Tuesday, February 24, 2015

የጦፈ ሙስና ከመንገድ ሥራ፣ ከባቡር መስመር ዝርጋታና ከቤቶች ልማት

February 24,2015
በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እየተዘረፈ ነው - ሚኒስትሩ

lightrail road

* ከ30 እስከ 40% የግንባታ ወጭ ይዘረፋል!!

የኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪ ልማት ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ሃይሌ ከስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን አጣሪ ቡድን ጋር ባደረጉት ውይይት ከመንገድ ስራ፣ ከባቡር መስመር ዝርጋታና፣ ከቤቶች ልማት ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እየተዘረፈ መሆኑን አምነዋል።

 የፀረ ሙስና ኮሚሽን ባካሄደው ጥናት በባቡር መስመር ግንባታ 2.3 ኪሜ የባቡር ሃዲድ መስመር በሙስና ምክንያት ከደረጃ ውጭ እንዲሆን በመደረጉ የ124 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ደርሷል። የአደጋ መከላከያ ብረቶች የተሰሩት ከወጣላቸው የጥራት ደረጃ በሶስት እጅ ያነሱ ሆነው በመገኘታቸው ጉዳዩ ለቦርድ ሰብሳቢው አርከበ እቁባይ ቢቀርብም ምላሽ ሳይሰጠው በመቅረቱ በቢሊዮየኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪ ልማት ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ሃይሌ ከስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን አጣሪ ቡድን ጋር ባደረጉት ውይይት ከመንገድ ስራ፣ን የሚቆጠር ገንዘብ የት እንደገባ ማወቅ አለመቻሉን ገልጿል።
የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን ያቀረበውን ሪፖርት ተከትሎ ምላሽ የሰጡት ሚኒስትር መኩሪያ ሃይሌ፣ ችግሩ የተፈጠረው ለምርጫው ሲባል የባቡሩ ግንባታ እንደ ትልቅ የምርጫ ማሳመኛ በመያዙ ነው ።
የግንባታ ኢንዱስትሪው ከሚያወጣው ወጪ ከ30 እስከ 60 በመቶ የሚሆነው በሙስና ይባክናል ሲሉም ሚኒስትሩ አክለዋል።
እንደዚያም ሆኖ በቅርቡ የተመረቀ የአዲስ አበባ መለስተኛ የባቡር ግንባታ፣ አገልግሎት ከመጀመሩ ከወዲሁ በርካታ የመፈራረስ ችግሮች እያጋጠሙት ነው። ለፖለቲካ ፍጆታና ለፕሮፓጋንዳ ሲባል ቶሎ ቶሎ እንዲሰራ ከማድረግ ዉጭ እነ አቶ አርከበ እቁባይ የሕዝቡን ፍላጎት ከግምት ያላስገቡ ሲሆን፣ አስፈላጊ የጥንቃቄ እርምጃዎች አልተወሰዱም። በዋናነት የባቡ ሃዲዱ ከተማዋን ለሁለት የከፈለ ሲሆን ከሃዲዱ በስተቀኝ እና በስተግራ ያሉ ነዋሪዎች ለመገናኘት እጅግ በጣም ብዙ ርቀት ለመጓዝ ተገደዋል።

No comments: