Tuesday, March 17, 2015

ልዩነታችን ጌጣችን፤ አንድነታችን ህልውናችን ነው

March17,2015
pg7-logoኢትዮጵያ ስንል ብዙ የተለያዩ ዘውጎች፤ ብዙ የተለያዩ ቋነወቋዎችና ሀይማኖቶች በአንድነት ይዛና አስተሳስራ ብዙ ፈተ ናዎችን በማለፍ ለረጅም ዘመናት ህልውናዋን ጠብቃ የቆየች ሀገር መሆንዋ መታወቂያዋ ሀገር ማለት ነው። እንዳ ሳለ ፈችው ረጅም ዘመናት ሁሉ እንደየዘመኑ በህልውናዋ ላይ ይቃጣ የነበረውን ጥቃት እነዚያ በዘውጎች፤ በቋነወቋዎችና ሀይ ማኖቶች የተንቆጠቆጡት ልጆችዋ በአንድነት በመሰለፍ ብሎም ድል በመምታት ህልውናዋን አስጠብቀው መዝለቃቸው የነጻነት ሀገር የመሆን መለያዋ ምክንያቶች መሆናቸውንም የሚያሳይ ነው።
ይህ ልዩነታችንን ጌጡ አድርጎ ያስተሳሰረን ኢትዮጵያዊነት በነፃነት የዘለቀ ህዝብ ከማድረግ አልፎ በአንድ ወቅት የስልጣኔ ምንጭና የአለማችን ሀያል ህዝብ ከመሆን ጫፍ አድርሶን እንደነበር አይዘነጋም። በዚያው ልክ ይህ በልዩነታችን ላይ የተገነባ አንድነታችን ሲላላ ህልውናችን ከገደል አፋፍ ላይ የደረሰበት ዘመንም በታሪካችን ውስጥ መታየቱ አልቀረም። “ዘመነ-መሳፍንት” በመባል የሚታወቀው ጥቁር የታሪካችን ክፍል አንዱ ተጠቃሽ ሲሆን ሌላው ዛሬ የምንገኝበት የወያኔ ዘረኛ ዘመን ነው። ትናንት በዘመነ መሳፍንት ህልውናችን አደጋ ላይ ወድቆ ነበር፤ ዛሬም በወያኔ ዘረኞች ዘመን ህልውናችን ከከፋ አደጋ ላይ እንዲገኝ ተደርጓል። በአጭሩ ልዩነታችን ጌጣችን አንድነታችን ደግሞ የህልውናችን ማስጠበቂያ ዋነኛው ቁልፍ መሆኑን መገንዘብ ለማናም አያዳግትም።
ሌላው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በታሪካችን ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ በህልውናችው ላይ የከፋ አደጋ ያንዣበበት ወቅት ላይ መገኘታቸው ከማንም የተሰወረ አይደለም። ዘመነ መሳፍንት ትናንት ቋንቋ ዘውግና ሀይማኖት ሳይለይ በእያንዳዱ ኢትዮጵያዊ ህይወት ላይ አስከትሎት የነበረውን ችግርና በሀገሪቱም ከአዘቅት የከተተ ከመሆኑም በላይ ይኸው እስከዛሬ ድረስ ውደ ቀድሞ ታላቅነቷ ለመመለስ ከባድ መሰናክል ተክሎ ማለፉን ከትናንት ታሪካችን መረዳት እየተቻለ ዛሬ በእኛ ዘመን ዳግም ከትናንቱ የከፋ ጥልቅ አዘቅት ውስጥእንድንፈቅ በዘረኞች እየተገፋን መሆኑንና ሊያስከትል የሚችለውንም ውጤት ለመረዳት የተለየ እውቀት አይፈልግም። ዛሬ ይህ ልዩነትን እያጎሉና ቂም በቀልን እየዘሩ መጓዛ የጥቂቶች ፍላጎት መሆኑ ባይካድም ከዚህ ቀደም ያስከተለውንና ዛሬም እየታየ ያለውን አደጋ ተገንዝቦ ከወዲሁ መከላከል የእያንዳዳችን ሀላፊነት ሊሆን ይገባል።
ጥቂቶች የህዝብ አሳቢ በመምሰል የሚረጩት የልዩነት መርዝ በሌሎች ሀገራት ላይ ያስከተለውን ፈተናም እንዲሁ ቆ ም ብሎ መፈተሽና ውጤቱንም መመዘን የፈሰሰ ውሀን አፋሽ ከመሆን ማዳኑን መጠራጠር የለብንም። የሶቭየት ህብረት መ ፍረስ፤ የዩጎዝላቪያ እርስ በርስ መባላት፤ የሶማልያ መቋጫ ያጣ ትርምስ ……. ወዘተ ንፁሀንን በገፍ የበላና ዜጎችን ለኢኮኖሚ ድ ቀት የዳረገ፤ በገፍ ስደትን ያስከተለ፤ የጦርነቶቹ መዘዝ ከልጅ ልጅ የማይታረቅ ቂም እያስቋጠረ መገኘቱ ሲታይ ዛሬ በእ ኛም ሀገር ጥቂት የመገንጠል አባዜ የተጠናወታቸው ይዘውን ሊጓዙ የሚፈልጉበትን መንገድ የት ሊያደርሰን እንደሚችል ከራ ሳችንም ያለፈ ታሪክ ሆነ በአለማችን ላይ የታዩ ክስተቶች ውጤት የሆነውን ትርምስና ሽብር በመመልከት ልንማርበትና ከወዲሁ አንድነታችንን በማጠናከር ለመከላከል መስራት ግድ ይለናል።
ከላይ እንደ ምሳሌ የተጠቀሱት ሀገራት በመበታተን ያተረፉተረ ሽብረ፤ ጦርነት፤ ስደትና ድህነት መሆኑ የታዘብነው የዘመናችን ክስተት ሲሆን ቀደም ሲል ለሁለት ተከፍላ የነበረችው ጀርመን ዳግም ከሁለትነት ወደ አንድነት መምጣቷዋ በሰጣት ሁለንተናዊ ጥንካሬ የዓለምችን ታላላቅና ሀብታም ሀገራት በኢኮኖሚ ውድቀት ሲመቱ ያለአንዳች ጭግር የፈተናውን ወቅት ያለፈች ሀገር ለመሆን መብቃትዋን ከአንድነት ሊገኝ የሚችለውን ሁለንተናዊ ጥንካሬ አጉልቶ የሚያሳይ ነው። ሌላው ከሀ ገራችን ህልውናን የማስጠበቅ ፍልሚያ ታሪኮች ውስጥ ጎላ ብሎ የሚታየው የአድዋ ጦርነትና ድል የአንድነትን ዋጋ ከፍ አድርጎ የሚያሳይ አኩሪ ታሪክ ነው። በዘመናዊ የጦር መሳሪያ ተማምኖ የመጣውን ወራሪ የኢጣልያ ጦር በተመጣጣኝ የጦር መሳሪበ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ተማምኖ የመጣውን ወራሪ የኢጣልያ ጦር በተመጣጣኝ የጦር መሳሪያና የሰለጠነ ሰራዊት ሳይሆ ን ቋንቋ፤ ዘውግና ሀይማኖት ሳይለያቸው ሁሉም በአንድነት ለሀገራቸው ህልውናና ለነፃነታቸው በአንድነት በመቆማቸው የተ ገኘ ድል መሆኑም መዘንጋት የለበትም።
ኢትዮጵያችን ደሀ ናት? አዎ ደሀ ናት። ህዝቧም ለዘመናት አንባገነን ስርአቶች እየተፈራረቁበት ህይወቱ የስቃይና የመከራ ሆኖ ቆይቷል? አዎ ቆይቷል። ሀገራችንን ከድህነትና ከዃላ ቀርነት፤ ህዝቧንም ከስቃይና ከመከራ ህይወት አውጥቶ የተሻለ ሀገር፤ ለመፍጠር ዛሬ የወያኔ ዘረኛ ቡድን የሚያራምደው የመንደር ፖለቲካ እውን መፈትሄ ነውን? ብለን ስንጠይቅ ያለፉት 23 የወያኔ የስልጣን ዘመናት እውነቱን ቁልጭ አድርገው ያሳያሉ። በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ ህዝብ በጅምላ ስደት፤ ለቁጥር በሚታክት ሁኔታከመኖሪያ ቀዬ መፈናቀል፤ እስር ቤት በእስር ቤተረ መገንባት፤ እናትና ልጅ ተፈራርተው መመካከር ያልቻሉበት ዘመን፤ ድህነት ከሚባለው ደረጃ ተወርዶ ጭራሽ የሆቴል ትርፍራፊ በጉርሻ የሚሸጥበት ዘግናኝ ወቅት ላይ ለመገኘት ምክኒያት ከመሆኑም በላይ ሀገር አለኝ ብሎ መኩራት እንኳ ከማይቻልበት ህልውናችን ከከፋ አደጋ ላይ የሚገኝበት ወቅት ሆኖ እናገኘዋለን።
ዜጎችን ነቋንቋ በዘውግና በሀይማኖት ከፋፍሎ ለመግዛት የሚያራምደው በታኝ የጥፋት ፖለቲካ ሌላው ቢቀር ዛሬ በቀን ሶስት ጊዜ በልቶ የማደር ሰዋዊ መብት እንኳ ማስከበር ከማይቻልበት ሁኔታ ላይ መደረሱ ከእያንዳዱ ኢትዮጵያዊ የተሰወረ አይደለም። በአንባገነኖች የተጫነበትን የአገዛዝ ቀንበር አስወግዶ የነፃነት አየር የሚተነፈስበት፤ ፍትህ የሰፈነበትና መብቶች የተከበሩበት ሀገር ለመፍጠር በተከፊለ የህዝብ ልጆች የህይወት ዋጋ ለስልጣን የበቃው ወያኔ በማር በተለወሰ መርዘኛ የዘር ፖለቲካው ሳቢያ የተገኘው ውጤት የእለት ጉርስን እስከማጣት የደረሰ ሆኗል ማለት ነው።
በአጭሩ ዛሬ ከ23 አመታት በዃላ እንደ ትናንቱ ሁሉ ይህን ርእሰ-ጉዳይ ማንሳታችን ያለ ምክንያት አይደለም። ይህ በለዩነታችን መካከል ለመገንባት ደፋ ቀና የሚባልለት የልዩነት አጥር እስካሁን የተፈለገውን ያህል ባይሳካም በጠንካራው አንድነታችን ላይ ያጠላው ጥላ ለምን አይነት አሰቃቂ ህይወት የዳረገን መሆኑና ጥያቄዎቻችን ለሆኑት ፍትህ፤ እኩልነትና ነፃነት ምላሽ ከማስገኘት ይልቅ ይባስ ለከፋ አፈናና አገዛዝ የዳረገን መሆኑን ተገንዝበን ቀኑ ሳይመሽ ከወዲሁ ለመፍትሄው በጋራ መስራትብቸኛ አማራጭ መሆኑን ሁሉም እንዲገነዘበው ነው።
3000 ዘመን ያለ ፈተና የተቆጠረ የነፃነት ዘመን አይደለም። የገጠሙን ፈተናዎች በሙሉ በልዩነቶቻችን ላይ በተገነባው ጠንካራ ኢትዮጵያዊ አንድነታችን ተጠብቆ የተገኘ እንጂ…… ዛሬም ቢሆን ዜጎች ልዩነቶቻቸውን የጥንካሬያቸው መሰረት በማድረግ በአንድነት ነፃነታቸው የተረጋገጠበት፤ መብቶቻቸው የተከበሩበት፤ ፍትህ የሰፈነበት ሀገር ለመፍጠር የተጀመረውን ሁለገብ ትግል በማጀብ ከዳር ለማድረስ ለመነሳት ያለፉት 23 አመታት ከበቂ በላይ መሆኑን አጢነን በቃ የምንልበት ወቅት ላይ እንደምንገኝ ለማሳሰብ ነው።
ትናንትም ዛሬም ነገም ልዩነቶቻችን ጌጣችን አንድነታችን ህልውናችን መሆናቸውን ተረድተን ሳይመሽ ሁላችንንም በእኩልነት የማታስተናግድ የሁላችንን ኢትዮጵያ ለመገንባት እንነሳ!!!!!
ኢትዮጵያችን ለዘላለም ትኑር!!!!

No comments: