶ አሸንፋለሁ ብሎ እየተራመደ ነው ያለው፤ ይሄን ደግሞ እርግጠኞች ነን። ለምን ካልን አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ ለውጥ ፈልጓል፤ ግን ለውጡን የሚሸከምለት ፓርቲ ይፈልጋል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ዛሬ በብዙ መልኩ መብቱ ተጥሷል። የሃገሪቱን የኢኮኖሚ ትሩፋት መጠቀም ተስኖታል፡፡ የቀን ሠራተኛው፣ ብሎኬት ሠራተኛው፣ ዶሮ አርቢው ሣይቀር ከውጭ እየመጣ ነው፡፡ የሀገሪቱ ዜጋ መጠቀም አልቻለም፡፡

Saturday, November 23, 2013

የመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች በአዛዦቻቸው ላይ ውጥረት ፈጥረውል::

November 23/2013
ጄኔራል አበባው ታደሰን እና የብኣዴን መኮንኖችን ያገለለ ስብሰባ መካሄዱ ጥያቄ አስነስቷል::



በወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ውጥረት መፈተሩን ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ተሰምቷል:: በወታደራዊ ጥቅማ ጥቅም እና በህገመንግሥቱ ዙሪአ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ አካል መጥፋቱ እና ዝም መባሉ ዉስጥ ውስጡን እየተብላላ ያለው የመኮንኖቹ ጥያቄ እንዳይፈነዳ የተሰጋ ሲሆን ከፈነዳ ሰራዊት ለሶስት ቦታ እንደሚከፈል ለምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮቹ ጠቁመዋል::

መኮንኖቹ በትምህርት በስራ እና በማእረግ እድገት በቤተሰብ እንክብካቤ በደሞዝ ጭማሪ እና በሕገመንግስታዊ የህዝብ መብቶች ዙሪያ ጥያቄ ያነሱ ሲሆን ወታደራዊ ጥቅማ ጥቅሞች ለአንድ ብሄር አባላት ብቻ ተመድበው እየተሰራባቸው ነው ከተማ ውስጥ ታጥቀው የመሸጉ እና ህዝብን እያጠቁ የሚገኙት የአንድ ብሄር አባላት ናቸው እንዱሁም ከሃገራዊ ጥቅም ይልቅ የፓርቲ ጥቅም እየተስተዋለ ነው:ወታደሩ የጦር ሳይንስን እና ዲሲፕሊን በጎደለው መልኩ እየተስተዳደረ ነው በሰራዊቱ እና በሃገሪቱ ሁሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን ሽፋን እና ማዘናጊያ በማድረግ የሙስና እና የዘረፋ መስፋፋት መልስ ሊያገኝ ይገባዋል ጄኔራል መኮንኖች አላቸው የተባለው ንብረት ይጣራ በሃገሪቱ የፖለቲካዊ እና የኢኮኖሚ ጥያቄዎች ሊመለሱ ይገባል የሚሉ እና ተመሳሳይነት ያላቸውን ጥያቄዎች ማንሳታቸው ታውቋል::የመከላከያ አባላቱ በኑሮ ውድነት እና በተቃዋሚዎች ህገመንግስታዊ መብቶች ላይ ያነሱት ጥያቄ አዛዦቹን ያስደነገጠ ከመሆኑም በላይ በአንድ ብሄር ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እስከመቼ የሚለውም ጥያቄ መመለስ አለበት በሚል የእግር እሳት እየሆነባቸው ነው::

ይህ ከዚህ ቀደም የተጀመረው እና አሁንም በሰሜን እዝ እና በምስራቅ እዝ የተከሰተው የሰራዊቱ ህገመንግስታዊ ጥያቄ እና የጥቅማ ጥቅም አቤቱታ በመላው ሃገሪቱ ተስፋፍቶ በሁሉም የሰራዊት እዞች ውስጥ ጥያቄው መነሳቱን ምንጮቹ አመልክተዋል::በተለያዩ ጊዜያት እየተንከባለለ የመጣው ይህ የሰራዊቱ አቤቱታ እጅግ አደገኛ አዝማሚያ እያሳየ ሲሆን በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እንዲወገድ እና ህገመንግስታዊ መብቶች እንዲከበሩ ጥያቄዎች ገፍተው መምጣታቸው ሲታወቅ ከፍተኛ የሕወሓት ጄኔራሎች በየቀኑ ካለማቋረጥ ምስጢራዊ ስብሰባዎችን እያደረጉ ከመሆኑም በላይ ከየእዙ የሚመጣላቸው ሪፖርት መፍታት የሚቻልበትን ጉዳይ እየተወያየ መሆናቸውን ከዚህ ቀደም ምንጮቹ ገልጸው ነበር::

ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስ ጡረታ ወቶ በምትኩ የብኣዴን ሜ/ጄ አበባው ይተካሉ ሲባል ወያኔ በድንገት የመለስ የቅርብ ሰው የነበሩትን እና በአንድ ወቅት የአማር ክልል አቶ አያሌው ጎበዜን ላንቻ አከባቢ በመኖሪያ ቤታቸው ለ3 ወር አግተው ሲያሰቃዩ የነበሩት ሌ/ጄ ዮሃንስ ገብረመስቀልን በማእረግ ሾሞ ሳሞራ የኑስን ለመተካት የሚያደርገውን ሩጫ የብኣዴን አባላት መቃወማቸውን ተከትሎ ጄኔራል አባባውን ጨምሮ የብኣዴን መኮንኖችን ያገለለ የሕወሃት አባላት የሆኑ ጄኔራሎች ብቻ የተሳተፉበት በትግሪኛ የተመራ ስብሰባ መደረጉን ውስጥ አዋቂ ምንጮቹ ተናግረዋል::በስብሰባው ላይ ቀሪ ከፍተኛ ባለማእረግ መኮንኖች እና የመምሪያ ሃላፊዎች ለምን አልተሳተፉም የሚል ጥያቄ ከአንድ ስማቸው ካልተጠቀሰ ብርጋዴር ጄኔራል መነሳቱን ምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮቹ ጠቁመዋል::

ይህ ስብሰባ ዋና አትኩሮቱ የነበረው በብሄር አደና ላይ ሲሆን እንደ ምንጮቹ መረጃ በአማራ እና በኦሮሞ መኮንኖች እየተመራ ያለውን የለውጥ ጥያቄ በማክሸፉ ዙሪያ እንደነበር እና አሁንም በስፋት የሕወሓትን የፓርቲ አቋም የሚቀበሉ እና የጥቅም ተጋሪ የሆኑ ሰዎችን ለመሾም የታቀደ ሲሆን እንዲሁም ከፖለስ ሰራዊት በከፍተኛ የማእረግ ሹመት ወደ ጦር ሰራዊቱ ለማምጣት የታሰበ ሲሆን በወታደራዊ ደህንነት ዙሪያ ሌላ ተጨማሪ ሰልጣኞችን ከፖሊስ ወስዶ በማሰልጠን ወደ ሰራዊት ማዘዋወር የሚሉ ውይይቶች ተካሂደውበታል:: አሁንም ስብሰባው የቀጠለ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን እንለቃለን::


ምንሊክ ሳልሳዊ :

ወቅታዊ ችግሮቻችን የራሳችን መንግሥት ባለቤቶች እንድንሆን ይበልጥ ሊያበረቱን ይገባል!

November 22/2013
በወያኔ አረመኔያዊ አገዛዝ ሳቢያ ከሀገራቸውና ከትውልድ ቀያቸው ተፈናቅለው በዐረቡ ዓለም በተለይም በሳዑዲ ዐረቢያ በሚገኙ ዜጎቻችን ላይ ሰሞኑን እየደረሰ የሚገኘውን ዘግናኝ ሰቆቃና ግድያ በመሪር ስሜትና በንቃት እየተከታልን ነው። አበው “ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳው አይቀበለውም” እንዲሉ እነዚህ ወገኖቻችን በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ‹የሀገራቸው መንግሥት ነው› የሚባልለት የወያኔው መንግሥት እንኳንስ በባዕድ ሀገር በሚገዛው ሀገርም ውስጥ የሚያካሂደውን የመብት ገፈፋና ሕዝቤ በሚለው ዜጋ ላይ በዘር እየከፋፈለ የሚያራምደውን የግፍ አገዛዝ ዐረቦቹም ሆኑ ቀሪው ዓለም ያውቁታል። በመሆኑም ለነዚህ ምሥኪን ዜጎች የሚጮኽላቸውም ሆነ ለመብታቸው መከበር የሚቆረቆርላቸው አንድም መንግሥታዊ አካል እንደሌለ ከበፊት የተገነዘቡት እውነታ ነው። በወገኖቻችን ላይ ይህን ሁሉ ሰማይና ምድር የማይችሉት የግፍ ቁልል እነዚህ የዐረብ መንግሥታት የፀጥታ ኃይሎች ሲከምሩባቸው ማንም ዝምባቸውን እሽ የሚል ወይም ጠንከር ባሉ ቃላት እንኳን ተቃውሞ የሚያቀርብ አካል እንደማይር ያውቃሉ። ለዚህም ነው ታላላቅ የሚዲያ አውታሮች ሳይቀሩ ሀገሪቷንና ሕዝን በመናቅ በዝምታቸው መግፋትን የወደዱት። ይህ ነገር ከሃይማኖትም ይሁን ከቀለም፣ ከዘርና ከፖለቲካዊ እሳቤዎች አኳያ የሰው ልጅ ተፈጥሮን ባሕርይና የሀገራትንና የመንግሥታትን ተጻራሪ ድርብ አቋሞችን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው።
 “ሰው ለሰው የሚጨነቀው፣ ምን ዓይነት ሰው ሲጎዳ ወይም ምን ዓይነት ሕዝብና የትኛው ሀገር ችግር ላይ ሲወድቅ/ሲወድቁ ይሆን?” በሚል ከፍተኛ ፍልስፍና ውስጥ የሚያስባ ልዩ አጋጣሚ ፈጥሯል። በእውኑ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ በበለፀጉ ሀገሮች የአንድ ንጉሥ-ንግሥት ንብረት ከሆነች ውሻ ያንሳሉን? ንግሥት ኤልሣቤጥ የሚወዷት የቤት ድመት ወይም የንጉሥ አብደላ የቤተ መንግሥት ውሻ ቢሞቱ ሲኤንኤንንና ቢቢሲን የመሳሰሉ ላለው የሚያሽቃብጡ ዓለም አቀፍ የዜና ተቋማት የመክፈቻ ዜናቸው እንደሚያደርጓቸው አይጠረጠርም። ወትሮም ብሂሉ “ላለው ይጨመርለታል” ነውና። እንደዚህ ያለው አካሄድ በውነቱ ቅስምን የሚሰብርና ከ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሰለጠነ የሚባል ማኅበረሰብ የሚጠበቅ አልነበረም።
በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ እየተደረገ ያለው ሰቅጣጭ የሕይወት ገጠመኝ በሌሎች ሀገራት ሕዝቦች ላይ ቢደረግ ኖሮ በአሁኑ ወቅት ዓለማችን ከዳር እዳር በተቃወሰች ነበር። በዚህ ዘመን እንደኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የተዋረደ የለም፤ ለዚህ ያበቃንም ይበልጡን በየምንሄድባቸው አካባቢዎች ያሉ መንግሥታት ብቻ ሳይሆኑ እቤታችን ያለው እሾህ፣ እዚያው ኢትዮጵያችን ውስጥ በአራት ከሎ ቤተ መንግሥት የመሸገውና በመላዋ ሀገራችን እንደመዥገር የተጣበቀው ወያኔ ነው። ስለዚህ ዋናው ጠላታችን ቤታችን ውስጥ ሁሉንም ነገር ተቆጣጥሮ ለመከራና እንግልት የዳረገን ወያኔ እንጂ ከዚህ ክፉ አውሬ የጭራቆች ቡድን ቀድሞ በኃላፊነት የሚጠየቅ ሊኖር አይገባም። እርግጥ ነው – በችግራቸው ጊዜ በጥሩ እንግዳ ተቀባይነት ከደረስንላቸው ወገኖች ይህን መሰል ግፍና ስቃይ ማየትና መስማት ዕንቆቅልሽ መሆኑ አይቀርም።
የአንድ ሀገር ዜጎች በተለያዩ ምክንያቶች በፍቅርም ይሁን በጠብ፣ በሥራና ለሥራም ይሁን በስደትና በጦር ምርኮኝነት ከሀገራቸው ወጥተው በሌሎች ግዛቶች የሚገኙበት ሁኔታ በተለይ በዚህ ዘመን በስፋት ይስተዋላል። በዚህን ጊዜ ባሉን ዓለም አቀፍ ሕግጋት መሠረት የዜጎች እንቅስቀሰሴና ዝውውር የዲፕሎማሲን መስመር በጠበቀ ሁኔታ ይከናወናል እንጂ እንዲህ እንደሰሞኑ አንዱ በሌላው ላይ ኢሰብኣዊ ድርጊትን አይፈጽምም። “በዚህን ጊዜ ውስጥ ሀገራችንን ለቃችሁ ውጡ፤ ካልወጣችሁ እንዲህና እንዲህ የመሰለ ችግር ይደርስባችኋል” ተብሎ ማሰጠንቀቂያ ይሰጣል እንጂ ድንገት ከመሬት ተነስቶ የሌሎች ሀገራት ዜጎችን ላልተጠበቀ ኢሰብኣዊ ድርጊት ማጋለጥ ሰብኣዊም ሃይማኖታዊም መደላድል የሌለው ዐይን ያወጣ ወንጀል ነው።
የአሁኑን የኢትዮጵያ መንግሥት ተብዬውን ዓይነት ሳይሆን ሁነኛ የሕዝብ አገልጋይ መንግሥታት ባሉባቸው ሀገራት ውስጥ ብዙ አስገራሚ ግን ተገቢና የሚጠበቅ መንግሥታዊ ፈጥኖ ደራሽነትንና ከአደጋ ታዳጊነትን ማየታችን በጣም የተለመደ ነው። ብዙ አብነቶችን መጥቀስ ቢቻልም የቅርብ ጊዜውን የሻሊትን ጉዳይ ብቻ ማውሳት በቂ ነው።
ሻሊት እሥራኤላዊ ወጣት ወታደር ነበር። ቀደም ሲል በሀገራዊ ግዳጅ ላይ እያለ በፍልስጥኤማውያን ይያዝና ሥውር ቦታ ይታሰራል። በሁለቱ ወገኖች መካከል ብዙ ጊዜ የወሰደ ድርድር ይካሄዳል። የአንድ ዜጋ ጉዳይ መላ እሥራኤላውያንን ማወዛገቡን ይቀጥላል። በመጨረሻም ከአንድ ሺህ በላይ እሥረኛ በአንድ ሻሊት አስፈትተው ፍልስጥኤሞች ይህን ወጣት ወታደር ይለቁታል። ለሀገርና ለሕዝብ ተቆርቋሪ መንግሥት ማለት እንደዚህ ነው። እሥራኤል ሕይወት ያለውን ዜጋዋን ብቻም ሣይሆን ለአንድ በጦርነት ለተሰዋና በጠላት ቁጥጥር ሥር የሚገኝ በድን ዜጋዋ ሕይወት ባላቸው በርካታ ምርኮኞች የምትለውጥ ለዜጎቿ ስሱ የሆነች ሀገር መሆንዋን ከበፊትም የምናውቀው ነው። በዘመናችን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በማድረግ ለዜጎች መብት መከበር ከመታገል አንጻር ሣይሆን በየትም ሥፍራ የሚኖሩ ዜጎች ለሀገር ውርደትና ለአጠቃላዩ የሕዝቡ ኅልውና ማክተም ሌት ከቀን ተግቶ በመሥራት አኳያ ከወያኔ መንግሥት ሌላ በዓለም ሌላ ሀገር ሊኖር እንደማይችል በልበ ሙሉነት መወራረድ ይቻላል። እኛ ላይ እሳት ነው የጣለብን።
“ጽድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ” እንዲሉ እኛ ኢትዮጵያውያን እንደእሥራኤል ያለ ለዜጋው እንስፍስፍ መንግሥት ማግኘቱ ቀርቶብን በዚህን ዓይነት አደጋ የበዛበት ወቅት የዜጎቹ ደኅንነት ካልተጠበ የዲፕሎማሲና የንግድ ግንኙነቶቹን እንደሚያቋርጥ ለማስመሰልም ቢሆን በማስፈራራት ለጨፍጫፊው መንግሥትና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት አቤት የሚል መንግሥት ቢኖረን ምንኛ በታደልን ነበር። ወያኔ ግን ተፈጥሮው እንደነዛው እንደጨፍጫፊዎቹ በመሆኑ እዚህ ግባ የሚባል ውኃ የማያነሣ ሰበብ በመስጠት ዜጎች እየተጨፈጨፉ ባሉበት ሁኔታ ሚዲያዎቹ ሁሉ በአሸሸገዳሜ ዘፈን ተሞልተው በሀገር ሰላም የተለመደ የማደንቆሪያ ልማታዊ ተብዬ ፕሮፓጋንዳውን በስፋት ቀጥሎበት ይታያል። ይህም በጣም ያሳዝናል።
ወያኔ ራሱ ህጋዊ መንግሥት የሆነ ይመስል ከሀገር የሚሰደዱ ዜጎችን ከህግ መስመር ውጪ ነው የወጡትና አያገባኝም በሚል ማደናገሪያ ከመንግሥታዊ ኃላፊነቱ እየሸሸ ነው። በመሠረቱ ቀድሞ መምጣት ያለበት ዜግነት እንጂ ሕግ አይደለም። ሰው የሠራው ሕግ በተፈጥሮ ከተገኝ ሰው መቅደም የለበትም። እንኳንስ ለዜጎቹ ምንም ነገር ካላሟላ ጨቋኝ መንግሥት ይቅርና ሁሉም ነገር ከተመቻቸላቸው ያደጉ ሀገሮችም ሳይቀር ከመንግሥታቸው በመቃረን ጭምር ሰዎች በተለያዬ ምክንያት ከሀገራቸው ይወጣሉ። ለምሳሌ ስኖውደን የተባለው አሜሪካዊ በቅርቡ ከሀገሩ ሸፍቶ በራሽያ ውስጥ ይገኛል። በዚህ ሰው ላይ ማንም አካል ተነስቶ ኢሰብኣዊ ድርጊት ቢፈጽምበት የአሜሪካ መንግሥት ራሱ እንደተዋረደ ይቆጥሩታልና ያ ስኖውደንን የሚያንገላታ አካል የዚህችን ልዕለ ኃያል የሆነች ሀገር ጡንቻ ይቀምሳል እንጂ “ከእኛ ጋር ተጣልቶና አስቀይሞን ስለወጣ እንኳን የእጁን አገኘ!” ከሚል የመሠሪዎች ቂም በቀለኝነት በመነሣት አሜሪካውያኑ እጃቸውን አጣጥፈው አይቀመጡም። ወያኔ ግን ተፈጥሮው በቂምና በበቀል የታጀለ በመሆኑ የሣዑዲን መንግሥት እንዲያውም በባለውለታነት እስካሁን ከሰጣቸው ሰፋፊ እርሻዎች በተጨማሪ ሌላ ትላልቅ መሬቶችን በሽልማት ሳይሰጣቸው አይቀርም። ይህ መንግሥት በሀገር ውስጥም በሰው ግዛትም እየገባ ዜጎቹን የሚጨፈጭፍ በመሆኑ ለዜጎች የሚቆረቆር ተፈጥሮ በጭራሽ የለውም። መባጽዮን ጃተኒን በሰላም በተቀመጠበት ኬንያ ውስጥ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮቹን አሰማርቶ ያሰገደለ ወያኔ ለዜጎች ይቆረቆራል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። ሰሞኑንም የግንቦት ሰባትን ሕዝባዊ ኃይል አመራር ለማስገደል እበላ ባይ ወንጀለኞችን አስርጎ ከፍተኛ የነፍስ ማጥፋት ወንጀል ሙከራ ያደረገ የባለጌዎች መንግሥት ራሱ ገፍቶ ያወጣቸውን ዜጎች ደኅንነት ለማስጠበቅ ከወዳጆቹና ከዓላማው አራማጆች የዐረብ መንግሥታት ጋር ይቀያየማል ብሎ ማሰብ ዘበት ነው። ለሕዝብና ለሀገር ውርደትና አጠቃላይ የሞራልም ሆነ የማኅበራዊ ዕሤቶች ውድቀት የቆመን አካል ደግ ነገር እንዲያደርግ መጠበቅ የወያኔን ሥረ መሠረትና የተፈጥሮ ባሕርይ በቅጡ አለመገንዘብ ነው። መፍትሔው ግን በያንዳንዳችን እጅ ውስጥ ነው።
እንደግንቦት ሰባት ያለው አማራጭ አንድና አንድ ብቻ ነው። ይሄውም ይህን የዜገች ፀር የሆነ የወንበዴ መንግሥት በሁሉም ሥልቶች ተረባርቦ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድ ነው። ይህ ሲሆን ነው ዜጎቻችን በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ አንገታቸውን ቀና አድርገው እንዲሄዱ የሚያስችላቸውን የኔ ነው የሚሉት ሕዝባዊና ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ማቆም የሚቻለው። ያኔ ነው ኢትዮጵያ ከተቀበረችበት ተነስታ በዜጎቿ የጋራ ምክክርና ስምምነት በአዲስ ጠንካራ መሠረት ላይ የሚገነባ ሁሉንም እኩል የሚያይ፤ ለሁሉም እኩል መኩሪያ የሚሆን መንግሥት ሊመሠረት የሚችለው። ያኔ ነው የሀገራችንን የሰውና የተፈጥሮ ሀብት ለሀገራችን በማዋል ድህነትንና ስደትን በተባበረ ክንዳችን የምንገታው። ያኔ ነው ሀብታችን በግለሰቦች እየተመዘበረ ለጥቂቶች መንደላቀቂያ መሆኑ የሚቀረውና ለሕዝቡና ለሀገሪቱ ዕድገት የሚውለው። ያኔ ነው በዓለም የተበተነው የተማረ የሰው ኃይላችንና በብዙ ዕውቀትና የሕይወት ልምድ የዳበረው ዜጋችን ወደ ሀገሩ መጥቶ ሀገር ቤት ካለው ኃይል ጋር በመተባበር ኢትዮጵያችንን ከገባችበት አረንቋ የሚያወጣትና ትንሣኤዋም በአዲስ መልክ የሚታወጀው። ለዚህ ሁሉ ተጨባጭ ምኞት እውንነት ደግሞ ሁላችን እጅ ለእጅ ተያይዘን ይህን የበሰበሰና የፈራረሰ ግን በቅርጹ ሲታይ ሕይወት ያለው የሚመስል የወሮበሎች መንግሥት በጋራ ትግል ከነሰንኮፉ ፈንቅለን ልንጥለው ይገባል። ዋናው የችግራችን ሁሉ መባቀያ አዲስ አበባ ላይ ቁጭ ብሎ መንስኤውን ትተን በውጤቶች ላይ ብቻ ማዘኑና መቆዘሙ እንዲሁም ባልተቋረጠ የሀዘን ድባብ ውስጥ ተቀምጦ ማንባቱ ዋጋ የለውም። የኛን ሥራ ወደጎን ትተን ወያኔ በሚፈጥራቸው አፍራሽ ተግባራትና ውጤታቸው ዝንትዓለሙን ማላዘኑ የነሱን ዕድሜ ከማራዘም ውጪ ለኛ የሚተርፍ አወንታዊ ፋይዳ የለውም። ከተባበርን የዚህ መንግሥት ዕድሜ ከሣምንታት አይረዝምም፤ ካልተባበርንና አንዳችን የአንዳችንን ጉድጓድ በመቆፈር ተግባር ከተጠመድን ወያኔ በጀመረው መንገድ ቀጥሎ ሀገራችን በለዬለት ሁኔታ ከዓለም ካርታ እንድትሰረዝ ፈቃደኞች ሆነናል ማለት ነው። ምርጫው የኛው ነው።
በመጨረሻም በሰሞኑ የወገኖቻችን ዕልቂት ምክንያት በቀጥታም ይሁን በተዛዋሪ የወያኔው ግፈኛ አገዛዝ ሰለባ የሆኑ ወገኖቻችንን ነፍስ ይማር እንላለን፤ ለቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ውርደቱና ታሪካዊ አንድምታው አሉታዊ ጥላውን ለሚያሳርፍበት ለመላው ሕዝባችንም መጽናናትን እንመኛለን።

በሳውዲ ለሚገኙ ወገኖቻችን በአፋጣኝ እንድረስ፤ በወያኔ ላይ በጋራ እንነሳ!!!

November 23/2013

በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው መጠን የለሽ የመብት ጥሰት ለመቃወም በተለያዩ የዓለም አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በየአገራቱ የሚገኙ የሳውዲን ኢምባሲዎችን በተቃውሞ እያጨናነቁ ነው። በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ባለው ዘግኛኝ በደል የተሰማቸውን ጥልቅ የመጠቃት ስሜት ኢትዮጵያን በተቃውሞ ሰልፎቹ ላይ በሚያሰሟቸው መሪር የሐዘን እንጉሮችና የቁጭት ንግግሮች እየገለፁ ነው። ከሐዘንና ቁጭት ባለፈም ለበደል ለተጋለጡ ወገኖቻችን አስቸኳይ ሰብዓዊ ርዳታ ለማድረስ እና የዲፕሎማሲ ድጋፍን ለማሰባሰብ ዓለም ዓቀፍ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ሥራውን ጀምሯል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ይህንን ዓለም ዓቀፍ ጥረት ለመደገፍ በውጭ አገራት የሚገኙ አባላቱ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ መመሪያ አስተላልፏል።
ይህ ሁሉ በውጭ አገራት እየተደረገ ያለ ጥረት ነው። ኢትዮጵያዊያን ባሉበት አገራትና ከተማዎች ሁሉ በዚህ ጉዳይ ላይ በአንድነት መንቀሳቀሳቸው የሚያስደስት ነገር ነው። ሌላው ቀርቶ በሳዉዲ ዋና ከተማ ሪያድ ውስጥ እንኳን ኢትዮጵያውያን የሳውዲን መንግሥት ተቃውመው ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል።
የሳውዲ መንግሥት በኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ የያዘውን ጨካኝ አቋም እና በመንግሥት እውቅና በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል መቃወም ያልተቻለው በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ!!! ይህ እጅግ ያማል፣ ልብን ያደማል።
ወያኔ የሳውዲ የንግድ ሸሪኮቹን ለማስደሰት የፈንሳይን ግማሽ የሚያህል ለም መሬት በነፃ መስጠቱ በቂ አልመሰለውም። በአገራቸው ኢትዮጵያዊያንን ሲጨፈጭፉ፣ ሲገሉና ሲደፍሩ በቸልታ መመልከቱ በቂ የወዳጅነት ስጦታ መስሎ አልተሰማውም። እናም ሸሪኮቹ የበለጠ እንዲደሰቱና ከእስከዛሬ በበለጠ ገንዘብ እንዲደጉሙት ለማበረታታት አዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲያቸው ፊት ለፊት ኢትዮጵያንን ደበደበላቸው።
ወያኔ ከሳውዲ ጋር ያለው ግኑኝነት “የቢዝነስ ሽርክና” ነው። ቢዝነሱም ኢትዮጵያዊያንን በቁማቸው መሸጥንም ያጠቃልላል። የወያኔ ሹማምንት እና የሳውዲም ቱጃሮች በዘመናዊ ባርነት ንግድ ውስጥ አቀባይና ተቀባይ ናቸው። ለዚህም ነው እየተነገደበት ያለው ምስኪን ኢትዮጵያዊ እጣ ፈንታ በአዲስ አበባና በሪያድ አንድ ዓይነት የሆነው። እዛ ዱላ፤ እዚህም ዱላ። እዛ እስር፤ እዚህም እስር። እዚያ ስድብ፤ እዚህም ስድብ። እዚያ ቶርቸር፤ እዚህም ቶርቸር። በባርያ ንግድ ውስጥ አቀባዩም ተቀባዩም ባርያዉን መግዛታቸው፣ መስበራቸው፣ መግደላቸው የማይቀር መሆኑ የታወቀ ነው።
ሌላው አሳዛኝ ጉዳይ ደግሞ የወያኔ ድኩማን ሹማምንት የሚሰጡት አስተያየት መስማት ነው። በሳውዲ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ፍትህ ለመጠየቅ በመላው ዓለም እና በአዲስ አበባ ደግሞ በሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪነት ወደ ጎዳና በወጡ ኢትዮጵያዊያን የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ተብየው “የፋሺሽት መፈክር አንግቦ በተጎሳቆሉ ዜጎች ስም የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት መጣር ብሎም መንግሥት በዜጎቹ ግዴለሽ እንደሆነ አስመስሎ ማቅረብ” ሲል ተሳልቋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተብየው ጨምሮ ሁሉም የወያኔ ሹማምንት “ሳውዲዎች በግዛታቸው ውስጥ ያሻቸውን የማድረግ “ሉዓላዊ” መብት አላቸው፤ መንግሥታችን የሳውዲ አረቢያን ሉዓላዊ መብት ያከብራል” እያሉ ይከራከራሉ። ለመሆኑ ይህንን የሚሉት ከልባቸው ነው? ፈጽሞ። ኢትዮጵያዊያንን ማሰቃየትና መግደል የቢዝነሳቸው አካል ስለሆነ ነው እንጂ የሉዓላዊነት ትርጉም ይህን ያህል ተምታቶባቸው አይደለም።
ሰብዓዊ መብቶች አገር፣ ድንበር፣ ዜግነት፣ ወይም ሌላ ማናቸው ሰው ሠራሽ ህግጋት ሊጥሷቸው እንደማይገቡ የወያኔ ሹማምንት ቢያንስ ሲነገር ሰምተው ያውቃሉ። ማንኛውም ሰው ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መገደል፤ ሰቆቃ (ቶርቸር) እንዲደርስበት ማድረግ፤ ጾታዊ ጥቃት እንዲደርስበት ማድረግ እንደማይቻል ሰምተው ያውቃሉ። ሰብዓዊ መብቶች ሰዎች ሰው በመሆናቸው ብቻ ሊያገኙት የሚገባ ክብር መሆኑ በተሳተፉባቸው በርካታ ዎርክ ሾፖች ሰምተዋል። ያም ሆኖ ግን በዘመናዊው ዓለም እንስሳ እንኳን ያገኘውን ክብር ኢትዮጵያዊያን ተነፍገው በሪያድ ጎዳናዎች ሲታረዱ፤ በጭካኔ ሲደበደቡና ሲገረፉ፤ ሴቶች ሲደፈሩ፤ ሕፃናት በረሀብና በእርዛት ሲቀጡ የወያኔ ባለሥልጣኖች የበዳዮች አፈቀላጤ ሆነው የሚከራከሩት በዳዮቹ ሸሪኮቻቸው ስለሆኑ ነው።
ይህ ድርጊት በወያኔ እየደረሰብን ያለው በደል ምን ያህል ሥር የሰደደ እንደሆነ እና የኢትዮጵያዊያን ሰቆቃ ምንጭ የት እንዳለ አመላካች ሆኗል።
“ትግላችን የነፃነት ትግል ነው” ስንል “ከማን ነፃ ለመውጣት?” እያሉ የሚሳለቁ እንደነበሩና እንዳሉም ይታወቃል። በወያኔ አገዛዝ ኢትዮጵያዊያን ወደ ባርነት ማሽቆልቆላቸው ይህ ተጨባጭ ማስረጃ ነው። ከወያኔ የባርነት አገዛዝ ነፃ እስካልወጣን ድረስ ሌሎች አገሮች መብቶቻችን የሚያከብሩልን በየአገራቱ ልምድ እና ከወያኔ ጋር ባላቸው ሽርክና መጠን ነው።
ለሳውዲ መንግሥትና ቱጃሮቹ ከነዳጅ ቀጥሎ የሀብታቸው ምንጭ ከየአገሩ የሚመጣላቸው የድሀ ጉልበት ነው። የሳውዲ ቱጃሮች ድሆችን ከባርነት ባልተሻለ መንገድ ረግጠው በመግዛት ኑሮዓቸውን ያደለቡ ናቸው። ለወያኔ አገዛዝ ደግሞ ከቡና ቀጥሎ ከፍተኛው የገቢ ምንጩ ዜጎቹን በመሸጥ የሚሰበስበው ነው። ለወያኔ፣ ኢትዮጵያዊያን ወንዶችና ሴቶች ትርፍ አምጪ ሸቀጦች ናቸው። ወያኔና ሳውዲ – ሻጭና ገዢ ናቸው።
ባርያ ከሻጩ ነፃ ሳይወጣ ከአንድ ገዢ ነፃ ቢወጣ ሌላ ገዢ ስለሚመጣ ዘለቄታነት የለውም። እኛም ከወያኔ ነፃ ሳንወጣ ከሳውዲ ነፃ መወጣት አይቻለንም፤ ቢቻልም ነፃነታችን ዘላቂነት አይኖረውም።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በሳዉዲ አረቢያ በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ በሚደርሰው ጥቃት ክፉኛ ተቆጥቷል። በዚህ የመከራና ጭንቅ ሰዓት ለወገኖቻችን ለመድረስ የሚቻለውን ጥረት ሁሉ ማድረግ እንዳለብን ያምናል። አባላቱ በነብስ አድን ርብርብ በግንባር ቀደምትነት እንዲሳተፉ መመሪያ አስተላልፏል። ይህ አጣዳፊ ሆኖም ጊዜዓዊ መፍትሔ ነው። በግንቦት 7 እምነት የችግሮቻችን ሰንኮፍ ያለው አዲስ አበባ ነው። ሰንኮፉን ሳንነቅል የሚደርስብንን ውርደት በዘላቂነት መቀልበስ አንችልም። ስለሆነም በችግር ላይ የወደቁትን ወገኖቻችን እየረዳን፤ የችግሮቻችን ምንጭ በሆነው ወያኔ ላይ የተባበረ ክንዳችንን እናንሳ ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

ዲፕሎማቱ በትዕዛዝ ኢትዮጵያውያኑን ስደተኞች ወዳልታወቀ ስፍራ ሰደዱ

November 22, 2013 

12ነፍሰ ጡሮችን ጨምሮ 200 ስደተኞች የደረሱበት አልታወቀም
saudi ethio11


በሳውዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ይገኙ የነበሩ 12 ነፍሰ ጡሮችን ጨምሮ ከ 200 በላይ ስደተኞች በዲፕሎማቱ ትዕዛዝ ወዳልታወቀ ስፈራ ተወሰዱ ።
በሪያድ ልዩ ስሙ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው አካባቢ ሰሞኑንን የተቀሰቀሰውን ሁከት ተከትሎ አያሌ ወግኖቻችን መገደላቸው እና በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ይታወቃል። ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ወገኖቻችን ህይወት አስከፊ ገጽታ ላይ ባለበት ሁኔታ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ውስጥ ከአንድ አመት በላይ ተጠልለው እንደቆዩ የሚነገርላቸው እነዚህ ወገኖች ወዳልታወቀ ስፈራ መወሰዳቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል።
አሰሪዎቻቸው ከሚፈጽሙባቸው ግፍ እና በደል ራሳቸውን ለመታደግ ቀደም ብለው ወደ ኮሚኒቲው ግቢ እንደመጡ የሚነገርላቸው እኚህ ወግኖች፤ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች ጉዳዩቻቸውን ተከታትለው ሊያስፈጽሙላቸው ባለመቻሉ በተጠቀሰው የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ በሚገኝ አንድ ኮንቴነር ውስጥ ሲሰቃዩ መኖራቸውን የአይን ምስክሮች አክለው ገልጸዋል። ከ12 በላይ ነፍሰጡሮች እና የአእምሮ በሽተኞችን ጨምሮ ከ200 በላይ ስደተኞች በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ያለምንም የህክምና እርዳታ ሲሰቃዩ ከከረሙት እህቶቻችን ውስጥ 3ቱ በሞት መለየታቸውንና 5ቱ ለአእምሮ ጭንቅት መዳረጋቸው ከኢትዮጵያ ህዝብ ልብ የማይጠፋ መሪር ሃዘን መሆኑንን የሚናገሩ ወገኖች ሰሞኑንን መንፉሃ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ሁከት ተከትሎ ወደ ሳውዲ አረቢያ እንደ ገባ ለሚነገርለት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ልኡካን ቡድን ገበናችንን ያጋልጣሉ በሚል ስጋት ዲፕሎማቱ እነዚህን ወገኖቻችንን ወደ አልታወቀ ስፍራ በአውቶብስ ጭነው መውሰዳቸው ታውቆል።
ስደተኞቹ ያሉበት ሁኔታ እስካሁን በውል እንደማይታወቅ የሚናገሩት የሪያድ ምንጮች ምናልባት ወደ አገራቸው ለመግባት ለፖሊስ እጅ ሰጥተው በየጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ከሚሰቃዩ ወገኖቻችን ጋር ቀላቅሎዋቸው ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ያጠናክራሉ። ዲፕሎማቱ የሚፈሩት ነገር ከሌለ በቀር እነዚህ ወገኖች በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ኮኔትንር ውስጥ ላለፉት ወራት ያሳለፉትን የችግር እና የመከራ ጊዜያቶች ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ጉዳዩቻቸውን ባሉበት በማስፈጸም ወደ ሃገር በመላኩ ረገድ ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባ እንደነበር ውስጥ አዋቂዎች ይገልጻሉ። ዲፕሎማቱ የፈጸሙት ድርጊት ወገናዊነት የጎደለው መሆኑን የሚገልጹ ምንጮች የተጠቀሱት እህቶቻችን ኮሚኒቲው መጠለያ ግቢ ውስጥ በነበሩባቸው ጊዜያቶች አንዳንድ እህቶቻችን ተመርጠው በዲፕሎማቱ ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ በሚል ሽፋን ማታ ማታ ከማደሪያ ኮንቴነር ክፍላቸው እየተጠሩ እዛው ኮሚኒት ግቢ ውስጥ በሚገኝ አንድ ጽ/ቤት ውስጥ ለሰአታት ቆይተው ይወጡ እንደነበር በማስታወስ በእህቶቻችን ላይ ጾታዊ ጥቃት ሳይፈጸምባቸው እንደማይቀር ጥርጣሬያቸውን ይገልጻሉ።
እንዲህ አይነት አስጸያፊ ድርጊት አልፎ አልፎ የሚሰማ መሆኑንን የሚገልጹ ወገኖች በሪያድ አንዲት ኢትዮጵያዊት ወጣት ላይ መከስቱን ተከትሎ ኮሚኒቲው አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ወጀለኛውን ፍ/ቤት በማቆም 60 ሺህ ሪያል ካሳ እንዲከፍል ማስወሰናቸውን የሚያወሱ አንድ አባት፤ ጉዳዩን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተከታትሎ እንዲያሰፈጽም አደራ ቢሰጡም ሃላፊነቱን በብቃት ሳይወጣ በመቅረቱ ወንጀለኛው ከእስርቤት ተለቆ ተበዳይ እህት ሰሞኑንን ከሌሎች ወገኖቻችን ጋር ወዳልታወቀ ስፍራ እስከተወስደችበት ጊዜ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቴ ግቢ ውስጥ በህመም ስትሰቃይ እንደነበር እማኝነታቸውን ሰጥተዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ በጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት በሚገኙ እህቶቻችን ላይ ተመሳሳይ ጥቃት መሞከሩን የሚናገሩ የአካባቢው ምንጮች አንዲት ወጣት በቆንስላው ጽ/ቤት ዘበኛ ጾታዊ ጥቃት ተፈጽሞባት ጉዳዩ ፍ/ቤት ደርሶ እንደነበርና በቆንስላው የመንግስት ባለስልጣኖች ተድበስበሶ መቅረቱ የሚያስታውሱ ወገኖች በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ጊቢ ይኖሩ ከነበሩ ስደተኞች ውስጥ የ12ቱ ነፍሰ ጡር እህቶቻችን ጉዳይ ሳይጣራ ሰሞኑንን በዲፕሎማቱ ትዕዛዝ ከኮሚኒቲው ግቢ ባስቸኳይ እንዲለቁ መደረጉ የአካባቢውን ማህበረሰብ ጥርጣሬ የበለጠ ያጠናክረዋል ብለዋል።
Ethiopian Hagere በፌስቡክ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ከጅዳ በዋዲ የላኩት

Friday, November 22, 2013

ሰማያዊ ፓርቲ፣ የዜጎችን ሰቆቃ እና በደል ችላ ማለት ከግፈኞች ጋር እንደመተባበበር ይቆጠራል!!

November 22/2013   
292643_197873413697583_587677658_n
ሰማያዊ ፓርቲ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎቻችን ላይ የሳውዲ መንግስት እያደረሰ ያለውን እስራት፣ ስቃይ እና ግድያ በመቃወም እና ህይወታቸው ላለፈ፣ ለተደበደቡ እንዲሁም የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ህዝቡ ሃዘኑን እንዲገልጽ በመጪው እሁድ በሚደረገው ታላቁ ሩጫ ላይ የሚሮጡ ተሳታፊዎች ጥቁር ሪቫን አድርገው እንዲሮጡ ጥሪ ማስተላለፉ የሚታወቅ ነው፡፡

ይሁን እንጂ የታላቁ ሩጫ አስተባባሪዎች ይህንን ጥሪ እንደሚቃወሙት እና በፕሮግራሙም ላይ ጥቁር ሪቫን ያሰረ ተሳታፊን እንደተሳታፊ እንደማይቆጥሩ መናገራቸው ፓርቲያችንን እጅግ አሳዝኖታል፡፡ ፓርቲያችን ይህንን ጥሪ ሲያስተላልፍ አላማው ፍጹም ፖለቲካዊ አንድምታ የሌለው ሲሆን ጥያቄውም በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እና ግድያ እንዲቆም እና ፍትሃዊ እርምጃም እንዲወሰድ ለመጠየቅ ብቻ እና ብቻ እንጂ ሌላ አላማ እንደሌለው እየታወቀ የታላቁ ሩጫ አስተባባሪዎች ግን ጉዳዩ ከፖለቲካ ጋር ለማያያዝ መሞከራቸው የሚያስተዛዝብ እና ህዝባዊ ወገንተኝነታቸውን ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው፡፡

ስፖርት ሰላማዊ ነገር የሚሰበክበት እንዲሁም እኩይ ተግባራት የሚወገዙበት መድረክ ነው፡፡ በአለማችን ላይ በተለያዩ ጊዜያት በተከሰቱ አሰቃቂ ሰው ሰራሽ አደጋዎች በተለያዩ ስፖርታዊ ዝግጅቶች ላይ ሲወገዙ እንዲሁም ለሰለባዎች ሃዘን የመግለጽ ስነ ስርዓትና የህሊና ጸሎት ሲደረግ መመልከት የተለመደ ነው፡፡ ታዲያ በጠራራ ፀሀይ በአደባባይ እናት ልጆችዋ ፊት እንዲሁም ሴት ልጅ ቤተሰቦችዋ ፊት ስትደፈር ከማየት የዘለለ ምን እኩይ ተግባርስ ሊኖር ነው? ታዲያ ስፖርት ይህንን ካላወገዘ ምንን ሊያወግዝ ነው?

በመጨረሻም የታላቁ ሩጫ አስተባባሪዎች የፓርቲውን ጥሪ መቃወማቸው ፓርቲያችንን ያሳዘነ እና ያስቆጣ መሆኑን እየገለጽን አሁንም ፓርቲያችን በድጋሜ በዝግጅቱ ላይ ተሳታፊዎች ጥቁር ሪቫን አድርገው እንዲሮጡ እየጠየቀ ጥቁር ሪቫኖችን ማግኘት ለማትችሉ በሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ተገኝታችሁ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
ክብር ለዜጎቻችን ይሁን!!

Thursday, November 21, 2013

ለሕዝቡ ግደ የለሹ የኢህአዲግ መንግስት መወገድ አለበት( ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ)

November 21/2013
ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ

 ሰሞኑንን በሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን እየደረሰ ያለው ግፍና በደል የብዙዎቻችን ኢትዮጵያኖች አይምሮ የጓዳ እና ያሳዘነ ነገር ነው እርግጠኛ ነኝ ማንም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን  መከራ በቸልተኝነት እንደማይመለከተው ምክንያቱም እየሆነ ያለው ነገር ኢትዮጵያዊ ክብርን የሚነካ እና አንገትን የሚያስደፋ ነገር ነው :: ወንድሞቻችን ተገርፈዋል ተደብድበዋል እንደ እንስሳ በአደባባይ ተቀጥቅጠዋል  የኢትዮጵያዊነትን ክብር የሆነውን ባንዲራ እንደያዙ በአደባባይ ተገለዋል ሴት እሕቶቻችንም ሳይቀሩ እንደዚሁ ዘግናኝ እና አሳፋሪ የሆነ በደል እየደረሰባቸው ነው:: እህቶቻችን በጨካኝ እና በአረመኔ የሳውዲ ጎረምሶች እና ፖሊሶች ተደብድበዋል ክብራቸው ተዋርዶል ተደፍረዋል ይህ ሁሉ በወገኖቻችን እየደረሰው ያለው ነገር ወደ ህዝብ ጆሮ ከደረሰበት ጊዚ ጀምሮ የመላው ኢትዮጵያንን ቁጣ በሀይል እና በንዴት የቀሰቀሰ ሲሆን ከየስፍራው እነዚህ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ሰይጣናዊ እና አረመናዊ ድርጊት እንዲቆም የኢትዮጵያኖ ጩኽት ከዳር እስከ ዳር በየሀገሩ እንደቀጠለ ይገኛል::ማንም ኢትዮጵያዊ የትኛውም ብሔር ቤሆን በወገኖቻችን ላይ የደረሰው በደል ያላሳዘነው ያላስቆጨው እና በህልኽ ያልቀሰቀሰው ያለ አይመስለኝም ኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያን ዜጓች እንደ ወንድም እና እህቶቻቸው የሚያዩ ኤርትራውያን ወገኖቻችን ሳይቀሩ ይህን በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ እና በደል በአደባባይ በመውጣት እያወገዙ ይገኛሉ:: 

ዜጕች ሀገራቸውን ጥለው ከሀገር እየወጡ ለስደት እና ለመከራ የሚዳረጉበት ምክንያት ብልሹ የሆነው የወያኔ የኢህአዲግ መንግስት አስተዳደር እንደሆነ በሁሉም ዘንድ የታመነበት ሀቅ ነው:: በሳውዲም ለወንዶች እና ለሴቶች እህቶቻን መሰቃየት፣ መሞት እና ማለቅ  ቁጥር አንድ ተጠያቄው ይሄው አገሪቷን እየመራው ነው ብሎ የሚናገረው ለሃያ ሁለት አመታት በስልጣን ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ ለኢትዮጵያ ህዝብ አንዳችም ሊፈይድ ያልቻለው በምትኩ ግን ህዝብን ለስደት  እና ለሞት የዳረገው ይኼው የወያኔ መንግስት እንደሆነ በብዙዎች ዘንድ እየተነገረ ይገኛል:: በርግጥም ሰሞኑን በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው መከራ ለመላው ኢትዮጵያውያን ሕዝቦች የኢህአዲግን መንግስት እንኮን ሳይቀር እየደገፉ ላሉ ወገኖቻችን የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ምን ያክል የኢትዮጵያን ሕዝብ ጥቅም ለማሰከበር ያልቆመ እና  ለሚመራው እና ተወክዪለታለው ለሚለው ሕዝብ ግድ የሌለው እንደሆነ በተግባር በአደባባይ እያሰመሰከረ ይገኛል ::

በሳውዲ የሚገኙ ዜጐቻችን   የወገን እና የሀገርን እርዳታን በሚሹበት በአሁኑ ሰአት የወገን እና የሀገር ህልውና እየተረገጠበት ባለበት ሰአት የኢህአዲግ መንግሰት ግን ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ለህዝባቸን ምንም ያክል እርዳታን አለማድረጉ በብዙዎች ዘንድ በርግጥ ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት አለ ወይ እያስባለ ነው የሚገኛው ::   ይህም ብቻ አይደለም በሳውዲ እየተፈፀመ ያለውን በደል በመቃወም በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያዊያን ድምፃቸውን በማሰማት ላይ በሚገኙበት በአሁኑ ሰአት ሰአት በሀገር ቤት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ግን በገዛ ሀገራቸው በዜጐቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ለመቃወም አልታደሉም :: በርግጥም እራሱን ትዝብት ላይ የሚጥለውን ተግባር በመፈጸም ድምጻቸውን ለማሰማት የወጡትን ዜጐች በመደብደብ በመግረፍ እና በማሰር ከሳውዲ አረቢያ መንግሥት ጐን በመቆም ዋና ተባባሪ መሆኑን  አስመስክሯል  አልፏል:: ይህ ሁሉ ሲሆን በራሱ በወያኔ ደገፊዎች ሳይቀር የወያኔ መንግስት እየተወገዘ እና እየተብጠለጠለ ይገኛል ምክንያቱም ነገሩ የፖለቲካ ነገር ጥያቄውም የፖለቲካ ጥያቄ እንዳልሆነ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በሚገባ ጠነቅቆ ያውቀዋል እና:: በሳውድ አረቢያ በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው በደል በጣም ያላስቋጨው እና ያላንገበገበው ኢትዮጵያዊ የለም አንድ የወያኔ የኢህአዲግ መንግስት እንደሆነች በሚገባ የማውቃት ከሀገር ውጭ የምትኖሩር በዜጓቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ የሳዘናት እና የመንግስት ግድ የለሽነት ያናደዳት ወጣት አትንኩብኝ እያለች በፊስ ቡክገጽ ሳይቀር ስትክበው የነበረችውን መንግስት በመቃውም በፊስ ቡከ ገጾ ላይ እንዲህ አለች የኢትዮጵያ መንግስት ሆድ እንጅ ጭንቅላት የለውም :: እውነቷን ነው ይህች ወጣት እህታችን  ለሆድ ሳይሆን በሚገባ ህዝቡን ለመመራት እና ለማስተዳደር የተቀመጠ መንግስት ቢሆን ኖሮ በሳውዲ በዜጐቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይ ግድ ብሎት የወገን አጋርነቱን ያሳይ ነበር ይህንን ግን የወያኔ መንግስት ሊያደርገው አልቻለም::ስለዚህም ለዜጕቹ ግድ የሌለው መንግስት ለህዝብ ጥቅም የቍመ መንግስት ስለሆነ መወገድ አለበት ::
         
     አምላክ በስቃይ ውስጥ ያሉትን ወገኖች ይጠብቃቸው

ኢህአዴግ ስለምን ይጮኻል? (ተመስገን ደሳለኝ)

November 21/2013

በረዥሙ የኢትዮጵያ ዘመነ መንግስት ታሪክ , በአስተዳደሩ ተመስግኖ በክብር የተሸኘ ገዥ ስለመኖሩ የሚያወሳ አንድም ድርሳን ፈልጎ ማግኘት የሚቻል አይመስለኝም . ሁሉም መንግስታት የተወገዱት በአመፅ አሊያም በተፈጥሮ ሞት ነውና . በ 1983 ዓ . ም ወርሃ ግንቦት በጠብ - መንጃ ኃይል ሥልጣን የተቆናጠጠው ኢህአዴግ - መራሹ መንግስትም ቢሆን , በቀድሞዎቹ ገዥዎች < የብረት ጫማ > ውስጥ ተከልሎና ተደላድሎ ዕለተ - ስንብቱን በመጠባበቅ ላይ ያለ ይመስለኛል . ዕለተ - ስንብቱ መቃረቡን የሚጠቁመው ደግሞ ከቅርብ በረዥሙ የኢትዮጵያ ዘመነ መንግስት ታሪክ , በአስተዳደሩ ተመስግኖ በክብር የተሸኘ ገዥ ስለመኖሩ የሚያወሳ በረዥሙ የኢትዮጵያ ዘመነ መንግስት ታሪክ , በአስተዳደሩ ተመስግኖ በክብር የተሸኘ ገዥ ስለመኖሩ የሚያወሳበረዥሙ የኢትዮጵያ ዘመነ መንግስት ታሪክ , በአስተዳደሩ ተመስግኖ በክብር የተሸኘ ገዥ ስለመኖሩ የሚያወሳ አንድም ድርሳን ፈልጎ ማግኘት የሚቻል አይመስለኝም .

ሁሉም መንግስታት የተወገዱት በአመፅ አሊያም

በተፈጥሮ ሞት ነውና . በ 1983 ዓ . ም ወርሃ ግንቦት በጠብ - መንጃ ኃይል ሥልጣን የተቆናጠጠው ኢህአዴግ -
መራሹ መንግስትም ቢሆን , በቀድሞዎቹ ገዥዎች < የብረት ጫማ > ውስጥ ተከልሎና ተደላድሎ ዕለተ - ስንብቱን
በመጠባበቅ ላይ ያለ ይመስለኛል . ዕለተ - ስንብቱ መቃረቡን የሚጠቁመው ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ልክ
እንደ ደርግ የመጨረሻዎቹ ወራት ሁሉ , ግንባሩና አጋር ፓርቲዎቹ ለየት ባለ መልኩ በራሳቸውና
በሹማምንቶቻቸው ላይ በአደባባይ የተቃውሞ ድምፅ ማሰማት መጀመራቸው ነው . የዚህ ፅሁፍ ተጠየቅም
ይህ ነውና ተጨባጭ እውነታውን ለማብራራት በቂ የሆኑ አስረጂዎችን በአዲስ መስመር በዝርዝር ለመመልከት እሞክራለሁ .

ስረጅ አንድ

በ 2005 ዓ . ም መጨረሻ ላይ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ዓመታዊ ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ባቀረበበት ወቅት ከአገዛዙ የተለየ
ድምፅ የተሰማው እንደ ወትሮው ሁሉ , በም / ቤቱ ተቃዋሚ ፓርቲን ከወከለው < አንድ ለእናቱ > አቶ ግርማ ሰይፉ ብቻ አይደለም ;
ኢህአዴግ በአምሳሉ ከፈጠራቸው አጋር ፓርቲዎችም ጭምር እንጂ .

በዕለቱ ሚንስትሩ ዶ / ር ሽፈራው ተክለማርያም በመንግስት በመገንባት ላይ ያለውን የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካን አስመልክቶ < አክራሪ >
ካላቸው መነኮሳትና < ጥቂት > መዕምናን < ግርግር የመፍጠር ሙከራ > ባለፈ የተከሰተ የጎላ ችግር አለመኖሩን በሪፖርቱ መጥቀሱን ተከትሎ

የአፋር ክልል ተወካዩ በአጋርነት ያነበረውን ስርዓት እንዲህ ሲል ነበር የተቸው -

<< ለፋብሪካው ግንባታ ተብሎ ከአካባቢው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች እንዲሰፍሩ የተደረገበት ቦታ ውሃና መብራት ያሌለው ነው ; ይህ ለምን
ሆነ ? ብለን ስንጠይቅ < ድሮም የነበሩበት ቦታ መብራትና ውሃ የለውም > በማለት ይመልሱልናል . በአጠቃላይ በአፋርና አካባቢው
በሪፖርቱ ያልተካተቱ ብዙ ችግሮች አሉ . >>

የሶማሌ ክልል ተወካይም በበኩሉ በዚሁ ዕለት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር < የሰብዓዊ መብት አያያዝ > ን በተመለከተ አድበስብሶ ማለፉን

የተቃወመው በሚከተለው አኳኋን ነበር -

<< በእኛ አካባቢ የሰብዓዊ መብት አይከበርም ; ሰዎች ይገደላሉ ; ይታሰራሉ ; ይደበደባሉ . >> ( በርግጥ በመልከዓ ምድር ለአካባቢው
ከማንም በላይ የሚቀርበው የሀረሪው ተወካይ ብዙውን ጊዜ በምክር ቤቱ ስለማይገኝ በዕለቱ በቀረበው ሪፖርት ላይ ቅሬታ ይኑረው ድጋፍ
ማወቅ አልተቻለም )

አስረጅ ሁለት

ጥቅምት 22 ቀን 2006 ዓ . ም የኢትዮጵያ የሰላምና ልማት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አቦይ ስብሃት ነጋ , በህዝብ ተወካዮች ም / ቤት
ለውጭ , መከላከያና ደህንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ , የዓመቱን በጀት ለማፀደቅ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት , ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
መ / ቤት ጋር ተግባብተው መስራት አለመቻላቸውን በግልፅ ተናግረዋል . ኢንስቲትዩቱ የተመሰረተበት አቢይ ዓላማ << የውጭ ጉዳይ
ፖሊሲ በሚያስገኘው ውጤት ዙሪያ ጥልቅ ጥናት ለማካሄድ >> መሆኑ ቢታወቅም , ውጭ ጉዳይ << ይህንን አጥኑልን >> ብሎም ሆነ አቅጣጫ

አሳይቶ እንደማያውቅ ከረር ባለ ድምፅ አስረድተዋል .

መንግስት በሚሊዮን የሚቆጠር ዓመታዊ በጀት የበጀተለትን ይህንን ተቋም በኃላፊነት እንዲያስተዳድሩ በዶ / ር ክንፈ አብርሃ ህልፈት
ማግስት የተሾሙት አቦይ ስብሃት , ለቋሚ ኮሚቴው ባቀረቡት ሪፖርት ላይ - << ኢንስቲትዩቱ በአዋጅ የተቀመጠለትን ዓላማ ከማስፈፀም
አኳያ ቀደም ሲልም አልነበረም ; አሁንም የለም >> ማለታቸው የሚያመላክተው የስርዓቱን ዝቅጠት ብቻ አይደለም ; ይልቁንም በአንድ
ፓርቲና በተመሳሳይ ርዕዮተ - ዓለም የሚመሩት መንግስታዊ ተቋማትም እንኳ እርስ በእርስ ተግባብተው መስራት ከማይችሉበት ደረጃ ላይ
መድረሳቸውንም ጭምር ነው .

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ኢህአዴግ ስለምን ይጮኻል? (ተመስገን ደሳለኝ)

November 21/2013

በረዥሙ የኢትዮጵያ ዘመነ መንግስት ታሪክ፣ በአስተዳደሩ ተመስግኖ በክብር የተሸኘ ገዥ ስለመኖሩ የሚያወሳ አንድም ድርሳን ፈልጎ ማግኘት የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ሁሉም መንግስታት የተወገዱት በአመፅ አሊያም በተፈጥሮ ሞት ነውና፡፡ በ1983 ዓ.ም ወርሃ ግንቦት በጠብ-መንጃ ኃይል ሥልጣን የተቆናጠጠው ኢህአዴግ- መራሹ መንግስትም ቢሆን፣ በቀድሞዎቹ ገዥዎች ‹የብረት ጫማ› ውስጥ ተከልሎና ተደላድሎ ዕለተ-ስንብቱን በመጠባበቅ ላይ ያለ ይመስለኛል፡፡ ዕለተ-ስንብቱ መቃረቡን የሚጠቁመው ደግሞ ከቅርብ በረዥሙ የኢትዮጵያ ዘመነ መንግስት ታሪክ፣ በአስተዳደሩ ተመስግኖ በክብር የተሸኘ ገዥ ስለመኖሩ የሚያወሳ በረዥሙ የኢትዮጵያ ዘመነ መንግስት ታሪክ፣ በአስተዳደሩ ተመስግኖ በክብር የተሸኘ ገዥ ስለመኖሩ የሚያወሳበረዥሙ የኢትዮጵያ ዘመነ መንግስት ታሪክ፣ በአስተዳደሩ ተመስግኖ በክብር የተሸኘ ገዥ ስለመኖሩ የሚያወሳ አንድም ድርሳን ፈልጎ ማግኘት የሚቻል አይመስለኝም፡፡ 

ሁሉም መንግስታት የተወገዱት በአመፅ አሊያም

በተፈጥሮ ሞት ነውና፡፡ በ1983 ዓ.ም ወርሃ ግንቦት በጠብ-መንጃ ኃይል ሥልጣን የተቆናጠጠው ኢህአዴግ-
መራሹ መንግስትም ቢሆን፣ በቀድሞዎቹ ገዥዎች ‹የብረት ጫማ› ውስጥ ተከልሎና ተደላድሎ ዕለተ-ስንብቱን
በመጠባበቅ ላይ ያለ ይመስለኛል፡፡ ዕለተ-ስንብቱ መቃረቡን የሚጠቁመው ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ልክ
እንደ ደርግ የመጨረሻዎቹ ወራት ሁሉ፣ ግንባሩና አጋር ፓርቲዎቹ ለየት ባለ መልኩ በራሳቸውና
በሹማምንቶቻቸው ላይ በአደባባይ የተቃውሞ ድምፅ ማሰማት መጀመራቸው ነው፡፡ የዚህ ፅሁፍ ተጠየቅም
ይህ ነውና ተጨባጭ እውነታውን ለማብራራት በቂ የሆኑ አስረጂዎችን በአዲስ መስመር በዝርዝር ለመመልከት እሞክራለሁ፡፡ 

ስረጅ አንድ
በ2005 ዓ.ም መጨረሻ ላይ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ዓመታዊ ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ባቀረበበት ወቅት ከአገዛዙ የተለየ
ድምፅ የተሰማው እንደ ወትሮው ሁሉ፣ በም/ቤቱ ተቃዋሚ ፓርቲን ከወከለው ‹አንድ ለእናቱ› አቶ ግርማ ሰይፉ ብቻ አይደለም፤
ኢህአዴግ በአምሳሉ ከፈጠራቸው አጋር ፓርቲዎችም ጭምር እንጂ፡፡
በዕለቱ ሚንስትሩ ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም በመንግስት በመገንባት ላይ ያለውን የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካን አስመልክቶ ‹አክራሪ›
ካላቸው መነኮሳትና ‹ጥቂት› መዕምናን ‹ግርግር የመፍጠር ሙከራ› ባለፈ የተከሰተ የጎላ ችግር አለመኖሩን በሪፖርቱ መጥቀሱን ተከትሎ
የአፋር ክልል ተወካዩ በአጋርነት ያነበረውን ስርዓት እንዲህ ሲል ነበር የተቸው፡-
‹‹ለፋብሪካው ግንባታ ተብሎ ከአካባቢው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች እንዲሰፍሩ የተደረገበት ቦታ ውሃና መብራት ያሌለው ነው፤ ይህ ለምን
ሆነ? ብለን ስንጠይቅ ‹ድሮም የነበሩበት ቦታ መብራትና ውሃ የለውም› በማለት ይመልሱልናል፡፡ በአጠቃላይ በአፋርና አካባቢው
በሪፖርቱ ያልተካተቱ ብዙ ችግሮች አሉ፡፡››
የሶማሌ ክልል ተወካይም በበኩሉ በዚሁ ዕለት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ‹የሰብዓዊ መብት አያያዝ›ን በተመለከተ አድበስብሶ ማለፉን
የተቃወመው በሚከተለው አኳኋን ነበር፡-
‹‹በእኛ አካባቢ የሰብዓዊ መብት አይከበርም፤ ሰዎች ይገደላሉ፤ ይታሰራሉ፤ ይደበደባሉ፡፡›› (በርግጥ በመልከዓ ምድር ለአካባቢው
ከማንም በላይ የሚቀርበው የሀረሪው ተወካይ ብዙውን ጊዜ በምክር ቤቱ ስለማይገኝ በዕለቱ በቀረበው ሪፖርት ላይ ቅሬታ ይኑረው ድጋፍ
ማወቅ አልተቻለም)
አስረጅ ሁለት
ጥቅምት 22 ቀን 2006 ዓ.ም የኢትዮጵያ የሰላምና ልማት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አቦይ ስብሃት ነጋ፣ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት
ለውጭ፣ መከላከያና ደህንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የዓመቱን በጀት ለማፀደቅ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
መ/ቤት ጋር ተግባብተው መስራት አለመቻላቸውን በግልፅ ተናግረዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ የተመሰረተበት አቢይ ዓላማ ‹‹የውጭ ጉዳይ
ፖሊሲ በሚያስገኘው ውጤት ዙሪያ ጥልቅ ጥናት ለማካሄድ›› መሆኑ ቢታወቅም፣ ውጭ ጉዳይ ‹‹ይህንን አጥኑልን›› ብሎም ሆነ አቅጣጫ
አሳይቶ እንደማያውቅ ከረር ባለ ድምፅ አስረድተዋል፡፡
መንግስት በሚሊዮን የሚቆጠር ዓመታዊ በጀት የበጀተለትን ይህንን ተቋም በኃላፊነት እንዲያስተዳድሩ በዶ/ር ክንፈ አብርሃ ህልፈት
ማግስት የተሾሙት አቦይ ስብሃት፣ ለቋሚ ኮሚቴው ባቀረቡት ሪፖርት ላይ፡- ‹‹ኢንስቲትዩቱ በአዋጅ የተቀመጠለትን ዓላማ ከማስፈፀም
አኳያ ቀደም ሲልም አልነበረም፤ አሁንም የለም›› ማለታቸው የሚያመላክተው የስርዓቱን ዝቅጠት ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም በአንድ
ፓርቲና በተመሳሳይ ርዕዮተ-ዓለም የሚመሩት መንግስታዊ ተቋማትም እንኳ እርስ በእርስ ተግባብተው መስራት ከማይችሉበት ደረጃ ላይ
መድረሳቸውንም ጭምር ነው፡፡
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ 

ኢትዮጵያ፣ በህዳርና በ… ሁልጊዜ አስታውሳለሁ!! (ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም)

November 21, 2013
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የህዳር ወር በኢትዮጵያውያን በአሰቃቂነቱ ሁልጊዜ ሲታወስ ይኖራል፡፡
እ.ኤ.አ ኖቬምበር 2013 ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በቃላት ለመግለጽ በሚዘገንን መልኩ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ ሰቆቃ የተፈጸመበት ወር ነው፡፡ ላለፉት ጥቂት ዓመታት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ፣ በሚሰሩና የፖለቲካ ጥገኝነት ለመጠየቅ ጥረት በማድረግ ላይ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ ስልታዊ የሆነ ጥቃት ሲሰነዘር ቆይቷል፡፡ እንዲያውም በግል በሚኖሩበት ቤት እምነታቸውን በማራመዳቸው ብቻ ኢትዮጵያውያኑ/ቱ ዜጎች ላይ የወንጀል ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል፣ እንዲጋዙም ተደርጓል፡፡Ethiopia November Victims never again, Alemayehu G. Mariam
እ.ኤ.አ 2011 የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ (Human Rights Watch) ዘገባ የሳውዲ አረቢያ ፖሊስ “ህገወጥ ስብሰባ በሚል ሰበብ 35 የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያወያንን/ትን“ “በአንድ ኢትዮጵያዊ የክርስትና እምነት ተከታይ የግል መኖሪያ ቤት በእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ዋዜማ ተሰባስበው ጸሎት በማድረግ ላይ እንዳሉ” በፖሊስ ቀጥጥር ስር ውለዋል” ይላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሳውዲ አረቢያ ጥገኝነት በሚፈልጉ እና ሌሎች ስደተኛ ኢትዮጵያውያት የቤት ሰራተኖች ላይ በሚደረገው ሰብአዊ መብት ረገጣ ምክንያት ምንጊዜም የማያቋርጥ ትችት እየተደረገ መሆኑን መግለጽ ማጋነን አይሆንም፡፡ በዚህ ወር በዕየለቱ በሚባል መልኩ የሳውዲ አረቢያ ፖሊሶች፣ የደህንነት ኃላፊዎችና ተራ የሳውዲ ዜጎች በየመንገዱ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎችን ያድናሉ፣ ይደበድባሉ፣ ያሰቃያሉ፣ አንዳንድ ጊዜም ይገድላሉ፡፡ የሳውዲ ፖሊሶች ኢትዮጵያውያንን ሲያሰቃዩ የሚያሳየው የቪዲዮ ቅርፅ ለህሊና የሚሰቀጥጥ ነው፡፡ የሳውዲዎች ኢትዮጵያውያንን በየመንገዱ የማባረር ሁከት፣ ጥቃት የመሰንዘርና የመግደል ድርጊት ምንም ዓይነት ማብራሪያ አያስፈልገውም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣ የሚያሳየው የፎቶግራፍ ምስል አስደንጋጭና ከሰለጠነ የሰው ልጅ አስተሳሰብ በእጅጉ የዘለለ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አስተዳደር 200 ሺ እና ከዚያ በላይ የሚሆኑትን በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያን/ት ለማገዝ ምን እያደረገ ነው? ምንም!!! እራሱ አምኖ በተቀበለው መሰረት ገዥው አስተዳደር ምን ያህል ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ እንደሚኖሩ እንኩዋን አያውቅም፣ ሆኖም ግን ተጨባጭነት በሌለው መልኩ ኢትዮጵያውያንን/ትን ከሳውዲ አረቢያ ሙሉ በሙሉ በተቻለ መጠን ወደ ኢትዮጵያ እመልሳለለሁ የሚል ቃል ገብቷል፡፡
የወባ ተመራማሪው “የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር”፣ ቴዎድሮስ አድሃኖም የሳውዲ መንግስት በግዛቱ በሚገኙት ስደተኛ ኢትዮጵያውያን/ት ሰራተኞች ላይ የፈጸመውን አረመኒያዊ የኃይል እርምጃ “መንግስቱ አውግዘዋል፡፡ ይኸ በፍጹም ተቀባይነት የለውም፡፡ ይህን ጉዳዩ የሳውዲ መንግስት እንዲያጣራ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ እዚያ በነበሩበት ጊዜ በክብር መያዝ የነበረባቸውን ዜጎቻችንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስም ደስተኞች ነን፡፡ ተቀባይነት የለውም” የሚለውን አባባል ገዥው አስተዳደር እንደ አስፈሪ የጭካኔ ድርጊቶች፣ ያለመሰልጠንነትና ዘግናኝ ጨካኝነትና ወንጀለኛነት የሚሉትን ቃላት ለመግለጽ የሚጠቀምበት የውግዘት ቃል ነው፡፡ አልጄዚራ እንደዘገበው ከሆነ በተፈጸመው ድርጊት ተበሳጭተው የነበሩ ኢትዮጵያውያን/ት አዲስ አበባ በሚገኘው የሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት ሰላማዊ ተቃውሟቸውን ለማሰማት በሄዱበት ጊዜ የገዥው አስተዳደር ፖሊስ በቁጥጥር በማዋል  ድብደባ ፍጽሞባቸዋል፡፡ “ፖሊሶች ከመጡ በኋላ ደብድበውናል፣ እና በአሁኑ ጊዜ ከ100 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በእስር ቤት ይገኛሉ” በማለት የተቃዋሚው የሰማያዊ ፓርቲ ነባር አባል ጌትነት ባልቻ ገልጿል፡፡ ጌትነት በመቀጠልም “የፓርቲው ሊቀ መንበርና ምክትል ሊቀመንበር ከታሰሩት ውስጥ ይገኙበታል” በማለት ሀሳቡን አጠቃሏል፡፡
ሆኖም ግን ኢትዮጵያውያን/ በሀዳር ወር መጎዳትና መጎሳቀል ለምን ይደንቀን? እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2005 ያለው የገዢ አስተዳደር ለመናገር በሚዘገንን መልኩ የጭካኔ ድርጊት በአትዮጵያኖች ላይ ፈፅሞአል:: በዚያው ዓመት የፓርላማውን ምርጫ ተከትሎ በግንቦት ወር በጠራራ ፀሐይ የተዘረፈውን የህዝብ ድምጽ በመቀወም ድምጻቸውን ባሰሙ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች እራሱ መለስ ዜናዊ ያቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን 193 ያልታጠቁ ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች በአዲስ አበባ መንገዶች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን በመግለጻቸውና እና ሌሎች በከፍተኛ ደህንነት በእስር ቤት የሚገኙ እስረኞችን ሆን ተብሎ በጥይት ደብድበዋል፣ ሌሎች 763 የሚሆኑት በጽኑ ቆስለዋል፡፡
እ.ኤ.አ ከ2007 ጀምሮ በየጊዜው በህዳር ወር እ.ኤ.አ የ2005 ምርጫን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጨዋና ያልታጠቁ ሰልፈኞች ተኩስ በመክፈት ገደሏቸው፣ አካለ ጎደሎ አደረጓቸው፡፡ እኔም ያንን ጊዜ ለማስታወሰ ስል መጻፌን ቀጥየ ነበር፡፡
በመጀመሪያው የማሰታወስ ጽሁፌ እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2005 እና በጁን 2005 የተከፈለው መስዕዋትነት ለዘላለም ይታወሳል! ለአንባቢ ዎቼም ሳስታዉስ በህይወት ላሉትና ለሞቱት ምስክርነት መስጠት እንዳለባችሁ የሞራል ግዴታ ተጥሎባችኋል ብዬ ነበር፡፡ ኤሊ ዌይሰል የዕልቂቱ ተራፊና የኖቬል ተሸላሚ በክብር እንዳስቀመጠው “ማስታዋስ አለብን ምክንያቱም የጋራ ትውስታችን የሆኑትን ያለፉ ድርጊቶች የወደፊቱን ትውልድ መብት መከልከል ስለማንችል ነው መርሳት መጥፎ ነገር ብቻ አይደለም ነገር ግን ስድብም ነው፡፡ የሞቱትን መርሳት ሁለተኛ ከመግደል እኩል ነው፡፡”
በ2005 ያለቁትን መርሳት ማለት በእነርሱ ላይ የተፈጸሙትን ግፎች መርሳት እንዲህም ያሉትን አረመኔአዊ ወንጀል መርሳትማለት ነው፡፡ እልቂቱን መርሳት ማለት ወንጀለኞች ተጠያቂ እንዳይሆኑ የልብ ልብ መስጠት ማለት ነው፣ ምክንያቱም ወንጀሎቹ ተረስተዋል፡፡ በመጨረሻም መርሳት ማለት በስልጣን ላይ ያሉ ወንጀለኞች እንደገና እና እንደገና የወንጀል ደረጃውን ከፍ በማድረግና ተጠያቂነት የሌለበትን ሁኔታ በመፍጠር ወንጀል እንዲሰሩ ማበረታታት ማለት ነው፡፡
አስታውሳለሁ! በምንም አይነት አልረሳምም፣ በፍጹም!!!
አስታውሳለሁ ምክንያቱም እኔ ካላስታወስኩ ማን ያስታዉሳል? አስታውሳለሁ ምክንያቱም የምረሳ ከሆነ ወንጀሎችና ወንጀለኞች ይረሳሉ፡፡ የምረሳ ከሆነ ታሪክ እንዴት ሊያስታውስ ይችላል? ታሪክ ሊያስታውስ የሚችለው ሌላ ሊያስታውስ የሚችል ሰው ሲኖር ነው:: በህዳር፣ በታህሳስ፣ በጥር፣ በየካቲት፣ መጋቢት፣ ሚያዝያ… ዛሬ ለኢትዮጵያ ወጣቶችና ነገ ለሚወለዱ ህጻናት አስታውሳለሁ፡፡
የእኔን ስራ በማድነቅና ለበርካታ ዓመታት ሲደግፉ ሲቆዩ ሌሎች ደግሞ ሲተቹ ሲቃወሙ የሚኖሩ አሉ። እኔ በኢትዮጵያውያን ሰበአዊ መብቶች ችኮ ነው ይሉኛል:: በኢትዮጵያውያን ሰበአዊ መብቶች ችኮ መሆን ለኔ ታላቅ ክበር ነው::
የ2005 ዕልቂትን አስታውሳሁ፡፡ እያንዳንዱን በግፍ የተገደሉትን አስታዉሳለሁ፡፡ አስታውሳለሁ ወጣት ሴቶች ወደፊት እናት ላይሆኑ፣ ወጣት ወንዶችን የአራዊቱን  ጭፍረኞች ገዳዮችን አልረሳም  ወደፊት አባት ላይሆኑ፣ ወላጅ የሌላቸውን ወላጆቻቸው የተገደሉባቸውን አስታውሳለሁ፡፡ ልጆቻቸው የተገደሉባቸውን እናቶችንና አባቶችን አስታውሳለሁ::
ወንጀለኞችን አልረሳም፣ ተንኮል የሰሩትን 237ቱን የፖሊስ አባላት አስታውሳለሁ፣ የወንጀለኞችን ቁንጮና መሪ የነበረዉን አራዊትን  አልረሳም:: የአራዊቱን  ጭፍረኞች ገዳዮችን አልረሳም::
አስታውሳሁ፣ መቼ ረሳለሁ: ሁልጊዜ  ህዳርን፣ ታህሳስን፣ ጥርን፣ የካቲትን፣ መጋቢትን፣ ሚያዝያን….አልረሳም፡፡
.
ስም
ጾታ
እድሜ
ስራ

መግለጫ
1
ሬቡማ ኢርጋታ
34
ግንበኛ
2
መለሳቸው አለምነው
16
ተማሪ
3
ሀድራ ኦስማን
22
አይታወቅም
4
ጃፋር ኢብራሂመ
28
ቢዝነስ
5
መኮንን
17
አይታወቅም
6
ወልደሰማያት
17
7
ባህሩ ደምለው
አይታወቅም
8
ፈቀደ ነጋሽ
25
መካኒክ
9
አብርሀምይልማ
17
ታከሲ ነጂ
10
ያሬድ እሸቴ
23
ቢዝነስ
11
ከበደ ገ/ህይወት
17
ተማሪ
12
ማቴዎስ ፍልፍሉ
14
ተማሪ
13
ጌትንት ወዳጆ
48
ቢዝነስ
14
ቃሰም ራሽድ
21
መካኒክ
15
ሸውሞሊ
22
ቢዝነስ
16
አሊየ ኢሳ
20
የቀን ስራ
17
ሣምሶን ያዕቆብ
23
የህዝብ ማመላ
18
አለባለው አበበ
18
ተማሪ
19
በልዩ ዛ
18
ትራንስ. ረዳት
20
ዩሱፍ ጀማል
23
ተማሪ
21
አብርሃም አገኘሁ
23
ትራንስ.ረዳት
22
መሀመድ በቃ
45
አርሶ አደር
23
ረዴላ አወል
19
የታክሲ ረዳት
24
ሀብታሙ ኡርጋ
30
ቢዝነስ
25
ዳዊት ፀጋዬ
19
መካኒክ
26
ገዛኸኝ ገረመው
15
ተማሪ
27
ዮናስ አበራ
24
አይታወቅም
28
ግርማ ወልዴ
38
ሾፌር
29
ደስታ ብሩ
37
ቢዝነስ
30
ለገሰ ፈይሳ
60
ቢዝነስ
31
ተስፋዬ ቡሽራ
19
ጫማ ጠጋኝ
32
ቢንያም ደገፋ
18
ስራ አጥ
33
ሚሊዮን ሮቢ
32
ትራንስ.ረዳት
34
ደረጀ ደኔ
24
ተማሪ
35
ነብዩ ሃይሌ
16
ተማሪ
36
ምትኩ ምዋለንዳ
24
ዶመስቲክ ሰራተኛ
37
አንዋር ሱሩር
22
ቢዝነስ
38
ንጉሴ ዋብግነ
36
ዶመስቲክ ሰራተኛ
39
ዙልፋ ሀሰን
50
የቤት እመቤት
40
ዋስይሁን ከበደ
16
ተማሪ
41
ኤርሚያስ ከበደ
20
ተማሪ
42
00428
25
አይታወቅም
43
00429
26
አይታወቅም
44
00430
30
አይታወቅም
45
አዲሱ በላቸው
25
አይታወቅም
46
ደመቀ አበበ
አይታወቅም
47
00432
22
አይታወቅም
48
00450
20
አይታወቅም
49
13903
25
አይታወቅም
50
00435
30
አይታወቅም
51
13906
25
አይታወቅም
52
ተማም ሙክታር
25
53
በየነ በዛ
25
አይታወቅም
54
ወሰን አሰፋ
25
አይታወቅም
55
አበበ አንተነህ
30
አይታወቅም
56
ፈቃዱ ኃይሌ
25
አይታወቅም
57
ኤሊያስ ጎልቴ
አይታወቅም
58
ብርሃኑ ዋርካ
59
አሸብር መኩሪያ
አይታወቅም
60
ዳዊት ሰማ
አይታወቅም
61
መርሀጽድቅ ሲራክ
አይታወቅም
62
በለጠ ጋሻውጠና
አይታወቅም
63
ብኃይሉ ተስፋዬ
20
አይታወቅም
64
21760
18
አይታወቅም
65
21523
25
አይታወቅም
66
11657
24
አይታወቅም
67
21520
21
አይታወቅም
68
21781
60
አይታወቅም
69
ጌታቸው አዘዘ
45
አይታወቅም
70
21762
75
አይታወቅም
71
11662
45
አይታወቅም
72
21763
25
አይታወቅም
73
13087
30
አይታወቅም
74
21571
25
አይታወቅም
75
21761
21
አይታወቅም
76
21569
25
አይታወቅም
77
13088
30
አይታወቅም
78
እንዳልካቸው ገብርኤል
27
አይታወቅም
79
ኃይለማርያም አምባዬ
20
አይታወቅም
80
መብራቱ ዘውዱ
27
አይታወቅም
81
ስንታየሁ በየነ
14
አይታወቅም
82
ታምሩ ኃይለሚካኤል
አይታወቅም
83
አድማሱ አበበ
45
አይታወቅም
84
እቴነሽ ይማም
50
አይታወቅም
85
ወርቄ አበበ
19
አይታወቅም
86
ፈቃዱ ደግፌ
27
አይታወቅም
87
ሸምሱ ካሊድ
25
አይታወቅም
88
አብዱዋሂደ አህመዲን
30
አይታወቅም
89
ታከለ ደበሌ
20
አይታወቅም
90
ታደሰ ፌይሳ
38
አይታወቅም
91
ሶሎሞን ተስፋዬ
25
አይታወቅም
92
ቅጣው ወርቁ
25
አይታወቅም
93
ደስታ ነጋሽ
30
አይታወቅም
94
ይለፍ ነጋ
15
አይታወቅም
95
ዮሀንስ ኃይሌ
20
አይታወቅም
96
በኃይሉ ብርሀኑ
30
አይታወቅም
97
ሙሉ ሶሬሳ
50
አይታወቅም
98
የቤት እመቤት
አይታወቅም
99
ቴዎድሮስ
23
አይታወቅም
100
ጫማ ሰሪ
ጫማ ሰሪ
101
በኃይሉ ብርሃኔ
30
አይታወቅም
102
ሙሉ ሶሬሳ
50
የቤት እመቤት
103
ቴዎድሮስ ኃይሌ
23
ጫማ ሻጭ
104
ደጄኔ ይልማ
18
መጋዝን ጠባቂ
105
ኡጋሁን ወልደገብርኤል
18
ተማሪ
106
ደረጀ ማሞ
27
አናጺ
107
ረጋሳ ፈይሳ
55
ላውንድሪ ሰራተኛ
108
ቴዎድሮስ ገብረዎልድ
28
የግል ንግድ
109
መኮንን ገ/እግዚአብሄር
20
መካኒክ
110
ኤሊያስ ገ/ጊዮርጊስ
23
ተማሪ
110
አብርሀም መኮንን
21
የቀን ሰራተኛ
111
ጥሩወርቅ ገ/ጻድቅ
41
የቤት እመቤት
112
ሄኖክ መኮንን
28
አይታወቅም
113
ጌቱ ምሀትተ
24
አይታወቅም
114
ክብነሽ ታደሰ
52
አይታወቅም
115
መሳይ ስጦታው
29
የግል ንግድ
116
ሙሉአለም ወይሳ
15
አይታወቅም
117
አያልሰው ማሞ
23
አይታወቅም
118
ስንታየሁ መለሰ
24
የቀን ሰራተኛ
119
ጸዳለ ቢራ
50
የቤት እመቤት
120
አባይነህ ሰራሴድ
35
ልብስ ሰፊ
121
ፍቅረማርያም ተሊላ
18
ሾፌር
122
አለማየሁ ገርባ
26
አይታወቅም
124
ጆርጅ አበበ
36
የግል ትራንስፖርት
125
ሀብታሙ ዘገየ
16
ተማሪ
126
ምትኩ ገ/ስላሴ
24
ተማሪ
127
ትዕዛዙ መኩሪያ
24
የግል ንግድ
128
ፈቃዱ ዳልጌ
36
ልብስ ሰፊ
129
ሸዋጋ ወ/ጊዮርጊስ
38
የቀን ሰራተኛ
130
አለማየሁ ዘውዴ
32
የቴክስታይል ሰራተኛ
131
ዘላለም ገ/ጻድቅ
31
የታክሲ ሾፌር
132
መቆያ ታደሰ
19
ተማሪ
133
ሀይልየ ሁሴን
19
ተማሪ
134
ፍስሀ ገ/ጻድቅ
23
የፖሊስ ተቀጣሪ
135
ወጋየሁ አርጋው
26
ስራ ፈላጊ
136
መላኩ ከበደ
19
አይታወቅም
137
አባይነህ ኦራ
25
ልብስ ሰፊ
138
አበበች ሆለቱ
50
የቤት እመቤት
139
ደመቀ ጀንበሬ
30
አርሶ አደር
140
ክንዴ ወረሱ
22
ስራ ፈላጊ 141
141
እንዳለ ገ/መድህን
23
የግል ንግድ
142
አለማየሁ ወልዴ
24
መምህር
143
ብስራት ደምሴ
24
መኪና አስመጭ
144
መስፍን ጊዮርጊስ
23
የግል ንግድ
145
ወሎ ዳሪ
18
የግል ንግድ
146
በሀይሉ ገ/መድህን
20
የግል ንግድ
147
ሲራጂ ኑሩ ሰይድ
18
ተማሪ
148
እዮብ ገ/መድህን
25
ተማሪ
149
ዳንኤል ሙሉጌታ
25
የቀን ሰራተኛ
150
ቴዎድሮስ ደገፋ
25
የጫማ ፋብሪካ ሰራተኛ
151
ጋሻው ሙሉጌታ
24
ተማሪ
152
ከበደ ኦርቄ
22
ተማሪ
153
ለሊሳ ፋጤሳ
21
ተማሪ
154
ጃገማ ባሻ
20
ተማሪ
155
ደበላ ጉታ
15
ተማሪ
156
መላኩ ፈይሳ
16
ተማሪ
157
እልፍነሽ ተክሌ
45
አይታወቅም
158
ሀሰን ዱላ
64
አይታወቅም
159
ሁሴን ሀሰን ዱላ
25
አይታወቅም
160
ደጀኔ ደምሴ
15
አይታወቅም
161
ዘመድኩን አግደው
18
አይታወቅም
162
ጌታቸው ተረፈ
16
አይታወቅም
163
ደለለኝ አለሙ
20
አይታወቅም
164
ዩሱፍ ኡመር
20
አይታወቅም
165
መኩሪያ ተበጀ
22
አይታወቅም
166
ባድሜ ተሻማሁ
20
አይታወቅም
167
አምባው ጌታሁን
38
አይታወቅም
168
ተሾመ ኪዳኔ
65
የጤና ባለሙያ
169
ዮሴፍ ረጋሳ
አይታወቅም
170
አብዩ ንጉሴ
አይታወቅም
171
ታደለ በሀጋ
አይታወቅም
172
ኤፍሬም ሻፊ
አይታወቅም
173
አበበ ሀማ
አይታወቅም
174
ገብሬ ሞላ
አይታወቅም
175
ሰይዴ ኑረዲን
አይታወቅም
176
እንየው ጸጋዬ
32
እረዳት ትራንስፖርት
177
አብዱራህማን ፈረጅ
32
የእንጨት ስራ ባለሙያ
178
አምባው ብጡል
60
የቆዳ ፋብሪካ ሰራተኛ
179
አብዱልመናን ሁሴን
28
የግል ንግድ
180
ጅግሳ ሰጠኝ
18
ተማሪ
181
አሰፋ ነጋሳ
33
አናጺ
182
ከተማ ኡንኮ
23
ልብስ ሰፊ
183
ክብረት እልፍነህ
48
የጥበቃ ሰራተኛ
184
እዮብ ዘመድኩን
24
የግል ንግድ
185
ተስፋዬ መንገሻ
15
የግል ንግድ
186
ካፒቴን ደበሳ ቶሎሳ
58
የግል ንግድ
187
ትንሳኤ ዘገየ
14
ልብስ ሰፊ
188
ኪዳና ሹክሩ
25
የቀን ሰራተኛ
189
አንዷለም ሺበለው
16
ተማሪ
190
አዲሱ ተስፋሁን
19
የግል ንግድ
191
ካሳ በየነ
28
ልብስ ሽያጭ
192
ይታገሱ ሲሳይ
22
አይታወቅም

የጸጥታ ኃይሎች እርስ በእርስ ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ በጥይት የተገደሉ ሰዎች፣

193
ነጋ ገብሬ
194
ጀበና ደሳለኝ
195
ሙሊታ ኢርኮ
196
የሃንስ ሶሎሞን
197አሸናፊ ደሳለኝ
198
ፈይሳ ገ/መንፈስ
በመቶዎቹ የሚቆጠሩትን የግድያ ሰለባዎች፣ አካለ ጎደሎዎች፣ ቁስለኞች፣ በኃይል የተመቱትንና ሰውነታቸው በጥይት የተበሳሱትን ሁሉ አስታውሳለሁ፡፡
..ኖቬምበር 2/2005ከቃሊቲእስርቤትለማምለጥሲሞክሩበታጣቂዎችበተከፈተተኩስበጥይትተደብድበውያለቁሰዎችስምዝርዝር፣
.
ስም
ጾታ
የተከሰሱበት ጥፋት፣
1
ጠይብ ሸምሱ መሀመድ
ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት
2
ሳሊ ከበደ
ምንም ዓይነት ክስ አልተጠቀሰም
3
ሰፊው እንድሪስ ታፈሰ
በአስገድዶ መድፈር
4
ዘገዬ ተንኮሉ በላይ
በዝርፊያ ወንጀል
5
ቢያድግልኝ ታመነ
የተወነጀሉበት ያልታወቀ
6
ገብሬ መስፍን ዳኘ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
7
በቀለ አብርሃም ታዬ
በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር
8
ጉታ ሞላ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
9
ኩርፋ መልካ ተሊላ
በማስፈራራት ወንጀል
10
በጋሻው ተረፈ ጉደታ
የህዝብን ሰላም በማደፍረስ ወንጀል
12
አብደልወሃብ አህመዲን
በዘርፊያ ወንጀል
13
ተስፋዬ አብይ ሙሉጌታ
ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት
14
አዳነ ቢረዳ
በነፍስ ማጥፋት ወንጀል
15
ይርዳው ከርሴማ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
16
ባልቻ አለሙ ረጋሳ
በዝርፊያ ወንጀል
17
አቡሽ በለው ወዳጆ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
18
ዋለልኝ ታምሬ በላይ
በአስገድዶ መድፈር
19
ቸርነት ኃይሌ ቶላ
በዝርፊያ ወንጀል
20
ተማም ሸምሱ ጎሌ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
21
ገብየሁ በቀለ አለነ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
22
ዳንኤል ታዬ ለኩ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
23
መሀመድ ቱጂ ቀኔ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
24
አብዱ ነጂብ ኑር
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
25
የማታው ሰርቤሎ
በአስገድዶ መድፈር
26
ፍቅሩ ናትናኤል ሰውነህ
በማስፈራራት ወንጀል
27
ሙኒር ከሊል አደም
በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር
28
ኃይማኖት በድሉ ተሸመ
ጽንፈኝትን በማራመድ
29
ተስፋዬ ክብሮም ተኬ
በዥርፊያ ወንጀል
30
ወርቅነህ ተፈራ ሁንዴ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
31
ሲሳይ ምትኩ ሁነኛ
በማጭበርበር ወንጀል
32
ሙሉነህ አይናለም ማሞ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
33
ታደሰ ሩፌ የኔነህ
በማስፈራራት ወንጀል
34
አንተነህ በየቻ ቁበታ
ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት
35
ዘሪሁን መርሳ
በንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ ወንወጀል
36
ወጋየሁ ዘሪሁን አስፋው
በዝርፊያ ወንጀል
37
በከልካይ ታምሩ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
38
የራስወርቅ አንተነህ
በማጭበርበር ወንጀል
39
ባዝዘው ብርሀኑ
ግብረሰዶም በመፈጸም ድርጊት
40
ሶሎሞን እዮብ ጉታ
በአስገድዶ መድፈር ወንጀል
41
አሳዩ ምትኩ አራጌ
በማስፈራራት ወንወጀል
42
ጋሜ ኃይሉ ዘገዬ
በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር
43
ማሩ እናውጋው ድንበሬ
በአስገድዶ መድፈር ወንጀል
44
እጂጉ ምናለ
በግድያ ሙከራ ወንጀል
45
ኃይሉ ቦስኔ ሀቢብ
የተቀደሰን ቦታ በማራከስ
46
ጥላሁን መሰረት
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
47
ንጉሴ በላይነህ
በዝርፊያ ወንጀል
48
አሸናፊ አበባው
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
49
ፈለቀ ድንቄ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
50
ጀንበሬ ድንቅነህ ቢለው
በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር
51
ቶሎሳ ወርቁ ደበበ
የዝርፊያ ወንጀል
52
መካሻ በላይነህ ታምሩ
የህዝብን ሰላም በማደፍረስ
53
ይፍሩ አደራው
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
54
ፋንታሁን ዳኘ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
55
ጥበቤ ዋቀኔ ቱፋ
ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት
56
ሶሎሞን ገብረአምላክ
የህዝብን ሰላም በማደፍረስ
57
ባንጃው ቹቹ ካሳሁን
በዝርፊያ ወንጀል
58
ደመቀ አበጀ
በግድያ ሙከራ ወንጀል
59
እንዳለ እውነቴ መንግስቴ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
60
አለማየሁ ጋርባ
እ.ኤ.አ በ2004 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አመጽ ጋር በተያያዘ መልኩ በቁጥጥር የዋሉ
61
ሞርቆታ ኢዶሳ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
ለምዘገባ፣ በዚህ እልቂት ላይ ተዋንያን የነበሩ 237 የተረጋገጠ የፖሊስ እና የደህንነት አባላት ዝርዝርን የያዘ ሰነድ ተቀምጧል፡፡
የኔሰው ገብሬን አስታውሳለሁ!
Yenesew Gebre from Dawro-Waka Ethiopia
የኔሰው ገብሬ
እ.ኤ.አ በ11/11/11 የኔሰው ገብሬ የተባለ የ29 ዓመት መምህር እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች በደቡብ ኢትዮጵያ በዳውሮ ዞን በተርጫ ከተማ ከህዝብ መሰብሰቢያ ዳራሽ ፊት ለፊት እሳት በመለኮስ እራሱን በእሳት አያይዟል፡፡ ለሶስት ቀናት ቆስሎ ከቆየ በኋላ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡ እራሱን በእሳት ከማያያዙ በፊት የኔሰው ከህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውጭ ለተሰበሰበ ህዝብ እንዲህ የሚል ንግግር አሰምቶ ነበር፣ “በእኩልነት ላይ ባልተመሰረተ አስተዳደር እና ፍትህ በሌለበት እንዲሁም የሰብአዊ መብት በማይከበርበት አገር ውስጥ እራሴን ለመስዋዕትነት አቀርባለሁ፣ ይህንንም በማድረጌ ወጣቱ ትውልድ ነጻ ይወጣል፡፡” የአትዮጵያ ጀግናዉ የእኔሰው ገብሬን አስታውሳለሁ
“ገዳዮችን አስታውሳለሁ፣ የግድያ ሰለባዎችንም አስታውሳለሁ፣ ለትግሌ የሚያግዙ አንድ ሺ እና ከዚያ በላይ ያሉ አሳማኝ ምክንያቶች እና ተስፋ ቢኖረኝም፡፡ ባስታወስኩ ቁጥር ተስፋየ ይሟጠጣል፣ ያንን ድርጊት ባስታውስኩ ቁጥር ደግሞ ተስፋቢስነቴን የማስወገድ ኃላፊነት እንዳለብኝ እገነዘበላሁ፣ ተስፋ ከተስፋቢስነት በላይ ነው፡፡“ ይላል ኤሊ ዊሴል!
**ለጥቃቱ ሰለባዎች ተጨማሪ መረጃ ይሆን ዘንድ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆኑት ያሬድ ኃ/ማርያም እ.ኤ.አ ሜይ 15/2006 በሰው ልጆች ላይ የተፈጸመ  ወንጀል በኢትዮጵያ፣ የጁንና ኖቬምበር 2005የአዲስ አበባው ዕልቂት በሚል ርዕስ ለአውሮፓ ህብረት ፓርላሜንት ለልማትና ውጭ ጉዳዮች እና ለሰብአዊ መብቶች ንዑስ ኮሚቴ አስቸኳይ ጥምር ጉባኤ የቃረቡትን ምስክርነት ይመለከቷል፡፡
***የመርማሪ ኮሚሽኑ ሪፖርት ሙሉ በሙሉ የጥቃቱ ሰለባዎችን ነጻ ሲያወጣ አጠቃላይ ኃላፊነቱን ግን በፖሊስና ታጣቂ ኃይሎች ላይ ደፍድፎታል፡፡ መርማሪ ኮሚሽኑ አስተያየቱን በመቀጠል እንደሚከተለው አጠቃሎታል፣ “በተቃዋሚዎቹ የተጎዳ ንብረት የለም፣ በመንግስት በሞኖፖል በተያዘው መገናኛ ብዙሀን እንደተለፈፈው ጥቂት ተቃዋሚዎች የእጅ ቦንቦችንና ጠመንጃዎችን ታጥቀዋል እንደሚለው ሳይሆን በተቃራኒው የእጅ ቦንብ እና ጠብመንጃ የታጠቀ አንድም የተቀዋሚ አባል የለም፣ በመንግስት ታጣቂ ኃይሎች የተከፈተው ተኩስ ሰላማዊ ሰልፈኞችን ለመበተን ሳይሆን በተቃራኒው የሰልፈኞችን ጭንቅላትና ደረት ለመበርቀስ ዒላማ ያደረገ ነበር፡፡” የመርማሪ ኮሚሽኑ የ193 የእልቂቱ ሰለባዎችን ስም ዝርዝር የያዘ ሰነድ የሚያካትተው እ.ኤ.አ ከጁን 6 – 8 እና ከኖቬምበር 1- 4/2005 በዚህ ጊዜ ብቻ ያለውን ድርጊት እንዲያጣራ ለአጣሪ ኮሚሽኑ የተሰጠው ስልጣን ነበር፡፡ አጣሪ ኮሚሽኑ ግን በፓርላማው ከተሰጠው የጊዜ ገደብ ውጭ ከህግ ውጭ በመንግስት የፖሊስና የደህንነት ኃይሎች የተፈጸሙ ግድያዎችን ስም ዝዝዝር ያገኘ ቢሆንም እነዚህ ግድያዎች ኮሚሽኑ እንዲያጣራ ተለይቶ ከተሰጠው ጊዜ ውጭ በመሆናቸ ለህዝብ ይፋ ሳያደርገው ቀርቷል፡፡