Sunday, July 19, 2015

አንድ ወታደር 3ት ኮነሬሎችና ሌሎች በርከት ያሉት ወታደሮች በመግደል ራሱን እጠፋ

July 19,2015
በአዲ ሃገራይ አካባቢ  የሚገኝ ለግዜው ስሙ ያልታወቀው ወታደር 3ት ኮነሬሎችና ሌሎች በርከት ያሉት ወታደሮች በመግደል ራሱን እንዳጠፋ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ገለጸ።ከሰሜን የደረሰን መረጃ እንዳስረዳው- በገዢው የኢህአዴግ ስርአት መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ታስረው የሚገኙ ወታደሮች የሰራዊቱ ከፍተኛ አዛዦች በሚከተሉት ከፋፋይ አሰራር ምክንያት ተማርረው የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ መሆናቸውን የገለጸው መረጃው አሁንም በአዲ ሃገራይ አንድ ወታደር ለ3ት ኮነሬሎች ከነ አጃቢዎቻቸው በኡርምታ ቶክስ በመግደል ለራሱም ህይወቱን እንዳጠፋ ለማወቅ ተችሏል።

ይህ በያዝነው ሳምንት በ3ት የኢህአዴግ ኮነሬሎች ላይ የተውሰደው እርምጃ ለብዙዎቹ በላያቸው ልይ ግፍ ሲፈፀምባቸው የነበሩ ወታደሮች እርካታ የሰጠ መሆኑና ሌሎች አዛዦችም በላያቸው ላይ ተመሳሳይ እርምጃ እንዳይወሰድባቸው ስጋት መግባታቸውን የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል።
adi hageray millitary killing

No comments: