Saturday, July 11, 2015

አካባቢውን የምታተራምሰው ኢትዮጵያ ነች - ኤርትራ

July 11,2015
የኢትዮጵያና የኤርትራ ካርታዎች ከየባንዲራዎቻቸው ጋርየኢትዮጵያና የኤርትራ ካርታዎች ከየባንዲራዎቻቸው ጋር
አካባቢውን እያተራመሰች ያለችው ኢትዮጵያ እንጂ ኤርትራ አይደለችም” ሲሉ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ዳይሬክተር አስታወቁ፡፡


የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ዳይሬክተር  አቶ ፀሐዬ ፋሲል ዛሬ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ኢትዮጵያ የራሷን የውስጥ ችግር ለመሸፈን ስትል የምታሰማው የተለመደ ፉከራ ነው፤ ኤርትራ ለአካባቢው መረጋጋት እየጣረች ያለች ሃገር ነች ብለዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሰላም ሰላም ቢሉም የሰው ግዛት በኃይል ይዘው ሰላም እንፈልጋለን ማለታቸው አስቂኝ ነው” ብለዋል አቶ ፀሐዬ፡፡

አቶ ኃይለማርያም ያስተላለፉትንን ዛቻ አዘል መልዕክት አስመልክቶም “ኤርትራ ከልማቷ አታፈገፍግም፤ ለፉከራውም ትኩረት አትሰጥም” ሲሉ አክለዋል፡፡የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃን አስመልክቶ የተናገሩት አቶ ፀሐዬ “በማንኛውም የሦስተኛው ዓለም ሃገር ውስጥ የሰብዓዊ መብቶች ችግር ሁልጊዜ ያለ ቢሆንም ኤርትራ ግን በተሻለ ሁኔታ ሰብዓዊ መብቶችን ታከብራለች” ብለዋል፡፡

የኤርትራን ወጣቶች መሰደድ አስመልክቶ ለተነሣላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ኢትዮጵያና ሌሎችም የውጭ ኃይሎች በቪዛና በመሣሰሉ አማላይ ጥሪያዎች ወጣቶቹ ሃገራቸውን እየጣሉ እንዲወጡ፤ ብዙ ገንዘብ መድበው የሚያካሂዱት ዘመቻ ውጤት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

No comments: