Tuesday, July 23, 2013

ሰበር ዜና: ወያኔ ኢህአዴግ አንድነት ፓርቲን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ

በደቡብ ወሎ ዞን በሚገኘው ኩታበር ወረዳ አንድነት ፓርቲ ሐምሌ 7 ቀን 2005ዓ.ም. በደሴ ያካሄደውን ህዝባዊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በመቃወም ህዝቡ ሰላማዊ እንዲወጣ ኢህአዴግ እያስገደደ መሆኑን ምንጮቻችን በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡

 የኩታበር ወረዳ ነዋሪ ሰልፍ እንዲወጣ የተደረገው ነገ ረቡዕ ሐምሌ 17 ቀን 2005 ዓ.ም. ጠዋት መሆኑም ታውቋል፡፡

 በተለይ ሰፊ የማስፈረሳሪያና የቅስቀሳ ስራ እየተካሄደ ያለው በወረዳው ቀበሌ 05፣06 እና 07 መሆኑንም ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

 ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢህአዴግ ካድሬዎች ገበሬውን በግድ ከአቅሙ በላይ የዘር ማዳበሪያ ውሰዱ እያሉ ከፍተኛ ገንዘብ ከማስከፈላቸው በተጨማሪ ለአልማ(ለአማራ ልማት ማኀበር)፣ለአባይ፣ ለመሬት ግብር እየተባሉ ከፍተኛ ዋጋ በመጠየቃቸው እና ነዋሪዎቹ አቅማቸው እንደማይፈቅድ ሲናገሩ ወደ እስር ቤት እየተወሰዱ በመሆኑ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ከአካባቢው እየተሰደዱ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

ማዳበሪያና ዘር አንወስድም ያሉ ገበሬዎችንም መሬታችሁ ይነጠቃል በሚል የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ደምሴን ጨምሮ የወረዳው ሹማምንት እያስገደዱ እንደሆነ ነዋሪዎቹ በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡

ስለጉዳዩ የዝግጅቱ ክፍሉ የወረዳውን አስተዳደር አቶ ደምሴን እና የወረዳውን ግብርና ጽህፈት ቤትና የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችን ለማናገር ጥረት ቢደረግም አልተሳካም፡፡

#milloinsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ

“I am Ethiopian first” Abebe Gellaw

by Abebe Gellaw
July 23, 2013

Abebe Gellaw Ethiopian Journalist and activist
It has come to my attention that my brief Facebook comment regarding a few controversial statements made by Jawar Mohammed has been posted on ECADF’s website as an article. I had no intention of writing a series piece on the issue. Quite obviously, there is a big difference between a well-thought out length y commentary and a brief message in a particular context.

My intention was just to appeal for calm and harmony, a necessary effort lacking in our political discourse. Often times, a message without its context is open to misinterpretation and misunderstanding. So there seems to be a need to clarify.


Politics, as far as I understand, is a mechanism of managing conflict of interests. It is a means of building consensus through dialogue and compromise. Since the early 1960s, the major political conflict in Ethiopia has been between ethno-nationalists and nationalists. The forces on both ends of the political spectrum have not still found a middle ground that can bring them towards consensus and compromise.

My understanding is that Jawar is an ethno-nationalist. As an ethno-nationalist, he says he is an Oromo first. Unlike him, I am a nationalist. But that is not the major problem. The problem is the way he has chosen to articulate and present his views in question that have been widely perceived as inflammatory and divisive.

I firmly and fervently believe that I am an Ethiopian first. I do not wish to allow the ethnic origin of my predecessors and parents to define me as a human being and overshadow my Ethiopian identity.
Jawar said Ethiopian identity was imposed on him. On the contrary, I argue that such a position is fundamentally flawed. Nowhere in the world is anyone given choices of national identity.

The Chinese-American writer, Eric Liu, once said: “The next time someone uses denial of citizenship as a weapon or brandishes the special status conferred upon him by the accident of birth, ask him this: What have you done lately to earn it?” Our predecessors, who have bequeathed us a country called Ethiopia with all its faults, challenges and problems, have made huge sacrifices in blood and flesh so that we’ll never be stateless. We should rather make sacrifices to reclaim our country and make our citizenship more meaningful by winning our rights, as citizens, to live in our country with full dignity, freedom and equality. We should make Ethiopia a country where every citizen and ethnic group is equal.

Unfortunately, our birthplaces also define the major problems and opportunities we inherit. Ethiopia is not a perfect nation. Far from it, it is defective and faulty as a result of the age-old tyrannies and injustices we have been condemned to suffer collectively.

Like any nation, it offers unique challenges as well as opportunities. With all its problems and baggage, Ethiopia is a nation of 80 million people. Our destiny is intertwined. We are diverse and yet we are all Ethiopians, whether we like it or not. I believe that rejecting Ethiopia as our country is not a solution to any of the problems we are supposed to confront. We should rather make strenuous efforts to reconstruct Ethiopia as a country where all of its citizens live in freedom, harmony, justice, peace and prosperity.

In the new Ethiopia we envision, there should be no room for inequality, injustice and tyranny. It should never be a prison for its children, regardless of their political, ethnic or cultural backgrounds. No ethnic or political group should be allowed to impose hegemony at the detriment of the majority.
The worst challenges all citizens of Ethiopia, except the oppressors, face are political oppression, grinding poverty, indignity, inequality, injustice and discrimination, just to mention a few among so many. At this time and age, what has been imposed on us is not national identity but the tyranny of the TPLF, an extremist ethno-nationalist group whose aim was nothing more than seceding Tigray. That is why we should continue struggling to throw off this backbreaking tyranny from our shoulders.

As I have clearly stated in another Facebook post, addressed to Jawar, “No nation-state was formed through consensus and democratic deliberations. Nation-states emerged out of conflicts, conquests, occupations and colonialism. While almost all African states were created by the colonial powers, Ethiopia was formed through internal processes. It was a painful process but not even as painful as what Native Americans and Europeans, who had gone through two devastating [world] wars.”

“We Ethiopians do not need to be bitter about the past. We are not part of the old history. But we certainly need to preserve our country and make it a nation for all correcting past injustices and mistakes. We need to move forward with a united spirit. As long as we can bring about real equality, justice, freedom and democracy, we will be fine. That is what we should all fight for rather than dwelling on the past [and gnaw old bones]. It is the present and the future that really matter….”
While I called for unity rather than condemning each other, making such inflammatory and controversial statements that turned out to be divisive are not only wrong but also damaging to our common cause for freedom. I said Jawar had misspoken. The dictionary definition of misspeak is not to endorse or approve. It means, “To speak mistakenly, inappropriately, or rashly.” I think that should be clear enough. It was particularly wrong for Jawar to speak in such a divisive ethno-religious tone at a time when we desperately need to unify to overcome and overwhelm the divide-and-rule tyranny of the TPLF. That is where he misspoke, in my humble opinion, without completely disregarding so many positive contributions.

I was under the impression that calling for sanity and unity at this critical juncture in our struggle would not also be misconstrued as a sign of weakness. I always see myself as a moderate.
Compromise for the sake of the greater good is at times a mechanism to avoid unnecessary conflict and feelings. Even if that was my intention, I believe that we Ethiopians should never compromise on anything that undermines our unity, freedom, harmony and peace.

After all, our aspiration is to rebuild a united nation that will accommodate every citizen as equal and guarantee the freedom of every individual citizen including those who believe that they are the byproducts of their cultural and ethnic heritage. For that to happen, we need to preserve Ethiopia, a country that we will all be proud of when we claim our freedom despite its troubles and predicaments.

Anyone is not entitled to apologize on behalf of Jawar. If any apologies are needed, no one but only Jawar is entitled to make. As far as I am concerned, I am nobody’s apologist.

That said, I will be disingenuous if I do not repeat my main message. Let us move on with a united spirit and focus on our just cause for freedom, equality and justice. That is much more important than the war of attrition and divisiveness that is derailing our gains. Whenever we have problems, we should first have the courage to address them in a civilized manner. Again let us move on united as Ethiopians…

ሃይማኖት እና ብሄር ካለፈው እና ከአሁኑ ታሪካችን ተምረን ለእውነተኛ ዲሞክራሲ እንታገል

July 22, 2013
by Ephrem Shaul

የዚህ ጹሁፍ አላማ ከታሪክ ስህተቶቻችን ተምረን ወደፊት የማይደገምበትን እውነተኛ ዲሞክራሲ ለሁላችን መፍጠር ላይ ትንሽ ሀሳቤን ለማካፈል ነው። የኢትዮጲያ ህዝብ ታሪክ ጥሩም መጥፎም ታሪክ እንደማንኛውም ሀገር አለን። አኩሪ ታሪክ ያመሰገብን እንደመሆናችን ሁሉ ክፉ የታሪክ አሻራም አለን። ዜጎች በነጻነት ለመኖር ያልታደልንበት አሳዛኝ እና አስከፊ ግዚያቶች በታሪካችን ጎልተው ይታያል። አሁንም በአስከፊ ሁኔታ በወያኔ ኢሃዴግ ተጠናክሮ አፈናው ቀጥላል። በዚህ እውነት ውስጥ የሚነሳው የኦሮሞ ህዝብ መበደል፣ አስከፊ እንዲሁም አሳዛኝ ሰቆቃ ነው። ይህ አስከፊ እንዲሁም አሳዛኝ ሰቆቃ መከሰቱ እጅግ አሳዛኝ ነው። መከሰቱን መካድ መፍትሄ አይደለም። የተፈጠረውን ግፍና ችግር በአግባቡ ተረድተን ስናበቃ ዘላቂ መፍትሄ የሚያመጣውን መንገድ መምረጥ ብልህነትና የዚህ ትውልድ የታሪክ ሃላፊነት ነው። የሰውነትና የዜግነት ግዴታም ነው። በተመሳሳይ የምናነሳው የኢትዮጲያ ሙስሊሞችን አሳዛኝ በደል ነው። አስልምና በአርብ ሀገራት ከፍተኛ ችግር በገጠመው የታርክ ዘመን ኢትዮጲያ ተቀብላ ያቆየችበት ታሪክ እንደመኖሩ ሁሉ አሳዛኝ ችግሮችም አሉ። ይህን በደል ተረድቶ ለሁሉም ዜጋ የምትሆን ኢትዮጲያን መፍጠር ግዴታችን ነው።

 ይህ የታሪክ ክፉ ኣሻራ በኦሮሞ ክርስቲያኖችም ላይም ተፈጽማል። የሁሉም ብሄር ተወላጅ በሆኑ ፕሮተስታንት ተከታዮች ላይ ተፈፅማል። ኣርቶዶክስ ኢትዮጲያዊያን ላይ አሁን ያለው ስርአት ጣልቃ ገብቶ መቆጣጠሩ የታወቀ ነው። በሃገራችን ታሪክ ኦሮሞ፣ ሶማሌው አፋሩ ጋንቤላው አማራው ትግሬው ውላይታው ጉራጌው ሲዳማው ከንባታው ሱሪው ኮንሶ ኮሬ አደሬዉ ቤንሻንጉሉ ወዘተ ተበድላል። ሁላችን በታሪካችን ውስጥ ብሶት አለን። ይህን እውነት (fact) በአግባብ መረዳትና ማስረዳት ወሳኝ የአክቲቪስትና የፖለቲከኛ ስራ ነው። በአንጻሩ ደግሞ እምነትን መስበክ በሰላማዊ ትምህርት ማስፋፋት የሃይማኖት አባቶች (ቄስ ሽክ ፓስተር ወዘተ) ስራ ነው።

ፓለቲከኞች የራሳቸውን እምነት ለራሳቸው ይዘው ለሁሉም ዜጋ የሚሆን (ለሁልም ብሄር እና እምነት) በነጻነት እና በክብር የምንኖርበትን ሀገር እውን ለማድረግ መረባረብ አለባቸው።  ግዜን እውቀትን ገንዘብን አቅምን ማዋል ያለብን እዚ ላይ ነው። የሚባክን ግዜ የለንም የዜሮ ድምር ፓለታካም አያስፈልገንም። የእምነት ትንታንኔ ስራና አስተምህሮት የሃይማኖት አባቶች ስራ ነው። የፖለትቲከኛ ስራ ጨርሶ አይደለም። ይህን ብሄር ያንን እምነት የበላይነት ለማምጣት መሞከር ኢፍትሃዊና ኢዲሞክሪያሲያው ነው። የታሪክን ችግር መድገም ነው። የዲሞክራሲ ትግሉን አላማ መሳትና ግዜውን ማርዘም ነው። የራስን በደል ብቻ መመልከት ሌላውን አይመለከተኝም ማለት የታሪክን በደል እንደመካድ ይህም ስህተት ነው። የሁሉንም በደል ተረድተን በጋራ መስራት አርቆ አሳቢነትና አስተዋይነት ነው። ለሁላችንም ነጻነትና ፍትህ የምትሆን አገርን መገንባት ትክክለኛ ራዕይ: ድፍረት: ቆራጥነት ይጠይቃል። የአመራር ችሎታ ግድ ይላል። ይህ ወያኔ ኢሃዴግ እንደሚለው በወሬ ሳይሆን ተግባራዊ ቁርጠኛነት ይጠይቃል። ይህ የትላንት እና የዛሬ በደሎችን እንዳይደገም ዋስትና ይሰጣል ዘላቂ መፍትሄውም ይህ ብቻ ነው። ቅንነትን ሁላችን ከያዝን ከባድ አይደለም። የአመራር ችሎታ ማለት (leadership quality) ህዝብን ፍትሃዊ በሆነ ስርአት የዜጎችን ነጻነት አክብሮ እና አስከብሮ መምራት ማለት ነው። ግጭት አምጪ ሀሳብችን ወይም ድርጊት ማስፋፋት ለማንም አይጠቅምም የአመራር ችሎታም ጨርሶ ኣይደለም። አሳዛኝ የታሪክ ስህተቶችን ተረድተን ካለፈው ስህተት መማር ወሳኝ ነው። ነገር ግን የተፈጠሩ ስህተቶችን ተከትለን ሌላ ኢፍትሃዊ ስርአት ለማምጣት ማስብ የለብንም በጣም አደገኛ ስህተት ነው። ከችግሩ ሳንወጣ እዛው እንድንዳክር ከማድረጉም በላይ እንደ እስተሳስብም የተሳሳተ አካሃድ ነው።

በኢትዮጲያ ውስጥ ለኢትዮጲያ አንድነትና ነጻነት የታገሉ የታሪክ ደማቅ አሻራ የጻፉ የተለያየ ብሄር ተወላጅ ኢትዮጲያዊያን (ሙስሊምና ክርስትያን) በገዛ ሀገራችን በታሪክ ተበድለን መቆየታችን አሳዛኝ ነው። ያልተበደለ ህዝብ የለም በዳዪ ደግሞ አንድ ቡሄር አይደለም። በአንድ ብሄር ስም ስልጣን ላይ የወጡ ገዥ መደቦች ናቸው (የተለያዮ አምባገነን ስርአቶች ናቸው) በስልጣልን ላይ ያለው የወያኔ ሰርአት ከትግራይ ህዝብ ተለይቶ መታየት አለበት። ስርአትንና ብሄርን ለይቶ ማየት ለአክትቪስት ወይም ፖለቲከኛ ሀሁ/ABCD ነው። አሁን ስልጣን ላይ ያለው ሰርአት በኦሮሞ ላይ የሚያደርሰውን በደል የሚያስፈፅምለት ኦህዴድ ተብሎ የተደራጀው የኦሮሞ ተወለጅ ናቸው። በተመሳሳይ በአዴን በአማራው ላይ፣ ህውሃት በትግራይ ህዝብ ላይ ደህዴን በደቡብ ፤ አጋር የሚላቸው ድርጅቶች በሶማሌው፣ በጋምቤላው በአፋሩ በቤንሻንጉሉ ላይ ተጋግዘው ነው ህዝቡን ስቃይ የሚያበሉት። ይህ እውነታው ነው፤ ይህንንም መቀበል የተሳሳተ መስመር ከመከትል ያድናል መፍትሄውም የአሁኑን የአንባገነንነት ስርአት የመጨረሻ አድርጎ ዲሞክራሲ ለሁሉም ለማስፈን መታገል ነው። ከታሪክ በአግባብ ተምረን ስናበቃ ስህተቱን አውግዘን መልካሙን ደግም ለማበልጸግ መስራት አለብን። ከታሪክ መማር እንጂ የታራክ እስረኛ መሆን የለብንም። ራእይ ያለው ትውልድ መሆን ያስፈልጋል። ራዕያችን ደግሞ ዲሞክራሲያዊና ሁሉን ያሳተፈ መሆን አለበት (inclusive democracy)። ውድድር የበዛበት አለም ውስጥ ነው የምንኖረው። ችግራችንን ለዘለቄታው በአፋጣኝ ፈተን አስከፊ ስርአትን ለውጠን በአዲስ መንፈስ በፍትህና ዲሞክራሲ መመራት አለብን። ከታሪክ መማር ወሳኝ የመሆኑን ያህል ፤ የታሪክ እስሪኛ መሆን ለግለሰብም፣ ለቤተሰብም፣ ለብሄርም፣ ለእምነትም፣ ለሃገርም ሆነ ለአለምም አይጠቅምም።  ወደ ሃላ እያዪ ወደ ፊት በትክክል መሄድ አይቻልም። አንድ ምሳሌ ልጨምር የመኪና ሹፌር በጎን መስታወቶቹ ወደሃላ አይቶ አደጋ እንዳይጥመው ይከላከላል ነገር ግን ወደፊት በአግባቡ ካላየ አደጋ የገጥመዋል፤ ወደፊትም መሄድ አይችልም። በዘላቂ በመፍሄ ላይ ያተኮረ አቅጣጫ ላይ ሙሉ አቅምን ማዋል አስፈላጊና ወሳኝ ነው። የምንታገለው ስርአት ሌት ተቀን ተግቶ ስልጣን ላይ ለመቆየት ይሰራል። ሲለው ይገላል ሲያሻው ያስራል የሃገሪቱን ሰልጣን ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ በሙሉ ተቆጣጥራል። ይህ ስልጣን ሊያረጋግጥ ፈፅሞ አይችልም። ወሳኙ የህዝብ ድጋፍ ነው። ይህ ደግሞ አንባገነን ስርአቶች ጨርሶ የላቸውም የህዝብ ድጋፍ ኖራቸው አያውቅም ሊኖራቸውም አይችልም።

ዲሞክራሲ እና ነጻነትን ለማምጣት ነው ትግሉ። ከዚህ የወጡ እርስ በርስ የሚያጋጩ አስትያየት ሲስነዘር ወደ መፍሄ እንደማይወስድ በግልጽ መንገር የሁላችንም ግዴታ ነው። ወደ መፍሄው እንጂ ወደ ብጥብጥ የማይወስደውን መንገድ መምረጥ  ደግሞ በሳልነት ነው። ስህተትን ተቀብሎ ማረም ስህተቱን የሰራው ወይም ሊሰራ ያሰበ አካል ሃላፊነት ነው። ከወያኔ ስህተት ተቃዋሚ መማር አለበት። የወያኔን አድሎአዊና ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲን ስንቃውም እኛ እንደማይደገም ማረጋገጥ መቻል አለብን። በታሪክ ጎልተው የሚታዩ አስከፊ በደሎች ኣሁን ባለንበት ዘመን በወያኔ ኢሃዴግ ተባብሶ ቀጥላል። ዜጎች በነጻነት እንዳያምኑ በእምነት ተቍማት ጣልቃ ገብነቱ ከፍታል። ዜጎች በነጻነት ሀሳባቸውን እንዳይገልፁና በነጻነት በሚመርጡት መሪዎች እንዳይተዳደሩ አፈናው ቀጥላል። ጋዘጠኞች፣ የፖለቲካ ድርጅት አመራሮች ኣባላትና ደጋፊዎች አሸባሪ ተብለው በሃሰት ተከሰው ታስረዋል። የሃይማኖት ነጻነት የጠየቁ ሙስሊም ኢትዮጲያዊያን አሸባሪ ተብለው በሃሰት ተከሰው የድራማ ፕሮፓጋንዳ በአደባባይ ተሰርቶባቸው በግፍ ታስረዋል። ሁሉ ብሄር በግፍ ተጨቁኖ ጥቂት የስርአቱ ደጋፊዎች ተንደላቀው የሚኖሩበት ሀገር ሆናለች ኢትዮጲያ። ይህ ፈጽሞ ፈትሃዊ አይደለም። መጻፍ እና ሀሳብን በነጻነት መግለጽ አሽባሪነት ተብሎ የሚያስፍርጅበት ክፉ ስርአት ተፈጥራል። ይህ ለማንም አይበጅም ለሀገር፣ ለህዝብ፣ ለራሱ ስልጣን ላይ ላለው አስከፊ ስርአት አደጋ ነው።

በተመሳሳይ ለሃይማኖት ነጻነት የሚደረግ ትግል የሌላውን እምነት ነጻነት ማክበር አለበት። እዚህ ላይ ትክክለኛውን መንገድ መምረጥ የሁሉም እምነት አባቶች እና የእምነቶቹ ተከታዮች ሃላፊነትና ግዴታ ነው። የሃይማነት ነጻነት ትግል ወሳኝ ነው ነግር ግን አካራሪነትን ጨርሶ በየትኛውም እምነት ውስጥ ማስከተል የለበትም። ሀይማኖት የግል ሀገር የጋራ እንደሚባለው። ሀይማኖትና ፖለቲካ መደበላለቅ የለባቸውም። ሀይማኖት የግል ስብእናችን ነው። እያንዳንዳችን ፈጣሪያችንን የምናመልክበትን መርጠን የምንከተለው ነው። በኛና በፈጣሪያችን መሃል የምንከተለውን መንገድ የሚመራን ነው። ለሁሉም እምነት መከበር ደግሞ በጋራ ሁላችን መስራት አለብን። በተመሳሳይ የተሳሳተ አስተሳሰብንም በጋራ ሁላችን መቃወም አለብን። የጋራ በሆነችው አገራችን ደግሞ ለሁላችን በፍትህና በነጻነት እንድንኖር በጋራ የምንመራበት ሁሉን አሳታፊ ዲሞክሪያሲያዊ ስርአት መገንባት አለብን። ሀይማኖትና ፓለቲካ መደባለቅ የለበትም ፤ የእምነት ነጻነትንም ለሁሉም ለማምጣት አይችልም። ይህ እውነታን ለመገንዘብ ፖለቲካል ሳይንስ ማጥናት አያስፈልግም ፤ ስፔስ ሳይንስም አይደለም። ይህን ችግር ለዘለቄታው መፍታት የዚህ ትውልድ የታሪክ ሃላፊነትና ግዴታ ነው። ሀገር እንድታድግ የዜጎች ነጻነት መከበር አለበት ፤ ይህ ደግሞ ዜጎች ያላቸውን በጥረት ራስን የማሳደግና የማበልጸግ ራእይ ለማሳካት ወሳኝ ነው። የሃገርም እድገ መሰረት ነው። ለብሄራዊ ራዕይ እና መግባባት ወሳኝ ነው። ባለንበት ግሎባላይድ አለም ተፎካካሪና ውጤታማ ለመሆን ትክክለኛ ራዕይ እና ጠንክሮ መስራት ወሳኝ ነው ። ለዚህ ደግሞ ዜጎች የምንሰራበትን እደል ለመፈጠር የዜጎች ነጻነት ያለማወላወል መከበር አለበት።  የምንመኛት ኢትዮጲያ ለሁላችን ሀገር መሆን አለባት። ለኦሮሞው፣ ለአማራው፣ ለሶማሌው ለትግሬው ለአፋሩ ለጋምቤላው ለሃረሬው ለቤንሻንጉሉ ለሲዳማው ለጉራጌው ለወላይታው ለሃዲያው ለኮንሶው ለሱሪው ለኒያጋቶም … ወዘተ  እንዲሁም ለክርስትያኑ ለሙስሊሙ ለባህል እምነት ተከታዩ እምነት ለሌለው በአጠቃለይ ለሁላችንም የምትሆን ኢትዮጲያን እውን ማድረግ ነው መፍትሄው።

አንድነታችን ሁሉንም ያከበረና ያቀፈ መሆን አለበት። የሁላችንም ኩራት የሆነች ኢትዮጲያን እውን ማድረግ አለበት። ለዚህ ደግሞ የውስጥ ችግሮቻችንን እውነትኛ ዲሞክራሲ ስርአት ላይ መስርተን በአፋጣኝ መፈታት አለብን። እውነተኛ ዲሞክራሲ ከገነባን አብዛኛውን ህዝብ ከሚውክለው ኦሮሞ፣ አማራ፣ ሶማሌ፣ ትግሬ ብሄሮች እስከ አነስተኛ ህዝብ ቁጥር ያላቸውን ቤንች፣ኮንሶ፣ አላባ፣ እና በጣም ጥቂት ህዝብ ቁጥር  ያላቸውን ኒያንጋቶም፣ ሙርሲ፣ ካሮ የሁሉም መብት ተከብሮ በሰላም በፍቅርና አንድነት የምንኖርባት ኢትዮጲያን እውን ማድረግ ነው ያለብን። በዚህ አይነት መሰረት ላይ የቆመ አንድነት ተሰሚነት ያላት በአካብያዊ ፖለቲካም ሆነ በአለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የራስዋን አውንታዊ ሚና የምትጫወት ጠንካራ ኢትዮጲያን እውን ማድረግ ያስችላል።

እንደ አገር አንድ መሆን ይበጀናል አንድነታችን ደግሞ ሁሉያን ያቀፍ እና ያሳተፈ (inclusive) እንዲሆን ሁላችንም መስራት አለብን። አሁን ያለንበት የአለም እውነታ የሚያሳየን የአንድነትን ጥቅም ነው። ሀገራት ጥቅማቸውን ማስጠበቅ የሚችሉት በጠንካራ መሰረት ላይ የቆመ አንድነት ሲኖር ነው። አለም ላይ ያለው ተጨባጭ እውነታ የሚያሳየን ይህን ነው። በአለማችን ጠንካራ አቅም ያላት ሀገር ስንሆን ተሰሚነታችን ይጨምራል። ፈተናዎችን በተሻለ አቅም ማሸነፍ ያስችለናል። አውሮፓ(EU)፣ አፍሪካ (AU)፣ ደብቡ አሜሪካ (ECLAC) የአንድነትን ጥቅም አስልተው አንድነቱን አጠናክራል። በአንድ ድምጽ በአለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የራሳቸውን ጥቅም ለማስከበር አየሰሩ ነው።  አውሮፓ የተለያዮ ሀገራትን አሰባስቦ ጠንካራ አቅም ገንብታል። እነዚህ ሀገራት በጣም አስከፊ የእርስ በርስ ግጭት አሳልፈዋል። ያሳለፉት ታሪክ እስረኛ ሳይሆኑ ከታሪክ ተምረው ጥቅማቸውን ለማስከበር በጋራ እየሰሩ ነው። እስያም በተመሳሳያ የራሳን ብዙ የትብብር መድርኮች ፈጥራለች (SASEC, ACD, APDC..)። አረብ አገራት የራሳቸውን የትብብር መድረክ ፈጥረዋል (Arab League, GCC )። አገራት የጋራ ጉዳያቸውን እየፈለጉ በጠንካራ ትብብር እየሰሩ ነው።

ከዚህ ሪጅናል ትብብር (regional cooperation) በተጨማሪ በተለያየ አካባቢ እና በተለያየ አለም ክፍል የሚገኙ ሀገራት የተለያየ የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካዊ፣ ውታደራዊ እና የጽጥታ ትብብር መስርተው ይሰራሉ። ጥቅማቸውንም በጋራ ያስከብራሉ። አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ (EU-US) ትራንስ አትላንቲክ ኮኦፐሬሽን፣ ኢስት ኤዥያ ላቲን አሜሪካ ኮኦፐሬሽን፣ ቻይና አፊሪካ ፣ ሰሜን አሜሪካ አፍሪካ ወዘተ። በዚህ በትብብር አገራት ጥቅማቸውን በሚያሰጠብቁበት አለም ጠንካራ አንድነት ከሌለን ተወዳዳሪ መሆን ይቅርና ተሰሚነትም አይኖረንም። መበታተን የራሳችንንም ሰላም አያስገኝልንም። መበታተን ዲሞክራሲን ፈጽሞ ጋራንቲ አያደርግም።

ይህን አለማቀፋዊ ሁኔታ፣ ተፈላጊውን ከፍተኛ ደረጃ ጠንካራ ፉክክርና ትብብር ግምት ውስጥ ያላስገባ ጥላቻን የሚያባብስ እርስ በእርስ የሚያጋጭ አክራሪነትን የሚያበረታታ አስተያየት ሲሰጥ ከየትም ይምጣ ከየትም፡ ከማንም ይምጣ ከማንም ስህተት መሆኑን ሁላችን በጋራ አንድ ሆነን ልንናገር ያስፍልጋል። ከታሪክ ስህተት መማር እንጂ የታሪክን ስህተት ማስቀጠልም ሆነ በሌላ አካል መድገም የለብንም። የምንኖረው ግሎባላይድ በሆነ አለም ነው (globalized world). ሀገራችን በውስጥ ትክክለኛ ዲሞክራሲ ላይ ተመስርታ ስታበቃ፤ ከምስራቅ አፍሪካ፣ አፊሪካ እንዲሁም ከመላው አለም ጋር ጤናማ ግንኙነት መፍጠር አለብን። በጅብቲና በአካባቢው ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ገብተን የምንበጠብጥበት (intervening in other countries internal affairs) በፓለቲካም ይሁን በኢኮኖሚ ወይም ሀይማኖትን መሰረት አድርገን ማስብም ይሁን ማቀድ ጤናማ አስተሳሰብ አይደለም፤ መልካም የጉርብትና ትብብር እና ሰላም አይፍጥርም። ከአለም አቀፍ ህግጋትም ጋር ይጣረሳል ከፍተኛ ችግርም ያስከትላል (severely violets international laws and results serious and long term consequences on our country).

በሃገራችን የውስጥ ጉዳይ ለፍትህ መታገል ለነጻነት መታገል ይገባል ትክክልም ነው። ይገባልም። ይህ ትግል ለኦሮሞ ሙስሊሞች ብቻ ሳይሆን ለኦሮሞ ክርስቲያኖች፤ ሙስሊምም ክርስቲያንም ለልሆኑ ኦሮሞዎች፤ ኦሮሞ ለልሆኑ ክርስያኖች፤ ኦሮሞ ላልሆኑ ሙስሊሞች በአጠቃላይ ለሁሉም ኢትዮጲያዊያን ነጻነትና ፍትህ መታገል የሰውነት፣ የኢትዮጲያዊነት የሞራል ግዴታ ነው። ለመብት ስንታገል የህዝቦችን አብሮ የመኖር አሴት (solidarity, coexistence, and multiculturalism, merits of unity) ፍቅር፣ መዋድድና መከባበር (love, tolerance, respect for diversity) ለግል ክብር፣ ተዋቂ ለመሆን፣ ለስልጣን ስንል ለመናድ መሞክር ማናችንም ጨርሶ ማድረግ የለብንም። እኛ ስናልፍ ሀገርና ህዝብ አያልፍምና።  ለኦሮሞ መብት መከበር ሁላችን መታገል አለብን። ለአማራውም፣ ለትግሬውም ለሱማሌው ለወላይታው  ወዘተ ፤ እንዲሁም ለሙስሊሙ ለክርስትያኑ ለማያምነው ወዘተ በአጠቃላይ ለሁላችን መብት ሁላችን በጋራ መስራት አለብን። ከአለንብት የበድል አዙሪት የምንወጣው ያኔ ብቻ ነው።

ያለፉ የታሪክ ስህተቶችን መካድም አይጠቅምም (denial of historical injustice) ። ችግሩን የፈጠሪው አንድ ብሄር ደግሞ አይደለም (blaming one ethnic group for historical injustice is unjust)። ጥቂት ገዥ መደቦች (few ruling group) ናቸው ። በተመሳሳይ በግል ጥቅምና ለተዋቂነት በሚደረግ ርጫ እንዲሁም በስሜት ላይ የተመሰረተ የጥላቻ ፖለቲካ (emotion driven politics) ፤ ግትርነትና (rigidity) አግላይ የፖለቲካ አቁአም (exclusionist  politics) ለማንም አይጠቅምም። የአጭር ግዜ ፓለቲካ (short termism) የጥላቻ ፖለቲካ (spreading of negative consciousness and hatred) ለማንም አይጠቅምም።

ለፍትሕና ለነጻነት መታገላችን ሰብአዊነትን እና ሁሉን ያሳተፈ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን። ኢንፓውርመንት (empowerment) ማለት ህዝብ መብቱን እንዲጠይቅ ማሳወቅ እና ማስተባበር ማለት ነው። ፈትሃዊነትን ከልብ የተቀበለ ህዝብና ህዝብን በሃይማኖት ማበጣበጥን ያወገዘ መሆን አለበት። ጤናማ አክቲቪዝም (activism for democracy, freedom, sustainable & long term peace and justice) እና ኢንፓወርመንት (empowerment) ትርጉሙ ይህ ነው። ለእውነተኛ ዲሞክራሲ እንታገል።
ይህን ጽሁፍ ወደ ኦሮመኛ እና ሌሎች የሃገራችን ቋንቋዎች በቀጥታ ለሚተርጉምልኝ ምስጋናዬ ወደር የለውም።  እንደ አስፈላጊነቱ የእንግሊዘኛ ትርጉሙን ከተጨማሪ ማብራሪያ ጋር አዘጋጅቼ ብቅ እላለሁ።

ከምስጋና እና ታላቅ አክሮት ጋር በዚህ ላብቃ።

ቤልጂየም (Belgium)

አስተያየቶን በሚከተለው ኢሜል ይላኩልኝ።   fiftoze@yahoo.co.uk

Monday, July 22, 2013

በቂሊንጦ የሚገኙ እስረኞች በሞት አፋፍ ላይ እንገኛለን አሉ

ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ አቶ ተሻለ በካሻ መዝገብ ተከሰው ከሁለት አመታት በላይ በእስር ቤት የቆዩት እስረኞች ሰሞኑን ከፍተኛ ድብደባ ከተፈጸመባቸው በሁዋላ ለተከታታይ ቀናት ምግብ ባለመመገባቸው ህይወታቸው አደጋ ላይ መውደቁን በመግለጽ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲደርስላቸው አቤት ብለዋል።

እስረኞቹ በጻፉት ደብዳቤ ላይ  ከውጭ የመጡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በፌሮ ክፉኛ እንደደበደቡዋቸውና ህክምና በማጣታቸው ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል። ፍርድ ቤት በቀጠሮአቸው ቀን እንዳይቀረቡ መከልከላቸውን ለመቃወም ለበላይ አካላት ደብዳቤ በመጻፋቸው ምክንያት ድብደባ እንደተፈጸመባቸው የገለጹት እስረኞቹ ፣ ጉዳዩን ለቂሊንጦ ዋና አስተዳዳሪ ኦፊሰር አምባየ ስናመለክት ” እስከ መግደል ድረስ እርምጃ ለመውሰድ መብት አለን፣ አርፋችሁ ካልተቀመጣችሁ በጥይት እንቆላችሁዋለን፣ የምግብ ማቆም አድማ እናደርጋለን ብትሉም ለእኛ ደንታችን አይደለም”  በማለት እንደመለሱላቸውና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እየተዛተባቸው መሆኑን ጠቅሰዋል። ለ4 ቀናት ምግብ ማቆማችንን ተከትሎ ማንም ስላልጠየቀን በሞት አፋፍ ላይ እንገኛለን ያሉት እስረኞቹ የኢትዮጵያ ህዝብ እና የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ እገዛ እንዲያደርግላቸውም እስረኞቹ  ተማጽነዋል።

ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸው ህክምና ከተከለከሉት መካከል ቀጀላ ገላና ገቢሳ፣ በላይ ኮርሜ ባይሳ፣ መንግስቱ ግርማ አየሳ፣ ተፈራ ቀበኔ ገመቹ፣ ሙላት ሽመልስ እጀታ፣ ኢብሳ አህመድ ሙሀመድ እና ሸምሰዲን የተባሉት ሲገኙበት ፣ ድብደባ ከተፈጸመባቸው መካከል ደግሞ ሌሜሳ ዲሴሳ፣ አለሙ ተሾመ ቦኬ፣ ዘርፉ መልካ አባይ፣ ቀበታ ገቢሳ ነባራ፣ ቀበና ነጋሳ ነገራ፣ መልካሙ መገርሳ፣ አዳሙ ሽፈራው፣ ቡልቻ ሱሪሳ ጌታቸው አብራ ቶሎሳ፣ ስለሺ ሶሬሳ፣ የፓርላማ አባል የነበረው ጉቱ ወልዴሳ፣ አለማየሁ ቶሎራ፣ በርሲሳ ሊሙ፣ ብርሀኑ እምሩ፣ ኡርቄና አጀማ፣ አህመድ አብደላ ጎዳ እና ለማ በዳዳ ይገኙበታል።

በኦነግ ስም በሽብረተኝነት ወንጀል የተከሰሱት እስረኞች ያቀረቡትን ተማጽኖ ተከትሎ በኢትዮጵያ የሚገኘውን ቀይ መስቀል ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግ የድርጅቱ ስልክ አይነሳም። የታራሚዎች ፍትህ አስተዳዳር ዳይሬክተር ለሆኑት አቶ ብርሀኔ ሀይለስላሴ  ስልክ ብንደውልም፣ ስልካቸው ቢጠራም አይነሳም።

ኢሳት በእስረኞች ላይ የደረሰውን ድብደባ ተከትሎ አካባቢው በደም በመበከሉ እንዲታጠብ መደረጉን መዘገቡ ይታወቃል። የቂልንጦ እስር ቤት ዋና ሃላፊ በቅጽል ስሙ ሻቢያ ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በእሰረኞች ላይ መፈጸሙን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የሳኡዲ መንግስት ኢትዮጵያን ሰራተኞችን አልፈልግም አለ፣ብዙ ኢትዮጵያውያኖች በፖሊስ ጣቢያ ማቆያ ቦታ ታግተዋል !

በዚህ ባሳለፍነው ሁለት ሳምንት የ6 አመት እድሜ ያላት የሴርያን ዜግነት እና እንዲሁም የሳኡዲ ዜግነት ያላት የ 10 አመት ታዳጊ ልጃገረድ በኢትዮጵያን የቤት ውስጥ ሰራተኞች ተገድለው መቀበራቸውን ባለፈው ሳምንት መዘገባችን ይታወሳል እንዲሁም የሳኡዲ መንግስት ኢትዮጵያን ሰራተኞችን አልፈልግም እያለ እንደሆነ ማተታችንን እየጠቆምን ዛሬም ቁርጥ ያለውን አቋም አሳውቆአል ።

በዛሬው እለት የመረጃ ማእከላችን ባገኘው መረጃ መሰረት የሳኡዲ መንግስት  ኢትዮጵያኖች ሰራተኞችን ከአሁን በሁዋላ ወደ ሃገሩ ለማስገባት ፍቃደኛ እንዳልሆነ ጠቁሞአል ።በከፍተኛ ደረጃ በወንጀል የተጠመዱ ናቸው ሲልም የወቀሰ ሲሆን ዜጎቼ ያለምንም ምክንያት ወደ ሞት እንዲሄዱብም አልፈልግም የደህንነታቸውንም ጥበቃ ለማድረግ ኢትዮጵያን ሰራተኞችን ማስቀረቱ ተገቢ ነው ሲል ገልጦአል ።

 የሰራተኞች ጉዳይ ሚንስትር በአፍሪካ የቤት ውስጥ ሰራተኞች ላይ የሚሰጠውን ቪሳ እንዲቆይ እና በወንጀል ስራቸው ላይ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቆአል ይህም ከሆነበት እለት ጀምሮ ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ ወደ ሃገሯ ማስገባት እንደማትፈቅድ የሳኡዲ መንግስት አስተዳደር የሰራተኞች ሚንስትር አስታውቃለች ።በሃገር ውስጥ ገቡ የተባሉት እና ስራ ያልጀመሩትን ኢትዮጵያውያኖችም በፖሊስ ጣቢያ እስር ቤት የማቆያ ቦታ እንዲቆዩ የተደረገ ሲሆን መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎቻቸው ዲፖርት ተደርገው ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ ጥያቄ በማቅረባቸው ወደ ሃገራቸው የሚላኩበት ቀን እስከሚቆረጥበት ቀን ድረስ በፖሊስ ጣቢያ ሊቆዩ እንደሚችሉ የፖሊስ ኮማንደር የሆኑት ኮሎኔል አብዱል ራህማን ጁሪያድ አሳውቀዋል።

ምክትል የሰራተኞች ጉዳይ ሚንስትሩ ደግሞ ሙፋር ቢን ሰአድ አል አቅባኒ እንዳሉት ከሆነ በየ እለቱ ከሁለት መቶ ኢትዮጵያኖች በላይ በሃገራቸው እንደሚገቡ ተናግረው እነሱንም በፖሊስ ጣቢያው ማቆያ እንዳስቀመጡአቸው የተናገሩ ሲሆን ለዚህ መፍትሄው ምን እንደሆነ ለማወቅ አስቸጋሪ ነው ሲሉ ተናግረዋል ከዚያም ውጭ ወደ አራት መቶ የሚጠጉ ሰራተኞችን ዲፖርት ለማድረግ ዝግጅት ላይ ሲሆኑ እነዚህ በአንድ ግሩፕ ሆነው ይመለሳሉ ተብለው የተወሰነላቸው ናቸው ሲሉ ለመገናኛ ብዙሃኖች አስታውቀዋል ።በሌላም በኩል የቪሳ እና ዶክመንቴሽን እንዲሁም ፓስፖርት ዲፓርትመንት ቃላቀባይ የሆኑት አህመድ አል ለሃዲን ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ ከተሰጠው የጊዜ ገደብ ውጭ ልናዎይ አንፈልግም በአሁን ሰአት ስራቸውን መቀጠል እና መቆየት የሚፈልጉትን የኢትዮጵያን ዜግነት ያላቸውን በሙሉ የስራ ፈቃዳቸውን ልናድስላቸው አንፈልግም ብለዋል።

ማንኛውም ዜጋ ወደ ሳኡዲ ለመኖር የሰበአዊ ዜግነት ሊኖረው ይገባል ሲሉም አክለው ጠቁመዋል ።ለመረጃው ማለዳ ታይምስ ከአፍሪካ ኢንተሊጀንሲ ጋር በመተባበር ያቀረበው ሪፖርት ነው ።ሙሉ ዘገባውን በአፍሪካ ኢንተሊጀንስ ሚድያ ያገኙታል ።

by maleda times

በወረባቡ የአንድነት አባላትን ጨምሮ 45 ወጣቶች ታስረዋል

በደቡብ ወሎ ዞን በረባቡ ወረዳ በስግደት ላይ የነበሩ የአንድነት ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ አብዱ መሐመድ እና አቶ እንድሪስ አህመድን ጨምሮ 45 ወጣቶች መታሰራቸውን ምንጮቻችን ከስፍራው በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡

ከታሰሩት መካከልም ወጣት ሱልጣን መሐመድ በከፍተኛ ህመም እየተሰቃየ እንደሚገኝና እስካሁንም የህክምና እርዳታ እንዳልተደረገለት ተጠቁሟል፡፡ መንግስት የወረዳውን ነዋሪዎች የደሴው ሼህ ኑሩ ይማምን መገደል በሰላማዊ ሰልፍ ካላወገዛችሁ የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ አይሰጣችሁም፣ ዘርና ማዳበሪያም አታገኙም የሚል ማስፈራሪያ በካድሬዎች አማካኝነት እየተሰጠ መሆኑንም ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡
በተለይ ከታሰሩት 45 ወጣቶች መካከል 3ቱ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች በመሆኑ የእድሜ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ እና ወጣቶቹ ከመስኪድ ውጭ በአካባቢው ሜዳ ላይ ሲሰግዱ ስለተወሰዱ አብዛኞቹ ቤተሰቦቻቸው እንደማያውቁና እስካሁንም እየፈለጓቸው መሆኑ ታውቋ፡፡ ወጣቶቹም ከታሰሩ ከሳምንት በላይ የሆናቸው ሲሆኑ እስካሁን ክስ እንዳልተመሰረተባቸው ተጠቁሟል፡፡ ይህን ዜና እስክናሰራጭ ድረስ ከታሳሪዎች መካከል  ከፊሉ በደሴ ቀሪዎቹ ደግሞ በሐይቅ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ እስር ላይ እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አመልክቷል፡፡ የዝግጅት ክፍሉም ከወረዳውና ከደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደርና የፀጥታ ክፍል ስለጉዳዩ ለማጣራት ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን በረባቡ ወረዳ በስግደት ላይ የነበሩ የአንድነት ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ አብዱ መሐመድ እና አቶ እንድሪስ አህመድን ጨምሮ 45 ወጣቶች መታሰራቸውን ምንጮቻችን ከስፍራው በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡
ከታሰሩት መካከልም ወጣት ሱልጣን መሐመድ በከፍተኛ ህመም እየተሰቃየ እንደሚገኝና እስካሁንም የህክምና እርዳታ እንዳልተደረገለት ተጠቁሟል፡፡ መንግስት የወረዳውን ነዋሪዎች የደሴው ሼህ ኑሩ ይማምን መገደል በሰላማዊ ሰልፍ ካላወገዛችሁ የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ አይሰጣችሁም፣ ዘርና ማዳበሪያም አታገኙም የሚል ማስፈራሪያ በካድሬዎች አማካኝነት እየተሰጠ መሆኑንም ምንጮቻችን ገልፀዋል፡

በተለይ ከታሰሩት 45 ወጣቶች መካከል 3ቱ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች በመሆኑ የእድሜ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ እና ወጣቶቹ ከመስኪድ ውጭ በአካባቢው ሜዳ ላይ ሲሰግዱ ስለተወሰዱ አብዛኞቹ ቤተሰቦቻቸው እንደማያውቁና እስካሁንም እየፈለጓቸው መሆኑ ታውቋ፡፡ ወጣቶቹም ከታሰሩ ከሳምንት በላይ የሆናቸው ሲሆኑ እስካሁን ክስ እንዳልተመሰረተባቸው ተጠቁሟል፡፡ ይህን ዜና እስክናሰራጭ ድረስ ከታሳሪዎች መካከል  ከፊሉ በደሴ ቀሪዎቹ ደግሞ በሐይቅ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ እስር ላይ እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አመልክቷል፡፡ የዝግጅት ክፍሉም ከወረዳውና ከደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደርና የፀጥታ ክፍል ስለጉዳዩ ለማጣራት ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም፡፡

- See more at: http://www.fnotenetsanet.

የእናት ጡት ነካሾቹ ህወሃት ና ጀሌወቹ

 ከዛሬ 21 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ህዝቦች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ስልጣን የተቆናጠጠው ህወሃት/ወያኔ ገና ከጅምሩ የሃገርና የህዝብ ሃብትና ንብረት መዝረፍና ማውደም መለያ ባህሪው የሆነው የእናት ጡት ነካሹ ህወሃት በሆድ አደር ጀሌዎቹ ተባባሪነት እንሆ ለ21 ዓመታት የሃገራችንን ቁሳዊይና አካላዊ ሃብቶች እያራቆታት ይገኛል::

  ህወሃት/ወያኔ በ 17 አመታት የጫካ የሽፍትነት ዘመኑ በቀመረው ፀረ-ኢትዮጵያ የጫካ ሕጉ በትግል ጎራ ሳይቀር አብረወት ሲቆስሉና ሲዋደቁ ከነበሩት እውነተኛ ታጋዮች መካከል፣ በሃገራቸው አንድነትና ልኡላዊነት ላይ ጽኑ እምነት የነበራቸውን፣የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትንና ዴሞክራሲ ስርአት በኢትዮጵያ መገንባት አለበት የሚል አቋም ያላቸውን እና የህዝብ ወገናዊነት የነበራቸን በየጊዜው በማሶገድ ፀረ-ኢትዮጵያ አቋም ያላቸው ሃይሎች ተሰባስበው ና ተማምለው እንሆ ዛሬ በአዝማቹ ህወሃት እና ከየብሄር ድርጅቱ ተወክለናል ባዮቹ ጀሌዎች በዚህ ትውልድ ላይም ለዜጎች መብትና ነጻነት የሚታገሉትን፣ በጹሁፍ ላይ የሰፈረው ሕገ መንግስት በተግባር ሊተገበር ይገባል የሚል ጥያቄ የሚያነሱ አካላትን፣ የህዝብ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ምላሽ ሊያገኝ ይገባል በማለትጥያቄ የሚያነሱ የህብረተሰብ ክፍልን፣በሃይማኖታችን ጣልቃ አይገባብን፣በሃገራችን ሁላችንም እኩል ልንስተናገድ ይገባናል፣የሠብአዊ መብት ሊከበር ይገባል፣ የመሰብሰብና የመደራጀት መብታችን ሊገደብ አይገባውም ወዘተ በማለት ጥያቄ የሚያነሱ የህብረተሰብ ክፍሎችን አሸባሪ ፣ነውጠኛ፣ ሙሰኛ፣ የአመለካከት ችግር ያለበት ወዘተ በሚሉት ተለጣፊ ቃላቶቹ በመጠቀም ትውልዱን በመግደል፣ በማሰር፣ ከሃገር በማባረር እያመከነው ይገ ኛል::

    የዛሬ የእናት ጡት ነካሾቹ ህወሃት ማ! ያ- ን- ዬ በታጋይ ስም በሚሉበት በዚያን ዘመን ደጉ ያገሬ ሰው የውስጥ የልባቸውን መርዝ ሳይረዳ የተባለለት ዴሞክራሲ ከፊቱ እየታየው ለተራበው በማጉረስ ፣ለተጠማው በማጠጣት፣መንገድ ለጠፋው መንገድ በማሳየት፣የተመታን ሸሽጎ ሂዎት በማትረፍ፣ገደል ፈንቅሎ መንገድ በመስራት፣ጅረት ጫካውን በማሻገር ፣ስንቅ ቋጥራ/ሮ/ ይቅናችሁ ብላ /ሎ/ ለመረቀ እናት/አባት፣እህት/ወንድም ህወሃት/ወያኔ በሃብት ላይ ሃብት አካብተው በዘረፉት ሃብት ደንዝዘው የህዝብን ጥያቄ ወደጎን ትተው ያ ሂዎታቸውን የታደጋቸውና ለድል ያበቃቸውን ህዝብ በፀረ-ዴሞክራሲ ህጋቸው መፈናፈኛ አሳጥተውታል ፥ ህዝቡይህንን ብሶቱን በንጉርጉሮ እንዲህ ሲገልጸው ይደመጣል::

 እሾህ ብቻ ሆኗል እግሬን ብዳብሰው
እንዴት መራመጃ መሄጃ ያጣል ሰው::

 ወ--ገ--ን በዚያን ዘመንታጋይ አይራብም ብላ ፈትፍታ ያጎረሰች እናት በኖረችበት ቀዬ /ቦታ/ ያረገዘችውን ልጅ እንኳን ሳትወልድ ቤንሻንጉል ጉምዝ አገርሽ አይደለም በሚል ከቤቷ ተፈናቅላ /ተገፍትራ /ጫካ ስትወልድ ዝምእንበል?

- የሃገር አለኝታ የሆነው አርሶ አደሩ ያ ትልቅ ሰው በግዳጅ ከ ቤንችማጅዞን ውጣ ሲባል ቤንችማጅዞን ሃገሬ ካልሆነማ ! ቀን ይሰጠኝ ሃብትና ንብረቴን ሰብስቤ እወጣለሁ ብሎ እጁን ዘርግቶ ሲማፀን እጣ ፋንታው ዱላ ሲሆን ምን እንፍጠር ? ምንእንበል ?

በሃገራችንና በህዝባችን ላይከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰ የመጣውን የሰብአዊ መብትጥሰት፣ እየደረሰ ያለውን የሃገር ውድመትእና የሕዝባችንን ሰቆቃ ለመታደግ ይህንን እኩይ ስርዓት ማሶገድ አማራጭ የሌለው ተግባር ነው::

 በመሆኑም በየትኛውም ቦታ የምንገኝ የህዝባችን ሰቆቃና ስቃይ የሚቆረቁረን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ልብ ለልብ ተገናኝተን ይህን ፀረ-ዴሞክራሲና ፀረ-ህዝባዊነት የተንሰራፋበትን ስርአት ሁለገብ ትግል ለማድረግ እንነሳ
ሁላችንም ለሃገራችን የድርሻችንን እናበርክት!

አዘጋጅ ብርሃኔ አሰበ አለሁድረስ
by maleda times

Sunday, July 21, 2013

ወያኔ የቀረበውን የሚያደማ እሾህ ነው

ሼህ ይማም ኑሩን ማን ገደላቸው?

በምርጫ 97 ማግሥት “ድምፃችን ይከበር” በማለታቸው ከሁለት መቶ በላይ ንፁሀን ዜጎች በግፍ መጨፍጨፋቸው በተነሳ ቁጥር የወያኔ ሹማምንት ከሰልፈኞቹ መሀል መሣሪያ የታጠቁ እንደነበሩና ሦስት ፓሊሶችም መገደላቸውን ይናገራሉ። የእነዚያ ፓሊሶች ሞት አሳዛኝ አውነት ሲሆን አሟሟታቸው ግን ጉዳዩን እንዲያጣራ ለተቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን እንኳን ምስጢር ነው። ለጊዜው እውነት ተዳፍናለች፤ ፍትህ ተረግጣለች። ጊዜው ሲደርስ ግን የፓሊሶቹ አውነተኛ ገዳይ መውጣቱ አይቀርም። ይኽ ዛሬ ምስጢር የሚመስለን የሦስቱ ፓሊሶች አሟሟት “ንፁሀን ዜጎችን ለመፍጀት ሰበብ ለማግኘት ሲባል በሥራ ገበታቸው ላይ በነበሩ የፓሊስ አባላት የተፈፀመ አጅግ መሠሪና አስነዋሪ ወንጀል” ተብሎ የሚጠቀስበት ወቅት ይመጣል። ይህ የወያኔ ድርጊት ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው የአንድ ወቅት የተናጠል ክስተት አለመሆኑ ነው።

ከአሜሪካ ኤምባሲዎች ሾልከው የወጡ በርካታ ሰነዶች የተዘረገፉበት ዊኪሊክሰ በተሰኘው ድረገፅ የተገኙ መረጃዎች እንደሚያረጋግጡት ወያኔ ሰዎችን ገደሎ በተቃዋሚዎች እንደሚያላክክ አሜሪካ ታውቃለች። ከእነዚህ ሰነዶች አንዱ – ለምሳሌ – ወያኔዎች ሚኒባስ ታክሲ ውስጥ ቦንብ አፈንድተው በተቃዋሚዎች ማሳበባቸው ተብራርቷል።

ከምርጫ 97ም ሆነ ከዊኪሊክስ በፊትም ሆን በኋላ ወያኔ በእንዲህ ዓይነት አኩይ ተግባራት መካኑ ተከታዮቹና ደጋፊዎቹ የነበሩ ሰዎች የሚመሰክሩት ሀቅ ነው። የሀውዜን ሕዝብ አንዲጨፈጨፍ የተደረገው የትግራይ ሕዝብ በደርግ ላይ እንዲያመር በወያኔ በተረቀቀ ስልት መሆኑ ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ የቀደሞ አባላቱ ደጋግመው የሰጡት ቃል ያረጋግጣል። በኦሮሞ ማኅበረስብ ተሰሚነት የነበራቸው አቶ ደራራ ከፈኔን በኮሜቴ ውሳኔ አስገድለው በኦነግ ማላከካቸው በወቅቱ ውስጥ አዋቂ የነበረ ጋዜጠኛ በፃፈው መጽሐፍ አሳውቆናል። የወያኔ መሠሪነት ልክም ድንበርም የለውም።

ከላይ የተዘረዘረው መረጃ ያለው ሰው ሼህ ይማም ኑሩን ማን አንደገደላቸው መገመት አይቸግረውም። ግምቱም ተራ ግምት ነው የሚባል አይደለም። ዋነኛው ተጠርጣሪ መርማሪ በሆነበት ሥርዓት ውስጥ ከዚህ የተሻለ ማስረጃ ማግኘት ይከብዳል። ዋነኛው ተጠርጣሪ መርማሪም ዳኛም በሆነበት ሥርዓት የሼህ ይማም ኑሩ እውነተኛው ገዳይ ለፍርድ እንደማይቀርብ እርግጠኛ መሆን ይቻላል።
ከዚህ አሳዛኝ የግድያ ድራማ የምንቀስመው ትምህርት ምንድነው?
ዜጎች ከዚህ የሚከተሉትን ነጥቦች በአንክሮ እንዲያጤኑ ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ይመክራል።
  1. ወያኔን መጠጋት ከህሊና ጋር ቢያጣላም እንኳን ጥቅም የሚያስገኝ “ቢዝነሰ” አድርጋችሁ ለምታዩ ሁሉ እውነታው የምታስቡትን ተቃራኒ ሊሆን የሚችል መሆኑን እወቁ። ወያኔ ጥቅም የሚያስገኝ መሰሎ ከታየው የራሱንም ሰዎች ለእርድ ያቀርባል። ወያኔ ከራሱ በስተቀር ወዳጅ የለውም። ወያኔ የቀረበውን የሚያቆስል የአጋም እሾህ ነው። ጥቅም የሚያስገኘለት ከሆነ ወያኔ የሚላላኩለትንም የሚበላ አኩይ ኃይል መሆኑን ከሸህ ይማም ኑሩ እጣ ፈንታ እንማር።
  2. ለጊዝያዊ ጥቅም ወያኔን መጠጋት በክፉ ቀን ከጎን የሚቆም አጋርን ማጣት እና የግል ታሪክን ማቆሸሽ መሆኑን እንገንዘብ። በታሪክ ውስጥ ሼህ ይማም የሚታወሱት በእምነት ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው እንደተነሱ ሰው መሆኑ የማይቀር ነው።
  3. ከፋሺስቱ ወያኔ ጋር በመሆን ፍትህ እንዲጓደል፤ ሰቆቃ እንዲበዛ አስተዋጽዖ እያደረጋችሁ ያላችሁ ዳኞች፣ ፓሊሶች፣ የመንግሥትም ሆነ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሠራተኞች ከዚህ ተግባራችሁ ተቆጠቡ። ወያኔ ለእናንተም አይበጅም።
ይህንን ምክር አልሰማ ብላችሁ ከወያኔ ጋር በማበር ሕዝብን ለሞት፣ ለእስራት፣ ለሰቆቃ፣ለመፈናቀል፣ ለስደት እና ለእንግልት የምትዳርጉ አድርባዮች ከህሊና ወቀሳ ብቻ ሳይሆን ከቅጣት የማታመልጡ መሆኑን ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በጥብቅ ያስታውቃል።

ድል ለኢተዮጵያ ሕዝብ!

በአዲስ አበባ ከተማ እንጻ ተደርምሶ በ ዘጠኝ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ :: የሞተመ አለ !

በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶው ጎጃም በረንዳ በተሰኘው አካባቢ ለባቡር ሃዲድ መስሪያ በሚል ሰበብ የመንገድ ቅየሳ በማድረግ ላይ በሚገኘው የግንባታ ስራ ላይ በአካባቢው በሚገኙት ቤቶች ላይ ይፍረስ ላይ የሚል ትእዛዝ የተላለፈባቸው ቤቶች በሙሉ እንፈርሱ እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት አሳውቆአል ሆኖም በዚህ ሳምንት ውስጥ ከፈረሱት ቤቶች መካከል አንዱ በዜጎች ላይ ክፉኛ አደጋ አድርሶአል ።

በቸልተኝነት ስራ በኑር ህንጻ ላይ የደረሰውን አደጋ ዝም ተብሎ ሲታለፍ በዛሬው እለት ደግሞ የአሰፋ ገለታ ሆቴል እንዲፈር ተደርጎ ሁለት ዎንዶች በመንገድ ላይ ሻይ የምትሸጥ ሴት ህይወታቸው ሲያልፍ እንዲሁም አራት ደላላ ሰዎች ክፉኛ አደጋ ሲደርባቸው ሻይ የሚጠጣ ሰው እና ሌሎችም ከአፍራሽ ቡድኑ ሃይልም በከፍተኛ አደጋ ላይ መውደቃቸውን እና ማንም ሰው ለዚህ ሃላፊነት ሊወስድ የቻለ አካል እንደሌለ ተገልጾአል ።

  መንግስት ለዚህ ሃላፊነቱን ሊወስድ ይገባዋል ሲሉ የአካባቢው ህብረተሰብ ገልጸዋል ።እንደዚህ አይነት አሰቃቂ ጉዳት እንዲደርስ ያደረገው መንግስት መንግስት ለግባታው ሲል ባቀደው ፕሮግራም ስለሆነ አሰቃቂ የሆኑ እና ያልታሰቡ አደጋዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ መገለጽ ሲገባው ምንም ነገር ሳይባል እና ለደህንነት ሲባል የተደረገ ጥንቃቄ ባለመኖሩ ለሚፈርሱት ቤቶች የቤታቸውን ድርሻ እና የህይወት ዋስት ወይንም ኢንሹራንስ መንግስት ሳይወድ በግዱ መስጠት ይገባዋል ሲሉም የህግ ባለሙያዎች አክለው ገልጸዋል ።

ምንጭ maleda times

አለን ብለነ እንዳናወራ! ዳግማዊ ጉዱ ካሳ

y maleda times
“እናት ሀገሬ ኢትዮጵያ አንዲት ናት!” ብሎ ለአሃዳዊ ግዛቷ ዐፄ ቴዎድሮስ ቆላ ደጋ የተንከራተተላት ኢትዮጵያ፣ “ኢትዮጵያዬ…” እያለ ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) በ‹ጃ ያስተሰርያል› አልበሙ የሚያለቅስላት ኢትዮጵያ፣ “እምዬ ኢትዮጵያ … ተራራሽ አየሩ…” እያለ ቴዎድሮስ ታደሰ ያቀነቀነላት ኢትዮጵያ፣ … አሁን የገባችበትን ማጥ ስናይ ናላችን የሚበጠበጥ የወዲያኛው ትውልድ አባላት ጥቂቶች አይደለንም፡፡ በሀገር ውስጥ የምኖረው እኔ ለጉድ የጎለተኝ ሰውዬ በዐይኔ በብረቱ የማየውን ሀገራዊ ስንክሣር xenedtlmdwe እንደተለመደው ጥቂት ላዋራችሁ ነውና ትንሽ ትቆዝሙ ዘንድ ፈቃዳችሁ ይሁንልኝ፡፡
በመጀመሪያ ‹ኢትዮጵያ ዐፄው ህመሟን አባባሱባት - ደርጉ ጣዕረ ሞቷን አጣደፈው - ወያኔው ገደላትና ቀበራት› በሚለው የብዙዎች እሳቤ የማምን መሆኔን መግለጽ እወዳለሁ - እየሞቱ ይሉኝታ የለም፡፡ ትንሣኤ ሙታን የመኖሩ ዕድል በታሳቢነት ተይዞልኝ የዘመኑ ግልጽ እውነት ታዲያን እንደዚያ ይመስለኛል፡፡ ይህችን ሀገር አንዳቸው ከአንዳቸው እየተቀባበሉ ወረደ መቃብሯን እንዳፋጠኑት ለማንም ግልጽ ነው፡፡ በአገዛዛቸው ወቅት የሚለብሱት ፖለቲካዊ ካባ ይለያይ እንጂ፣ በሀገርና በሕዝብ ያደረሱት ወይ የሚያደርሱት ጥፋትና በደል በደረጃ አይመሳሰል እንጂ፣ ለሕዝብና ለሀገር ያላቸው ፍቅርና ብሔራዊ ስሜት የአንዳቸው ከአንዳቸው በተለይም የሁለቱ ከሦስተኛው የሚቀራረብ አይሁን እንጂ ለጥፋተኝነቱ ሁሉም በየደረጃው ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ በቀ.ኃ. ሥላሤ ህመሟ እንደጸናባት፣ በደርግ ጣዕረ ሞት ውስጥ እንደገባችና በወያኔው የማፊያ ቡድን የከፋፍለህ አውድም ዘመነ ጽልመት ደግሞ ለይቶላት እንደሞተችና በምዕራባውያንና ምሥራቃውያን የፖለቲካ ሊቃነ ጳጳሣት ጉዞ ፍትሓት አማካይነት የቀብር ሥነ ሥርዓቷ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ መመሥከር ይቻላል፡፡ (ዐፄው በሥልት ያስወገዷቸውን አንጎሎች፣ ደርጉ በምሕረት የለሽ ጭካኔው የጨፈጨፋቸውን ሀገር ገምቢ ወጣቶችና የጦር አበጋዞች ስናስታውስ የመረገማችን ዕዳና ባሳለፍናቸው ጥቂት የማይባሉ አሠርት ዓመታት ውስጥ የዕዳችን ተከፍሎ አለማለቅ ክፉኛ ይሰማናል፤ አለመታደላችን በሚያስከትልብን ጸጸትም ለማንወጣው ውስጣዊ ቁጣ እንዳረጋለን - ጨጓራን ለመላጥ፡፡ የቀደሙት ሁለቱ አመቻችተውት በሄዱት ገላጣ ቦታ ላይ ወያኔ ያለ ተቀናቃኝ ጉብ አለበት፤ ይሄ የወያኔ ጥፋት አይደለም፡፡ ጥፋቱ መደላድሉን አበጅተው የጠፉት ወገኖች ነው፡፡ ሀገር በስንት ወጪ ያሰለጠነቻቸውን በተለያዬ የሙያ ዘርፍ የሰለጠኑ ምሁራንን በቀይ ሽብር መፍጀትና በርካታ የጦርና የፖሊስ ጄኔራሎችን በአንድ ቀን ጀምበር መረሸን ማለት የጠላትን የ500 ዓመት ጦርነት በ500 ዓመታት ማሳጠር ማለት መሆኑን ዛሬ ላይ ሆነን ሳይሆን ያኔውኑ ማሰብ ይገባ ነበር፡፡ ለአንድ ሰው የሥልጣን ጥም እርካታ ወይም ወንዝ ለማያሻግር ርዕዮተ ዓለማዊ ፍልስፍና ሲባል ሀገር ጠፋች፤ ወገን ተሰደደ፤ ርሀብና ድርቅ፣ ጦርነትና ግዞት ባል ሆኑ፤ በስተመጨረሻም ዘረኝነትና ጎጠኝነት አዲስ የፖለቲካ ዘይቤ ሆነው በመተከላቸው አካማሌ ሆነን ከሀገርም ከሰውም ተራ ወጥተን ቀረን፡፡)
ትናንትና ወደ አንድ ወንድሜ ቤት ሄድኩ፡፡ ወንድሜ የምለው ላለማራቅ እንጂ የብዙ ዘመን ጓደኛየ ነው፡፡ እቤቱ ስደርስ የአሥር ዓመት ዕድሜ ልጁን አጠገቡ አስቀምጦ ጋቢውን ለብሶ ልቅሶ የተቀመጠ መስሏል፡፡ የወረወርኩለትን የተለመደ ሰላምታም በቅጡ ሊቀበለኝ አልቻለም፡፡ ደነገጥኩ፡፡ “እንዲህ ሆነን ዐረፍነው!” ይለኛል - የሚለው ሳይሆን ያለበት ምክንያት ሳይገባኝ፡፡
“ይሄውልህ ዳግምዬ፡- ጉዴን ስማልኝ - አሁን እኔ ሰው ነኝ? ከአሁን በኋላስ በሕይወት መኖር አለብኝ? ሀገርስ አለኝ? መንግሥትስ አለኝ? ኧረ ምንድን ነኝ ለመሆኑ? ወዴት እየሄድን ነው? ከእንግዲህ ምን ይዋጠኝ? …”
መነሻው በማይታወቅ የብሶት እሩምታ ብዙ መቆየቱ አስጨነቀኝና አቋርጬው “እንዴ! ምን ሆነሃል? አለወትሮህ ዛሬ ምን ነክቶሃል?” ስል ጠየቅሁት፡፡ ሊያዳምጠኝ አልቻለም፡፡ ብሶቱን ማዥጎድጎዱን ቀጠለ፡፡ የአፍንጫና የጉንጭ አምላክ ባይታደጋቸው ኖሮ በሚያስፈራ አኳኋን ተጉረጥርጠው ከማኅደራቸውም ወጥተው የሚታዩት ዐይኖቹ ወደመሬት ወርደው ሊፈጠፈጡ ምንም አልቀራቸውም፡፡ እንዲሰክን ውትወታየን አላቋረጥኩም፤ ተሳካልኝ - ቀስ እያለ በረድ ማለት ጀመረ፡፡
“ይሄውልህ፡፡ እንደምታውቀው ይህ የመጨረሻው ልጄ ነው፡፡ ዕድሜው አሥራ አንድ ዓመት ነው፡፡ ገቢየ አነስተኛ በመሆኑ የማስተምረው በመንግሥት ትምህርት ቤት ነው፡፡ እንደ መጥፎ ልማድ ሆኖብኝ ልጆቼን የመከታተል ባህል ከዱሮውም  አላዳበርኩም፡፡ በዚህ አዝናለሁ፡፡ በስንትና ስንት ሀገራዊና የመሥሪያ ቤት ችግር ስለምወጣጠር እቤት ገብቼ እንደብዙ አባቶችና እናቶች ‹ዛሬ ምን ተማርክ? ሰሞኑን ምን ተማርሽ?› ማለቱን አላዘወተርኩም - እንዲያው በደፈናው እመክራለሁ ፣ እንዲተጉ አስጠነቅቃለሁ እንጂ ጠለቅ ብዬ የምከታተለው ነገር የለኝም፡፡ እናታቸውም ከኔ የበለጠች ሰነፍና ዝንጉ ናት፡፡ ዛሬ ታዲያ በጋው ከመድረሱ እስኪ አንዳንድ ነገር ላስጠናው ብዬልህ መጽሐፍ ገዝቼ ላስነብበው ስል በመጪው የ2006 መስከረም አምስተኛ ክፍል የሚገባ ልጅ ከነአካቴው ማንበብ አይችልም፡፡ እነ ‹ጀ፣ኀ፣ኸ፣ጨ፣ጰ›ን ይቅርና የ‹ሀ›ንና የ‹ለ›ን ዘሮች እንኳን አልለየም፡፡ እንግሊዝኛውንማ ተወው፡፡ ይገርምሃል - የመጀመሪያውን ሆሄ ስትጠራለት ብቻ በሽምደዳ የያዘውን እንደበቀቀን ያነበንባል እንጂ ፊደላቱን ለይቶ በዘር በዘራቸው አያውቃቸውም፤ በዚያም ምክንያት ማንበብ ፈጽሞ አይችልም፡፡ ይሄ ታዲያ አያሳንቅም ትላለህ? ሞት ሲያንሰኝ ነው!”
ችግሩ አሁን ገባኝ፡፡ ‹ያሳንቃል› ብዬ አስተያየቴን ለመስጠት ግን ከበደኝ - ሆድ ለባሰው ማጭድ አታወሰው ይባላል፡፡ ወዳጄ ዛሬ ገና አንድ ነገር የገባው ይመስላል፡፡ በየቤታችን ያለውን ጉድ ቢሰማ ምን ሊል ነው? በደመ ነፍስ የምትነዳ ሀገር ውስጥ መኖራችን ዛሬ ገና ነው የታየው መሰለኝ፡፡ አሁን ምን ማድረግ እንደሚችል አላውቅም፡፡ ምን ብዬ እንደምመክረውም ግራ ገባኝ፡፡ “የምትችለውን አድርግለት እንጂ ያን ያህል ዕብድ አትሁን፤ አንተ ብታብድ ልጆችህም አንተም ሁላችሁም ትጎዳላችሁ እንጂ የሚጠቀም የለም፤ አይዞህ - በሁላችንም ቤት ያለ ነው” እያልኩ አጽናናው ገባሁ፡፡ ብዙ አብነቶችንም እየጠቀስኩ ያለንበት አደገኛ ሁኔታ እገልጥለት ያዝኩ፡፡
ይሄውልህ - የአንድ ዘመዴ ሴት ልጅ ሰባተኛ ክፍል ደርሳለች፡፡ በዕውቀት ግን አዲስ ከተወለደ እንኳን ሕጻን አትሻልም፡፡ አታነብም፤ አትጽፍም፡፡ ግነት እንዳይመስልህ - አታነብም ፤ አትጽፍምም፡፡ እንዴት ሰባተኛ ክፍል ደረሰች ብሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ ይህን ጥያቄ የሚመልስልን ግን ጊዜው ሲደርስ ራሱ ወያኔ ይሆናል - ለአሁኑ ግን “ ባልተማረ መምህር ስለሚማሩ፣ በአብዛኛው የሙያና የሀገር ፍቅር በሌለውና አነስተኛ ክፍያ በሚከፈለው  መምህር ስለሚማሩ…” ብለን እናልፋለን፡፡ በሠፈሩት ቁና መሠፈር አለና ያኔ እነማን ማይም ሆነው ቀርተው እነማን እንደተማሩ፣ እነማን መንገድ ጠራጊ ሆነው ቀርተው እነማን መሀንዲስና ዶክተሮች ሆነው ከፍተኛ ደረጃ እንደተቆጣጠሩ ሲጠየቁ ወያኔዎች ራሳቸው ሊመልሱት የሚገደዱበት ምድራዊና መለኮታዊ ጥያቄ ነው፡፡ ሰው ለሆነ ፍጡር የኢትዮጵያ ሁኔታ እጅግ የሚዘገንን ነው፡፡ ጣሊያን እንኳን ይህን ያህል አልጨከነም፤ ይህን ያህል ሕዝብን አላደደበም፤ ይህን ያህል ሰውን ከእንስሳት በታች ቆጥሮ ወደ ድንጋይነት አልለወጠም፡፡ ይህን ያህል ዜጎችን ለይቶ አንዱን በሃሳብም በቋንቋም እንዲበለጽግ ሌላውን በሁሉም እንዲደኸይ አላደረገም፡፡ የወያኔን ይህን መሰል ኃጢኣትም እንበለው ወንጀል ሰይጣን ራሱም ቢሆን ከአሁን ቀደምም ሆነ ወደፊት ሊሠራው አንጀቱ የሚጨክንለት አይመስለኝም፡፡ የነዚህ ወያኔዎች አንጀት የተሠራው ግን አይገባኝም፤ ምናልባት ከጅብ ቆዳና ከባሌስትራ ሳይሆን አይቀርም፡፡
እኔ ያጽናናሁት እየመሰለኝ እንዲህና እንዲያ እያልኩ የማውቀውንም የሰማሁትንም ዘለባበድኩለት፡፡ በዲግሪ ከተመረቁ ወጣቶች ብዙዎቹ ስማቸውን በእንግሊዝኛ ይቅርና በሌላ በቅርብ በሚያውቁት ሀገርኛ ቋንቋ አስተካክለው እንደማይጽፉ አከልኩለት፡፡ ዛሬ ዛሬ ዕድሜ ለወያኔ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ይቅሩና የኮሌጅ ተማሪዎች ሳይቀሩ የለዬላቸው ማይማን ናቸው፡፡ በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ የሚበረታቱት ጫት ቤት እንዲውሉ፣ ሺሻ እንዲምጉ፣ አረቂና ጠላ እየተጋቱ በመስከር ጭንቅላታቸውን እንዲያላሽቁ፣ ሀሽሽና ቁማር ቤት እንዲያዘወትሩ፣ ከሃይማኖትና ከሞራል እንዲያፈነግጡ፣ ወጥ ማንነት ኖሯቸው ለአብሮነት የጋራ ሕይወት እንዳይጥሩ ነው…፡፡ ወያኔ የውጪ ወራሪ ኃይል ይመስል ከውጪ ወራሪና ቅኚ ገዢም በከፋ ደረጃ የራሴ በሚላቸው “ሕዝቦቹ” ላይ እየፈጸመ የሚገኘው ግፍና በደል ተዘርዝሮ አያልቅም፡፡ ለዚህም ነው የሀገሩ ባንዲራ የተበጣጠቀችበት ወጣቱ ትውልድ በማንነት ኪሣራ እየዳከረ የራሱን ሰንደቅ ሳይሆን በህልም የሚቀላውጣቸውን የፈረንጆችን ዕራፊ ጨርቅ የሚመስል ባንዲራ ግንባሩ ላይ አሥሮ የሚታየው፤ ለዚህም ነው ወጣቱ የአነጋገር ሥልቱ፣ አካሄዱና አለባበሱ ሳይቀር በፊልም የሚያየውን እየኮረጀ ከነሱም ከራሱም ሳይሆን በመሀል ከራዳር እንደወጣ አውሮፕላንና ኮምፓስ እንደሌላት መርከብ የትሚናውን ጠፍቶ ራሱንም ለመፈለግ ፍላጎት አጥቶ በሁለት ዓለማት ስብዕና እየባዘነ የሚታየው፡፡ ምን አለ በለኝ - ወጣቱን ለዚህ ያበቁት ወያኔዎችና ለወያኔዎች ምቹ ሁኔታን የፈጠሩ እርጉማን ሁሉ ዋጋቸው ይሠፈራል፡፡
ወዳጄን ለማስተዛዘን በምሥጢር መያዝ የሚገባኝን ብዙ ዘግናኝ ሀገራዊ እውነቶችን ዘከዘክሁለት - ሴትዮዋ ‹መንግጌ አባስኳት› እንዳለችው ጓደኛየ ሶበረልኝ ብዬ ላጥናናው በምነግረው እውነተኛም የተጋነነም ታሪክ በቀላሉ ሊጽናናልኝ ግን አልቻለም፤ “ወደዚህ ቤት ያመጣኝን እግሬን በሰበረው” አልኩና ተማረርኩ - መማረር ችግርን የሚፈታ ይመስል፡፡
እኔ ግን ቀጠልኩ፤ አልኩም፡- ቢኤውን ከያዘ ገና አራት ዓመት በቅጡ ያልደፈነ የአንድ ጓደኛየ ልጅ ሰሞኑን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በእንግሊዝኛ ቋንቋ በማስተርስ ዲግሪ ይመረቅና ማመልከቻ እንድጽፍለት ወደኔ ዘንድ ይመጣል፡፡ ይህን ምን ይሉታል?
 
ማመልከቻ ጻፍልኝ፤
የምን ማመልከቻ?
የሥራ ማመልከቻ፤
ለየትኛው መሥሪያ ቤት?
ለ … ት/ቤት ነው የምትጽፍልኝ፤ አንድ የእንግሊዝኛ መምህር ይፈልጋሉ አሉ፤ በራፖርተር ጋዜጣ ወጥቷል፡፡
በ‹ሪፖርተር› ማለትህ ነው? ታዲያ አንተው አትጽፍም እንዴ? በቋንቋ አይደል እንዴ የተመረቅኸው?
አይ፣ ግዴለህም አንተው ጻፈውና ባይሆን እኔ የምጨምረውን እጨምራለሁ ወይ እቀንሳለሁ፡፡
የለም፣ እንደሱማ አይሆንም፤ አንተው ጻፍና እኔ ኋላ ላይ ልይልህ፡፡
በዚህ ተስማማንና የሚከተለውን የማመልከቻ ደብዳቤ በእንግሊዝኛ ጽፎ አሳየኝ፡፡
 
Deer Sirs or deer madams:
I was written these letter for apply to the teacher post advertising on the reporters newspaper printed dated on julay 18, 2013(hamillie 11/2005). I am interesting to hire you in your school, if possible.
My name is Gudayehu Zendro and I am 27 old. I am graduation from Addis Ababa University in MA degree for about english. I can writting  and speeking English very good and I can teaches these languge on your school if you gives me the chances to accepted me their and allow me to work with no matter salary amount to paid me.
As high school english teacher, I worked in Zebider school for 2 yers. On top of that I have been written two modules and I have been served another school for six months. And I had made unit ledder their four a month.
If you chose or selects me to your butifull school, by the way I love it, I will is happy to becoming interviewed on your inconvenient time and don’t afraid me to contact me anytime you may dislikes.
Semisterly yours,
Tank you very match
 
ማሽላ እያረረ ይስቃል እንላለን - አበውም ይሉት ነበር፡፡ ይህ ማመልከቻ ቀልድ ቀመስ መሆኑን የሚያጣው ያለ አይመስለኝም - ግን ጠጣር እውነትን ያዘለ ነው፡፡ አንድ ሂስ እቀበላለሁ - ‹ትንሽ ጨከን ብለሃል› ለሚለኝ እውነት ነው እላለሁ፤ የጨከንኩ ይመስላል፡፡ ሆድ ቢብሰኝ ነውና አትታዘቡኝ፡፡ ነገር ግን መሬት ላይ ያለው እውነት ከዚህ ብዙም የሚለይ እንዳልሆነ ብዙ ተጨባጭ ማስረጃዎችን በማቅረብ ማስረዳት ይቻላል፡፡ ከበርካታ ‹ምሁራን› ይህን መሰል ወይም ወደዚህ የሚጠጋ አስደንጋጭ የማመልከቻ ወይም የሌላ ጉዳይ ጽሑፎችን ማየት ከጀመርን ውለን አድረናል፡፡ ዘመኑ የቴክሎጂ በመሆኑ ዕድሜ ለዚህ ለኮፒ/ፔስት አዳሜ ከየድረገ ገጹ እየኮረጀ ወይም በተቀጣሪ አሰለጦች እያሠራ በዲግሪ ይንበሸበሻል - ሥራው ዓለም ላይ ግን ከዜሮ በታች ነው - የዱሮ ስምንተኛ ክፍል የዛሬን የዲግሪ ምሩቅ ሰጥ ለጥ አድርጎ ያሰለጥነዋል ይባላል፡፡ በቴክኒክ ሥራዎች ከሆነ በተለይ ልዩነታቸው ሰማይና መሬት ነው - ደመወዙ ግን ግፍ የሚታይበት ነው - ዲግሪ የሌለው ነገር ግን ሥራውን በዘመኑ ቋንቋ አድምቶ የሚሠራው የሚከፈለው መሃያ በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ እይዐርግ እይወርድ - ወጣም ወረደ - ይህ በወያኔ ሆን ተብሎ የታወጀ የትምህርት ጥራት ዝቅጠት - መቅሰፍትም ሊባል ይችላል - ሀገሪቱን ሰው አልባ የሚያደርግና የነገ ሀገር ተረካቢ የሚያሳጣ ከችግሮች ሁሉ የከፋው አደገኛ ችግር ነው - ርሀብና ጠኔ የሚገድለው አካልን ነው፤ ያልፍማል፡፡ የትምህርት ጉዳይ ግን ከሀገር ኅልውና መቀጠል አለመቀጠል ጋር በቀጥታ የተቆራኘና መንፈስን የሚገድል ነው፡፡ ብዙዎቻችን በዚህ ረገድ ጠፍተናል፡፡ያልጠፋን እንዳይመስለን፡፡
በዚህ ላይ አንድ አስገራሚ ነገር ለመጨመር ያህል - የዘመኑ ምሩቃን አለማወቃቸውን በጭራሽ አያውቁም፡፡ አለማወቅን አለማወቅ የመሰለ ጠንቀኛ ችግር ደግሞ የለም፤ አለማወቅን አለማወቅ አንድም ዕብሪታዊ ደደብነት ነው አንድም ትዕቢት ነው - ወይም የሁለቱ ቅልቅልም ሊሆን ይችላል፡፡ አለማወቅን አለማወቅ ያልታወቀ በሽታ እንደማለት ነው - መድሓኒት የማይገኝለት፡፡ በሁሉ ዘርፍ ሀገር እየጠፋች የምትገኘው አለማወቃቸውን ባለማወቅ እነሱ የሚያውቁት ሁሉ እንደትክክለኛ ዕውቀት እንዲወሰድ በሚፈልጉ ጭንቅላታቸው በትምክህት ሞራ ወይም በማይምነት ጥቁር ሱቲ በተሸፈነ ሰዎች ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ማስታወቂያ የሚጽፍ ድርጅት ከደንበኛ የተሰጠውም እንኳን ቢሆን ተማክሮ ይለውጣል እንጂ ”enklish gramer school”  የሚል ማስታወቂያ ትልቅ ቢልቦርድ ላይ ጽፎ ሊሰጥና በዕውቀትና ጥበብ አምባ ላይ ልግጫና ፌዝ እንዲበረታ ሊያደርግ አይገባም፡፡ በዚህ ረገድ የምናያቸው ብዙ ጥፋቶች እንግዲህ ‹ዕውቀት ከኔ በላይ ላሣር!› ባሉ የወቅቱ ምሁራን ወይም ‹ኮሌጅ የበጠስን ነን› በሚሉ ሰዎች የተሠሩ ናቸው ማለት ነው - መዝገበ ቃላትን እንኳን ማገላበጥ ማንን ገደለ? ኧረ ወዴት እየሄድን ነው ጎበዝ! ለማለት የፈለግሁት ይበልጥ ግልጽ እንዲሆን እፈልጋለሁ - አንሳሳት ወይም ሰው አይሳሳት እያልኩ አይደለም፡፡ ስንሳሳት ግን ስህተትን ባህላችን ለማድረግ ቆርጠን የተነሣን መሆናችንን በሚያሳብቅ ሁኔታ መሆን የለበትም ነው እያልኩ ያለሁኝ፡፡ እንጂ ያልሞተ ይሳሳታል -  ቆም ብሎና በምክክር ግን ይታረማል፡፡ የአሁኑ ዘመን ግን በሁሉም አቅጣጫ ሲመዘን ስህተት እንደቅቡል ይትበሃል በመንሠራፋት ላይ የሚገኝ ይመስላል፡፡ መሳሳት እንደጀብድ የሚቆጠርበት ዘመን ላይ ሳንገኝ አልቀረንም፡፡ ሰውን ስህተቱን ስትነግረው ‹ምን ይጠበስልህ!› ለማለት “So what?” ይልሃል፤ ታፍራለህ - ትደነግጥማለህ፤ ለሌላ ጊዜ አፍህን በዳቦ ወይም ዳቦም ባቅሙ ካረረብህ በመዳፍህ ትይዛለህ፡፡ አቤት! አቤት! አቤት! ያለንበት ዘመን!!
የአዲስ አበባን የመንገድ ላይ ማስታወቂያዎችን፣ የንግድና የአግልግሎት ማግባቢያና ማሻሻጫ በራሪ ወረቀቶችን … ብንመለከት ብዙዎቹ የሚታዩባቸው የፊደላት ስህተትና የሃሳብ ፍሰት አለመጣጣም የወያኔው የማፊያ ቡድን ትምህርትን በማውደም ሀገርን ተረካቢ አልባ አድርጎ ለማስቀረት የነደፈው ዕቅድ ምን ያህል እንደተሳካለት ያሳያሉ፡፡ ከዚህ ጎን ለጎንም ለንግድ ቤቶችና ለትምህርት ቤቶች የሚሰጡ ስያሜዎችን ስንመለከት ሀገራችን ምን ያህል በማንነት ኪሣራ ውስጥ እንደተዘፈቀች እንረዳለን፡፡ በሀገር ውስጥ እያሉ በሀገር ውስጥ መኖራቸውን ማመን በማይፈልጉ ኢትዮጵያውያን ለልጆች የሚወጡ ስሞችና ለተቋማት የሚሰጡ መጠሪያዎች በግልጽ የሚያሳዩን ነገር ቢኖር ከሞላ ጎደል ሁሉም ሰው በገዛ ሀገሩና በገዛ ቋንቋና ባህሉ ላይ ማመጹን ወይም መሸፈቱን ነው፡፡ አለበለዚያ እነታንጉትና አንጓች እነጫልቱና ዘርመጪት ተዘንግተው ባልጠፋ የሰው ስም ‹ሊሊ፣ ቲቲ፣ሊዱ› ባልተባለ፤ ባልጠፋ የትምህርት ቤት ስም ‘School of Americana’ ፣ እነመቻልና ቡቺ ተረስተው ባልጠፋ የውሻ ስም ‹ጃኪ. ሮኪ› ባልተባለ፣ ባልጠፋ ሀገርኛ የንግድ ቤት ስም ‘ቴክሳስ ጫማ ቤት›ና ‹አልባንያ ቁርስ ቤት’ ማለቱም ለትዝብት ከመዳረግ ውጪ የሚፈይደው አንዳች ነገር እንደሌለ በታወቀ፡፡ ቦሌ መንገድ ብትሄድ ከቋንቋው ጀምሮ አለባበሱና የሰውነት መለወጫ ኮስሞቲክሱ ድረስ ሲታይ “ኢትዮጵያ ውስጥ ነው እንዴ ያለሁት? ለመሆኑ ይህች ሀገር የማን ናት?› ማለትህ አይቀርም - እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ፤ የውጪውማ ቢያንስ ርቀዋልና ግዴለም ሊባል ይችላል፡፡ የትናንት አበቅየለሽ ወይ አምለሰት ዛሬ ቦሌ ገብታ በሞተ ከዳ የነጭ ጋለሞታዎች ፀጉርና ሰይጣናዊ ቅብዓ-ርኩስ ፈረንጅ መስላና ስሟን ወደ ቲና ለውጣ መቀመጫዎቿን ቆላ ደጋ ደንገላሣ እያዝበጠበጠች ስታዩ በትውልዱ የቁም ሞት ታለቅሳላችሁ - ወይኔ ምነው ይህን ሳላይ እንዳያት ቅድማያቶቼ አፈር ውስጥ ገብቼ በመሸግሁ - እያላችሁ፤ ‹ይህችን ሀገር ማን ነው የሚረከብ?› ብላችሁም የሚረከባት የሚጠፋ ይመስል በ‹ከንቱ› ልትጨነቁ ትችላላችሁ - ‹ይብላኝ ለእኛ እንጂ ተረክቦ የሚግጥ ውሻና ግሪሣማ መች ጠፍቶ ያውቅና!› ለማለት ፈልጌ ነበር ግን ቀና ሀገራዊና ሕዝባዊ ዓላማቸውን ያልተረዳሁላቸው መስያቸው ከወደፊት መሪዎቼ ጋር ያቃርነኛልና ይሄኛውስ ይቅርብኝ - ግን ግን ሳስበው ‹ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከምቢያው ቂጢጥ› እያለ ተቸገርን እኮ ምዕመናን፡፡ መጥኔ ለሚቆዩ! መጥኔ ለወጣቶች፡፡
ጎበዝ - ተወርረናል! እነዚህ ወያላ ወያኔዎች ሀገራችንን ሙሉ በሙሉ አዋርደዋታል፡፡ ሰው ራሱንና ሀገሩን እስኪጸየፍና አምርሮ እስኪጠላ በሀገሩ ላይ አመጽ እንዲያስነሳ አስገድደውታል፡፡ ከቦሌ እስከ ጉለሌ፣ ከኮተቤ እስከ ካራቆሬ፣ ከሳሪስ እስከ እንጦጦ መላዋን አዲስ አበባ ብትጎበኙ ብዙ ጉድ ታያላችሁ፡፡ ቋንቋችንን መጠየፍ፣ ባህላችንን መጠየፍ፣ ራሳችንን መጠየፍ፣ አብሮነታችንን መጠየፍ፣ መተሳሰብንና መተዛዘንን መጠየፍ፣ ሰብኣዊነትን መጠየፍ፣ ወገናዊ ፍቅርን መጠየፍ፣ ዕውቀትን መጠየፍ፣ ጥበብን መጠየፍ፣ ዕርቅን መጠየፍ፣ ተቻችሎ መኖርን መጠየፍ፣ አማራ ትግሬን መጠየፍ፣ ትግሬ አማራን መጠየፍ፣ ኦሮሞ - አማራ - ትግሬ - እርስ በርስ መጠያየፍ… ሁሉን መልካም ነገሮች መጠየፍ አብዝተናል፡፡ የእርግማኑ ዑደታዊ ጡዘት ከመቼውም ጊዜ በላይ ከርሯል - ለጤናም አይመስልም ፡፡ በምትኩ በራስ ወዳድነትና በግለኝነት ሱስ መለከፍ፣ በሴሰኝነት ዳንኪራ መጠመድ፣ በሥልጣን አራራ መቃተት፣ በዘረኝነት የደዌ  ልክፍት መንጠራወዝ የዘመኑ ፋሽናችን የሆኑ ይመስላል፡፡ (በነገራችን ላይ በአዲሱ የወያኔ ቤተ ሙከራዊ የሕዝብ ቆጠራ ትግራይ ክልል የመሪነቱን ሥርፋ - ማለትም ሥፍራ - ስትይዝ ሶማሌ ሁለተኛ - ኦሮሞ ሦስተኛ - አማራ አራተኛ እንደሆኑ ሰማሁ፡፡ የዕብድ ቀን አይመሽም፡፡ የወያኔ ቀንም አልመሽ ብሎ በቴዲ አፍሮ ምናባዊ ግሩም አገላለጽ - በእያነቡ እስክስታ ውስጣችን እያረረና በሀዘን እየተኮማተረ በዕድለቢሶቹ የወያኔ ተውኔቶች ግን መገልፈጣችንን ቀጥለናል - አንድ ቀን እንኳን ተኣማኒ ትያትር መድረስ እንዴት ያቅታቸዋል? ለምን ሰው አይቀጥሩም፡፡ ይህን የ‹ቁጥር መበላለጥ› አሁን ቢያስጠጉት፣ ትንሽ ቆይተው ቢያቀርቡት፣ ከዛም ቢደርቡት… አሁን ምን አጣደፋቸው? ለነገሩ ማን ነው ወንዱ “ የጅብ ችኩል …” ብሎ ስማቸውን በከንቱ የሚያነሳ ? ከፉኛ ንቀውናል እኮ!
አነሳሴ ትምህርት ሞታለች ነው፡፡ በአዲስ አበባ ሁለት ትምህርት ቤቶች እንዳሉ ልጠቁም፡፡ እጅግ ውድ የሆኑ የግል ት/ቤቶችና የመንግሥት የሚባሉ የተዋጣላቸው ትውልድ ገዳይ ት/ቤቶች፡፡ የግሎቹ ዋጋቸው ለድሃው ቀርቶ ለንዑስ ከበርቴ ተብዬውም አይቀመሱም፡፡ የማኅበረሰብ ክፍፍሉ ሁለት መደብ ሆኗል - አንድም ያለው አንድም የሌለው፡፡ በያለውና በየሌለው መካከል ያለው ክፍተት የሰማይና ምድርን ርቀት ያስከነዳል፡፡ በድሆች ትምህርት ቤት ከነአካቴው ትምህርት የለም ማለት እንችላለን - ያለው ኮታና ቀልድ ነው፡፡ ወያኔ ለወሽካታው የእስታትስቲክስ መዝገቡ ሲል ይህን ያህል ት/ቤት ተከፈተ፤ ይህን ያህል ልጅ ተመዘገበ … ለሚለው የማስመሰያና ፈንድ ማወራረጃ ድራማው እንጂ ከአንጀት አዝኖ ትውልድን በተገቢው ዕውቀት ለመቅረጽ የሚፈልግ መንግሥት አይደለም፡፡ የትምህርት አመራሩ በጠቅላላውና በየትኛውም እርከን በወያኔዎች መያዙ ችግር እንደሌለው ቆጥረን ሥራው ሲታይ ግን የግብር ይውጣና እውነትም የጠላት ሤራ ትግበራ ይመስላል፡፡ የትምህርት ባለሞያ ይባልና ሰውዬው የሰለጠነው ግን ውትድርና ወይም ቆዳ አፋፋቅና ዓሣ ማስገር ሊሆን ይችላል፡፡ ለነገሩ የፖሊስ አዛዥን የትራንስፖርት ሚኒስትር ከማድረግ የማይመለስ የጉዶች መንግሥት እንጨት ጠራቢን አልጋ አንጣፊ፣ የቢሮ ጸሐፊን ገንዳ ጠባቂ አድርጎ ቢመድብ አይገደውም - አድርገውታልም፡፡ ዋና ዓላማው ሀገርን ማውደምና ትውልድን በቀቢጸ ተስፋ ሀሽሽ ማደንዘዝ፣ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተብዬውንም በሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ማታለል ነው፡፡ ይህ ሀገራዊ አሳዛኝ ቲያትር እስከመቼ ይዘልቃል? ጊዜና እግዚአብሔር የሚፈቱት ነው፡፡ እኛ ግን ግዴለም ዝም ብለን በባዶ ቦታ እንፋጅ፤ ባገኘነውም መድረክ ሁሉ እናምቧትር - ሕዝቡንም ከምጣድ በማይወጣ የተስፋ ዳቦ እንቀብትት፡፡ አየ እኛ!! መጨረሻችንን ያዬ፡፡
በግሉ ዘርፍ ብዙ ት/ቤቶች አሉ - ጥሩዎችም አስመሳዮችም፤ በጣም ውዶችም መለስተኛ ውዶችም (ወላጅን ለማታለል በተማሪ መግቢያና መውጫ ሰዓት ያልተማረ ደንቆሮ ፈረንጅ ቀጥረው በር አካባቢ የሚያቆሙ ት/ቤቶች እንዳሉ ሰምታችኋል? ለማስታወቂያ፡፡ የገዛውን ትልቅ አሮጌ አውቶቡስ ያላንዳች ሥራ ባዶውን ከተማዋን የሚያዞር የኮሌጅ ባለቤት እንዳለስ ታውቁ ነበር? ከመሪ እስከ ነጋዴ፣ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ፣ ከነጭ እስከ ቢጫ - ደካማ ሥነ ልቦናችንን የማይጠቀም የለም፡፡) በነዚህ የግል ትምህርት ቤቶች ከሚማሩት ተማሪዎች ውስጥ በጨዋ ግምት ከ90 በመቶ የማያንሱት የወያኔ ልጆች መሆናቸው በስፋት ይወራል፡፡ ሌላው አቅም ስለሌለው ልጆቹን የሚልከው አንድም ወደ መንግሥት ት/ቤቶች አለዚያም ወደሸቅልና ወደ ጎዳና ተዳዳሪነት - ወደሽርሙጥና - እልፍ ሲልም ወዳረብ አገር ግርድና … ነው፤ በወያኔ አልፎልናል(ሴቷ ልጄ ለአቅመ -ዐረብ ግርድና አልደርስ ብላኝ ተቸግሬያለሁ - ወያኔ ሌላ ምን አመጣልኝ?)
[ኅያው አባት ቅዱስ እግዚአብሔር ሆይ! የኔን የባርያህንና የመሰል ወንድምና እህት ኢትዮጵያውያን ወገኖቼን ዕንባ አብስ! በቃችሁ በለንና ከነዚህ የሲዖል ትሎች ነጻ የወጣን እንድንሆን አድርገን፤ ከዚህ ውጥንቅጥና የተደራረበ ችግር የሚያወጣን በቅዱስ መንፈስህ የሚመራ አንድ ሙሤያዊ ኃይል በአፋጣኝ ላክልን፤ እንደኛ የኃጢኣት ቁልል ሣይሆን እንደምሕረትህ ብዛት ይሁንልን፤ አሜን፡፡]
ኢትዮጵያ ሳያናግሯት ብዙ እየተናገረች ናት፡፡ ወደ በረንዳዎች ሂዱ፤ ወደ ት/ቤቶችም ሂዱ፤ ወደ ንግድ ቤቶች ሂዱ፤ ወደ መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሂዱ… ብቻ እናንተ ለመሄድ አትሰልቹ እንጂ ወደ የትም ሂዱ፡፡ ወደ ገጠርም ውጡ፤ ወደከተሞችም ግቡ፡፡ በምትሄዱባቸው ጥቅም የሚያስገኙ ቦታዎች ሁሉ ቀድመው የሚጠብቋችሁ ወያኔዎች ናቸው - ‹የታገልንበት የደም ዋጋችን ነው› እያሉ በግልጽ ሲቦጠቡጡ ታያላችሁ፡፡ በዚህ ታሪካዊ ስብራታችን ልባችሁ ይነካል፡፡ ‹ሰው እንዴቱን ያህል ክፉ ቢሆን ነው መሰል ወንድሞቹንና እህቶቹን ከሁሉም ማዕዶች አውጥቶ በኅሊናዊና እውናዊ ርሀብ እየገረፈ የራሱን ኑሮ ብቻ የሚያመቻቸው?› ብላችሁ ለሰው ልጅ አጠቃላይ ተፈጥሮ ትጨነቃላችሁ፡፡ ይህን ግላዊ ምቾቱን ለማረጋገጥ ሲልም የሚሠራውን የመቶና የሁለት መቶ ዓመታት ሲአይኤያዊና ሞሳዳዊ ሸርና ተንኮል ስታስቡ ደግነቱ እግዚአብሔር በመሃል በመኖሩ እንጂ ተስፋ ቆርጣችሁ እናንተም የክፋትን መንገድ ልትከተሉ ትከጅላላችሁ፡፡ ግን እንተማመን - እንደጠቢቡ አባባል ሁሉም ነገር ከንቱና የከንቱ ከንቱ ነው፡፡
እዩልኝ እንግዲህ - በግል ት/ቤቶች የሚማሩ የወያኔ ልጆችን የማውቅበት መንገድ አለኝ፡፡ እውነት እላችኋለሁ - ቁም ነገረኛ ልጅ የወጣላቸውን ቱባ ወያኔዎች ማስታወስ አልችልም፤ ስም እያነሳሁ ማፍረጥረጥ ባላቃተኝ - ነውር ባይሆንብኝ፡፡ ገንዘብና ሥልጣን አላግባብ ከተያዘ እንደማባለጉ የነዚህ ወያኔዎች አብዛኞቹ ልጆች ገና ከአሁኑ ጠፍተዋል፡፡ ለመጥፋት የወላጆቻቸውን ዕድሜ ያህል መጠበቅ አላስፈለጋቸውም - አሸዋና ድንጋይ ላይ በዕለተ ሰንበት የተዘሩ የእርኩሳን ዝሪቶች ናቸውና፡፡ ሕዝብ የረገመው፣ ሀገር ያሳቀለው ዜጋ መቅኖ የለውምና እነዚህ ልጆች ምንም እንኳን በልዩ ትምህርት ቤቶች እንዲማሩ ቢመዘገቡም ገንዘቡ አናታቸው ላይ ወጥቶ ስላሰከራቸው አይማሩም፤ ትምህርት ቤት አይገቡም፤ ቢገቡም በዲሲፕሊን ችግር ት/ቤቱን ያውካሉ፡፡ ሊባረሩ ሲወሰን የትምህርት ቢሮ ባለሥልጣናት ከሚኒስትር ጀምሮ ተረባርበውና የት/ቤቶችን ባለቤቶች በ‹ት/ቤታችሁን እንዘጋባችኋለን› አስፈራርተው ራሳቸው ያወጡትንና ያሰራጩትን ሕግ በመጣስ ያስመልሷቸዋል፡፡ ሕግ በየትም አይሠራም፡፡ በትምህርትም ሆነ በሌላው ዘርፍ ወያኔን በቀጥታም ሆነ በተዛዋሪ የሚነካ ሕግ ሥራ ላይ አይውልም፡፡ ሀገሪቱ በወለድ አግድ በነሱው ሥር ስለዋለች ሕግ የሚሠራው ለሌሎች ምሥኪኖች እንጂ ለወያኔዎች አይደለም፡፡ የምለው የምታውቁትን እንደሆነ ባውቅም እንደመምሬ አውግቼው እየደጋገምኩ ላውጋችሁ ብዬ ነው፡፡ በዚህ እንኳን ቢወጣልኝ፡፡ ጨስን እኮ ምዕመናን!!
በአንድ ‹ምሁር› አነጋገር ፈገግ ላሰኛችሁ ልሞክርና አንዳንድ ነገሮችን ጣል ጣል አድርጌ ልሰናበታችሁ፡፡ ሰዎች አንዱን ጓደኛቸውን ሲተርቡት የሰማሁት እውነተኛ ታሪክ ማለትም ገጠመኝ  ነው፡፡ የዩኒቨርስቲ ጓደኛውን ለበርካታ ዓመታት ሳያየው የኖረ አንድ ሰው ያን ድራሹ የጠፋበትን ጓደኛውን መንገድ ላይ አገኘው አሉ፡፡ ያኔ እንደምንም ለየው(ዐወቀው)ና “እንዴ! አንተ እንትና የምትባለው የዩኒቨርስቲ ጓደኛየ አይደለህም እንዴ? በስማም! በጣም develop አድርገሃል፤ በድምጽህ እኮ ነው ያወቅሁህ!” ብሎት ዕርፍ፡፡ ምን ማለቱ መሰላችሁ ‹ ወፍረሃል፤ ተለውጠሃል፤ ተስማምቶሃል…› ማለቱ ነው፡፡ አንዱ ምሩቅ ደግሞ እንዲህ ብሏል አሉ፡- ‹ፐ ፐ ፐ ያ ልጅ እንዴት ያለው cooked የሆነ ልጅ መሰለህ!› - የዚህኛውስ ገባችሁ? የአማርኛውን በቀጥታ ተርጉሞ ‹በሳል ልጅ› ለማለት ነው፡፡ የወያኔን ጊዜ ምሁራን - ሁሉም አይደሉም በነገራችን ላይ - ገድል እንጻፈው ብንል አውሎ ያሳድረናል፡፡ እዚህ ላይ በራሳቸው ጥረት በግል በሚያደርጉት ጥናትና ምርምር ምክንያት ራሳቸውን በዕውቀት ያደረጁ፣ በየትኛውም የተሰማሩበት መስክ የማያሳፍሩ ወጣትና ጎልማሣ ምሁራን መኖራቸውን መጠቆም እፈልጋለሁ - በደረቅ አበሳ እርጥብ መቃጠል የለበትም፡፡ እነዚህኞቹ ወገኖች በልዩ ድካማቸውና ያልተቆጠበ ጥረታቸው ከወያኔ ሀገርንና ትውልድን የማምከን ሤራ ያመለጡ ናቸውና የምሥጋና ብፅዓት ይገባቸዋል፡፡
በሌላ አቅጣጫ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው እንዳይኖሩ ሲገደዱ ወደ ውጪ በመፍለስና በመሰደድ በነዚያ ሀገሮች በሚገበዩት ዕውቀትና ጥበብ ለወደፊቱ ሀገራቸውን የሚጠቅሙና በእንደገና ግንባታው በከፍተኛ ደረጃ የሚሣተፉ እንደሚሆኑ ከፍተኛ ግምት አለኝ - በበኩሌ፡፡ እናም ተስፋዎቻችን ናችሁና በርቱልን እላለሁ - ፍሉሳንን፤ ደግሞም ከብት እንጂ በየሄደበት እሚለምድ እናንተ ሰዎች በመሆናችሁ ቆንጆና ገና ያልተነካ የተፈጥሮ ሀብት ያላት ሀገር ባለቤትም ስለሆናችሁ ልቦናችሁን ወዳገራችሁ ማቅናት ይኖርባችኋል፤ ጠፍታችሁ እንደምትቀሩ ሳይሆን አንድ ቀን የራሳችሁ ሀገር ባለቤት እንደምትሆኑ አስቡና ዓላማችሁን ከዚህ ቅዱስ ሃሳብ ጋር ቃኙ፡፡ በሀገር ቤቱ ግን ብዙም ተስፋ አናድርግ፡፡ በጣት ከሚቆጠሩ ጥቂቶች በስተቀር ብዙዎቻችን ራስ ወዳዶችና ለወያኔው ሥርዓት አጎብዳጆች ነነ፡፡ ቄስ የለ፣ ገበዝ የለ፣ ጳጳስ የለ፣ ኤጲስ ቆጶስ የለ፣ ምሁር የለ፣ ጨዋ የለ፣  ከሞላ ጎደል ሁላችንም ተንበርካኪዎች ሆነናል፡፡ ‹ጊዜው ነው› ልበልና በጊዜ ላላግጥ ይሆን? እኛው ነን! ጥፋተኞች እኛው ነን፡፡ ቆይ ልኮርጅ፡- የውድመታችን መሃንዲሶች እኛው፤ የመጥፋታችን የገንዘብ ምንጮች እኛው፤ የችግሮቻችን መፍትሔዎች እኛው … ታላቁን ግድብ በሚመለከት ‹ታላቁ› መሪያችን እንዲህ የመሰለ ቀልድ ሲናገር ሰምቻለሁ፡፡
ሀገር ስትጠፋ ሃይ የማይል የሃይማኖት አባት የጥፋት ተባባሪ ከመሆን አይዘልም፡፡ ሀገር ስትጠፋ ሃይ የማይል በሀገር ሀብት የተማረ ምሁር የጥፋት ተባባሪ ከመሆን አይድንም፡፡ ግፍና በደል ሲፈጸም ዝም ብለን ያየን ሁሉ - በቻልነው ያልተቃወምን ሁሉ - ኋላ ላይ የየድርሻችን ወዮታ አለብን፡፡ ስለዚህም ነው በኢትዮጵያ ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ የዘመናዊ ትምህርት ምሁርና የሃይማኖት አባትም ሆነ ተራ አገልጋይ የለም በሚለው የማምነው፡፡ ውሸት ነው፤ ሁላችንም ማለት በሚቻል መልክ ለሩህያችን እንሳሳለን - ሥጋችንንም ከሁሉም አስበልጠን እንወዳለን፡፡ ለኅሊናውና ለነፍሱ ያደረ ሰው ሥጋውን ይጠየፋል፤ ለኅሊናውና ለነፍሱም አድሮ ግፍን ይቃወማል - በዚያም የጽድቅ ሥራው የሞት ጽዋንና የእሥራት መቁነን ሳይቀር ይጋፈጣል፡፡ እነ አንዷለም አራጌና እስክንድር ነጋ የነፍሳቸውን መክሊት ተረድተው የኢትዮጵያዊነታቸውን አሥራት ብኩራት እየከፈሉ በመገኘታቸው እቀናባቸዋለሁ፡፡ የነሱን ያህል በማይሆን አነስተኛ ወጪ ሀገራችንን ከክፋት መታደግ የምንችል ሚሊዮኖች ዝም ብለን ተቀምጠን ስመለከት ደግሞ በራሴ አፍራለሁ፡፡ የእናት ሆድ ዥንጉርጉር መባሉም ለዚህ ነው፡፡ በሀገር ደረጃ ግፍና በደል ናኝቶ ሕዝብ ሲረገጥና ሲጨቆን ዝም የሚል የሃይማኖት አባት ካለ ያ ሰው የሰይጣን ተባባሪ መሆኑን ለመገንዘብ መጽሐፍ መግለጥ ወይ ጠንቋይ መቀለብ አያስፈልግም፡፡ ለሥጋው ያደረ ነፍሱን እንደሚያጣ ከኔ የበለጠ ቀሲስ አስመሮምና ደብተራ ጓንጉል ያውቃሉ፤ ግፍ ሲፈጸም ‹ተው! በሠይፍ የሚገድሉ በሠይፍ ይገደላሉ› ብሎ የማይገስጽ የሃይማኖት አባት ለዓለማዊ ኑሮው የተሸነፈና ለመብል መጠጥ እንዲሁም ለርክብክብ ሥጋ የተንበረከከ መሆኑ ግልጽ ነው - ቃሉም ጠፋኝ፡፡ ሰውንና ሥልጣኑን በመፍራት የእግዚአብሔርን ቃል የሚሽሩ ካህናትና ጳጳሳት በእግዚአብሔር ኅልውና ስለማመናቸው ማወቅ ይከብዳል፡፡ እውነትን የሚቀብሩ ሀሰትን ግን የሚያነግሡ ካህናትና ሊቃነ ጳጳሣት በእግዚአብሔር የማያምኑ ለጨለማው ንጉሥ ግን ቅን ታዛዥ የሆኑ የሥጋዊው ዓለም ሰዎች ናቸው - በዚያ ላይ ‹ለሁለት ጌቶች አትገዙ› የሚለውን ቅዱስ ቃል ለሥጋቸው ሲሉ ሽረውታልና ጽድቅ ከነሱ ጋር አትገኝም፡፡ እንቅልፍ የሞት ታናሽ ወንድም እንደሆነ ሁሉ ኃጢኣተኝነትም የሰይጣናዊነት መገለጫ ነውና ከሚባርኩን ውስጥ የትኞቹ በወዲያኛው ሊባረኩ እንደሚችሉ ለማወቅ ጥልቅ መንፈሳዊነትንና ልባዊ ጸሎትን ይጠይቃል፡፡ ይህን በማይም ቃሌ የምናገረውን ማስተባበል የሚቻለው አንድም ካህን ሊኖር አይችልም፤ ቢኖር እርሱ አንድም ገነት ውስጥ ነው አንድም እኔ አላውቅም፡፡ መሀል ቤት እንደሌለ ግን ይገባኛል፡፡ በተጠየቁ መሠረት ጽድቅና ኩነኔ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ሊሆኑ አይችሉም፤ ጧት ማጉራትና ማታ ዳዊት መድገም እንደማይቻል ሁሉ በእግዚአብሔር ስም እየነገዱ ፍጡራኑን ለአረመኔዎች ጅራፍ አጋልጦ ከአረመኔዎች ጋር መሞዳሞድና ዲያብሎሳዊ ቅኔ ማኅሌት መቆም አይቻልም፡፡ ይህን እውነት ኢትዮጵያ ውስጥ እየኖረ ነግር ግን ለሥጋው ተሸንፎ መስቀሉን ለኃጥኣን ግሣጼ ያላዋለ የሃይማኖት አባት ነኝ የሚል ሐሳዊ መሢሕ ሁሉ ይገንዘብ፡፡ ደረታቸውን ለጦር አንገታቸውን ለሠይፍ የሰጡ እነቅዱስ ጳውሎስንና መጥምቁ ዮሐንስን ያስቧል፡፡ ባማረ ፎቅ እየኖሩ፣ ያማረን እየለበሱ፣ በዲኤክስና በቪታራ እየተንፈላሰሱ የክብር አክሊል ይገኛል ማለት ዘበት ነው - እንደዚህስ የዚያኛው ጎራ አባላትም አያቅታቸውም፡፡ ቀደምት ጻድቃንና ሰማዕታት ያን ሁሉ መለኮታዊ ክብር የተጎናጸፉት የተላጠ ሙዝ እንደሚመስሉት እንደኋለኞቹ ዘበናይ አባቶች በወርቅና በነሐስ መስቀል እየተሸሞነሞኑ፣ ከእግዚአብሔር ይበልጥ በምዕመናን ዘንድ እንደጣዖት ሊከበሩ እየቃጡ፣ መንፈሣዊ ተልእኳቸውን ንቀው (ፈጣሪን ንቀው) ከዓለማዊ መንግሥታት ጋር በመሻረክ ለዓለማዊ ድሎታቸው እያደሉ፣ ከቃለ ዐዋዲው ውጪ አሥሩ ቦታ እየደቀሉና በድብቅ ልጅ እያሳደጉ የሁለት ዓለም ሰዎች ሆነው  ሳይሆን የተቆጠረች ውሱን ሽምብራ እያንቀራጩና ዐይን ያላያት ሥጋ ያልሳሳባት የበረሃ ቅጠል ተሲያት ላይ ቀንጥሰው እየቀመሱ፣ ከእባብና ዘንዶ እንዲሁም ከአንበሣና ከነብር ጋር በዱር በገደል እየታገሉ፣ ከከሃዲያንና ከአረመኔ መንግሥታት ጋር እየተፋለሙ ነው፡፡ መንፈሣዊ ተጋድሎ ቀላል አይደለም፤ በዘረጥ እምቦጥም የሰማያዊ መንግሥት ወራሽ አይኮንም፤ ልብ እንበል - ከዚህ አኳያ ቤተ ክርስቲያናችን ብዙ የምታወራርደው ዕዳ ከፊት ለፊቷ ተደቅኗል፡፡ በግልቡ ለየዋሃን እንደሚታየው ነገሩ ጥምጥም የማሳመርና ቃለ እግዚአብሔርን የማነብነብ ወይም በያሬዳዊ ዜማ ምእመናንን የመመሰጥ ጉዳይ አይደለም … ብዙ ማለት ይቻላል፡፡ በዚህ ረገድስ ጊዜው ሲደርስ በግልጽ ለመነጋገር ያብቃን፡፡
ልጨረስ ነው አይዞህ፡፡ የኑሮ ውድነቱ እንደወትሮው ሁሉ ህዝብን ባልተወለደ አንጀቱ እየሸነቆጠ ነው፡፡ ቲማቲምም ባቅሙ 25 ብርን ከዘለለ ሰነበተ፡፡ ዱሮ የሥጋ ቁርጥ ነበር የሚያምረን፡፡ አሁን ደግሞ የቲማቲም ቁርጥ - ሰላጣ ከሥጋ ቁርጥ ሊስተካከል ተቃርቧል፡፡ ሥጋ ለብዙዎቻችን የመዝገበ ቃላት ቃል ከሆነ ከረመ፡፡ የ300 ብር ደሞዝተኛ በአማካይ የ150 ብር ቁርጥ ሲበላ ይታይህ፡፡ የ600 ብር ደሞዝተኛ የ180 ብር ኪሎ ቅቤ ሲገዛ ይታይህ፡፡ የ1000 ብር ደሞዝተኛ የ40ና 50 ብር እዚህ ግባ የማይሉት አንድን ሕጻን እንኳን የማያጠግብ የበሬ ይሁን የበግና የፍየል ወይም ለባህላዊና ሃይማኖታዊ የአመጋገብ ሥርዓታችን እንግዳ የሆነ የሌላ ፍጡር ሥጋ ጥብስ እቡና ቤት ገዝቶ ሲመገብ ይታይህ፡፡ የ1500 ብር ደሞዝተኛ በደህናው ቀን ለገዛው አልጋው የ700 እና የ800 ብር ብርድ ልብስ ወይም የ450 እና የ600 ብር አንሶላ ሲገዛ ይታይህ፡፡ የ400 ብር የጽዳት ሠራተኛ በታክሲና በከተማ አውቶቡስ ስትጓዝና የ15 ብር የፍራፍሬ ጭማቂ ስትጠጣ ትታይህ፡፡ እኔ ዳግማዊ መጠኑን በጭራሽ በማልነግርህ የሦስት ሺህ ብር ወርሃዊ የተጣራ ደመወዜ ለአሥር ቤተሰቤ የሚበቃ (ለሥጋና ወተቱ ዐርብና ረቡዕን ሳይጨምር) በየቀኑ 3 ኪሎ ሥጋ፣ 3 ኪሎ ጤፍ፣ ግማሽ ሊትር የምግብ ዘይት፣ ለአንድ የወንድና ለአንድ የሴት በድምሩ ለሁለት ዕድሮች የሚከፈል፣ አንድ ሊትር ላምባ፣ 3 ነጠላ ሻማዎች፣ 3 ሊትር ወተት፣ 3 ኪሎ አትክልትና ፍራፍሬ፣ 3 ጃምቦ ድራፍት፣ 3 ለስላሳ (ከውኃ ጋር አብቃቅቶ ለመጠጣት)፣ 3 ቡና፣ 6 ኪሎዋት ኮረንቲ፣ ሩብ ኪዩቢክ ሊትር ውኃ፣ በአማካይ አሥር የቤት ሥልክ ጥሪ፣ በቤተሰብ የሚከፋፈል የ100 ብር ሞባይል ካርድ፣  አንድ ኪሎ ከሰል፣ ግማሽ ኪሎ ስኳር ከነቀጠፉ፣ የ30 ኪሎ ሜትር ቤት/መሥሪያ ቤት ደርሶ መልስ ጉዞ፣ ኦ! ደከመኝ … ይህን ሁሉ ስገበይ ይታይህ፡፡ ባይገርምህ ከ40 ዓመታት በፊት በነበረ ገበያ እነዚህንና ሌሎችንም ጨምሮ ቤትን ለማሟላት በከፍተኛ ግምት የ200 ብር ደሞዝተኛ ብቻ መሆን ነበር የሚያስፈልግ፡፡ ዛሬ ወያኔ መጣና ሁሉን ነገር እንዳይሆን እንዳይሆን አደረገና የአሥር ሺህ ብር ደሞዝተኛ ሳይቀር በኑሮው ብዙ እየጎደለበት ከድሃው ጋር የሚያላዝን ሆኗል፡፡ አልፎለት የምታየው ኅሊናውን በየቤቱ ታዛ ሸጉቦ አቅሉን ለገንዘብ ሸጦ በመጣው ይምጣ ከወያኔ ጋር የወየነ ብቻ ነው - ወቅቱ ራስን የማዳን ነው፡፡ ተንደላቅቀህ ለመኖር ኅሊና፣ አእምሮ፣ አስተሳሰብ፣ አመለካከት፣ ምናምን እንዲኖርህ አያስፈልግም፡፡ ሌላውና ብዙኃኑ ይልሰውንና ይቀምሰውን አጥቶ በሞትና በሕይወት መካከል እየተንጠራወዘ በሆዳቸው የሚያስቡና ነገን የማያውቁ ብቻ በቆንጆ ሁኔታ እየኖሩ ናቸው፡፡
ባክህን ትንሽ ላክል - መለየቱ አሳሳኝ፡፡ የ700 ብር ደሞዝተኛ ፖሊስ የ800 ብር ቤት ተከራይቶ ከነቤተሰቡ ሲኖር ይታያችሁ፡፡ የ500 ብር ደሞዝተኛ ርካሹን የ300 ብር ጫማና የ16 ብር ካልሲ ሲገዛ ይታያችሁ፡፡ ዛሬ ሸሚዝ ለመግዛት ቁብ መግባት አለብህ - ጥሩ ሸሚዝ ከብር 400 ይጀምራል፡፡ የጥንቱ የ120 ብር የሎንዶን ሱፍ ዛሬ ከ12000 ብር በላይ ነው፤ የቻይና ፍርጅድ ሱፍ ራሱ ከ2000 ብር በላይ ይሸጣል - እንደዝምብ አማካይ ዕድሜ አገልግሎታቸው በ15 ቀናት ውስጥ በሚጠናቀቅ የፎርጅድ ዕቃዎች ተጥለቅልቀናል - ለነገሩ ሁሉም ነገራችን ፎርጅድ ሆኗል፤ ትምህርቱ፣ ሰው ሁሉ ፎርጅድ፣ መስተንግዶው ፎርጅድ፣ ፈገግታው ፎርጅድ፣ አገልግሎቱ ፎርጅድ፣ ቅዳሤውና ማኅሌቱ ፎርጅድ፣ ንስሃ አባቱ ፎርጅድ፣ ስብከቱ ፎርጅድ፣ … ፎርጅድ ያልሆነውና ጄኒውን የምንለው እንደእንስሳት ኖረን እንደሰው መሞታችን ብቻ ነው፡፡ ምን አለፋህ ወንድሜ - የምንኖረው በተዓምር ነው፡፡ የሰዎችን ገቢ ስትሰሙና ቀኑ እንዴት ነግቶላቸው እንደሚመሽ ስትታዘቡ ከአእምሮ በላይ በሆነ አንዳች ስሜት ትወጠራላችሁ፡፡ የመንግሥትን ጭካኔ አይታችሁ፣ የግል ኢንቬስተሮችንና ሀብታሞችን አረመኔነት ተመልክታችሁ በሥራቸው የሚገኙ ምዝብር ድሆች እንዴት እንደሚኖሩ ስታጤኑ መፈጠራችሁን ትጠላላችሁ፤ የዓለምን  ፍጻሜም ትመኛላችሁ - ልክ እንደኔ፡፡ ‹ሰውን መግዛት እያስራቡና እያሰቃዩ ነው› የሚለው ነባር የኢትዮጵያው ብሂል ይከሰትላችኋል፡፡ መንግሥትና አብዛኛው ኢንቬስተር sadist ናቸው ተብሎ ቢታመን ድርብርብ እውነት ነው፡፡
ሰሞኑን ደግሞ ይሄ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚባል የቅዱሱን ስም አላግባብ አስካሪ መጠጡ ላይ የለጠፈ ቢራ ኮማሪ ድርጅት አብዝቶታል፡፡ ከወያኔ ጋር እየተባበረ በብሻን ጮረሬ የፋብሪካ ጠላው ሕዝብን መግፈፉ አነሰውና በየስድስት ወሩ በሚጨምረው ዋጋው ምድረ መኢጠማን (መላው የኢትዮጵያ ጠጪዎች ማኅበር) እያማረረው(ን) ይገኛል፡፡ ነሸጥ ባረገው ጊዜ ሁሉ እየባነነ በሚጨምረው ዋጋ የአንድ ነጠላ ድራፍት ዋጋ ከ85 ሣንቲም እኔ የማውቅለት ዋጋ ተነስቶ ዛሬ 6 ብር እንዲደርስ አድርጎታል፡፡ ከግንቦት 97 በፊት ባማካይ 2.70 የነበረው ጃምቦ ዛሬ በብዙ ቦታዎች 12 ብርን አሻቅቧል፡፡ የሚገርመው ጊዮርጊሶች ከጨመሩ ሌሎቹም እንዲጨምሩ መገደዳቸው ነው፡፡ የሕዝቡን - ማለትም የጠጪውን ማኅበረሰብ የልብ ትርታና የሥነ ልቦና ቀመር ሳይረዱት አልቀሩም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ዋጋ ሲጨምር ገበያ ይደራል፡፡ በውሰት አገላለጽ ባሕርያችንን ለመጠቆም ያህል - እኛ ኢትዮጵያውያን ወደ አውሮፓውያን የገበያ ሥሪት ከምንገባና መብታችንን በጋርዮሻዊ አድማ ከምናስከብር ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ብትሾልክ ሳይቀላት አይቀርም፡፡ የምንገርም ሕዝብ ነን፡፡ ድራፍትና ቢራ የዕድሜ ማራዘሚያ ኤ.አር.ቪ የሆነ ያህል፣ ድራፍት ለአንድ ሣምንት ባንጠጣ የምንሞት ይመስል፣ አልኮል መጠጣትን ለአንድ ቀን ብንተው የምንዋረድና ድህነታችንን ለ‹ጠላት ለወዳጅ› የገለጥን ይመስል … በራሳችን ገንዘብና በድንቁርናችን ምክንያት ሻጮችና ኮማሪዎች በላያችን ላይ ለዘላለሙ እንዲነግሡብን ተመቻቸንላቸው፡፡ አህያና አጋሰስ መጋጃ ሆንልናቸውና አምቡላቸውንና አተላቸውን በፈለጉት ዋጋ ይቸረችሩልን ያዙ፡፡ በመሠረቱ ይሄ የኛ እንጂ የነሱ ጉዳይ አይደለም፡፡
እነሱማ ከመንግሥት ጋር እየተመሳጠሩ ገቢያቸውንም በስንጥቅ ትርፍ እያሳደጉ በሚከፍሉት ከኛው አላግባብ የሚዘረፍ የመንግሥት ግብርም መትረየስ ከነአረሩ እየተገዛ በኛው በድሆቹ ልጆች አናት ላይ ይርከፈከፋል - መብታችንን በጠየቅን ቁጥር፡፡ በእግረ መንገድም በቡና ቤት ለመዝናናት አቅም ያጣን ዜጎች እንደዶሮ በጊዜ ወደየቤታችን ስንሰተር መንግሥትን አናማም፤ አንቦጭቅም፡፡ ያኔ ወያኔው አንጻራዊ ዕረፍት ያገኛል፡፡ ለአንድ ቡና ወይ ማኪያቶ  8 እና 10 ብር ካልከፈልክ፣ በተለይ በቦሌ መስመር ለአንድ ኬክ ሃያና ሠላሣ ምናምን ብር ካልተዘረፍክ፣ ከጉሮሮ ለማያልፍ በአረፋ የተሞላ አንድ ድራፍት አሥራ ምናምን ብር ቁጭ ካላደረግህ፣ … እንዲያው ተጎልተህ የማንን ወንበር ታሞቃለህ? ማንስ ያስቀምጥሃል? ኤዲያ! የኢትዮጵያ ነገርስ … ምነው እግዜሩም እንደሰው ጨከነ ግን? እነዚህ ወያኔዎች እኮ የማይገቡበት የለም፤ እሱንም ‹ሆስቴጅ› አድርገውት ይሆን እንዴ? መጠርጠር ነው! ለማንኛውም እንዲህ ማለቴን አትፍረዱብኝ - ቢጨንቀኝ ነው - “እስከማዕዜኑ ትረስዓኒ ሊተ” ብሏል አሉ  ዳዊት እንደኛው ቢጨነቅ፡፡ ኢዮብም ክፉኛ ይወቅስ ነበር፡፡
ያገሬ ባላገርስ እንዲህ ያለው ወዶ ነው?
ቀና ብዬ ባየው ሰማዩ ቀለለኝ፤
አንተንም ሠፈራ ወሰዱህ መሰለኝ፡፡
እርግጥ ነው - የእግዚአብሔርን ሥልጣንና ኃይል አይዘባበቱበትም፤ ሰው ሲጨነቅ ብዙ ይላል እንጂ የፍርዱ ቀን መምጣቱ በጭራሽ አይቀርም፡፡ እንዲያውም ወንጀልና የክፋት ሥራ ሲበዛ ቀኑ እንደቀረበ ምልክት ነውና ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ በአስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ የሚገኝ እንደኔ ዓይነቱ ሆደ ባሻ ሰው ብዙ ያስቀይማልና በድምብርብር አነጋገሬ የተከፋችሁ ይቅርታ ታደርጉልኝ ዘንድ ከልብ እለምናለሁ፡፡ ቻው፡፡

አሸባሪዉ ኢህአዴግና የፀረሽብር ህጉ መወገድ አለባቸዉ

July 21/2013

ኢትዮጵያንና ህዝቧን የአብሮነትን መሠረት  እና ፍቅር ለመሸርሸርና ብሎም ለማጥፋት ሌተ ቀን የማይተኛዉ የህወሀት የወያኔው የወያኔው አሸባሪ መራሹ መንግስት በህዝብ ጫንቃ ላይ ተቀምጦ የኢትዮጵያን ሀብት እና ንብረት እየዘረፈ የሕዝባችንን ደም እየመጠጠ እና ዜጎችን ማሰቃየት ከጀመረ እነሆ 22 አመት ተቆጥሮዋል። 

 ነገር ግን የ22 አመት ቆይታዉ ህዠብን  እና ንጹሐነን ዜጓቸ ከማሸበር፣ ከመግደል፣ ለመብታቸው እና ለህዝብ ነጻነት የቆሙትን እውነተኛ ጋዚጠኞችን እና የፖለቲካ ሰዎችን ከማሰር ከማሰደድ፣ከመግረፍና ከማፈናቀል አልፎ በተመቸዉና የጥፋት ምርቃናዉ በመጣለት ቁጥር በዘረኞች መሪዎቹ አማካይነት በፈለገዉ ሰዐት ከራሱ ህግና ስርአት  ውጪ ከእንቅልፋ እንደሚነቃና የሚያደርገዉን እንደማያቅ ህፃን ልጅ የተለያዮ ህጎችን በማዉጣት ጭምርህዝባችንን ከህዝባችን እንዲሁም ሀገሪቱዋን ባለቤት የሚያሳጣ አስነዋሪ ህጎች በማርቀቅና ድራማ በመስራት ማፍያ ስርአት መሆኑ ይታወቃል።  ከእነዚህ የህወሀት ኢህአዴግ አስነዋሪ ህጎች አንዱ የፀረ ሽብሩ ህግ አዋጁ በሙዋቹ ቀንደኛ ማፍያ መሪያቸዉ መለስ ዜናዊ መሪነትና በሌሎች አጭበርባሪ ሆዳም የሀገር ፍቅር በሌላቸዉ ተከታዮችአማካይነት የፀረ ሽብር ህግ አዉጥቶ አምስት መቶ አርባ አንድ  እጅ በሚያነሱለት የፓርላማ  የወያኔ አሻንጉሊቶቹ ድጋፍ ማፀደቁ የሚታወቅ ነዉ አሳዛኝ ድርጊት ነው ።

ይህ ህግ አሁንም አንባ ገነን በነበረው መሪያቸዉ የሙት መንፈስ ራእይ ስምና አሁንም በተተካዉ አሻንጉሊት በሙት መንፈስ በሚመራው  ሀይለማርያም ደሳለኝ ህጉ እንደቀጠለ ሲሆን ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚያሸብረ ወያኔ ሆኖ ሳለ ነገር ግንበመሣርያ የበላይነት በሀገሪቷ ዉስጥ ከወያኔ የተለየ ሀሳብ ያላቸዉ በህጉ የስቃይ ሰለባ እየሆኑ ነዉ በየቦታውም እየተሰቃዩ ነው ።

          ለዚህም ማስረጃ ሰሞኑን ወገናችን አንድ ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ በአንድነት ፓርቲ ጽህፈት ቤት ዉስጥ የሚሊዮኖች ድምፅ በሚል በሰጠዉ ቃለ ምልልስ ለሃያ ሶስት ወራት፣ ለሶስት ወር ማዕከላዊ ለ19 ወር ደ ግሞ በዝዋይ እስር ቤት በወያኔ ካድሬዎች በግፍ ኢሰብአዊና በረመኔያዊ የጭካኔ በደል እየቀጠቀጡ እና እየደበደቡ ፍዳዉን አብልተዉ የቁም ሞት ገለዉ ከለቀቁት በዉኃላ በዚህ የፀረ ሽብር ህግ ምክንያት ህይወቱ ጉዳና ላይ ወድቋል ንፁሀን ዜጎች ከሱ ጭምር የህጉ ሠለባ መሆናቸዉን ከአንደበቱ ሰምተናል።

          ስለዚህ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ በአንድነት ዛሬ ነገ ሳይል እንደ ተስፋዬ ተካልኝ እይነት ሚሊዮኖችን  በየቦታው ከተለያዮ ግልፅና ስዉር የማሰቃያ ቦታዎች ሊታደጋቸዉ እንዲሁም አሸባሪዉ ህወሀት ወያኔ  ፀረ ሽብር ህጉን ከኢትዮጵያ ማስወገድ አለበት። አሸባሪው እሱ እራሱ ወያኔ ስለሆነ መወገድ አለበት ምክንያቱም ህዘባችን በህዚ ሽብርተኛ ህጉ መሰረት በእየቦታው እየተሰቃየ ነው :: 

       ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ   

Saturday, July 20, 2013

በዳያስፖራ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ

ሐምሌ  13 ቀን 2005 ዓ.ም
MillionsVoice1«ነጻነትን ማንም አይሰጥህም። እኩልነትና ፍትህንም ማንም አይሰጥምህ። ሰው ከሆንክ፣ አንተዉ እራስህ  ተቀበለው» ነበር ያሉት፣  የሰብአዊ መብት ተሟጋች ማልኮም ኤክስ። ነጻነትና ሰላም፣  ዴሞክራሲና ፍትህ፣ እኩልነትና መልካም አስተዳደር፣ ሌሎች የሚሰጡን ሳይሆን፣  ፈጣሪ በቸርነቱ የለገሰን፣ ደፍረንና ፈቅደን የምንቀበላቸው፣  የኛዉ የሆኑ በረከቶች ናቸው።
ነገር ግን ለአመታት መብታችንና ነጻነታችን፣  በጥቂቶች ተገፎ፣ ሁላችንም በየጓዳችን ስንናደድ፣ ስናማርር፣ ስናዝን፣ ስንራገም፣ ልባችን ሲደማ፣ «እንደዉ ምን ይሻላል? » እየተባባልን ስናወራ ቆይተናል። ለዜጎቿ ሁሉ እኩል የሆነች፣ ሕግ የበላይ የሆነባት፣ ፍትህ የሰፈነባት፣ ሕዝቡ ለመሪዎች ሳይሆን መሪዎች ለሕዝብ የሚንበረክኩባት፣ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለማየት ትልቅ ጉጉት አለን።
ማልኮም ኤክስ እንዳሉት፣ ፍትህንና እኩልነትን እንዲያመጡልን፣  ሌሎችን መጠበቅ የለብንም። እያንዳንዳችን መንቀሳቀስ ይኖርብናል። በአገር ቤት፣ በጎንደርና በደሴ እንደታየው፣  ከፍተኛ፣ ሰላማዊ፣ የሰለጠነ የፍቅር ፖለቲካ ላይ ያተኮረ፣ እንቅስቅሴ እየተደረገ ነዉ። እንቅስቅሴዎቹ በባህር ዳር፣ በፍቼ፣ በጂንካ፣ በአርባ ምንጭ፣ በአዳማ፣ በመቀሌ፣ በወላይታ ሶዳ፣ በጋምቤላ በአሶሳ .. እያለ ይቀጥላል። በአገሪቷ ክልሎች ሁሉ ያለው ሕዝቡ  መብቱንና ነጻነቱን እንዲያስከብር ቅስቀሳ ይደረጋል። ለምን ? የምንፈልጋት ኢትዮጵያ ልትመጣ የምትችለው እኛን ጨምሮ ሕዝቡ ቀን ሲል ብቻ በመሆኑ።
በዉጭ አገር ያለነዉ ፣ አገር ቤት ያለው ሕዝብ አካል ነን። «ምን ተደረገ?» እያልን የምንከታተል ብቻ ሳይሆን፣ የሚደረጉት እንቅስቃሴዎች አካል መሆን መቻል አለብን። እምነት ያለን በጸሎታችን፣ ገንዘብ ያለን በገንዘባችን፣ ጠቃሚ፣ ትግሉን ወደፊት ሊያስኬዱ የሚችሉ ምክሮችና አስተያየቶች ያሉን፣  ሃሳቦቻችን በማቅረብ፣  ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረግ እንችላለን። ይገባናልም።
የአንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ግብረ ኃይል፣  ለሕዝብ ይፋ ያደረገዉን የሶስት ወራት እንቅስቃሴ ለመደገፍና ለማገዝ፣ በዳያስፖራ የሚሊየኖች ድምጽ ለነጻነት ግብረ ኃይል ተቋቁሟል። ግብረ ኃይሉ የተለያዩ መርሃ ግብሮችን  አውጥቶ፣ ዳያስፖራዉ እንዴት ሊረዳ፣ ሊደግፍና የሚሊዮኖች አንዱ ሊሆን እንደሚችል መረጃዎች የሚያቀርብና አቅጣቻዎችን የሚያሳይ ይሆናል። በዉጭ አገር የሚገኙ ሬዲዮች፣ ቴሌቭዥኖች ፣ ድህረ ገጾች፣  የሲቪክ ማህብራትና በዉጭ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ ድጋፋቸዉን እንዲሰጡንም በአክብሮት ጥሪ እናቀርባለን።
በኢትዮጵያ ወገኖቻችን ትልቅ ዋጋ እየከፈሉ ነዉ። በዉጭ አገር ያለን ኢትዮጵያውያን፣  ከዚህ በፊት ብዙ ለአገራችን ደክመናል። አሁን ወሳኝ ወቅት ላይ እንዳለን ተረድተን፣ ከዚህ በፊት ካደረግነዉ በላይ ለማድረግ እንነሳ። ትላንት ወድቀን ቆስለን ሊሆን ይችላል። የትላንቱ ጠበሳ ወደፊት እንዳንሄድ ሊያግደን ግን አይገባም። ከወደቅንበትና ከተኛንበት ተነስተን፣ ከቆምንበት ተንቀሳቅሰን፣ ወደፊት በመሄድ መቻል አለብን።
ከሚሊዮኖች አንዱ እንሁን ! በዚህ ወቅት እኛ ካልተባበረን ማን ? ?  ዛሬ ካልሆነ መቼ ?

Privatizing EFFORT and all Other EPRDF Controlled Companies to Build Abay Dam

July 19, 2013
by Asress Mulugeta

Meles Zenawi, From ethnic liberator to national atrocitiesAll dictators on the African continent have sought immortality by leaving a legacy that will outlive them and endure for the ages. But all have inherited the wind. Kwame Nkrumah led the first sub-Saharan African country to gain independence from colonialism in 1957. Nkrumaism sought to transform Ghana into a modern socialist state through state-driven industrialization. He built the Akosombo Dam on the Volta River, at the time considered the “largest single investment in the economic development plans of Ghana”. He promoted the cult of personality and was hailed as the “Messiah”, “Father of Ghana and Pan Africanism” and “Father of African nationalism”.

  He crushed the unions and the opposition, jailed the judges, created a one-man, one-party state and tried to make himself “President for life”. He got the military boot in 1966. He left a bitter legacy of one-man, one-party rule which to this day serves as a model of dictatorship for all of Africa. Nkrumah died in exile and inherited the wind. Gamal Abdel Nasser of Egypt left a legacy of military dictatorship in Egypt and inherited the wind. Mobutu Sese Seko of Zaire left a legacy of kleptocracy and inherited the wind. Moamar Gadhafi left a legacy of division and destruction in Libya and inherited the wind. Idi Amin Dada of Uganda left a legacy of death, destruction and ethnic division in Uganda and inherited the wind.

Like all those African dictators, the late Meles Zenawi, sought to make himself larger than life. He was not only Ethiopia’s savior but Africa’s as well. He sought to project himself as a “visionary leader”, “inspirational spokesman for Africa” and supreme practitioner of “revolutionary democracy. Like all those African dictators before him, Meles had illusions, delusions and obsessions. Meles’ Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) created an Ethiopia based around ethnically defined regions and political parties, state control over land and other key economic assets and a strong authoritarian political party. Due to the monopoly of Power and the economy by Meles’s wing TPLF and the implementation of ethnic-based federalism, ‘ethnicisation’ of socio-economic disputes is increasing exponentially all over Ethiopia.

Few years before his death, Meles Zenawi started an extremely ambitious plan to build the 6,000MW Grand Renaissance Dam on the Nile River just in five years period. The Ethiopian government made clear that it will not seek external financing for the Renaissance Dam ($4.5billion). The other plan of Meles is to construct 4,744km national railway in two phases by seeking loan from China, India, Brazil and Turkey. There are also many mega projects that are included in the Growth and Transformation Plan (GTP) of the Meles Zenawi. A year before Meles died before seeing any those grand projects completed. After his death, the Ethiopian officials have vowed to implement the vision of Meles zenawi.  If they failed, the other face of Meles that is his bitter legacy of one-man, one-party rule and ethnic division will only be remembered by Ethiopians.

It is true that in modern times no country has managed to substantially reduce poverty without greatly increasing the use of electrical energy. It is also true that Railways in India has contributed a great deal to the commercialization of agricultural sector and to the rapid industrialization of a country by moving labor and capital easily. Railways have helped in diluting the intensity of famines by carrying the food-grains from surplus to famine-stricken areas. The recent attempt by the Ethiopian government to develop the railway and energy sector is a good step to boost the development of country but getting the money to finance those grand projects is a big challenge. The Ethiopian foreign minister has done a futile attempt to collect money from Ethiopians in the Diaspora.  The good idea is sell-off (privatize) the EPRDF controlled companies to finance Nile Dam and other mega projects.

The Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF), a ruling political coalition in Ethiopia is an alliance of four groups. All those four political parties have endowments. Tiret, an endowment fund under the Amhara National Democratic Movement (ANDM) owns only five companies in Ethiopia. Those are Ambassel Trading House, Belesa Logistics & Transit, Dashen Brewery Plc, Tikur Abbay Transport and Zeleke Agriculture Mechanization. Dinsho, an endowment fund under the Oromo People’s Democratic Front (OPDO) owns a group of five small companies such as Dinsho Agro-Industry private limited company, Dinsho Transport Service Company, Dinsho Trading Company, Biftu Dinsho trading company and Din-System P.L.C. The Southern Ethiopian People’s Democratic Movement (SEPDM) also owns a company called Wendo trading.

EFFORT, an endowment fund under Tigrayan people’s liberation Front (TPLF) owns more than 60 companies.  EFFORT owns almost all the major industries in Ethiopia including Banking, Construction, Agribusiness, Mining, Communication, Insurance and other pillars of the economy that are vital to the well-being of the country. Some of the EFFORT companies include Messobe Cement Factory, Mesfin Engineering, Ezana Mining, Sur Construction, Almeda Textile, Addis Pharmaceutical production, Africa Insurance, Trans Ethiopia, Star Pharmaceuticals, Sheba Tannery Factory, Mega Net Corp, Tana Trading, Express Transit, Dedebit Saving & Loan, Experience Ethiopia Travel, Segel Construction, Global Auto Spare part, Hiwot Agriculture Mechanization etc…

TPLF’s economic empire has monopolized the private sector of the Ethiopian economy to the extent never seen anywhere in the African continent. Due to the monopoly of Power and the economy by TPLF and the implementation of ethnic-based federalism, ‘ethnicisation’ of socio-economic disputes is increasing exponentially all over Ethiopia. Even though the military and the security are still under complete grip of TPLF, recently the appointment of Hailemariam Desalegn from the South Ethiopian Peoples’ Democratic Front as a prime minister of Ethiopia is a good start in Power-sharing among ruling coalition. But a lot has to be done especially in the economic area.

If privatized, the companies under the control of Oromo People’s Democratic Front (OPDO), Amhara National Democratic Movement (ANDM), Southern Ethiopian People’s Democratic Movement (SEPDM) can have a net worth of around 1 billion dollar, whereas, the companies under Tigrayan people’s liberation Front (TPLF) can have a net worth around 6 to 7 billion dollar. With total generated money of 7 to 8 billion dollar, the Ethiopian government can accelerate the construction of the Renaissance Dam, the 4,744km national railway system and other mega projects in the country.

መድረክ በመቀሌ በሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ እንዳይቀሰቅስ ተከለከለ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር(መድረክ) የፊታችን እሁድ ሐምሌ 14 ቀን 2005ዓ.ም. ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ በመቀሌ ከተማ ማጋጃ ቤት አዳራሽ ውስጥ ለሚያካሂደው ህዝባዊ ስብሰባ በመኪና ቅስቀሳ እንዳያደርግ መከልከሉን ከስፍራው የዓረና ትግራይ እና የአንድነት/መድረክ አመራሮች ገለፁ፡፡ መድረክ በሀገራዊ አንገብጋቢ ጉዳዮች ዙሪያ ከመቀሌና አካባቢዋ ነዋሪዎች ጋር ለመወያት ዝግጅቱን ያጠናቀቀ በመሆኑ ህዝቡ በነፃነት ይመክር ዘንድ በተዘጋጀው መድረክ ላይ እንዲገኝ በድምፅ ማጉያ እና በመኪና ቅስቀሳ ማድረግ እንደማይችሉና ለዚህም እውቅና እና ጥበቃ እንደማያደርጉ የከተማው ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ገ/ህይወት ካሳዬ መናገራቸውን የስብሰባው አስተባባሪ ከሞቴዎች ከመቀሌ በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡

የዓረና ትግራይ/መድረክ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ብርሃኑ በርሄ ስለጉዳዩ ጠይቀናቸው መድረክ ሐምሌ 7 ቀን 2005ዓ.ም. ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ በማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ህዝባዊ ስብሰባ እንደሚያደርግ ለሚመለከተው አካል ብናሳውቅም በድምፅ ማጉያና በመኪና ቅስቀሳ ማድረግ አትችሉም ተባልን፤ ነገር ግን ለህወሓት/ኢህአዴግ ጠቅላላ ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ በየጊዜው በድምፅ ማጉያና በመኪና ቅስቀሳ ይደረግ የለም ወይ? የሚል ጥያቄ ስናነሳ ህወሓት/ኢህአዴግ ሰላማዊ ሰልፍ ስለሚያደርግ ነው የፈቀድነው፣ አሁን ግን የመቀሌ ህዝብ ድምፅ ማጉያ እየረበሸን ነው በማለቱ በከተማው ምክር ቤት ተወስኗል የሚል አሳዛኝ ምላሽ ተሰጥቶናል ሲሉ ገልፀውልናል፡፡ ሌላው የስብሰባው አስተባባሪ ኮሜቴ አባል በትግራይ የአንድነት/መድረክ ዋና ፀሐፊ አቶ ክብሮም ብርሃነ በበኩላቸው የከተማው ፖሊስ አዛዥና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ቅስቀሳ እንዳናደርግ ቢከለክሉንም ህዝባዊ ስብሰባው መካሄዱ ስለማይቀር በየቤቱና በየአካባቢው እየተንቀሳቀስን  በራሪ ወረቀት  እየበተንን እና እያሳወቅን ነው፣ ህዝቡም እየተባበረን በመሆኑ የበለጠ ጥንካሬ ሆኖናል ሲሉ በተለይ ለፍኖተ ነፃነት አስታውቀወዋል፡፡

የዝግጅት ክፍሉም በጉዳዩ ዙሪያ በቀጥታ የሚመለከታቸው የከተማውን ፖሊስ ኮሚሽንና ከንቲባውን ለማናገር ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም፡፡ መድረክ የፊታችን እሁድ ለማድረግ ያዘጋጀውን ህዝባዊ ውይይት ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ በመቀሌ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እራሽ ለማድረግ መወሰኑንና ጅግጅቱን ማጠናቀቁን መረዳት ተችሏ፡፡

መድረክ እሁድ ከመቀሌና አካባቢዋ ነዋሪዎች ጋር ለመወያየትን የመፍትሄ ሐሳቦች ዙሪያ ሊመክርባቸው ያሰባቸው ዋነኛ ጉዳዮች፡-የመልካም አስተዳደር እጦት፣ የአብዛኛው ወጣቶች አሰቃቂ ስደትና ሞት፣ ኢ-ፍትሃዊ የግብር አወሳሰን ፣ የኃይማኖት ነፃነት፣የዜጎች መፈናቀል፣የአባይ ግድብ ጉዳይ፣ የትምህርት ጥራትና ልማት ችግር፣ የሊዝ አዋጅና የካሳ አወሳሰን ችግር እንደሚገኙበት ከአስተባባሪዎቹ መረዳት ተችሏል፡፡

በረመዳን ጾም ሙስሊሙ ተቃውሞውን አጠናክሮ ቀጥሎአል

ሐምሌ ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት በረመዳን ጾም ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የጀመሩት ተቃውሞ ይበርዳል የሚል እምነት የነበረው ቢሆንም፣ ተቃውሞው ከሳምንት ሳምንት እያየለ በመምጣቱ፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት በአንዳንድ አካባቢዎች የሀይል እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል።

ከሀሙስ ጀምሮ በፌደራል ፖሊስ አባላት ክትትል ስር የነበሩት የወልድያ ሙስሊሞች በዛሬው እለት በመስጊዳቸው ውስጥ ታግተው መዋላቸውና አንዳንዶች መደብደባቸውን ሌሎች ደግሞ መታሰራቸው ታውቋል።

የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ሰላም መስጊድ ቅጥር ግቢ በመግባት ተቃውሞ ሲያሰሙ የነበሩ ወጣቶችን ደብድበዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ወላጆች ደግሞ ከመስጊዱ እንዳይወጡ ታግተው ለሰአታት ቆይተዋል። ፖሊሶቹ ቀንደኛ ያሉዋቸውን ወደ 38 የሚጠጉ ሰዎችን አፍሰው የወሰዱዋቸው ሲሆን ከ30 ያላነሱት ሴቶች ናቸው። ከሰአት በሁዋላ የታገቱት ወላጆች ወደ ቤታቸው በሰላም እንደሚለሱ ተደርጓል።

በትናንትናው እለትም እንዲሁ 2 ወር ያልሞላት አራስ እናትን ጨምሮ ከ15 ያላነሱ ሙስሊሞች በፖሊሶች ተወስደው ታስረዋል።
ከፍተኛ ተቃውሞ በሚካሄድበት በአዲስ አበባ አንዋር መስጊድም ረመዳን የሙስሊሙን ጉልበት ያዳከመው አልሆነም። በከፍተኛ ጩኸት “መሪዎቻችን ይፈቱ፣ አሸባሪዎች አይደለንም፣ መንግስት ራሱ ገዳይ፣ ራሱ ካስሽ፣ ሳይፈቱ ሰላም የለም፣ ኮሚቴው ይፈታ፣ አንድነን እኛ” የሚሉትን መፈክሮች አስምተዋል። ኢሳት ለመራጋገጥ ባይችልም በአንዋር የተካሄደውን ተቃውሞ ተከትሎ ከ10 በላይ ሰዎች ታስረዋል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ቀስ በቀስ እየተቀጣጠለ የመጣው ተቃውሞ ያሰጋው የአውሮፓ ህብረት የልኡካን ቡድን ኢትዮጵያን መጎብኘቱ ይታወሳል። ሰማያዊ እና አንድነት ፓርቲዎች የጠሩዋቸው የተቃውሞ ሰልፎች በስኬት መጠናቀቃቸው ፣ የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ እየተጠናከረ መሄድ እና የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ ድርጅቶች ጉልበት እያገኙ መምጣት ያሰጋቸው አንዳንድ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ኢህአዴግ የፖለቲካ ሜዳውን እንዲከፍት እየወተወቱት ነው። የዚህን አዲስ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ በተመለከተ ኢሳት በቅርቡ እየተከታተለ መረጃውን ለህዝብ ይፋ ያደርጋል። በመንግስት በኩልም የቀድሞ የድርጅቱን ታጋዮች ለማሰባሰብ እና የፖለቲካ አንድነት ለመፍጠር እንቅስቃሴ መጀመሩን ለማወቅ ተችሎአል።

በአንድ ሳምንት ሁለተኛ አደጋ!

“አውሮፕላኑ አየር ላይ እያለ ሊፈነዳ ይችል ነበር”
ethiopian
ከአዲስ አበባ ወደ አክሱም ይጓዝ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ረቡዕ ለት በጭንቅ እንዲያርፍ መደረጉ ተገለጸ፡፡ አደጋው ከአምስት ደቂቃ በፊት ቢከሰት ኖሮ አውሮፕላኑ አየር ላይ እያለ ሊፈነዳ ይችል እንደነበር ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡
 
78 መንገደኞችንና ሠራተኞችን አሣፍሮ ይጓዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ (Bombardier Q400) አውሮፕላን ከክንፎቹ በአንዱ ጭስ መነሣቱን የሚጠቁም ማስጠንቀቂያ በመደወሉ እጅግ አስጨናቂ በሆነ መልኩ እንዲያርፍ መደረጉን ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል፡፡ ጋዜጣው ስማቸው ከመግለጽ የተቆጠቡ ባለሥልጣንን ጠቅሶ እንደጻፈው አውሮፕላኑ ከማረፉ ከአንድ ደቂቃ በፊት የግራው ክንፍ እየጨሰ መሆኑን ማስጠንቀቂያው ማመልከቱንና አንዱ ሞተር ደግሞ እንደሚገባው ይሰራ እንዳልነበረ ገልጸዋል፡፡
 
ሱዳን ትሪቢዩን በስልክ ያነጋገራቸው ተሳፋሪ ጭስ ከአውሮፕላኑ ክንፍ ሲወጣ መመልከታቸውን፤ ተሳፋሪው ሁሉ በጭንቅ ውስጥ የነበረ መሆኑንና ሁኔታው በጣም አስደንጋጭ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ የአቪዬሽን ባለሙያዎችን በመጥቀስ የአየር መንገዱ ባለሥልጣናት እንደሚሉት ከሆነ አደጋው አውሮፕላኑ ከማረፉ አምስት ደቂቃ በፊት ተከስቶ ቢሆን ኖሮ አውሮፕላኑ አየር ላይ እያለ ሊፈነዳ ይችል ነበር፡፡
 
ሁኔታውን በጥንቃቄ ያስተዋለው የአውሮፕላኑ አብራሪ ካፒቴን ፈጣን እርምጃ በመውሰድ አውሮፕላኑ ወደ ዋናው ማቆሚያ ከመድረሱ በፊት በማቆምና ተሣፋሪዎቹ በፍጥነት እንዲወጡ በማድረግ ሊከሰት የነበረውን የእሣት አደጋ መከላከሉ ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል፡፡ የካፒቴኑ ውሳኔ የሚደነቅ መሆኑን ባለሥልጣናቱ የገለጹ ሲሆን ተሣፋሪዎቹም ህይወታቸውን ከአደጋው በመታደጉ የጀግና ክብር በመሥጠት ማመስገናቸው ጨምሮ ተጠቅሷል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለሥልጣናት የጭሱ መነሻ እየተመረመረ ነው ቢሉም አየር መንገዱ አደጋውን አስመልክቶ እስካሁን ይፋዊ መግለጫ አላወጣም፡፡
 
ባለፈው ሳምንት በቆመበት እሣት የተነሳበት ሌላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋው ከታወቀ ጀምሮ የውጭ አገር የዜና ወኪሎች በየደቂቃው ዘገባ ሲያቀርቡበት የነበረ መሆኑ ቢታወቅም ከዚህ በባሰ መልኩ በርካታ ተሣፋሪዎችን ጭኖ ለአደጋ ተጋልጦ የነበረው አውሮፕላን ጉዳይ አደጋው ከተከሰተበት ረቡዕ ጀምሮ እስካሁን በመንግሥትም በኩል ሆነ በአየር መንገዱ ይፋ አለመሆኑ በበርካታዎች ዘንድ ጥያቄ መጫሩ የማይቀር ነው፡፡

ጉልጎል http://www.goolgule.com/
 

Friday, July 19, 2013

ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የምናደርገው ትግል በስም ማጥፋትና በፍረጃ አይገታም!!!!

Submitted by Admin on Fri, 07/19/2013 - 12:30

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ


 ሰማያዊ ፓርቲ በሃገራችን የሚፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጥሰትና የአስተዳደር ብልሹነት እንዲስተካከል የመንግሥት አካላት አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ነገርግን እነዚህ ጥያቄዎቻችን በመንግሥት በኩል ምላሽ ስለተነፈጋቸው ጥያቄዎቹ ከፍ ባለደረጃ ትኩረት እንዲያገኙ ሆነው መቅረብ እንዳለባቸው ተገንዝበናል፡፡ በዚህም መሰረት ጥያቄዎቹን በሰላማዊ ሰልፍ መጠየቅ እንዳለበት ወስኖ ግንቦት 25 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም በአዲስ አበባ ባካሔደው ታላቅ ሠላማዊ ሠልፍ ጥያቄዎቹ እንዲመለሱ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

 በተጨማሪም ጥያቄዎቻችን ከመንግሥት በኩል በሦስት ወር ጊዜ ምላሽ የማያገኙ ከሆነ ሌላ የተቃውሞ ሠልፍ ከፍ ባለ ደረጃ የሚጠራ ስለመሆኑ ፓርቲው አቋሙን በሰልፉ ዕለት አሳውቋል፡፡

 ይሁንእንጂ ሰልፉ ከተጠናቀቀበት ዕለት ጀምሮ በገዥው ፓርቲና በመንግሥት ተወካዮች የተሠጡ መግለጫዎች ያስገነዘቡን መፍትሔ እንዲሠጣቸው ለቀረቡ ጥያቄዎች መንግስት ተገቢውን መልስ ለመስጠት ምንም ዓይነት ፍላጐት እንደሌለው ነው፡፡ ከዚህም አልፎ መንግስት ጥያቄዎቹ የቀረቡበትን መንፈስ እንኳ በቀናነት ለመቀበል ያልፈለገ መሆኑን ያሳያል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ፓርቲያችንን ለመጫንና ስሙን ለማጉደፍ በፕሮግራሙም ሆነ በሥራ እንቅስቃሴው የሌለበትን በአክራሪነትና በአሸባሪነት ለመወንጀል ተደጋጋሚ ጥረት እያደረገ መሆኑን ከሚሠጣቸው መግለጫዎች ተረድተናል፡፡

 ይህ የመንግስት አካሔድ የጥያቄዎቻችንን አቅጣጫ ለማስቀየር ከሚደረግ ሙከራ ውጭ የትግሉን እንቅስቃሴ ሊገታው እንደማይችል ዛሬ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች እያደረጉ ያሉት የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ አብይ ማስረጃ ነው፡፡ በተጨማሪም መንግስት የሚያደርጋቸውን ፍረጃና ስም ማጉደፍን በመፍራት የኢትዮጵያ ህዝብ የሚደርስበትን የሰብአዊ መብት ጥሰትና የአስተዳደር ብልሹነት ከዚህ በላይ ተሸክሞ ለመኖር የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ያሳያል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በአሁኑ ወቅት ለነፃነትና ለፍትህ መገኘት እያደረጉ ያለውን እንቅስቃሴ ፓርቲያችን እያደነቀ ትግላቸንን አጠናክረን እንድንቀጥል መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

 ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2ዐዐ5 ዓ/ም. ካካሄደው ታላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ዕለት ጀምሮ በገዥው ፓርቲና በመንግሥት የተወሰዱ አቋሞችን በመገምገም ፓርቲው ላቀረባቸው ጥያቄዎች የተሠጠ ምላሽ አለመኖሩንና አንዳንዶቹም ችግሮች እየተባባሱ መሔዳቸውን ተገንዝቧል፡፡

ስለሆነም ፓርቲያችን ለሕዝብ በገባው ቃል መሠረት ነሀሴ 26 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም ከፍ ያለ የተቃውሞ ሰልፍ በማካሄድ አሁንም በሃገራችን የሚካሄዱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና የአስተዳደር ብልሹነቶች እንዲስተካከሉ፣ በተለይም የፖለቲካና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ፣ የመንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ገብነት እንዲቆም፣ የተፈናቀሉ ዜጐች ወደመኖሪያቸው እንዲመለሱና አፈናቃዮችም ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ ሙስናና የተበላሹ አሰራሮች እንዲወገዱ ላቀረባቸው ጥያቄዎች ምላሽ እስኪያገኙ ድረስ ትግሉን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

 በዚሁም መሰረት መንግስት በፓርቲዎች ላይ ከሚነዛው ስም ማጥፋትና ፍረጃ እንዲቆጠብና ፓርቲያችን ላነሳቸው ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፣ የፓለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ማሕበራት ነሀሴ 26 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም በምናደርገው ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በመሳተፍ የየበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ሐምሌ 12 ቀን 2005 ዓ.ም

 አዲስ አበባ
 

የኢትዮጵያ ወታደሮች የሞርሲና ቦዲ ሴቶችን የደፍራሉ ሲል አንድ የምርምር ተቋም አስታወቀ

ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኦክላንድ ኢንስቲቲዩት ባወጣው መግለጫ በኦሞ ሸለቆ የሚገኙ የሙርሲና የቦዲ ነዋሪዎች አካባቢያቸው ለሸንኮራ ገዳ ምርት ይፈለጋል በሚል በሀይል ቀያቸውን እንዲለቁ ከመደረጉ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መፈጸሙን ገልጿል። ድርጊቱ በአሜሪካ እና በእንግሊዝ መንግስት እርዳታና  እውቅና እየተካሄደ መሆኑም ገልጿል፡፡
የእንግሊዝ መንግስት የልማት ተራድኦ የውጭ ግንኙነት ክፍል ቃል አቀባይ ፣ ” የእኛ ድጋፍ ለዘመናት በጦርነትና በረሀብ ስትሰቃይ ለኖረችዋ ኢትዮጵያ ረድቷል” ብለዋል።
ኦክላንድ ተቋም በበኩሉ የልማት አጋር አገራት ከሰብአዊ መብቶች ጥሰት ጎን ለጎን የሚካሄደውን ልማት መደገፋቸው አሳሳቢ ነው ብሎአል።  አንድ የሙርሲን አባወራ ” ወታደሮች በየአካባቢያችን ተሰማርተው የቦዲን ሴቶች ወስደው ደጋግመው ደጋግመው ደፈሩዋቸው፣ ከዛም የእኛን ሚስቶች ደፈሩዋቸው” በማለት ለተቋሙ መናገራቸው ተገልጿል።
የእንግሊዝ የልማት ተራድኦ ሰብአዊ መብቶችን በሚጥስ መንግስት የሚገኙ ህዝቦችን አትርዱ ማለት፣ ለተረጅዎች ሁለተኛ ጉዳት ነው በማለት የተቋሙን ሪፖርት ሳይቀበሉት ቀርተዋል።
ኢትዮጵያ በየአመቱ ከለጋሽ አገራት  ከ50 እስከ 60 ቢሊዮን ብር የሚደርስ ገቢ እርዳታ ታገኛለች።
ኢትዮጵያ መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ የሰጠው አስተያየት የለም።

አንድነት የተቃውሞ ፊርማ የማሰባሰብ ሂደቱ በደህንነቶችና በፖሊስ ጥምረት እየተደናቀፈ ነው አለ

ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲው  በህገ ወጥ የዘመቻ እስር የሚሊዮኖች ድምፅ አይታጠፍም” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ በአዲስ አበባ ከተማ የጸረ ሽብር አዋጁ በህገ መንግስቱ እውቅና የተቸራቸውን መብቶችን የሚጨፈልቅና ከህገ መንግስቱ ድንጋጌዎች ጋር የሚጋጭ በመሆኑ መሰረዝ ይገባዋል የሚሉ ዜጎች ወደ ዋናው የፓርቲው በጽ/ቤት በመምጣት የተቃውሞ ፊርማቸውን እንዲያኖሩ የሚጠይቅ ‹‹ከሚሊዮኖች ለምን አንዱ አይሆኑም›› የሚል በራሪ ወረቀት በሁሉም የአዲስ አበባ ወረዳዎች ለማሰራጨት የተጀመረውን እንቅስቃሴ መታወቂያቸውን ለማሳየት በማይፈቅዱ ደህንነቶች ነን ባዮችና በፖሊስ ጥምረት በሕገወጥነት መንግድ እየተደናቀፈ መገኘቱ ” አሳዝኖኛል ብሎአል።
“ፖሊስ የአንድ ፓርቲ ወገንተኛ ሳይሆን ህዝብን ማገልገልና ሁሉንም በህግ መነጽር መመልከት የሚገባው አካል ቢሆንም ሚዛናዊነትን ባልጠበቀ ሁኔታ ህገ መንገስታዊ መብታችንን በመጠየቅ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የምናቀርበውን አቤቱታ ለማደናቀፍ መሞከሩና አባላቶቻችንን እግር በእግር እየተከታተለ ለእስር መዳረጉን በቸልታ ለመመልከት አንፈቅድም” አንፈቅድም ሲል ፓርቲው አክሎአል።
በራሪ ወረቀቶችን መበተን ከጀመርንበት ደቂቃ ጀምሮ አባሎቻችን እየታሰሩና ፍርድ ቤት እየቀረቡ ይገኛሉ ያለው አንድነት፣ ፖሊስ ፍርድ ቤት ባቀረባቸው ወጣቶች ላይም አንድነት የሚባል ፓርቲ መኖሩን አጣርቼ እስክመጣ የ10 ቀን ጊዜ ይሰጠኝ ማለቱና ፍርድ ቤቱም የተጠየቀውን መፍቀዱ የምንገኝበት ሰዓት ምን ያህል ፈታኝ እንደሆነ እንድንገነዘብ አድርጎናል ብሎአል።
አንድነት በአባላቶቹና በእንቅስቃሴው ላይ የተከፈተውን ህገ ወጥ የፖሊስ ዘመቻ ለማስቆምና በደል ፈጻሚዎቹም በታሪክ፣ በህዝብና በህሊና ዳኝነት ይጠየቁ ዘንድ ወደ ፍርድ ቤት እንደሚያመራም አስታውቆ ፤ የጸረ ሽብር አዋጁ እንዲሰረዝ እያሰባሰበ በሚገኘው የህዝብ ድምጽ እንደሚገፋበትም ግልጽ አድርጎአል።