Sunday, July 19, 2015

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ወደ ጦር ግንባር!

July 19,2015
Bilderesultat for berhanu nega
ከቃሊቲ እስር ቤት ከተፈታ በሁዋላ ወደ አሜሪካ በመመለስ በተማረበት ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ረዳት ፕሮፌሰር በመሆን ሲያገለግል ከቆየ በሁዋላ ከጥቂት ወራት በፊት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማእረግ ተሰጥቶት በበክኔል ዩኒቨርሲቲ በስራ ላይ ቆይቷል። ሙሉ የፕሮፌሰርነት ማእረግ እንደ ተሰጠው የሰሙ ጋዜጠኞች ደስታቸውን ገልጸው ዜናውን ለመዘገብ ሲጠይቁት "ፕሮፌሰርነት ተራ ነገር ነው። የእኔ ስራ ማስተማር ሳይሆን በአስከፊ ጭቆና እና ዘረኝነት ስር ወድቆ የሚማቅቀውን ህዝቤን ነጻ ማውጣት ነው" ሲል ጋዜጠኞቹ ተደምመው ነበር። ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዚህ በአሜሪካን ሃገር የፕሮፌሰርነት ህይወቱን ትቶ በረሃ የወረደው ምንም ጎሎበት አይደለም።

 የኢትዮጵያ ህዝብ እንባና መከራ፣ ህመምና ሰቆቃ እንቅልፍ ስለነሳው ብቻ ነው ዛሬ ያፈራውን ሃብትና ንብረት ሽጦ ህዝቡን ነጻ ሊያውጣ ከፊት ሆኖ ሊመራ ከድካሙ አረፍ ብሎ በመኖሪያ እድሜው በረሃ የወረደው። የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ወደ ግንባር መሄድ ያለው ትልቅ እንድምታ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። የቆረጠ ለውጥ ማምጣቱ አይቀርም። ፕሮፌሰር ብርሃኑ የሚሞላው አንድ ታላቅ ክፍተት ህዝባችን የሚከተለው መሪ በአስተማማኝ ሁኔታ ማግኘቱ ነው። 

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ በተግባር እና በእሳት የሚፈተን መሪ ለመሆን ወስነህ ሁሉን ትተህ ወደ ግንባር መውረድህ የሚያመጣው ለውጥ ቀላል እንዳልሆነ እኛ ብቻ ሳንሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላቶችም ጠንቅቀው ያውቃሉ። ታላቅ መሪ በተግባር ይፈተናል። እስከ መጨረሻው የነጻነት መዳረሻ ከጎንህ እንሰለፋለን። ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!


አበበ ገላው

No comments: